Thursday, March 13, 2014

ተረፈተሀድሶ በደብረ ብርሃን


(አንድ አድርገን መጋቢት 2 2006 ዓ.ም)፡- ባገኙት አጋጣሚ ራሳቸውን በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በመሰግሰግ ከዋኖቻቸው የተሃድሶ መናፍቃን የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በሰጧቸው ስትራቴጅ መሰረት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከቱ ህግ ክፍል ኃላፊ መ/ር አክሊል አንዱነው፡፡ እስካሁን በብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ጸሎትና ተሀድሶ በሃገረ ስብከታቸው እንዳይገቡ በወሰዱት ቆራጥ አመራር ሀገረ ስብከቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ያደረጉ ቢሆንም መጋቤ ሀዲስ ይልማ ቸርነት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ‹‹ጥሩ ማገልገል ይችላሉ›› በማለት ወደ ሀገረ ስብከቱ አባ ማርቆስ ብርሃኑ እና መ/ር አክሊል በሀገረ ስብከቱ ሾልከው እንዲገቡ እድል አግኝተዋል፡፡

‹‹መምህር›› አክሊል ማነው ምንስ እየሰራ ይገኛል
ቀደም ሲል በደ/ብርሃን ጠባሴ ደብረ ሰላም መድኃኔአለም እና ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በድቁና ሲያገለግሉ በነበሩበት ወቅት ዘመቻ ፊሊፖስ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በነአባ ዘውዱ እና አባ ዮናስ አማካኝነት በደ/ብርሃን ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት በነበረው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ከአባ ዘውዱ ርዝራዦች ኑፋቄን የቀሰሙት ‹‹መምህር›› አክሊል ቅዱስ ጊዮርጊስ የነበረውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በአላማ የሚመሳሰሏቸው አገልጋዮች ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት በመኖራቸው ከጠባሴ እየተመላለሱ አጥቢያቸውን በመተው በቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት ቤት ያገለግሉ ነበር፡፡ ከዚያም የጀመሩትን አላማ በተሳካ ሁኔታ ማስፈጸም ይችሉ ዘንድ በቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመግባት ከመሰሎቹ ጋር በመሆን እንቅስቃሴውን በኮሌጁ በህቡዕ ሲያጠነክሩ ከቆዩ በኋላ እነ በጋሻው ደሳለኝ ከኮሌጁ በተባረሩበት ወቅት አብሮ ከኮሌጅ አብሮ ተባሯል፡፡ከዚያ በኋላ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጁ ተመልሶ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከምረቃ በኋላ አዲስ አበባ እውነታኛ አገልጋይ መስሎ ከቤተክርስቲያን ልጆች በመጠጋት በመላላክ አንዳንድ ስራዎችን ይሰራ በነበረበት ወቅት ሀገረ ስብከቱ በወጣት ሀይል ተደራጅቶ የተጠናከረ አገልግሎት እንዲፈጸም የተወሰነውን አጋጣሚ በመጠቀም በመጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት በተደረገለት ጥሪ በሀገረስብከቱ ህግ ክፍል ሃላፊ ሆኖ ከተቀጠረ በኋላ የሚከተሉትን የተሀድሶ ስትራቴጅዎችን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡

1.  ስልታዊ በሆነ መንገድ የተሃድሶ ኑፋቄዎችን ማስፋፋት ከነዚህም አንዱ በሀገረ ስብከቱ ካህናት ማሰልጠኛ የ2003 .ም ሰልጣኞች ለሚማሩ ተማሪዎች ‹‹አማላጅ ኢየሱስ ነው›› በማለት ያስተማረ ሲሆን በወቅቱ በተማሪዎቹ መካከል አከራካሪ ሃሳብ በማንሳት በመካከላቸው ነውጥ እንዲፈጠርና የእምነት መሰረታቸውን እንዲስቱ የማድረግ ስራ ሰርቷል፡፡

2.  በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ገዳማትን ማተራመስ ፤ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ማዳከም እንዲፈቱ ማድረግ አንዱ የሚፈጽመው ተልዕኮ ሲሆን ፤ በደብረ ብስራት አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ለገዳሙ መፋታትና ለገዳማውያኑ መበተን ዋናው ተዋናይ ይህ ግለሰብ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ካሉ ጥቅመኞችና ከወረዳ ቤተክህነቱ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በገዳሙ ያሉ ተቀጣሪ ካህናትን ለአመጽ በማነሳሳትና ለአቤቱታ በሃሰት ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት እንዲሄዱ በማድረግ ብጹዕነታቸው ገዳሙ እንዳይፈታ ከዕነዋሪና ከደነባ የተውጣጣ ኮሚቴ በማቋቋም በገዳሙ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱና መናንያኑም ወደ ባዕታቸው እንዲመለሱ ባደረጉበት ወቅት ችግሩ እንዳይፈታ ለሁለተኛ ጊዜ ካህናትን ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ለአቤቱታ እንዲሄዱ በማድረግ ብጹእነታቸውን ሀገር አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅት ደብዳቤ አዘጋጅቶ ብጹዕነታቸውን በማሳሳትና በማስፈረም በቅዱስ ፓትርያርኩ የተሾሙትን የገዳሙን አበምኔት በህገወጥ መልኩ በመሳገድ መናንያኑ እንዲበተኑ ተደርጓል፡፡  በሌሎች ገዳማት ማለትም ሚዳ አቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ፤ ሳማ ሰንበት ገዳም አስተዳዳሪውን ከካህናትና ከምዕመናን በማጋጨት በፈጸመው ሴራ በአረርቲ ፍርድ ቤት ተከሷል ፤ ደብረ ከርቤ ዳግማዊ ጎልጎታ ገዳም አበምኔቱን ከመናንያኑ ጋር በማጋጨት መስቀሌ መድኃኔአለም ልማት ኮሚቴውንና ገዳሙን በማጋጨት በአጠቃላይ በየገዳማቱና በየአጥቢያዎቹ በሚፈጸሙ ችግሮች በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ በመግባት በማተራመስ ላይ ይገኛል::

3.  የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ማዳከም አንዱ ሲሆን በተለይ በአጣዬ ፤ በበረሀት ፤ በለሚ ፤ በመዳወረሞ በደብረሲና ፤ በእነዋሪና በአንጾክያ ወረዳዎች በቤተክህነት በሰበካ ጉባኤና በሰንብት ት/ቤት መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ የሰ/ት ቤት አገልግሎት እንዲዳከም በአውደምህረት የሚሰጡ ትምህርተ ወንጌል እንዲቋረጡ በማድረግ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ በሀገረ ስብከቱ ካሉ ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ የሁከት ቤት እንድትሆን በማድረግ በምዕመናን እንድትጠላ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

4.  እውነተኛ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ማሳደድ ተስፋ ማስቆረጥ

5.  የክህነትን ክብር ዝቅ ለማድረግ የማይገባቸውን ክህነት እንዲያገኙ ማድረግ ፤ ብጹዕነታቸውን በማሳሳት እና በሌሎችም ወረዳዎች ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ  ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ለአላማቸው ተገዥ የሆኑትን ሰዎች ክህነት እንዲቀበሉ አድርጓል

6.  ተሀድሶዎችን ማበረታታትና መረጃዎችን መስጠት፡፡ ለምሳሌ በነበረባቸው የተሃድሶ ኑፋቄ በብጹዕነታቸው የታገዱት የደ/ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩት ‹‹አባ›› ማርቆስ ብርሃኑ እንደይታገዱ በወቅቱ ብጹዕነታቸውን ለማሳመን ጥረት ሲያደርግ “ይህንን ከተቃወማችሁ እናንተም ችግር አለባችሁ” ስለተባለ ለጊዜው የተደናገጠ ሲሆን ለምስክርነት በብጹዕነታቸው ፈት የቀረቡትን ካህናትና ምዕመናንን ማመናጨቅና ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ የነበረውን የጸረ ተሀድሶ ዘመቻ ለማደናቀፍ ከአባ ማርቆስ አላማ አስፈጻሚዎች ጋር በየሆቴሉ በሚያደርጉት ስብሰባ ለማደናቀፍ ጥረት ቢያደርግም አላማው የከሸፈ ቢሆንም ከተባረሩም በኋላ በሀገረ ስብከቱ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን ለአባ ማርቆስ አሾልኮ በመስጠት እንዲመለሱና የጋራ ተልዕኮአቸውን ለማስፈጸም ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
7.  አብያተ ክርስቲያናትን መመዝበር ለምሳሌ በደ/ብርሃን ጠባሴ ገብርኤል በአገልጋይ ካህናት መካከል ከፍተኛ የአስተዳደር በደል እንዲደርስ በማድረግ ችግራቸው ተባብሶ የጸጥታ ችግር በመሆኑ የዞኑ አስተዳደርና ጸጥታ ሰብስቦ ያለው ችግር ብጹዕነታቸው በተገኙበት ችግራቸውን እንዲያቀርቡ ቢደረግም ከህናቱ ችግራቸውን እንደይናገሩና መፍትሔ እንዳይሰጣቸው በማስፈራራታቸው ትዝብት ውስጥ ጥሎአቸዋል፡፡ ከአስተዳዳሪው ጋር ባላቸው የጥቅም ትስስር ከፍተኛ ብር ለህንጻ ገቢ የተደረገው እንዲመዘበር ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በህዝብ አቤቱታ ከቦታው ላይ የተነሱት የቀድሞው የጠባሴ ገብርኤል አስተዳዳሪ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ ኦዲት እንዳይደረግ ታፍኖ እንዲቀር ከግብረ አበሮቹ ጋር አድርጓል፡፡

8.    ይህ ሰው በሀገረ ስብከቱ ሁለት ቦታ ተቀጥሮ በሁለት ስራ ሁለት ደመወዝ እያገኝ ይገኛል፡፡ እንደ አስተዳደራዊ መመሪያ አንድ ሰራተኛ በአንድ ተቋም ውስጥ ሁለት ቦታ ተቀጥሮ መስራት እንደማይችል ይታወቃል ሆኖም ይህ ሰው  የሐገረ ስብከቱ የህግ ክፍል አላፊ በመሆን እንዲሁም በልማት ኮሚሽን የሴት ልጅ ግርዘትና ፕሮጀክት አስተባባሪ በመሆን ሁለት ቦታ ተቀጥሮ በሁለቱም ደመወዝ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ 

4 comments:

  1. Thank you for your on time information.

    This may be the write time to comment on < Like' Mezemer Mengiste Hailiye > on his mesery deba on the church. Debre berhan should be cleared by the strong measure of Abune Ephrem. Let God give strength to Our father abune Ephrem. Like' Mezemer seems honest on Oude mihret, but cruel inside the church administration. He must be left home by < tureta>, other wise we will fight to.

    Yekoselew tazabi from addis abeba

    ReplyDelete
  2. thanks for your on time information.i know realy it was occure what you have talk ....but others didnot know it so i would like to say thanks for your correct info

    ReplyDelete
  3. betam enazinalen betekristiianachinine egziabiher yitebikilin kemanim belay lebeterchristian yemiyasib amilak alen egziabiher betechristianachinin yitebikilin

    ReplyDelete
  4. Ewnetu ewnet newu. Gin Sintun weksen kesen enzelkalen? Members of sunday schools and mahibe kidusan and largely members of sebeka gubaei yemiawkutin hulu yemaynagerut eko sintu tewekso yizelekal belew newu. Abro eyeseru andandun mot sigelagilew andandun ykfawe hatiyatu brasu siyarekew eyayu keriwen lefetari masasbe yishala elalehu. beye hagere sibeketuna dberu sinte ale meselachu. Esti ande negeren entewachew. Gin eniketatelachew. YERASACHININIM HIWOT anersa. Yenesun yenesun becha sinasib tesfa enkrtalen. Betekristian Tebakiwa AYTEGNAM AYANKElAFAM. Abet zemenu endet kefa!!!! Lemesheshegia kesum menekusewem ye politika derejit agobedaje honena Egziabeheren erestona defero balesiltanatune tegen aderege. Weyo zemenu siasfera. Gin Enitsina. Yewah Yetselot Abatachin Abune Ephrem Tsinat Endayatu yaderegilin.

    Dekamaw ke sheno

    ReplyDelete