(አንድ አድርገን ጥር 28 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የነነዌ ፆም በደረሰ ቁጥር የከበደ ሚካኤል ይችህ ግጥም ትዝ ትለኛለች ፤ የትንቢተ ዮናስን ምዕራፍ እንዴት በግጥም መልክ ማስቀመጣቸውን ሳስበው ይገርመኛል ፤ ይህኛውን ግጥማቸውን ሳነብ መጽሀፍ ቅዱስ ያነበብኩ ይመስለኛል ፤ ከበደ ሚካኤል በርካታ መጽሀፍትን በነበሩበት የህይወት ጊዜያት ለማህበረሰባችን አበርክተዋል ፤ በስነ ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ ገናና ከሆኑ ደራሲያን አንዱ ናቸው ፤ ትምህርታቸውን ከቤተክህነት ቢጀምሩም በ1990 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሊቀበሉ የቻሉ ታላቅ የስነ ፅሁፍ ባለሙያ ናቸው ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስራቸውን መዝኖ የክብር ዶክትሬት በሰጠበት ወቅት ‹‹ በድርሰቶቻቸው ውስጥ የሚታዩት የእኒህ ታላቅ ደራሲ የሀሳብ መግለጫዎች ፤ ቃላት ዘይቤዎች ፤ ሌሎች የአፃፃፍ ስልቶች በኋላ ለመጡ ደራሲዎች ያደረጉት አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም ፤ ›› ብሏል ፡፡
የነነዌ ሰዎች ፆም ብዙ ነገር ያስተምረናል ፤ የዮናስ ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የዮናስ መልስ ፤የመርከቡ መናወጥ ፤ የዮናስ ጥፋተኝነቱን አምኖ ወደ ባህር ጣሉኝ ማለት ፤ ዮናስ ሲጣል የወጀቡ ፀጥታ ፤ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ወደ አምላኩ ያደረገው ጸሎት ፤ እግዚአብሔር ዮናስን ያዳነበት መንገድ ፤ የቅሏ በአንድ ቀን አድጋ ለዮናስ ጥላ መሆኗ መልሳ መክሰሟ ፤ የህዝቡ አዎን አጥፍተናል ፤ በድለናል ማለት ፤ የነነዌ ህዝብ የሶስት ቀን ፆም ፤ እሳት ከሰማይ ወርዶ መመለስ ፤ በጠቅላላ እግዚአብሔር ዮናስን ያስተማረበት መንገድ ፤ አስተማሪ ነው፡፡ ለመርከበኞቹ ፈተና የሆነው ከአምላኩ ተጣልቶ የመጣው ዮናስ ነው ፤ አዎን አሁን ለቤተክርስትያናችን ፈተና የሆናት ማነው ? የቤተክርስትያን ፈተናዋ እየባሰ ሲሄድ እንጂ ሲቀንስ ለማየት አልታደልንም ለምን ይሆን ? ጥፋተኛ ነው እንጂ ፤ ጥፋተኛ ነኝ የሚል ሰው በመካከላችን የለም ፤ የነነዌ ሰዎች አሁን ላለነው ክርስትያኖች ብዙ ትምህርት ይሰጡናል ፤ ማስተዋሉን እግዚአብሔር ካደለን ፤ ዮናስ ሀጥያተኛነቱን አምኖ በራሱ ሲፈርድ ‹‹አንሱኝና ወርውሩኝ›› ሲል ወጀቡም ጸጥ ብሏል ፤ እኛ ሰው የሰራው ሀጥያት እንጂ የራሳችን ለምን አልታየን አለ? ለዘመናት ሲበድሉ የነበሩት የነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቁጣ በመጸጸታቸው ፤ ንስሀ ገብተው ከልብ አዝነው በመፆማቸቸው ጸሎታቸው አምላክ ፊት በመድረሱ ቁጣውን በምህረት ሊመልሱት ችለዋል ፤ የእኛም ፆም መርከቢቷ ላይ የተነሳውን ወጀብ ጸጥ የሚያደርግ እንዲሆን የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሁንልን፡፡
ለማንኛውመ ከበደ ሚካኤል በማይረሳ መልኩ ከትበው በዚህ መልኩ ማስቀመጣቸው ያስመሰግናቸዋል ፤ ይችን ግጥም የማታውቋት አንብቧት ያነበባችዋትም ድገሟት፡፡
‹‹ትንቢተ ዮናስ››
በህዝብዋ መካከል ዓመጽ ስለ ፀና
በጣም ተቆጥቼ አዝኛለሁና
ይህን ለነነዌ ንገራት በአዋጅ
አለና ለዮናስ ለአሚታይ ልጅ
እግዚአብሔር አዘዘው እንዲሄድ በቶሎ
ዮናስ እምቢተኛው አሰበ ኮብልሎ
ከአምላክ ተደብቆ አምልጦ ሊጠፋ
ወደ ተርሴ ሊጓዝ ፤ ሄደ ወደ ያፋ
ዋጋ ከፈለና በመርከብ ተሳፍሮ
አያጉረመረመ ባህሩን ተሻግሮ
ዮናስ ተደብቆ ሊሄድ በግስገሳ
ከእግዚአብሄር ተልኮ ማዕበል ተነሳ
ታላቅ ሞገድ ሆኖ ባህሩ ተቆጣ
መርከበኞች ፈሩ ትልቅ ሽብር መጣ
መርከቡ እንዲቀለው እናድርግ እያሉ
አንስተው ብዙ እቃ ወደ መርከብ ጣሉ
ባህሩም ባሰበት በጣም ተናወጠ
መርከከቡ መሰለ የተገለበጠ
ሰው ሁሉ ተነሳ ጸሎት ለማድረስ
ይህ ሁሉ ሲሆን ተኝቷል ዮናስ
ወደ ዮናስ ሄዶ የመርከቡ አለቃ
ቀሰቀሰው እና ከእንቅልፉ ሲነቃ
እግዜር እንዲድነን ከዚህ ክፉ ጥፋት
ተነስ ፀልይ አለው ይብቃህ ማንቀላፋት
በመርከብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሰብስበው
ተመካከሩ እና በነገሩ አስበው
አለ ሀጥያት ሰርቶ ከእኛ ጋር የመጣ
ለይተን ለማወቅ እንጣጣል እጣ
አለዚያ አንድንም ስለተባባሉ
ተሰበሰቡ እና እጣ ሲጣጣሉ
እውነትም እንዳሉት አጥፊው ሰው ታወቀ
በእንቢተኛው ነብይ በዮናስ ወደቀ
ዮናስ ተረዳና እጁ እንደተያዘ
ያጠፋውን ጥፋት ገልፆ ተናዘዘ
ምነው ባትመጣ ተጣልተህ ከጌታ
እየው መርከባችን እንደሚንገላታ
ቁጣው እንዲታገስ ለማግኝት ጸጥታ
በል አንተው ፍረደን ምን ይበጃል ቢሉ
ዮናስ መለሰና እዚህ ያለህ ሁሉ
ስለምን ይጠፋል በኔ የተነሳ
ወደ ባህር ጣሉኝ አለብኝ አበሳ
ተመልከቱ እነሆ ስራውን አወቀ
ጥፋቱን ገለጠ ይህው መች ደበቀ
እሱ ከፈረደ መልሶ በራሱ
ምን እናድግ ብለው ሊጥሉት ተነሱ
ከደሙ አንፃን ሲሉ ለእግዜር አመልክተው
ወደ ባህር ጣሉት ዮናስን አንስተው
በዮናስ ላይ ኖሮ የመጣው ይህ መዓት
ባሕሩ ፀጥ አለ ልክ በዚያው ሰዓት
ምዕራፍ 2
ዮናስን እንዲውጥ ሕይወቱን ሳይጎዳ
አንድ ትልቅ አሳ እግዜር አሰናዳ
ዮናስም ተውጦ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሲያድር በአሳ ሆድ
ተቀይመህ ኖሮ ከላይ ብተቆጣ
ይህን ያህል መዓት በራሴ ላይ መጣ
የባህሩ ሞገድ እኔን አዋከበኝ
ውሀና ጨለማ ሲኦልም ከበበኝ
አያለ በአሳ ሆድ ዮናስ ሲቀመጥ
አምላኩን ለመነው በመለማመጥ
የታዛዥነትም ጠባይ እያሳየ
አዝኖ ተጸጽቶ ከልቡ ጸለየ
ምን ጊዜመ ቢቆጣ ነው እና መሓሪ
ፊቱን መልሶለት ታረቀው ፈጣሪ
አሳውም ዮናስን ውጦ ሳያስቀረው
ከባህር ተፋና መሬት ወረወረው
ምዕራፍ 3
ይህንን የእኔን ቃል ስማና በቶሎ
ሄደ ለነነዌ እንድትነግራ ብሎ
ደገመና እግዚአብሄር ዮናስን አዘዘ
ነነዌ ሊገባ ዮናስ ተጓዘ
ድምጹን ከፍ አድርጎ ነብዩ ዮናስ
‹‹ ከዛሬ ጀምሮ አርባ ቀን ድረስ
ነነዌ ጠፊ ነች ከሥር ተገልብጣ ››
አለና ለፈፈ የእግዚአብሔርን ቁጣ
ሳያንገራግሩ ሁሉም ስላመኑ
የነነዌ ሰዎች ተጨነቀው አዘኑ
ከትልቅ ጀምሮ ህጻኑ ድረስ
ሕይወቱ የቆመች በስጋ በነፍስ
ሰውም ሆነ እንስሳ ይቀበል ንስሓ
ፍጡር ሁሉ ይጹም ይለይ ከእህል ውኃ
ሁሉም ከልብ አዝኖ ማቅ እየለበሰ
ከክፉ ወደ ደግ እየተመለሰ
መቼም ወሰን የለው እግዚአብሔር ምሕረቱ
ይጸልይ አለና ይለምን በብርቱ
ንጉሡ አሳወጀ ከነመኳንንቱ
የነነዌ ሰዎች በውነት ከልቦና
መጸጸታቸውን እግዚአብሔር አየና
ፍጡር ቢለምነው እንባ እያፈሰሰ
ምህረቱን አውርዶ መዓቱን መለሰ
ምዕራፍ 4
የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ
ዮናስ ተቆጥቶ እያጉረመረመ
እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ
አስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄ
ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ
ምህረትህ የበዛ መሐሪና ታጋሽ
በደል የምትረሳ ከቁጣ ተመላሽ
የቁጣህን ያህል ምሕረትህ የጠና
መሆንህን ጥንቱንም እኔ አውቄአለሁና
እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ሀሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር
አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር
ከከተማ ወጥቶ በምስራቅ በኩል
ከወደ ዳር ሆኖ ነነዌን ሊያስተውል
ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ
ተሰርቶ ተቀመጠ አንዲት ትንሽ ዳስ
እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ
ቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎ
የዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላ
ከጸሀዩ ንዳድ ሆለት ከለላ
በዚህ በቅል ነገር ዮናስ ደስ አለው
እንዲህ ቶሎ ደርሶ ስላገለገለው
እግዜር በማግስቱ ጧት በማለዳ
ቅል የሚበላ ትል ፈጠረ አሰናዳ
ትሉ ቅሉን በልቶ በፍጥነት ደረቀ
ፀሀይ ወጣችና ጊዜው በጣም ሞቀ
እግዜር አዘነና ትኩስ ንፋስ መጣ
የሚከለልበት መጠጊያ ስላጣ
ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው
ዮናስ ተበሳጭቶ ለአምላክ እንዲህ አለው
እንደዚህ ሆኜ ቆሜ ከመኖር
እባክህ ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ደረቀብኝ ብለህ ይህን ቅል በማጣት
እውን ይገባል ሆይ ያንተ እንዲህ መቆጣት?
ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ
በንዴት ብዛት እስክሞት ድረስ
አዎን ይገባኛል መናደድ መጤስ
እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል
ይህ ያለፋህበት ያልደከምክበት ቅል
አንተ ስትናደድ ፈጥሬያት እኔማ
ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ
መቶ ሀያ ሺህ ነው የህዝቧ ብዛት
ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንላት
ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ
ለዮናስ ነገረው የምህረቱ ጌታ
ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይድረስ
በዚህ ተፈፀመ ትንቢተ ዮናስ
ከ ከበደ ሚካኤል ‹‹የዕውቀት ብልጭታ›› ፤ (1999 ዓ.ም ) ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ
Thanks for sharing.
ReplyDeleteGreat it is! God bless you for sharing us.
ReplyDeleteya...many years ago I used to read it...and I was in doubt what was happening....but now ...I know what is happening to Yonas..thank u dear
ReplyDeleteThanks !!
ReplyDeletekeep up the good work !
Thanks.that was realy nice poam and as you said it is the same as the bible.
ReplyDeleteEnameseginalen!! Ye zarewochu "megabe hadis nen bayoch-tehadisowoch"ewinet ye betekiristian memihiran bihonu...ende Yonas ...nisiha begebu...tselot betseleyu...neber...Gin min yadergal..Yebeg lemid yelebesu tekulawoch silehonu...ke bota bota eyezoru...yirebishalu...Egiabher ye Yonasin Libona Yistachew Bilen entseliyilachew!!
ReplyDeleteSome intetst group here in USA working over time to demolish the great job of patriarc paulos that he appointed abune fanuel to serve all eotc with out discrimination. Look this the point yemetelachu mereku. As this reason people such like false priest of mk spending money to campaign some zemawi monk and priest as charged to fire abune fanuel with false alegation. So any informatiom come from this group 100% not question of eotc in usa. Death to mk peace to our church. Be as eotc take action to clean up our church from devil mk.
ReplyDeleteYekerebew Zegeba melkam new neger gin Abune Fanueiln Alkebelim yalew Mahibere Kidusan New enj lelaw bemulu tekebiloal yetetsekesew komitem Abune Abirham Letenkol Ketenesu behala yesebesebut new Hulum Mahibere kidusan Dr Mesifin Kesis Ergete Kal kesis Birhanu Gobena Aba Gebre Wold yehulunim maninet wedefit enzerezirewalen kahin mehonachewn enayewlen Aba Gebre Wold Diredawa-Girk-DC yeserut Lelawm shiro meda -Dalas -Atilanta Birhanu Gobena Papas Tekawami Dr Mesifin Papas Asadag yikoyen
ReplyDeleteYekerebew Zegeba melkam new neger gin Abune Fanueiln Alkebelim yalew Mahibere Kidusan New enj lelaw bemulu tekebiloal yetetsekesew komitem Abune Abirham Letenkol Ketenesu behala yesebesebut new Hulum Mahibere kidusan Dr Mesifin Kesis Ergete Kal kesis Birhanu Gobena Aba Gebre Wold yehulunim maninet wedefit enzerezirewalen kahin mehonachewn enayewlen Aba Gebre Wold Diredawa-Girk-DC yeserut Lelawm shiro meda -Dalas -Atilanta Birhanu Gobena Papas Tekawami Dr Mesifin Papas Asadag yikoyen
ReplyDeleteአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች በማታውቁት ነገር ገብታችሁ የምትፈተፍቱ፤
ReplyDeleteአንዳንዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ቲፎዞነት እንጂ ነገሩን በፅሞና ያላያችሁ፤
አንዳዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ጥላቻ እንጂ ነገሩን በደንብ ሳታውቁ፤
ሌላው ደግሞ በተለይ በተለይ ጥቅሙ የተነካበትና ከሁዋላው ጉድና ጎድጎዳ የሞላበት፤
በመጨረሻ ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ የንግድ ድርጅትና የፖለቲካ ሥራ
እንደበፊቱ መሥራትና ማጭበርበር ያልቻለው የማህበረ ሰይጣን ድርጅት የሚሰጠው
የሞት የሽረት የመሰሪነትና የቅናት አስተያየቱን ነው የሚያስነብበን። የሆነው ሆኖ
ግን ሁልጊዜ አሸናፊው የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለው ነው። እስኪ አሁን ማ ይሙት
በእውነት ለቤተክርስቲያን የምናስብ ከሆነና አላማችን የእግዚአብሔርን መልካም
አገልግሎት ለማገልገል ከሆነ ምን ያጣላናል \ በእውነትስ ክርስቲያን ከሆንን
ክርስቲያን መጣላት አለበት\ ይህንን ደግሜ እላለሁ አላማችን አንድ \ክርስትና\
ከሆነ ምንድን ነው የሚያባላን\ በእውነት አቡነ ፋኑኤል ምን አደረጉ\ ተመድበው
መጡ፣ ሥራቸውን መሥራት ጀመሩ የሥራ ሰው እንጅ የወሬና የአሉባልታ ካህን
አይደሉም። ደግሞስ እኛ ማነንና ነው በስነሥርአት ሲኖዶሱ መድቡአቸው ለክርስትና
አገልግሎት እንዳይሰጡ የምንፈራገጠው፣ አረ ተው መቼም ክርስቲያኖች እንኩአን
አይደላችሁም ፤ ስለ እግዚአብሔር ብትባሉም አልሰማችሁምና አለቃችሁም የቀደመው
ጠላታችን ያ ዲያብሎስ በመሆኑ ነው መሰለኝ እርሱን በማስደሰትና ቤተክርስቲያንን
በመበጥበጥ ላይ ትገኛላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ተዋጊ ነው አታውቁም እንዴ\
ምንም አላችሁ ምንም አሁን ጊዜው የእግዚአብሔር ሰዎች የሚፈተኑበት ጊዜ ስለሆነ
እስከመጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናልና፤ አባታችን እስከመጨረሻይቱ ሰአት ድረስ እውነተኛ
ሥራን መሰራት ብቻ ነው፣ ከእናንተ ጋር አፍ መካፈትም አያስፈልግም። ጨው ለራስህ
ብትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ነውና፣ ማቅ መንፈሳዊ ድንቁርናችሁ
የትም አያደርሳችሁም፣ ለቤተክርስቲያን ጠላት ማቅ ይገባዋል ሞት፣ ለቤተክርስቲያናችን
ግን አንድነት፣ እድገትና ፍቅር ለዘለአለሙ ይሁን። አሜን።ሰላምንና ፍቅርን የማይወደው ማቅ
ይግባ መቀመቅ። ባታወጡትም ካነበባችሁት ይበቃል።ሳትሰሩ የህዝቡን ገንዘብ እየበላችሁ
አየር ላይ ለቀራችሁት ህገ ወጥ የድርጅቱ ኮሚቴ ነን ባዮች፣ እናንተ ማለት ደግሞ ማንም ናችሁና
ካአቅማችሁ በላይ አትዘለሉ ወደ ላይ። ይቆየን።
setan milasu hule rejim newna kidus mikael wede siol yitalew. setanoch silehonachihu gize yelenm.
DeleteThank you for sharing. Incredible work!
ReplyDeleteGod bless you abundantly!
ውድ አንባቢ @ AnonymousFeb 6, 2012 11:16 PM
ReplyDeleteማንበብዎ፣ አስተያየት መስጠትዎ ጥሩ ሳለ፤ ምግባርዎን ግን....
ለመሆኑ አንቱ ስለ ክርስትና ለመምከር ሲሞክሩ መቼ ክርስቲያን መሰሉና። ክርስቲያን እኮ ሲያስተምርም ሆነ ሲመክር ክርስቲያናዊ ጸባይ ኑሮት ነው እንጂ እንዲህ በመሳደብ፣ ክፉ በመመኘት አይደለም። የኛ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ያስተማረን ፍቅርን እንጅ ስድብን፣ ለሰዎች ክፉ መመኘትን አይደለም። እኔም እርስዎ ክርስቲያን ስለመሆንዎ እጠራጠራለሁ። ማለቴ ከጽሑፍዎ ውስጥ ምንም ክርስቲያናዊ ለዛ አላገኘሁበትም። ምናልባት ዘመኑ ካፈራቸው አውቆ አበድ ነጫጭ ተኩላዎች ወገን ይሆኑ ይሆን? ወይንስ እንዲያው በየዋህነት በሰው ግፊት ወደ እነርሱ/ ነጫጮቹ ተኩላዎች/ የተቀላቀሉ ይሆን? ለማንኛውም እራስዎትን ይመርምሩ። እስኪ እንዲያው እግዚአብሔር ይፍረድና ማቅ የሰይጣን ማህበር ነውን? እስኪ ስራው ይመስክር፣ እውነት እንዲያው ማቅ መንፋሳዊ እውቀቱ እና ብስለቱ ምን ያክል ነው? እኔ የምለው ጽሑፍዎን ሲጽፉት አእምሮዎ ተቀበለልዎት? ስራውን እያዩ። መቼም ስራውን አይደለም አይን ያለው፣ አይነ ስውር እንኳ፤ አይደለም ጆሮ ያለው፣ መስማት የተሳነው የሚመሰክረው ነው። አንቱ ግን ስድብዎት ሳይበቃ ዛቻዎንም ቀጠሉበት። መሳደብ፣ ክፉ ምኞት፣ ዛቻ እና በኃይል መመካት እኮ የክርስቲያን ጠባይ፣ ባህሪ ሳይሆኑ የዲያቢሎስና የአበሮቹ ጠባይ ነው። ስለዚህ እርስዎም ሳያውቁትም ሆነ እያውቁ ወደ አበርነት ጎራ ተቀላቅለው እንዳይሆን ስጋቴ ነው። ምክንያቱም የጽሑፍዎት ለዛ የክፉ መንፈስ ባህሪ ስሜት አለበት። እንዲሁም ዝም ብለው በሰው ላይ የማቅ የጥላቻ መንፈስ ለመንዛትና በቤተ ክርስቲያ ላይ ፈተናን ለማምጣት ብለው ከሆነ አይድከሙ፣ ጊዜዎትንም አያጥፉ። ምክንያቱም ማህበሩም በቤተ ከርስቲያናችን ስርዓትና መመሪያ መሰረት ህግና ደንብ በቅዱስ ሲኖዲዎስ ጸድቆለት፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ አደራ ተጥሎበት ያለ ማህበር ነው። አደራውንም ከሞላ ጎደል እየተወጣ ያለ ነው። ቤተ ክርስቲያኗም ብትሆን በክርስቶስ ንጽህ ደም ላይ የታነጸች፣ በሐዋሪያት ስልጣን የጸናች አንዲት ናት። ልትፈርስም፣ ልትጠፋም፣ ልትታደስም የማትችል በአለት ላይም የተመሰረተች ናት። ሰውን ግን የምታድስ፣ የምታንጽ ናት። ስለዚህ ድካምዎ ሁሉ ከንቱ ነው። ለማንኛውም እራስዎትን መርምረው ወደ ትክክለኛይቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቢመለሱ መልካም ነው ባይ ነኝ። ከእንደዚህ አይነት የክፉ መንፈስ ጽንዋቴም ቢላቀቁ ምን ያክል ያማረ ነው።
"ለሚያሳድዷችሁ፣ ሁሉ ፍቅርን ስጡ፣ ጸልዩላቸው" ብሎ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምር እና እኔም እርስዎ ትክክለኛው ኃይማኖት ገብቶዎት መልካም ስራን እንዲሰሩ ጸሎቴም ምኞቴም ነው። እግዚአብሔር ከክፉ መንፈስ ይጠብቅዎት!!! አመሰግናለሁ
I have been surfing online more than 3 hours today,
ReplyDeleteyet I never found any interesting article like yours.
It is pretty worth enough for me. In my view, if all website
owners and bloggers made good content as you did, the web will be a lot more useful than ever before.
My webpage - GFI Norte