Sunday, March 30, 2014

በአደጋ ላይ ያሉት የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በአስቸኳይ እንዲጠገኑ ፓርላማው አሳሰበ


(ሪፖርተር መጋቢት 21 2006 ዓ.ም)፡- ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት በንጉሠ ነገሥቱ ቅዱስ ላሊበላ (1173 ..-1213 ..) አማካይነት የታነፁትና በአደጋ ላይ የሚገኙት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በአስቸኳይ እንዲያስጠግን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) አሳሰበ፡፡
በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡትን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የደረሰባቸውን የመሰነጣጠቅ አደጋ ጎብኝቶ የነበረው የፓርላማው የባህል፣ የቱሪዝምና የመገናኛ ብዙኀን ቋሚ ኮሚቴ፣ ባለፈው ረቡዕ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተጠሪ መሥሪያ ቤቶች ጋር ባደረገው ውይይት፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የመሰነጣጠቅ አደጋ የደረሰባቸውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለመጠገን የያዘውን ዕቅድ በአፋጣኝ ይተግብር ብሏል፡፡

በሚኒስቴሩ የተጠሪ ተቋማት የመንፈቅ ዓመቱ አፈጻጸም የተመለከቱት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ / ፈትያ ዩሱፍ፣ ቅርሶቹ የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸውና ይዞታቸውን ጠብቀው ለዘለቄታው እንዲቆዩ ለማድረግ ባለሥልጣኑ የያዘውን የጥገና ዕቅድ በፍጥነት መተግበር እንደሚገባው አሳስበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ባለፈው ጥር 12 ቀን ሚኒስቴሩን ስለላሊበላ ቅርሶች ባነጋገረበት ጊዜ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ በተለይም ቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ጎልጎታ፣ ቤተ አባ ሊባኖስ፣ ቤተ መርቆሬዎስና ቤተ ደናግል በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ከላከው ቡድን መረዳቱን ለኃላፊዎቹ ሪፖርት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ፣ ከሦስት ወራት በፊት  ተቋማቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን፣ በመጪዎቹ ወራት ውስጥም መፍትሔ የመስጠት ሥራ እንደሚጀመር፣ በቅርሶች ጥገና ላይ ልምድ ያለውና ከጣሊያን የተመለሰውን የአክሱም ሐውልት ለተከለው  ኩባንያ ሥራው መሰጠቱንና በዚህ ወር እንደሚመጣ ለፓርላማው መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ከአዲስ አበባ 645 .. ርቀት የሚገኘውና ‹‹አዲሲቷ ኢየሩሳሌም›› የሚል ቅጽል ስም ያተረፈው ባለ 11 ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ ላሊበላ፣ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት፣ በምሕፃሩ ዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው 1970 .. (... 1978) ነበር፡፡
………..
ቤተክርስቲያኒቱ የባለፈው ዓመት ጠቅላላ ገቢዋ ከአንድ ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ መሆኑ መረጃዎች ያመለክታል ፤ ታዲያ ይህን ያህል ብር ምን አይነት ሥራ ላይ እየዋለ ይገኛል? የአብነት ትምህርት ቤት ካልተቋቋመበት ፤ ቀድድ የተጀመሩ መማሪያ ቤቶች ካልተረዱበት ፤ አዲስ ቤተክርስቲያን ካልተሰራበት ፤ ያሉትን ካላደስንበት ፤ ዘመኑን የዋጀ የወንጌል አገልግሎት ካልተሰጠበት ፤ ቀጣይ ትውልድ ካላፈራንበት ብሩ ጥቅሙ ምኑ ለይ ነው? ቤተክህነቱስ ሃይ የሚለው አካል ማነው? ቤተክርስቲያኒቱን በዘርፈ ብዙ ሥራ እየደገፋት የሚገኝውን ማኅበር መቆሙን ከምትገዳደሩ ስለምን ሥራችሁን አውቃችሁ በአግባቡ አትሰሩም?


አሁንም አምላከ ቅዱሳን ይመልከተን..አሜን

No comments:

Post a Comment