Sunday, March 16, 2014

ሃይማኖት ፤ ብሔር እና የቁጥር ጨዋታ


(አንድ አድርገን መጋቢት 8 2006 ዓ.ም)፡- ከሁለት ወር በፊት በኢንተርኔት ላይ በተለቀቀ አንድ የቪዲዮ ምስል ላይ አቶ ጅዋር መሀመድ በርከት ያሉ ሰዎች በሚገኙበት አዳራሽ እስልምና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 98 በመቶ እንደሚሆን እና ኦሮሞነትን ለእስልምና ጋር አንድ ላይ አድርጎ ማስኬድ እንደሚቻል ፤ አንድም መሆን እንዳለባቸው ሲናገር ነበር፡፡ ይህን የተመለከቱ ሰዎች እውን እስልምና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ምን ያህል በመቶ ነው? ጅዋር እንዳለው 98 በመቶ ወይስ…? በማለት ጥያቄ ሲያነሱ ተስተውሏል፡፡ አቶ ጀዋር ‹‹98 በመቶ በኦሮሚያ ክልል የምንገኝ ሰዎች ሙስሊሞች ነን›› ብሎ ሲናገር ተሰብሳቢው ጆሮውን ብቻ ሰጥቶ ሲያደምጥ ይስተዋላል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን በአንዱ ብሔር ጠርዝ አቁመው የብሔረሰቡ ታጋይ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች የማሕበረሰቡን ትክክለኛ ቁጥር ሲቀበሉ አይስተዋልም እስኪ በኢትዮጵያ ውስጥ በ1999 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ ስሌት መሰረት አማኝ ብዛት በዘጠኙ ክልሎች ምን ይመስላል የሚለውን መሰረት በማድረግ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ 

ክልል
ኦርቶዶክስ %
ፕሮቴስታንት %
ካቶሊክ %
ሙስሊም %
ትግራይ
96.7
0.0
0.3
2.9
አፋር
1.4
0.4
0
98.1
አማራ
83
0.1
0
16.8
ኦሮሚያ
27.5
17.8
0.5
49.9
ሶማሊ
0.1
0.0
0.0
99.1
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
29.8
12.6
0.6
48.2
ደቡብ
17.8
56.7
2.5
14.2
ጋምቤላ
14
73.4
3.1
3.7
ሐረሪ
1.8
0.3
0.0
97.9
አዲስ አበባ
74.7
7.8
0.5
16.2
ጠቅላላ
43.5
18.6
0.7
33.9
v  0.0 % ማለት ምንም አማኝ በክልሉ የለም ሳይሆን ከሌሎች ጋር በተነጻጻሪነት ሲቀርብ ወደ ዜሮ ይጠጋል ለማለት ነው፡፡

3 comments:

  1. k10 ametu gar degmo bitanetsaherw degmo arif nber...

    ReplyDelete
  2. ጅዋር መሀመድ ጽንፈኛ የሆነ ሰው ሲሆን ሲፈልግ አንድ ጊዜ ለኦሮሞ ህዝብ አንድ ጊዜ ለእስልምና ሃይማኖት ተከራካሪ በመምሰል ተቻችሎ የሚኖርን ህዝብ ለመበታተን የተነሳ ያለበሰለ ጥሬ ፖለቲከኛ ነው

    ReplyDelete
  3. he is not an ethiopian ...please guyes go and work with your collageu ...terioriest

    ReplyDelete