Saturday, March 15, 2014

አብደው ሊያሳብዱን የሚፈልጉት ‹‹ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያሳውያን››



  • “ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ተጠየቀ
  • መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
  • ደብዳቤው ለእስራኤሉ /ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል፡፡

   (አዲስ አድማስ መጋቢት 6 2006 ዓ.ም)፡- ከተፃፈ 2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡   ማህበሩ፤የመጽሐፉን ኮፒዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ለብፁዕ አቡነ ማትያስ  ህዝቡን እንዲያስተምሩበት ከሚያሳስብ ደብዳቤ ጋር መላኩን አስታውቋል፡፡


አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አባል የሆነችበት ማህበረ ሥላሴ፤ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ለሁለት ሺህ ዘመን ስትጠብቀው የቆየችውን ምስጢራዊ መጽሐፍ በአደራ የመረከብና ለዓለም ሁሉ የማሳወቅ ፅኑ ኃላፊነትን ይመለከታልበሚል ርዕስ ለፓትርያርኩ፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትናሁ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው  ደብዳቤማህፈድ ብርህት ዘዲዮስቆሮስ አንበሳበሚል ርዕስ በግዕዝ ቋንቋ የተፃፈውን መጽሀፍ፣ የቤተ-ክርስቲያኗ ሊቃውንት ተቀብለው ምእመናኑን ስለ ቅዱስ ኤልያስ እና ትክክለኛይቱ ሰንበት እንዲያስተምሩበት አሳስቧል፡፡
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከው ኢትዮጵያና እስራኤል በመንፈሣዊ አሰራር አንድ ስለሚሆኑበት ሁኔታ ለማመልከት ነው ያሉት የማህበሩ አመራሮች፤ለተባበሩት መንግሥታት የተላከውም መልእክቱ ለዓለም ሁሉ እንዲዳረስ ስለሚፈለግ ነው ብለዋል፡፡

2 ሺህ ዓመታት በፊት እንደተፃፈ የሚነገርለት መጽሐፉ፤ ስለ ቀዳሚት ሰንበት ምንነትና ዘለዓለማዊነት በግልፅ እንደሚያብራራ እንዲሁም የኢትዮጵያና የእስራኤልን አንድነትና ትንሳኤ ምስጢር ተንትኖ እንደሚያስረዳ ተጠቁሟል፡፡

ማህበሩ በላከው መልዕክት፣ ቅዱስ ኤልያስ ከብሄረ ህያዋን ይዞት የመጣውን መጽሀፍ፣ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት እንዲመረምሩት፣ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲተረጎምና እንዲታተም፣ ምዕመናንም እንዲያነቡት የማድረግ ግዴታ ፓትርያርኩ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ይህ ሳይሆን በእንቢተኝነትና በቸልታ ለዘመናት በተስፋ የተጠበቀውን ይህን መጽሀፍ እንዳይቀርብ ቢያደርጉ፣ ከብሄረ ህያዋን የመጣው ቀናኢ ነቢይ ዓለምን ሁሉ እየገሰፀ ባለበት ኃያል፣ ስልጣኑ ፅኑ ፈራጅነቱና ቁጣው የሚፈርድ መሆኑን አረጋግጠን እንነግርዎታለንብሏል፡፡ለቤተ-ክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ እና ካህናት ጥፋትና የመጨረሻው ውድቀት ነውሲልም ለመፅሃፉ ትኩረት እንዲሰጥ ማህበሩ  አበክሮ አሳስቧል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ የፓትርያርኩን /ቤት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን /ቤት በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡



የዚህ ማህበር መስራች(‹‹አባ›› ዮሴፍ) የጀርባ ታሪክ…. ይጠብቁን

5 comments:

  1. የዚህ ማህበር መስራች(‹‹አባ›› ዮሴፍ) የጀርባ ታሪክ…. ይጠብቁን በጉጉት ነው የምንጠብካችሁ በርቱ ተበራቱ
    አቤቱ ርስትህን ባርቅ አሜን

    ReplyDelete
  2. የቀውስ ስብስብ :የሰይጣናት ስብስብ ማህበር:ስሙን አሳምረው ባይረብሹን ምነው ?ሐይ ባይ የጠፋበት ሀገር ሆነ እኮ?

    ReplyDelete
  3. Ye enezih Chiferam yetim aydersme. Bicha tsenten mekom new. Zemenu yaleke newna rasachinen entebik.

    Tesfaye from hawasa

    ReplyDelete
  4. i used to play football with this guy. 15 field

    ReplyDelete