Saturday, March 22, 2014

ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ኢቲቪ ሊያዘጋጅ ነው

‹‹ፋክት›› ከወራት በፊት ይዛ የወጣችው የፊት ገጽ……
 (ፋክት መጋቢት 13 2006 ዓ.ም ) ፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡


መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው 2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡


በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎየአገልግሎት ቅኝቱን የማስተካከልዓላማ እንዳላቸው የገለጸው የዜና ምንጩ፣ ይህም ካልተሳካ በተከታታይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችና የተቃውሞ ቅስቀሳዎች ማኅበሩን በማወከብ ተቋሙን ለዘለቄታው የማፍረስ ውጤት ሊኖረውም እንደሚችል አመልክቷል፡፡

ከአዲስ አበባ /ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች የሚሳተፉበት እንደኾነ የተገለጸና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማኅበሩ አገልግሎት ላይ ቁጥጥሩን እንዲያጠብቅ የሚጠይቅ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በቤተ ክህነቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሔድ የተዘገበ ሲኾን ዓላማውም ‹‹በአክራሪዎችና ጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግነት፣ የቤተ ክህነቱን አሠራር ባለማክበርና ከቤተ ክህነቱ በላይ ገዝፎ በመውጣት›› ማኅበሩ የሚከሰስባቸውን ኹኔታዎች በማጠናከር ለታቀዱት ርምጃዎች የሚያመቻች ነው ተብሏል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን÷ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በማተኮር የተማረው ትውልድ ሃይማኖቱን የሚወድ፣ ግብረ ገብነት ያለው፣ ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በሞያውና በገንዘቡ የሚያገለግል ብቁ ዜጋ ይኾን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በመሥራት ላይ እንዳለ የሚገልጹ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎቹ፣ ማኅበሩ ለቀረቡበት ክሦች የሚመች አደረጃጀት ይኹን ባሕርይ እንደሌለው በመግለጽ ተጠሪ ከኾነለት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ በአሠራር ሒደት የሚፈጠር ክፍተትን በማጦዝ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

የተጠቀሱትን ክሦች ለሚያቀርቡት አካላት ‹‹የሚነገረውና የሚጻፈው እኛን የሚገልጸን ስላልኾነ ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለሠለጠነ ውይይት ፍላጎት እንደሌላቸው አባላቱ አስረድተዋል፤ በምትኩ ‹‹ርምጃ እንወስዳለን›› በማለት በተለያዩ መድረኮች ማኅበሩን ማሳጣትና መክሠሥ እንደሚመርጡም ፋክት መጽሔት አስታውቀዋል፡፡ ታቅዷል የተባለው የዶኩመንተሪ ዝግጅት እውነት ከኾነም ማኅበሩን ብቻ ሳይኾን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አጠቃላይ ዘመቻ አንድ አካል አድርገው እንደሚቆጥሩትና በቀላሉ እንደማይመለከቱት አሳስበዋል፡፡

13 comments:

 1. The challenge on MK is not new. Since it is of the church, MK will bear what ever the challenge coming on the church. People, few Government officials are doing their assignment of breaking the church for a) Political mission, b) for religious interest. Strong church and strong Mosq are both ' threats ' of weak state. Therefore, we must not blame them; they are strong for their vision and Mission. The problem is we members of the tewahido church are very loose, ..... As one said << Enen yasichenekegn yetelat rucha sayhon yewedag zimita newe >. Any way let Government try his best. The corner stone of the church will damage who ever is challenging the church, be it GOV, Tehadiso, Tikmegna sewoch, Yehaset Mereja sechi Nibure Ed, Aba, ..... The documentary film might bring another documentary in another direction. Like that of Yebilate Zemecha, it brings unity for the church new generation. Yekidusan Enba endihu ayfesim.

  ReplyDelete
 2. ኢህአዴግ ምን ነካው ዝም ብሎ ከሁሉም ጋር ሁሉ ጋር ይላተማል እንዴ?ማህበረ ቅዱሳን ምን አደረገ? የአመራር አባላቱስ ከዘራፊና ውሸታም የኢህአዴግ አመራር አባላት በጣም የተሻሉ ህይወትና ራሳቸውን ለመልካም ነገር የሰጡ አኮ ነው! ኢህአዴግ በቃ ምንም አማካሪ የለውም! በቁሙ የሞተ ድርጅት ሆነ! እስቲ ዶክመንታሪውን ያውጣና ምን እንደሚፈጠር ያያል!

  ReplyDelete
 3. ከነርሱ ጋር ካሉት ከኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉና አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠረም
  ስለ ተዋህዶ እንሆናለን ሁሉን

  ReplyDelete
 4. በዚህም ተባለ በዛ ማኅበሩን ማዳከም ቤተክርስቲያንን የማጥቂያ አንዱ መንገድ ነው :መናፍቃን ዛሬም በ አዲሱ ፓትርያርክ የልብ ልብ ያገኙ ይመስላሉ ::ለማንኛውም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ ::ጠላት ዲያብሎስንም ያስታግስልን :

  ReplyDelete
 5. ልንፀልይ ይገባናል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አነዚያ በሠረገላ አነዚህም በፈረሶቻቸው ይመካሉ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ……..እነዚህ ሰዎች እየመሸባቸው ይሆን ………

   Delete
 6. ፈተና ለክርስቲኖች የበረከትና የጸጋ ምክንት ነው! ዋናው ነገር በፈተና ጌታ እንዲያጸናን የሱ ፈቃዱ ይሁንልን!

  ReplyDelete
 7. ፈተና ለክርስቲኖች የበረከትና የጸጋ ምክንት ነው! ዋናው ነገር በፈተና ጌታ እንዲያጸናን የሱ ፈቃዱ ይሁንልን!

  ReplyDelete
 8. ከነርሱ ጋር ካሉት ከኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉና አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠረም
  ስለ ተዋህዶ እንሆናለን ሁሉን

  ReplyDelete
 9. አነዚያ በሠረገላ አነዚህም በፈረሶቻቸው ይመካሉ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ……..እነዚህ ሰዎች እየመሸባቸው ይሆን ………

  ReplyDelete
 10. እንደኔ እንደኔ መንግስት ለዚህ ዕኩይ ተግባርና አላማ መነሳቱ ብቻውን ተጠያቂ አያደርገውም ባይ ነኝ ምክንያቱም የዚችው ቤተክርስቲያናችን የበላይ ሃናፊዎች ናቸው የገዛ ልጆቻቸውን በሐሰት እየወነጀሉና አዲስ ስም እየለጠፉ አሳልፈው በመስጠት ላይ ያሉት። እኛ ምዕመናዕን ደግሞ በካባ ውስጥ ተደብቀው እነምላን ምን እየሽረቡ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው። ክርስትና ደግሞ እንደቀደሙት ፈሪሳውያን ካባን አንዠርጎ በመሄድ ሳይሆን በተግባር የሚታይ መሆኑን የዚህ ዘመን ትውልድ ጠንቅቆ ያውቃልና ስለዚህ እኛ የቀደሙት አባቶቻችን እንዳስተማሩን በጎ ጎዳና የሚያሰተምሩንን እንከተላለን። እያወቁ ለሚያጠፉት ግን እግዚአብሔር አምላክ ልቦናቸውን ወደራሳቸው ይመልስልን አሜን።

  ReplyDelete
 11. እንደኔ እንደኔ መንግስት ለዚህ ዕኩይ ተግባርና አላማ መነሳቱ ብቻውን ተጠያቂ አያደርገውም ባይ ነኝ ምክንያቱም የዚችው ቤተክርስቲያናችን የበላይ ሃናፊዎች ናቸው የገዛ ልጆቻቸውን በሐሰት እየወነጀሉና አዲስ ስም እየለጠፉ አሳልፈው በመስጠት ላይ ያሉት። እኛ ምዕመናዕን ደግሞ በካባ ውስጥ ተደብቀው እነምላን ምን እየሽረቡ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው። ክርስትና ደግሞ እንደቀደሙት ፈሪሳውያን ካባን አንዠርጎ በመሄድ ሳይሆን በተግባር የሚታይ መሆኑን የዚህ ዘመን ትውልድ ጠንቅቆ ያውቃልና ስለዚህ እኛ የቀደሙት አባቶቻችን እንዳስተማሩን በጎ ጎዳና የሚያሰተምሩንን እንከተላለን። እያወቁ ለሚያጠፉት ግን እግዚአብሔር አምላክ ልቦናቸውን ወደራሳቸው ይመልስልን አሜን።

  ReplyDelete