Thursday, February 16, 2012

ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል



(አንድ አድርገን የካቲት 08 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-  የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቀዳማዊት ንፅሂት እመቤት ቅድስተ ቤተክርስትያን ዙሪያዋን በጠላት ጦር  እየደማች ትገኛለች፡፡ አረማውያን ቤተመቅደስ እያፈረሱ መናፍቃን ቅጥሯን እየጣሱ ፤ ተሀድሶዎች የራሷ ያልሆነውን እያቀረቡ ወላጅ እንደሌለው ልጅ እያስጨነቋት ይገኛሉ ፡፡ ከጠላቶቿ በላይ እየጎዳት የሚገኝው የቤተክርስትያን አስተዳደር የተማከለ አለመሆኑ ነው፡፡

የሰሜን ሸዋ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እምነት ተከታይ ነው ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ወደ ማዕከላዊ ቤተክህነት ፈሰስ የሚያደርገው ገንዘብ ቀዳሚ ከሆኑት ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ይመደባል፡፡ ሆኖም ግን ሀገረ ስብከቱ ሲዳሰስ ከዝናውና ከክብሩ የማይስተካከል ገጽታ ይነበብበታል ፡፡ በሀገረ ስብከቱ የሚንቀሳቀሰው የደብረ ብርሀን ማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ከሌሎች ማዕከሎቹ የተሻለ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ቢወራለትም በተግባር ግን የሚሰማውን ያህል ሆኖ እየሰራ አይደለም፡፡ በአሁኑ ሰአት በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ አብያተክርስትያናት በንዋየ ቅዱሳን እጦት የመዘጋት አደጋ አጋርጦባቸው ይገኛሉ፤  አብዛኞቹ መቀደሻ ጧፍ ፤ ማጠኛ እጣን ማግኝት አገልግሎቱን እያደናቀፈ እና እየተፈታተነ የሚገኝበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ሀገረ ስብከቱ ያለባቸውን ችግር አጥንቶ የመፍታት አቅጣጫ ሲከተል ለማየት አልቻልንም ፤ ቤተክርስትያናቱ አካባቢው ላይ የሚኖረው ምዕመን ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ቤተክርስትያናቱ የሚያስፈልጋቸውን ንዋየ ቅዱሳት ለማሟላት የአቅም እጥረት መኖሩ አንዱ ምክንያት ነው ፤ ሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ፈሰስ የሚደርገው ብር እነዚህን የመሰሉ ችግሮች ፈተው መሆን ያለባቸው ይመስለናል፡፡ ቤተክርስትያናቱ እየተቸገሩ ፈሰስ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም፡፡ 

የሀገረ ስብከቱ ላይ የሚታዩ ችግሮች1.      አስታዋሽ ያጡ ቤተክርስትያናት ቁጥራቸው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣት ጧፍ እጣን ዘቢብ መንበረ ፤ የካህናት ደመወዝ መጋረጃ ጽና የሌላቸው (በትውስት የሚገኝባቸው) አብያተ ክርስትያናት በዝተዋል፤ ለእነዚህ አብያተክርስያናት መፍትሄ ሲሰጥ አላየንም
2.     ልተማከለ የገንዘብ ፍሰት ፤ ሀገረ ስብከቱ ወደ ማዕከላዊ ቤተክህነት ፈሰስ የሚያደርገው ገንዘብ ከሌሎች ላቅ ያለ ቢሆንም ሊፈርሱ የደረሱና ፤ ካህናት ያጡ አብያተክርስትያናት ቁጥራቸው ከጣት ቁጥር በልጧል
3.     የደብረ ብርሀን አንሳስ መንበረ ብርሀን ቤተክርስትያን አራቱም ጉባኤያት ትምህርት ቢሰጥም የተማሪዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በመቀነስ ላይ ይገኛል ፤ ይህን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ አለመመልከት የመፍትሄ አቅጣጫ አለማስቀመጥ የሀገረ ስብከቱ ችግር ነው፡፡ በቦታው ላይ ሄደን መመልከት እንደቻልነው ተማሪዎቹ የእለት ጉርስ በማጣት ከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛሉ፡4.     የአስተዳደር በደልና  የወንጌል አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ዋንኛ ችግሮቹ ናቸው

በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የመዘጋት አደጋ ካጋረጠባቸው እና እኛም በአይናችን ያየናቸው አብያተክርስትያናት ውስጥ ስድስቱን እነሆ..............
1.    ጅማይ ቆላ ሚካኤል ፤
የሚገኝበት ቀበሌ፡-  ጋንአራዳ
የምዕመን ብዛት፡-  36
ችግሮች ፡- ጧፍ እጣን ዘቢብ

2.     ጋንቆላ ካህናተ ሰማይ
የሚገኝበት ቀበሌ፡- ጋንአራዳየምዕመን ብዛት፡- 62


3.     ጋንቆላ ጊዮርጊስ
a.     የሚገኝበት ቀበሌ፡- ጋንአራዳ
b.     የምዕመን ብዛት፡-  29
c.     የቤተክርስትያኑ ወለሉ አፈር በመሆኑ ምስጥ የቤተክርስያኑን መገልገያ እቃዎችን እድሜ እያሳጠረ የሚገኝበትን ሁኔታ ተመልክተናል ፤ በተጨማሪ ለተለያዩ አገልግሎት የሚያገለግሉ የስርዓት መፅሀፍት ባለመኖራቸው ምክንያት አገልግሎቱን ዲያቆናት እና ካህናት በአግባቡ እንዳያገለግሉ እንቅፋት ሆኖባቸው ይገኛል ፤ መጎናጸፊያው ታቦት ለማልበስ የማይመጥን የመሆን ችግር
4.     ዛሮ ኪዳነ ምህረት
a.     የሚገኝበት ቀበሌ፡- ጋንአራዳ
b.     የምዕመን ብዛት፡- 90
c.     በእድሳት ላይ የምትገኝ ቤተክርስትያን

5.     አዘዥ አንባ ሚካኤል
a.     የሚገኝበት ቀበሌ፡- ብርቃ
b.     የምዕመን ብዛት፡- 30
c.     የዘዥ አንባ ቤተክርስያና ካሉት ሁሉ በጣሙን ችግር ያለበት ቤተክርስያን ሲሆን (እጣን ፤ ጧፍ ፤ ዘቢብ ፤ መጽሀፍት ፤ መቋሚያ ..ወንጌል ፤ መጎናጸፊያ መንበር ችግር ያለበት ቤተክርስትያን ነው)

6.    ጉይ መድሀኒአለም
a.     የሚገኝበት ቀበሌ፡- ጉይ ጽጌረዳ
b.     የምዕመን ብዛት፡- 90

እነዚህን የጠቀስናቸውን ቤተክርስትያናት ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ ፤ በዋነኝነት የተቸገሩ ቤተክርስትያናት ናቸው ፡፡ አንዳንዶቹ ችግራቸው ጠለቅ የሚሉት ቤተክርስትያኖች መጽሀፍት ፤ መቋሚያ ..ወንጌል ፤ መጎናጸፊያ መንበር እና ሌሎቹንም መሰረታዊ ነገሮች ማግኝት ከባድ ሆኖባቸዋል እኛ ከአዲስ አበባ በጥቂጥ ኪሎሜትር ተጉዘን ይህን ችግር ለማየትና በቃን እንጂ በየበርሀው በየገጠሩ የሚገኙትን አብያተክርስትያናት ከዚህም የዘለለ ችግር ይኖርባቸዋል ብለን እናስባለን፡፡ ሀገረስብከቱ ፤ በአካባቢው ላይ ያለው የማህበረ ቅዱሳን ማዕከልና ፤ ምዕመናን ተንቀሳቅሰው እነዚህን አብያተክርስትያናት ላይ የተደቀነውን አደጋ በማጤን ጊዜያዊ እና ቋሚ መፍትሄ  ሊፈልጉላቸው ግድ ይላቸዋል፤ እኛም የአቅማችንን ያህል የመርዳት ክርስትያናዊ ግዴታ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡



ከ4 ወር በፊት ሀረር መንገድ አዋሽን አለፍ ብሎ የሚገኝው ኮራ ገብርኤል ላይ በቦታው ተገኝተን ያየነውን ነገር በብሎጋችን በመፃፍ ምዕመኑ የቻለውን ያህል እንዲረዳ መልዕክት አስተላልፈን ነበር ፤ በጽሁፉ ምክንያት ምእመናን ባሳለፍነው ታህሳስ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ላይ  በቦታው በመገኝት ለማየትና የቻሉትንም የረዱ ሲሆን በቦታው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 23 ሺህ ብር መሰብሰቡን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ስንት ቤተክርስትያኖች በበረሀ እና በገጠር ላይ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚኖሩ ለአንድ ጊዜ እንኳን አስበን አናውቅም ፡፡ ከተማ ላይ የምንኖር ምዕመናኖች የገጠሪቱን ቤተክርስትያን ጧፍ እጣን የቤቱ መገልገያዎችን የማሟላት ግዴታው አለብን፡፡ ስንቶቻችን ነን ግሸን ማርያም፤ አክሱም ፅዮን ፤ ቁልቢ ገብርኤል ስንሔድ መንገድ ላይ ያሉትን ቤተክርስትያኖች ጧፍና እጣን የምንሰጠው? ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ያሉበትን ሁኔታ የምናስታውሰው?  ችግራቸው ችግራችን መስሎ የሚታየን ? በየገጠሩ  እንደ እነዚህ ላይ አብያተክርስትያናት ግማሾቹ የአፅራረ ቤተክርስትያናት ተቋቁመው ሲኖሩ ፤ ገሚሶቹ ደግሞ ፤ ቅዳሴ ለመቀደስ  ጧፍና እጣን በጣም ይቸገራሉ፡፡  


አቅራቢያችን ያሉ አብያተክርስትያናት እና ገዳማት እንዲህ አይነት ችግር ሲገጥማቸው ላናይ እንችላለን ነገር ግን የምእመኑ ቁጥር አነስተኛ በሆነበት ፤ በገጠርና  ላይ የሚገኙ አብያተ ቤተክርስትያናት ይህን የመሰለ ችግር በየጊዜው ያጋጥማቸዋል ፤ እነዚህ አብያተክርስትያናት ከመዘጋታቸው በፊት የሚያስፈልጋቸውን ነገር በአቅማችን ያህል እንረዳለን ካላችሁ ይህን ስልክ መጠቀም ቤተክርስትያኖቹን ከመዘጋት ትታደጓቸው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡
( አቶ ጥበበ 0913-164550) 

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን››


6 comments:

  1. beatkiristiyanen yemitebk amlak yirdan!!1

    ReplyDelete
  2. Well done on the cora Gebriel achievement. Pay pal binorachu arif new.

    ReplyDelete
  3. ጥሩ ምልከታ ነው በዝህ ቀጥሉ የቻልነውን እናደርጋለን

    ReplyDelete
    Replies
    1. yetkbrachehu yamdu azgagoche Yemetesrute sera bego bemehonu weladiteamelak kexnanet gare tehune.

      Delete
  4. በቤተ ጳውሎስ ብሎግ ላይ ስለ ቫለንታይን ቀን ያነበብኩት አስደስቶኛል እናንተም ለአንባቢያን እባካችሁ አቅርቡት

    ReplyDelete