(አንድ አድርገን የካቲት 12 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አዲስ አበባ የሚገኝው ሲኖዶስ እና በአሜሪካን ሀገር ስደተኛው ተብሎ የሚታወቀው የሲኖዶስ አባላት መካከል እርቀ ሰላም ለማካሄድ እና ቤተክርስትያኗን ወደ አንድ ለማምጣት ከአዲስ አበባ በአቡነ ገሪማ የሚመራ ልኡካን ቡድን ወደ አሪዞና አሜሪካ ማቅናቱ ይታወቃል ፡፡ ይህ የእርቅ ጉባኤ ብዙዎች የማይሳካ በማስመሰል በድህረ ገፅ ፤ በቴሌቪዥን በመጽሄቶች በጋዜጦች ትልቅ ሽፋን ሰጥተው ዘግበውታል፡፡ ኢሳት የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነገሮችን ሁሉ ወደ ፖለቲካ በማዞር የሰዎችን ቀልብ በመሳብ ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ በቴሌቪዥን ጣቢያው አማካነት አስተላልፏል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሲኖዶስ አባላት አብረው እራት ለመብላት እንኳን ፍቃደኛ አልሆኑም›› በማለት ከእውነታው ጋይ የማይጣጣም በሬ ወለደ ዘገባውን አስተላልፏል፡፡
ከአዲስ አበባ አሜሪካ አሪዞና ድረስ ለእርቀ ሰላም የሄዱ አባቶች እንዴት ይህን ያደርጋሉ ብለው አለማሰባቸው እኛንም አስገርሞናል፡፡ በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ በየ15 ቀኑ የሚታተሙ መፅሄቶች አንዱ የሆነው ‹‹ላይፍ›› መፅሄት መረጃዎችን በትክክል ሳይቀበል ግራቀኙን ሳይመለከት ‹‹ የሁለቱ ሲኖዶሶች ጉባኤ ያለ ስምምነት ተበተነ›› የሚል ዘገባ አውጥቷል፡፡ እንደ መረጃ ምንጭ የተጠቀመበት ድህረ ገፅ ተአማኒነቱን ሳያረጋግጥ በማውጣቱ በጣም አዝነናል፡፡ እኛ ይህን የመሰለ ዘገባ መዘገቡ በሁለት መልኩ ለማየት ተገደናል አንደኛ በቅን ልቦና ካሰብነው ፤ መረጃ በአግባቡ ሳይደርሳቸው ቀርቶ ይሆናል ብለን ብናስብም በሌላ መልኩ ሁለቱ ሲኖዶሶች እንዳይታረቁ እርቀ ሰላሙ ቤተክርስትያኗን ወደ አንድ ጎዳና እንዳይመራት የቤተክርስትያን አፅራረ ቤተክርስትያን ሀይሎች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በመገናኛ ብዙሀን የተሳሳተ ዘገባ በማቅረብ የእርቀ ሰላሙ ሂዳት ላይ ተፅህኖ እያሳደሩ ነው የሚል ግምት አለን፡፡ እኛም አንድ እንዳንሆን የቻሉትን ያህል ስራ እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ እንደ ‹‹ነጋድረስ›› የመሰለ ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘወትር ከአባ ሰላማ ድህረገፅ አዘጋጅ ጋር እጅ እና ጓንት በመሆን ሚዛናዊ ዘገባ ባለማቅረብ ምዕመኑን ማወዛገብ እና ትክክለኛውን እውነታ እንዳያውቅ እያደረጉት ይገኛሉ ፡፡ ቤተክርስትያኗ ሌላ የማያባራ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ የቻሉትን ያህል ቀን ከሌት ለእኩይ አላማቸው ያለ ድካም እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡ በዚህ አጋጣሚ አባ ሰላማ የሚባለው የድህረ ገፅ አዘጋጆች ከነጋድረስ ጋዜጣ ጋር ምን አይነት ግንኙነት እዳላቸው ፤ ምን ያህል ጊዜ ፅሁፍ እንደላኩላቸው ፤ ምን ያህሉን በጋዜጣ እንደወጡላቸው ፤ ምን ያህሉን ደግሞ በህግ ስለሚያስጠይቅ በጋዜጣቸው ላይ እንዳላወጡት መረጃ አለን ፤ 90 በመቶ ዘገባዎቹ ገንቢዎች አይደሉም ፤ ሚዛናዊነትም ይጎላቸዋል ፤ የፃፉት ፅሁፍ አልበቃ ብሏቸው ጋዜጣው ላይ የተፃፈውን ፅሁፍ ከብሎጋቸው ጋር በማቆራኝት በመፅሀፍ መልክም አሳትመውታል ፡፡ ይህን አላማቸውን በሌሎች መፅሄቶች ላይ ማካሄድ ያመቻቸው ዘንድ ‹‹እንቁ››ን ለመሰሉ መፅሄቶች ፅሁፎቻቸውን ቢልኩም ፅሁፉ የጋዜጠኝነትን ምግባር ያልተከተለ እና ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ ስለሆነ ሳያስተናግዷቸው እና ከበር ሊመልሷቸው ችለዋል፡፡ እንደ ‹‹ማራኪ›› እና ‹‹ላይፍ›› የመሰሉ መፅሄቶች ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መልካም ያስባሉ መልካምም ይጽፋሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ሳናመሰግን የማናልፈው የእንቁ መፅሄት ሚዛናዊ የሆነ ዘገባ በማውጣቱ እውነታውን ማስቀመጥ በመቻሉ ምዕመኑ ምን እየተደረገ እንዳለ ሚዛናዊ ፅሁፍ በማቅረቡ ምስጋናችን ለመቸር እንገደዳለን፡፡
እውነቱ ግን ይህ ነው ፡፡ በእርቀ ሰላሙ በሰላም ተጠናቋል ፤ ለቀናት የተነጋገሩ አባቶች የጋራ መግለጫቸውን አውጥተዋል ፡፡ ሁለቱ ሲኖዶሶች አባቶች የእርቅ ድርድር በሰሜን አሜሪካ አሪዞና ስቴት በውጩ ሲኖዶስ በኩል ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ሊቀ ካህናት ምሳሌ፣ መላከ ገነት ገዛኸኝ፣ የቀረቡ ሲሆን። ከሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አትናስቴዎስ፣ ንቡረ ዕድ ኤልያስ ቀርበዋል። ሁሉም አባቶች ጉባኤው ሲጠናቀቅ አጀንዳቸውን ለአስታራቂ ኮሚቴው አቅርበዋል። መግለጫው ስለደረሰን ሙሉውን መግለጫ አቅርበነዋል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል
ቸር ወሬ ያሰማን ፤ ሁለቱ ሲኖዶሶት አንድ እንደሚሆኑ አንጠራጠርም ፤ አንድ የምንሆንበት ጊዜ ብዙ እንደማይርቅ ሙሉ እምነታችን ነው፡፡
‹‹አንድ አድርገን››
That is a good beginning. Let's pray to God to bring our church together, as we fast in the following 2 months. We need to respect their wishes and refrain from blaming anyone.
ReplyDeleteyemigermew neger ESAT yetebalew tv chanal yezgebew lela,ezih gare yemenanebew lela.enesu yezegebut biys biyas erat enkwan aberew lemebelat yethiopia sinodosoch lemebelat fekadegna edalehonuna,sayesemamu edetetenakeke new yemigeletsut....Amlakachen e/gr yerdan
ReplyDeleteI couldn't able to read the press release. Would you plz look for other means
ReplyDelete