Tuesday, March 25, 2014

የበረከት ጉዞ


(መጋቢት 16 2006 ዓ.ም)፡- በኢትዮጵያ በረሃዎችና አውራጃዎች እየተዘዋወሩ በልዩ ልዩ አምልኮ የነበረውን ሕዝብ የክርስቶስ ወንጌለ መንግሥትን አስተምረውና አጥምቀው የክርስቶስን መንግሥት እንዲወርሱ ያደረጉት  ቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግዚአብሔር በመራቸው መሠረት የሐዋርያ አሠረ ፍኖት በመከተል ዘር ልዝራ ትዳር ልያዝ ሳይሉ ታላላቅ ተዓምራትን ካከናወኑባቸው ቦታዎች  ውስጥ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከደብረ ብርሃን አካባቢ የሚገኝው ወይንዬ ተክለ ሃይማኖት ስፍራ አንዱ ነው፡፡ ይህ ቦታ የሚገኝው ከደብረ ብርሃን ከተማ  በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በግምት 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቀጥ ባለ ገደል ተከቦ ሲሆን እዚህ ቦታ ላይ ጻድቁ አቡነ ህጻኑ ሞአ የተወለዱበትና እንደ በሬ ተጠምደው በማረስ ገድላቸውን የፈጸሙበት ታላቅ ስፍራ ይገኛል፡፡ በዚሁ ስፍራ ላይ ‹‹እስትንፋስ›› የሚባል ቦታ ከመሬት ሳያቋርጥ በሚወጣው እስትንፋስ አማካኝነት በርካቶች ከተለያዩ በሽታዎች የዳኑበትና እየዳኑ የሚገኙበት ልዩ ስፍራ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በቦታው ቀድሞ  ከኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ትላልቅ ገዳማት የመጡ አባቶች የሚያገለግሉበትና የሚገለገሉበት ቦታ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በካህናት እጦት የተነሳ አገልግሎቱን የማይሰጥበት ደረጃ ይገኛል ፡፡ 
 
የገዳሙ ሰበካ ጉባኤ በቀጣይ መጋቢት 27 ምዕመናንን ወደ ቦታው በመውሰድ የቦታውን ታሪክ ፤ የተጀመረውን ቤተክርስቲያን እና የአብነት ተማሪዎችን ሁኔታ  ለማሳየት  አንድም ቀጣይ መፍትሄ ለመሻት በሌላም በኩል የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጉዞ አዘጋጅቷል፡፡ እርስዎም የዚህ የተቀደሰ አላማ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡


መነሻ ቀን ፤ - መጋቢት 27 2006 ዓ.ም
              ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
መመለሻ ቀን፡-  መጋቢት 28 28 2006 ዓ.ም

በጉዞው፡-
  • አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወይን ተክለው ለ12 ዓመታት በቦታው በመቀመጥ ሲጸልዩበት የነበሩበትና በርካታ ተዓምራትን ያከናወኑበት  ፤ ጸበል አፍልቀው አህዛብን ሲያጠምቁበት የነበረውን ቦታ ያዩበታል፡፡
  • ጻድቁ አቡነ ህጻኑ ሞአ የተወለዱበትና እንደ በሬ ተጠምደው በማረስ ገድላቸውን የፈጸሙበት ታላቅ ስፍራን ይመለከቱበታል፡፡
  • ያለማቋረጥ ለዘመናት የሚተነፍሰውን መሬት ‹‹እስትንፋስን›› ይመለከቱበታል ፡፡
  • የቦታውን የቀደመ ታሪኩን ያውቁበታል ፤ ዛሬን ያዩበታል ፤ ነገን ያሳስብዎታል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0911-616317 ይደውሉ
የገዳሙ ሕንጻ አሰሪና ሰበካ ጉባኤ

No comments:

Post a Comment