Wednesday, March 5, 2014

ለክርስቲያን ጎሳው ማነው?



ዳንኤል አዲስ
(አንድ አድርገን የካቲት 26 2006 ዓ.ም)፡- ለክርስቲያን ጎሳው ማነው? ዘሩስ ከወዴት ነው? ወገንተኝነቱስ ለየትኛው ብሔር ነው? አለም በዲያቢሎስ ሃሳብ ታነክሳለች ፤ በክርስቶስ ሃሳብ ግን ትፀናለች አለም በዲያቢሎስ ወሬ ትከፈላለች  በክርስቶስ ግን አንድ ትሆናለች ዘርህ ማነው? ይሉኛል፡፡ እኔ ግን የክርስቲያን ዘሩ ምንድን ነው? እላቸዋለሁ፡፡ አማራ ነህ ? ይሉኛል አዋ አማራ ወገኔ ነው እላቸዋለሁ፡፡ ትግሬ ነህ? ይሉኛል አዋ ትግሬም ወገኔ ነው እላቸዋለሁ፡፡ ኦሮሞ ነህ? ይሉኛል አዋ ኦሮሞም ወገኔ ነው እላቸዋለሁ፡፡  ለትግሬ አድልቼ አማራን ጎድቼ ቢሆን ለአፍንጫዬ አድልቼ አይኔን እንደማጥፋት በቆጠርኩኝ ለአማራም አድልቼ ኦሮሞን ጎድቼ ቢሆን ለቀኝ እጄ አድልቼ ግራ እጄን እንደማስቆረጥ በቆጠርኩኝ፡፡ ነገር ግን እኔ ክርስቲያን ነኝ ክርስቲያንም ለመሆን ውዴታ አለኝ ክርስቶስንም ስለመምሰል ስራ አለብኝ እንግዲህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምናዊ ናቸው? እኔ ግን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጅ ነኝ ይህን እምነቴን የሚወስድብኝ አንዳች እንኳን ኃይል የለም ፡፡ ወይንስ አቡነ ሀብተ ማርያም ምናዊ ናቸው? እኔም የአቡነ ሀብተ ማርያም ልጅ ነኝ ይህን እምነቴን የሚቀማኝ አንዳች እንኳን ኃይል የለም ወይንስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምናዊ ናቸው? እኔም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልጅ ነኝ ይህን እምነቴንም የሚቀማኝ አንዳች እንኳን ኃይል የለም፡፡


ስለ ክርስቶስ በክርስቶስ ለክርስቶስ ልጃቸው ሆንኩኝ እኔም ስለዚህ በክርስቶስ የሆነ ሁሉ ወንድሜ እህቴ አባቴም እናቴም ነው:: ከክርስትናዬ ይልቅ ትግራዋይነቴ በልጦ ከሆነ ከክርስትናየ ይልቅ አማራነቴ አኩርቶኝ ከሆነ ከክርስትናየ ይልቅ ኦሮሞነቴ አይሎ ከሆነ እስካሁን በድቅድቅ ጨለማ እጓዛለሁ፡ የክርስትናውንም ብርሃን አላየሁም ፡፡ ነገር ግን እኔ በክርስቶስ የሁሉ ዘመድ ነኝ ኢትዮጵያም ርስቴ ናት ኢትዮጵያውያንም ወገኖቼ ናቸው፡፡ አንዷን ክርስትናዬን እወዳታለሁ አንዷ ኢትዮጵያዊነቴንም እወዳታለሁ፡፡ ክርስትና አንድ እንደሆነች ግማሽ መሆንም እንደማይስማማት ኢትዮጵያም አንድ ናት ጎዶሎ መሆን አይስማማትም፡፡ የክርስቶስም ሃሳብ ሁሉን አንድ አድርጎ በፍቅር ማኖር ሲሆን የዲያቢሎስ ሃሳብ ግን ሁሉን ከፋፍሎ እያናከሰ ማጋደል ነው፡፡ ነገር ግን እንደምን የብርሃን ልጆች በጨለማ ሰባኪወች ይመራሉ? እንደምን የፍቅር ክርስቶስ ልጆች ከጥላቻ አስተማሪወች ጋር ይተባበራሉ? ህይወት ነውና ወደ ክርስቶስ እንቅረብ የማይጠቅም ተራ ነውና ዲያቢሎስንና ሃሳቡን ግን እንቃወመው፡፡

14 comments:

  1. መልካም አገላለጽ ነው እንዲህ ያለውን ጽሑፍ ሁሌም ባነብብ አይሰለቸኝም፡፡ በብሎጋችሁ ሁልጊዜ መታየት ያለበት እንዲህ ዓይነት ጽሑፍ መሆን አለበት

    ምልካም ጾም

    ReplyDelete
  2. ቃለ ሕይወት ያስማልን።
    እግዚአብሔር የሚያስተውል ልቡናን ይስጠን።
    ፍቅርን ያድለን።
    አሜን።
    ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete
  3. It is good when we put our comments in writing, explain them in our speech, preach them with nice factual resource, etc. but why are we then not living with them practically? Why are we found doing the opposite when it comes to reality? We see people pointing 1 figure on someone about ethnicity & when we look back with the remaining folded 3 figures & ask the speaker saying what about you what are you really doing we rarely get a matching reality which is a worst behavior that endangers the efforts, goodwills, goodness & scarifications of the hard working & honestly true orthodox Christians. Yet no matter what we still have to encourage the good advice.

    ReplyDelete
  4. In addition to the comment I mentioned earlier I want to say that speaking ethnic language for religious or other purpose shouldn't be considered as ethnocentric. Language is just a means of communication amharic is not more blessed than oromifa or tigrigna or other language & vice versa. It is what we do or learn express or show through the languages that makes the difference between blessing & non blessing. We see people profiling as Weyane when they see Tgriga speaker, Oneg when they see oromifa speaker, Amhara( neftegna) when they see amharic speaker, etc but they pretend they are working for unity, they declare their race is Ethiopia, etc. It is when we stop such bias & profiling that a true orthodox christian spirited brotherhood & sisterhood prevail over ethnocentric attitude.

    ReplyDelete
  5. እግዚአብሔር ይመስገን ማህበር ቅዱሳን ብሎግ ላይ ደህና ነገር አነበብን እንዲህ ነው ክርስትና ሁሉ በክርስቶስ አንድ መሆኑን መስበክ እኔ የኬፋ ነኝ እኔ የአጵሎስ ነኝ አትበሉ ክርስቶስ የሞተው ለአዳም ዘር ሁሉ ሁሉን ሊያድን ነውና አሁን ጌታ እየረዳችሁ ነው፡፡ ጊዜው ቀርቧልና ሰውን ወደ ክርስቶስ በማቅረብ ልንበረታ ይገባል፡፡ ስለሰው ሀጥያት ከማውራት ተጠብቃችሁ እንዲህ እንደ ክስርቲያን ስታወህሩ ደስ ይላል፡፡ እንግዲህ አምላካችን ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን፡፡ አሜን

    ReplyDelete
    Replies
    1. hi sergut, how says this is the blog of MK?

      Delete
  6. kale hiwot yasemaln

    ReplyDelete
  7. ክርስትና አንድ እንደሆነች ፡ ግማሽ መሆንም እንደማይስማማት ፡ ኢትዮጵያም አንድ ናት ፡ ጎዶሎ መሆን አይስማማትም

    ReplyDelete
  8. qale hywet yasemaln.

    ReplyDelete
  9. wondime hih Yemahibere kidusan blok aydlem ante alemehonu teftoh sayhon hon bleh sewn litasaste new
    bihonme gin memesgenem Yalebachew baleblogochu nache. Yeማህበር ቅዱሳን
    blog www.eotc-mkidusan.org new.

    ReplyDelete
  10. aye sirgu kentu nesh yi thefachew alehubet yemitiyiw hiywot enquan ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,.

    ReplyDelete
  11. I wonder how this article is posted here. This is really wonderful and please keep it up.

    Selam

    ReplyDelete
  12. What a great article!
    It shows that Christianity is (and should be) practiced beyond the boundaries of race, color, economic status , nationality, etc. Orthodox Tewahedo has been and will be teaching this good christian practice. But, some groups try to dismantle the Church using our ethnic diversity. We should be alert to such groups and strength our christian unity. Jesus suffered and died to save all mankind regardless of our race and ethnic group.
    God save our Church.

    ReplyDelete
  13. What a great article!
    It shows that Christianity is (and should be) practiced beyond the boundaries of race, color, economic status , nationality, etc. Orthodox Tewahedo has been and will be teaching this good christian practice. But, some groups try to dismantle the Church using our ethnic diversity. We should be alert to such groups and strength our christian unity. Jesus suffered and died to save all mankind regardless of our race and ethnic group.
    God save our Church.

    ReplyDelete