በፊት በፊት የመዝሙር ግጥሞች ሲፃፉ እግዚአብሔር እንዲመራቸው በፆምና በፀሎት እግዚአብሔርን መጠየቅ የነበረ ሲሆን አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተብሎ የሚወጣው መዝሙር ግጥም ከመናፍቃን የመዝሙር ካሴት ግጥም ኮፒ እየተደረገ መቅረብ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተጨማሪም ሆን ተብሎ ለቸብቸቦ የሰውን ስሜት እንዲገዛ ተደርጎ ከመፃፉም ባሻገር አንዳች ነገር ለመዝሙር ሰሚው ወንጌልን የማስተላለፍ ሚናው በሙሉ ጠፍቷል ፡፡ ለምሳሌ ለማሳያ ያህለል ዘርፌ ከበደ አወጣሁት ካለችው መዝሙር ሁለት ያህል ግጥሞች አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፃፍኩ ያለው ሲሆን በጊዜው እነዚህ ግጥሞች ከመናፍቃኑ ካሴት ምንም ለውጥ ሳይኖራቸው የተገለበጡ በመሆኑ የግጥሙ ባለቤት ግጥሜ ተሰርቆብኛል ሲል አቶ በጋሻው ደሳለኝን ፍርድ ቤት መክሰሱ የሚታወስ ቢሆንም የፍርድ ቤት ሂደቱ በአጭር እንደቀረ ያለፈ ትውስታችን ነው፡፡
አቶ በጋሻው ደሳለኝ የመናፍቃንን ካሴት እየቃረመ ለእኛ ማቅረቡን የለመደው የቀን ተቀን ስራው መሆኑን ለማወቅ ‹‹የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን›› የሚለውን መፅሀፍ ለመፃፍ የፓስተር መለሰ ወጉን የስብከት ካሴት ቁጥር 107 ገልብጦ የተጠቀመ ሲሆን ይህን ስራውን በዘርፌ ካሴት ላይም ደግሞት ለማየት በቅተናል፡፡ ለማስረጃ ያህል የሚቀጥለውን ካሴት ስቲከር ይመልከቱ
አሁን አሁን የምሰማቸው የኦርቶዶክስ መዝሙሮች ከመናፍቃኑ የሚለዩበትን ነገር አይታይባቸውም ፤ የመናፍቃኑ መዝሙሮች የሚያዘልሉ ተደርገው የሚሰሩት ሆን ተብሎ ነው፡፡ እኛን ደግሞ በአንድ ጊዜ ከያሬዳዊ ዜማዎቻችን አውጥተው መዝሙሮቻችንን ወደ እነርሱ ጎራ ለመቀላቀል በአንድ ጊዜ ስለማይቻል በሂደት እያለማመዱን ይገኛሉ ፤ ህገወጥ ተብለው በሲኖዶስ የታገዱት ዘማርያን እና ሰባኪዎች ፤ እጅ ‹‹ወደ ላይ ፤ ወደ ላይ›› እያሉ ህዝቡን ሲያለማምዱት ነበር ፤ እንደ መናፍቃን አውደ ምህረቱ ላይ ሲዘሉም ለማየት ችለን ነበር ፡፡ ዘርፌ ከበደ ካሴት ላይ አንድ ግጥም አቶ በጋሻው ደሳለኝ ከሙሉ ወንጌል ዘማሪ ላይ ምንም ሳይቀይር ሌባ በሚያስብል መልኩ ግጥሙን ገልብጦ የሰጣት ሲሆን ፤ የግጥሙ ደራሲ በጊዜው በዚህኛው እና በሌላ አንድ ተጨማሪ የግጥም ስርቆሽ በፍትሀ-ብሔር ህግ አቶ በጋሻው ደሰለኝን ፍርድ ቤት በአዕምሮያዊ ስርቆት ከሶት የፍርድ ቤት መጥሪያ በእጁ ደርሶት ነበር ፤ ከዚህ በኃላ ግን አቶ በጋሻው ከፓስተሮቻቸው ጋር ያለው መስተጋብር ጥሩ ስለሆነ ፤ ለኦርቶዶክስ ኢየሱስን ሰባኪ ወንጌል አድርገው ስለሚመለከቱት ፤ የአላማ አንድነትም ስላላቸው ፤ በጊዜው የፍርድ ቤቱን ፋይል ከከሳሽ ጋር በመነጋገር ወደ መዝገብ ቤት ሊመልሱት ችለዋል፡፡ በምን አይነት ሁኔታ የፍርድ ቤቱ ፋይል እንደተዘጋ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ይህን ግጥሙን ከእኛ ግጥም እና ዜማ ጋር አቆራኝተን ወደፊት እናቀርብላችዋለን፡፡
አቶ በጋሻው ደሳለኝ ይህን ተግባር የጀመረው ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ከመባረሩ በፊት ነበር ፤ በዚያ ጊዜ ከእጁ ላይ የማትጠፋ አንዲት ወክማን ነበረችው ፤ ይችን ወክማን አዘውትሮ ይዟት ለተመለከተ አንድ ወዳጄ ፤ በጋሻው የምትሰማውን እኔ ላደምጥ እችላለሁ ? ብሎ ቢጠይቀው መልሱ አይሆንም ነበር ፤ እንዲህ ብሎ ሲመልስለት ይባስ የሚያዳምጠውን ነገር ለማዳመጥ ጉጉት አደረበት ፤ አንድ ጊዜ በአጋጣሚ ሻይ ቡና እያሉ ሳለ ይችን ወክማን እረስቷት ተንስቶ ኖሮ ፤ ውስጥ ያለውን ካሴት ከፍቶ ሲሰማ ልጁ ጆሮውን ማመን ነው ያቃተው ፤ ለስለስ ያለ የመናፍቃኑን መዝሙር ኖሮ ውስጥ ያለው በጣም ደነገጠ ፤ ከደቂቃዎች በኋላ መርሳቱን አስታውሶ በጋሻው ሲመለስ ቦታ ላይ አስቀምጠውለት ምንም እነዳልተፈጠረ ዝም ቢሉት አሱም ወክማኑን ብድግ አድርጓት ሊሄድ ችሏል ፤ ለካ ለዘመናት ይህን ያደምጥ ኖሯል ፤ እንዴት አንድ የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ይህን ያደምጣል? ብሎ ለራሱ ጥያቄ ቢጠይቅ ጊዜው ስላልነበረ መልስ ሊያገኝለት አልቻለም ነበር ፤ አላማቸው ‹‹ሐይማኖት አትለውጥ ራህን ለውጥ›› እንደሆነ ለማወቅ ጊዜ ወስዶብ ነበር፡፡ ይህ ድርሰት ወይም የሰውን ስም የማጥፋት ወሬ አይደለም ፤ የሆነ እና የተደረገ የአይን እማኝ ምስክር ነው፡፡
እናውቃለን አብረውን በሺህ የሚቆጠሩ የኛ ያልሆኑ ነገር ግን ከእኛ ጋር ያሉ ሰዎች እንዳሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች የቤታችንን የላይኛውን ወለል ላይ በተመቻቸላቸው መንገድ ወንበሩ ላይ ፊጢጥ ብለው እንደተቀመጡ እናውቃለን ፤ እናውቃለን በሰበካ ጉባኤ ፤በሰንበት ትምህርት ቤት አባል ፤ ለሆዳቸው ያደሩ የኛ ያልሆኑ ሰዎች አብረውን እንዳሉ ፤ እናውቃለን የመዝሙር ግጥም ብለው ከሌሎች እኛን ከማይመስሉት ገልብጠው እንደሚያመጡልን ፤ እናውቃለን ‹‹ድምፃቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሀድሶ›› የሆኑ ሰዎች እንደከበቡን ፤ እናውቃለን የጠበቀ በቀላሉ የማይደረስበት ትስስር ከመናፍቃን ፓስተሮች ጋር እንዳላቸው ፤ እናውቃለን የሌላቸውን ማዕረግ በማናቃቸው ሰዎች ስም ፤ ቤተክርስትያን ባልሰጠቻቸው ማዕረግ ተጠቅመው ህዝበ ክርስትያንን ለማወናበድ መፅሀፍ እየፃፉ እንዳሉ ፤ እናውቃለን ከቤተክህነት ከምን አይነት አባቶች ጋር የጠበቀ ‹‹ልከክልህ እከክልኝ›› አይነት ግንኙነት እንዳለቸው ፤ ይህን ሁሉ ግን አውቀን ዝም አንልም ሰዎችም እንዲያውቁ ከተጨባጭ መረጃ ጋር እናቀርባለን፡፡
እኛን የአቶ በጋሻው ጠላቶች አድርገው የሚያዩን ብዙዎች ናቸው ፤ ማንም ለእኛ ጠላታችን አይደለም ፤ ነገር ግን የቤተክርስትያናችን ስም፤ ክብሯን በሚያዋርድ መንገድ የሄደ ፤ ስርዓተ ቤተክርስትያንን የማያከብረው ሰውን ስራውን ገልጠን ከማረጃ ጋር ለሰዎች እናደርሳለን ፤ ሰው ያቀረብነውን አይቶ ራሱ ይፍረድ እንላለን፡፡ ለእነ ዘርፌ ከበደ ፤ ሃብታሙ ሽብሩ ፤ ለእነ ትዝታው ሳሙኤል እና እሱን ለሚመስሉት ሰዎች አቶ በጋሻው ብዙ ግጥም የሰጠ ሲሆን እነርሱም በጋሻው የፃፈው መስሏቸው ዘምረው ፤ ካሴቶቻቸው ብዙ ኦርዶክሳውያን ቤት ይገኛል፡፡ የሚቀጥለውን የመዝሙር ግጥም ይሄን ግጥም ለምን ከፕሮቴስታንቶች ላይ ወሰድክ ? ብላችሁ ብትጠይቁት ፡፡ ደፋሩ በጋሻው ‹‹መንፈስ ቅዱስ ገልፆልኝ ነው›› እንጂ ኮፒ አድርጌ አይደለም እንደሚላችሁ እርግጠኛ ነኝ ፡፡
የምናወጣው መረጃ ያልጣማቸው የቤተክርስትያናችን ጠላቶች በተለያዩ የበሬ ወለደ ብሎጋቸው ላይ ትልቅ አርዕስት ሰጥተው ‹‹አንድ አድርገን›› የማህበረ ቅዱሳን ልሳን ነው ፤ ሌላኛው ‹‹የደጀ ሰላም›› እስትንፋስ ነው ብለው ሲፅፉ ተመልክተናል፡፡ እኛ ግን ‹‹አንድ አድርገን››ኖች እናንተ እንደምታስቡት አይደለንም ፤ እኛ ስለቤተክርስትያን የሚገደን ጥቂት ሰዎች ነን ፡፡ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን› ግን በሺህ የሚቆጠር አባላት ያለው ጠንካራ ማህበር ነው ፡፡ ሁለትና ሶስት ሰዎችን ከግዙፍ አካል ጋር ማመሳሰል ተገቢ አይደለም ፤ አላማችን የሆነውን ፤ የተደረገውን ፤የሚደረገውን ፤ ሊደረግ የታሰበውን ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ነገሮችን ለሰዎች ማድረስ ነው፡፡ ስለዚህ መሳደብም ከፈለጋችሁ እኛኑ ስደቡን፤ ማመስገን ከፈለጋችሁም እኛኑ አመስግኑን ፡፡ እንጂ እጁ የሌለበትን ‹‹ማህበረ ቅዱሳንን›› እና የደጀ-ሰላም ዌብ-ሳይት ጋር አንድ ላይ ጨፍልቃችሁ አትናገሩ፡፡ እኛ እኛ ነን ፡፡
በዚህ መረጃ የምትናደዱ ካላችሁ ፤ ገና የምትናደዱበት ጊዜ አልደረሰምና ቀስ ይበሉ ብለን እንመክሮታለን ፤ የፃፋቸው ፤ ያፃፋቸው ደብዳቤዎችን ጊዜው ሲደርስ ስለምንዘረግፍልዎ ፤ የልጁንም ማንነት ስለምንነግርዎ ረጋ ይበሉ ፤ ጊዜው የመረጃ ነው ፤ ስራቸውን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም ፤ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ቢወጣ መልካ አይደለም ብለን እናስባለን ፤ በጊዜ ሂደት በጋሻውን ፤ትዝታውን ፤ምርትነሽን ፤የዘርፌን ካሴቶች ፤ ሀብታሙ ሽብሩን ከነስራዎቻቸው ከበቂ መረጃ ጋር እናቀርብሎታለን፡፡ ሰዎች ስህተታቸውን አምነው ቢመለሱ ደስተኞች ነን ፤ ልባቸውን ካደነደኑ ግን ማንነታቸውንና ስራቸውን ሚዛን ላይ እናቀርብሎታለን፡፡ እርስዎ አይተው ይፈርዳሉ
ይህን ወሬ ሌላ ጊዜ እንነግሮታለን
አቶ በጋሻው ደሳለኝ ለሰሜን አሜሪካ የስብከተወንጌል ሃላፊ ተደርጎ በአቡነ ጳውሎስ እና በግብር አባቱ አቡነ ፋኑኤል ታጭቶ ነበር፡፡ ለምን አቡነ ፋኑኤል ሲሄዱ አርሱ ለምን የቀረ ይመስሎታል ? አሜሪካ አቶ በጋሻውን የሚያክል ብዙ ደጋፊ ያለው ሰውን ቪዛ አልሰጥ ብላው ይሆን ? የእነርሱ የተስፋይቱ ምድር(አሜሪካ) ተቀባይ አይኖረው ይሆን? ምክንያቱን በቅርብ ቀናት ውስጥ እንነግሮታለን ይጠብቁን፡፡
በዚህው ከቀጠልን ነገ ያሬዳዊ መዝሙር ላለመስማስ ረዥም ጊዜ የሚወስድብን አይሆንም፡፡ ግጥሙን ፤ ዜማውን ሁለቱን መዝሙሮች አድምጠው ፍርዱን ለመስጠት ለእርስዎ ትተናል፡፡
ያስተውሉ የፕሮቴስታንቶቹ መዝሙር ከእኛ በዓመታት ቀድሞ የወጣ ነው
ካልባረከኝ አለቅህም ካልባረከኝ አለቅህም
አምላኬ ነህ ለዘላለም
ጌታዬ ነህ ለዘላለም
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ
ጌታዬ ነህ ለዘላለም
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ
ሌላው አይገደኝም ህይወቴ ከዳነ
ሲሆን እስከ ንጋት ልታገልህና
ስደደኝ ጌታዬ ሆይ ሕይወቴን ክባርና
ስደደኝ ጌታዬ ሆይ ሕይወቴን ክባርና
በመንበርከክ ብዛት በጸሎት ትግል
ፈቃድህ ከሆነ ጉልበቴ ይዛል
እያለቀስኩ ሁሉ እከተልሀለሁ
እጅህን ዘርጋብኝ በርከት እሻለሁ
ፈቃድህ ከሆነ ጉልበቴ ይዛል
እያለቀስኩ ሁሉ እከተልሀለሁ
እጅህን ዘርጋብኝ በርከት እሻለሁ
ሊነጋ ሲጀምር ሰማዩም ሲቀላ
ወዴት እሔዳለሁ ነፍሴ እንዲህ ዝላ
ሕይወቴን ብቻ ባርክ ሌላ አልመኝም
ስም እንደው ቀሪ ነው ስም አያድነኝም
እንደ ያዕቆብ ዛሬ ጩ¤ቴን ስማና
ስደደኝ ጌታሆይ ህይወቴን ባርካና
ፈቃድ ከሆነ ስሜንም ለውጠው
ሰው እንዳለው ሳይሆን አንተ እንደወደድከው
ወዴት እሔዳለሁ ነፍሴ እንዲህ ዝላ
ሕይወቴን ብቻ ባርክ ሌላ አልመኝም
ስም እንደው ቀሪ ነው ስም አያድነኝም
እንደ ያዕቆብ ዛሬ ጩ¤ቴን ስማና
ስደደኝ ጌታሆይ ህይወቴን ባርካና
ፈቃድ ከሆነ ስሜንም ለውጠው
ሰው እንዳለው ሳይሆን አንተ እንደወደድከው
የኦርቶዶክስ
ካልባረከኝ አለቅህም ካልባረከኝ አለቅህም
ካልባረከኝ አለቅህም ካልባረከኝ አለቅህም
አምላኬ ነህ ለዘላለም
ጌታዬ ነህ ለዘላለም
ሊነጋ ሲጀምር ሰማዮ ሲቀላ
ወዴት እሔዳለው ነፍሴ እንዲህ ዝላ
እያለቀስሁ ሁሉ እከተልሀለሁ
እጅህን ዘርጋልኝ በረከት እሻለሁ
ጌታዬ ነህ ለዘላለም
ሊነጋ ሲጀምር ሰማዮ ሲቀላ
ወዴት እሔዳለው ነፍሴ እንዲህ ዝላ
እያለቀስሁ ሁሉ እከተልሀለሁ
እጅህን ዘርጋልኝ በረከት እሻለሁ
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ
ሌላውን አልሻም ሕይወቴ ከዳነ
ሌላውን አልሻም ሕይወቴ ከዳነ
ሲሆን እስከ ንጋት ልታገልህና
ስደደኝ ጌታዬ ሕይወቴን ባርክና
ስደደኝ ጌታዬ ሕይወቴን ባርክና
አምላኬ /2/ታምሜ ስላደርኩኝ ሞልቶኝ በረከትህ
አየሁ ጌታዬ ዛሬስ ፊትለፊትህ
አየሁ ጌታዬ ዛሬስ ፊትለፊትህ
ድምፄን አሰምቼ አልኩኝ ጵንኤል
ስሜም ተለወጠ ተባለ እስራኤል/2/
የሞቷን ከተማ ሴኬምን ትችአለው
የሞቷን ከተማ ሴኬምን ትችአለው
ጌታ እንደቃልህ ቤቴል ወጥቼአለሁ
ሁሉን ስለምትወድ ስልምተራራዓለምን አስረሳኝ ልኑር ካንተ ጋር/2/
እኛም ይህን ሰው አቶ በጋሻውን ለዚህ ነው እየተቃወምነው ያለነው
Keyamandaru eyetalekame yebetachristiyan siriatina danbe tabiko yetazegaje eyetabale eko nawu mazmur sayihun shaket lemiemanu yemichabechabe yihe hay libal yigebawal!!! E/r yibarkachu endih kemaraja gar yetadegafa tsuf katilubat gana bizu gud ale!
ReplyDeleteየቦታ ለውጥ እንጂ ሌላ ምን ልዩነት አለው? ‘እዚህም እዚያም ክርስቶስ ከተሰበከ ምን ችግር አለው’ አሉ እነ እከሌi የዛ ውጤት ስለሆነ ነው፡፡ “ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ”
ReplyDeleteምን አይነት ጉድ ነው እባካችሁ???
ReplyDeleteባሕረ ጥበባት በምትባል ቤ/ክ ሆኖ ሌብነት???
ያሳዝናል!!!!!!!!!!!!!!!!
So are you telling me after people see this, still follow this person. What a foolishness is it? It is obvious. He copied it.
ReplyDeleteaye Begashaw sitechaweteben norek !!
ReplyDelete¨lemin yiwashal?¨ale ....
ReplyDeleteWe don't have the problem with the words, as they are from bible. However, 100% copy and paste might have a motive behind. Please do the same and expose such evil deeds in our Church.
ReplyDeletetazabiw
ለማይረባ አይምሮ አሳልፎ የሰጣችሁ የተንኮለኞች ቡድን ብትኖሩ እናንተ ናችሁ። ክርስቲያን አይደላችሁም እንጂ ብትሆኑማ ኑሮ መዝሙርም ሆነ ትምህርት የሚወጣው ከአንዱ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነው መፅሀፍ ቅዱስ ስለሆነ ተመሳሳይነትም ሆነ ተቀራራቢነት ሊኖረው ግድ ይላል። ያም ሆነ ይህ እናንተ ጭንቅላታችሁ አንዴ ለማይረባ ነገር
ReplyDeleteአሳልፎ ሰለተሰጠ ፣ በሰይጣናዊ ቅናት ተይዛችሁ ፀጉር ስንጠቃ ብትገቡና ክፉውን ሁሉ በውሸት ብታወሩበት መጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው እንደሆነ በእግዚአብሔር የተመረጠ የዘመኑ ጳውሎስ መሆኑን እንድትረዱ ያስፈልጋል። እናንተና እንናንተን የመሰሉ አላዋቂዎች በሚያወሩት ወሬ ፤ ክርስቲያኖች የበለጠ ማንነታችሁን እየተረዳን ሰለመጣን ሌላ ሥራ ፈልጉ እንጂ ይህ የሥም መስጠት እኩይ ተግባራችሁ የተበላ እቁብ ሆኖአል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይም ሁሉ ይህንን ጠንቀቆ አውቆባችሁዋልና ለመላላጥ አትፈራገጡ። በሐይማኖት ካባ ስውር ደባ ከማድረግና እንደ አለቃችሁ ሰይጣን ሰላምን በማደፍረስ ያገለገላችሁ እስከሚመስላችሁ ድረስ ብትሮጡና ብትደክሙ ሁሉም ነገር ዋጋ
የሌለው ነው። ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን የህግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ስለሆነ በከንቱ ትደክማላችሁ ፍቅር እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር የላችሁም። እንደ ግብረአበራችሁ እንደ ዘመድኩን ፤ በመምህር በጋሻው ክርስትና ከቀናችሁበት ደግሞ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ፣ ይቅር ይበላችሁ። ቅናት ሐጢያት ነውና ።
ይቆየን። Any way We Love Begashaw don't worry.
who will be a witness for whom? lemehonu sireat silemibal neger tiredaleh? yih bihon noro ye dogma liyunet liredah yichil neber
DeleteAny way We Love Begashaw don't worry. yaleh sew antem yetesasateh yemeselale mekeneyatum ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን የህግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ስለሆነ በከንቱ ትደክማላችሁ ፍቅር እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር የላችሁም። እንደ ግብረአበራችሁ እንደ ዘመድኩን ፤ በመምህር በጋሻው ክርስትና ከቀናችሁበት ደግሞ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ፣ ይቅር ይበላችሁ። ቅናት ሐጢያት ነውና bemaleteh antem feker yelehum malet new mekeneiatum antem tesadabi ye seytan tanash wondem neha !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!egzeabher lebona yeseten!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
DeleteMay God bless your efforts. This is a wonderful info supported by evidence. This is a very important work for people who want evidence at hand. May God keep our church intact.
ReplyDeleteአንተ ጥላቻህን ጥላቻ አይደለም ብለህ ያጥናክርልህ ዘንድ መረጃዬ ነው ያልከውን ነጥብ አቀረብክልን። ዘመኑ ግን ሰው በመረጃ ቀርቧል የሚባለውን ጽሁፍ ሁሉ «ይገርማል!» እያለ የሚቀበልበት ሳይሆን ከዚያ አልፎ መመራመር እንደሚችል የሚታወቅበትም መሆኑ ሊጤን ይገባል። ስለዚህ ጥያቄዎችን ላቅርብልህ፣
ReplyDelete1/ አንተ ራስህ የጴንጤ መዝሙር እንደምታዳምጥ ራስህ እየመሰከርክ ነው። ለምን?
2/ የበጋሻው ግጥም ከጴንጤ ገጣሚ የተገኘ ነው ከምትል በስተቀር እንደቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከእግዚአብሔር ቃል ይጋጫል ወይ? እስኪ አሳየን?
3/ በእስራ ምእት አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያናችን ራሷ ማሳተም እስከቻለችበት ድረስ ሀ/ አጼ ምኒልክ በጣልያን ፍራንቸስካን ማተሚያ
ለ/ አጼ ኃ/ሥላሴ በእንግሊዝ ፎቶ ኦፍሴት
ሐ/ በአቡነ ተ/ሃይማኖት ጊዜ ደግሞ ኬንያ ውስጥ በወንጌላውያን ማተሚያ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን አሳትመው ለህዝብ አዳርሰዋል።
ኬንያ ከጴንጤዎቹ ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ገበያ ውስጥ አሁንም ድረስ አለ። የእስራ ምዕቱንም አዲሱን መጽሐፍ ቅዱስ በገንዘብ የረዱት የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አባል የሆኑት ካቶሊክና ጴንጤው ነው።
4/ታዲያ ምነው በጴንጤ ርኩስ ማተሚያ ቤት የታተመ መጽሐፍ ቅዱስ አንቀበልም፣ ይወገዝልን ያላላችሁ?
5/አሁንስ በገበያ ላይ ቤተክርስቲያን በራሷ ማተሚያ ቤትና ሊቃውንት ያልታተመውን ሰብስባችሁ ያላቃጠላችሁ?
6/የመስቀል ስር ቁማርተኛ የሚለው ቃል በመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በመለሰ ወጉ ነው እንዴ?
7/ የመስቀል ስር ቁማርተኛ የሚለው ቃል መቼም ቢሆን መነገር ያለበት በመለሰ ወጉ ነው እንዴ?
8/መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ቃል ጴንጤ ቢያነሳና ቢጽፍ፣ ኦርቶዶክሳዊውም ያንኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ቢያነሳና ቢጽፍ፣ ከመጽሐፉ ምንጭነት አንድ መሆን ቢመሳሰል እንደክህደት ይቆጠራል? ጴንጤ የማይጠቅሰው ግን ኦርቶዶክሳዊ የሆነው ቃል የቱ የቱ ነው?
9/ እስኪ በተለመደው ክሳችሁ ይህንን ግጥም ሰርቋል ወይም ኦርቶዶክሳዊ ትርጉምን ያፋልሳል በሉና ለሊቃውንት ጉባዔ አቅርቡ!! በእርግጠኝነት እንደማታደርጉ እናውቃለን። አዝናችሁለት ወይም ለፍቅረ ቢጽ ብላችሁ ሳይሆን አንዳችም ሊያስከስስ የሚችል ጭብጥ ስለሌላችሁ ብቻ ነው።
ሳጠቃልል በጋሻውን የምትጠሉት ጴንጤ ስለሆነ ሳይሆን ወገቡን ሰብራችሁ ስላልጣላችሁት ወይም አጥፍቼያለሁ ብሎ እጁን በሽንፈት ስላልሰጣችሁ ብቻ ነው። ነገ በሆነ አጋጣሚ እንታረቅ ብሎ ሽማግሌ ቢልክባችሁ እጁን ስማችሁ ትቀበሉታላችሁ። ለማንኛውም እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ፣የምታደርጉትን አታውቁምና!!!!!
3/
thank u so much. carryon
ReplyDeleteahunim asteway loibona yistachew ena wede kidist betekirstiyan yimelisachew
ReplyDeleteአንዱን እግዚአብሔርና በአንድ መፀሐፍ ቅዱስ እየተጠቀምን እንዴት ነው ይህ ለቤተክርስቲያን ከመቆርቆር አንፃር ነው የሚባለው የህ ምክንያት አይሆንም ምክንያቱም ለኦርቶዶክስ የተለየ መፀሐፍ ቅዱስ የለውምና፡፡
ReplyDeleteReally Shame on Begashaw!!!!!! What does it mean to copy from protestant? The song may not have problem in content but why an orthodox writer copy from protestant??? Shame shame shame.
ReplyDeletenigusie dz
ReplyDeletelibona yistew iwunet na nigat iyader yegaletal ina yemayitawek iyemeseleh siriatachinin at nadew tewahidon degmo God yitebikatal Bege atilifa
የምቀኞችና የቅናተኞች ሃሳብ ያላችሁ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ተቆርቀዋሪ እየመሰላችሁ የራሳችሁን የውስጥ ስሜት ትገልጻላችሁ፡፡ ለመሆኑ ለእምነታችን አሳቢ ከሆናችሁ ትናንተትና ወጣቱ ከቤተክርስቲያኗ በቂ እውቀት የሚያስጨብጠው አጥቶ ውልቅ ብሎ ወደ ጴንጤ ሲለወጥ እያንዳንዲሽ የራሳችሁን ጉዳይ ታስድዱ ነበር፡፡ ይኸ ወንድማችንና ሌሎች ችግዚአበብሔር ያስነሳቸው ወንድሞችና እህቶቻችን በሚገርም ሁኔታ አገሪቷን በሙሉ አዳርሰው ወንጌልን በመስበካቸውና በዝማሬ በማጥለቅለቀቃቸው የወወጣው ሁሉ አብዛኛው ማለት ይቻላል ወደ እናት ቤተክርስቲያኑ ተመልሷል፡፡ ይህ ድንቅ ነገር ነው የእናንተ እራስ ምታት፡፡ ለመሆኑ ቤተክርስቲያን ከማመስና ምዕመኑ እርስ በርሱ እንዲቃረን ከማድረግ ለፈ ምን ሠራችሁ; አሁን አሥር ዓመት ብትደክሙ ዲያቆን በጋሻው ያገኘውን ቦታ ማግኘት አትችሉም፡፡ ይልቁንም ያሬዳዊ ዝማሬ እያላችሁ ህዝቡን በማሳሳት ግራ አታጋቡት፡፡ ይኸ ማንነታችሁን መሸፈኛ ያደረጋችሁት ጭብል ነው፡፡ እውነተኛ ማንነታችሁ ተነቅቶበታል፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ከሆናችሁ አምላክ ያዘዘውን እርስ በራሳችሁ ተዋደዱ የተባለውን ተግባራዊ ለማድረግ ተጣጣሩ፣ ቆም ብላችሁ አስቡ፣ እውነተኛ ክርስቲያን ከሆናችሁ እነዚህን ሰዎች ማሳደድ አቁሙ፡፡ ቅናት ምቀኝነት ሐጢአት ነው፡፡
ReplyDelete@Ande Adiregen...I don't think you can use this as escape goat for the merciless war you opened on Begashaw...everybody knows you hate him and your war on him can not be justified by any means. The main reasons is even if you pretend to be Christians, your war on him is not to bring him back to the right direction but just to get rid of him which is not by no means a christian behavior.
ReplyDeleteSuch activity has been done by Mihrteab and others who are highly attached to your group but you haven't complained about it. If you are really a true Christan without any group affiliation, you would be against such act whoever done it.
For me copy and past is not only a sinful act but also a crime and hence we all have to fight irrespective of the personality involved in it.
I condemn such act definitely and should be stopped as soon as possible.
Enante Yematastewulu ebakachihu betekrstianachinen likekuln min alebet yepente mezmur bebetekrstianachihu bizemer eyalachihun ekonew betekrstian eko yelikawunt hager nat yeraswan habt meche tetekemechibet ena new yihin emtadergew. Yilkuns tenektobachhual ena nisiha gibu.
ReplyDeleteBetekrstianin lemades ke'egna kalhonu sewoch gar maber yemnkebelew aydelem
Silezih gorachihun leyuln, ke'and metsihaf new yetekedaw bezihm temesaslual bilachihu litatalilu atmokru
Yebegashaw alama berkash sira genzeb magbesbes ena mades new silezih eyewashachihu litadsul atmokru alfobachihual ena mastewl yistachihu
Those who are supporting Ato Begashaw to copy from other religious groups for our church, are not the followers of our church they are protestants. Are you insult us by telling all of the Muzmurs copied from one bible
ReplyDeleteQ1,‹‹በአምባ ፈረስ ላይ ሆነህ›› yemilew mezmur yezerfe new yerasachhu zemari yezemerechhun enkuan betkekel satawku yemenafkun lemadamet rotachu
ReplyDeleteyegtem memesasel yagatmal yemigermew enante kemetechet yilk yaredawi zema yemibalutn bitgeltsu evaluate enaderg neber enante gin yehone telko yalachhu yimeslegnal" tilachan yemezrat"
Q2, ‹‹የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን›› may be the title are the same but different in content,lemehonu bekrbu abune pawlosen sittechu yeneberachhu enante aydelachhum esu yelayignawn ries siletetekeme new..
lemangnawm esum hone enante lebona yistachhu merejachu hulu kentu techbachnet yelelew.
gin 1 begashaw bicha new yebetekrstinanen sirat eyatefa yalew yesus beglts litawok yichlal yewst yegir esatochs betekhnet dires yegebu meserwochs eza lay lemn atserum yetegelete kemtgeltu
Q3,ካልባረከኝ አለቅህም begashawm sereke kalun yetenagerew yakob new enji yemenafku zemari berasu alfeterewm silezi ayasgermem erasachu yakenaberachhuts mehonun bemen enawkalen...zemenu yetechnology new egna anshewedm...esti degmo lemsmatu yesemi semi enji erasachu eskalsemachu hametegna nachhu
selam lenante yehun ketetsafew melket belay yetelakew comment betam yemigerm new. wanaw neger melktu yetun yahel medresun selehone yemiyamelektew des lilachuh yegebal enji manem tewahdo yehone sew zefenen kemezmur awakin kalawaki saynegerw meleyet neberebet ahunem kezih belay entebkalen egzihabher ke enante gar yehun
ReplyDeleteየመዝሙር ቤታችሁ ገበያ ስለቀዘቀዘ የቤተክርስቲያን አሳቢ በመምሰል ያረዳዊ ዝማሬ በማለት በየቀኑና በየቤተክርስቲያኑ ትለፍፋላችሁ፡፡ ለመሆኑ የእናንተ ሬዳዊ ዝማሬ የትኛው ነው; እየደበላለቃችሁ ሰውን ግራ የምታጋቡ ሁሉ ያሬዳዊ ዝማሬ መሆኑን ሁላችንም እንደግፋለን፡፡ ቀድማችሁ ስህተት በመፈለግ ወንድማችሁን ከማሳደድ ተቆጥባችሁ አግባብ ባለው መንገድ ለማስተማር ቅድሚያ ስጡ፡፡ በየቤተክርስቲያኑ ግዕዝ ካልዘመራችሁ እያላችሁ ምዕመኑን ግራ እያጋባችሁ ያላችሁበትን ሁኔታ አስተካክሉ፡፡ በተለየ ሁኔታ ከተማሩት በስተቀር ወይም የቤተክርስቲያን የቅርብ አገልጋይ ከሆኑት በስተቀር ሌላው ምዕመን ገግዕዝ ከየት አምጥቶ ነው የሚዘምረው; መንግሥት እንኳን በህገ መንግስቱ ላይ ሁሉም በሚገባውና በሚያውቀው ቋንቋ እንዲማርና እንዲናገር ነው የፈቀደው፡፡ እናንተ ግን ሰውን ባልተማረውና በማያውቀው ቋንቋ ካልዘመርክ እያላችሁ ግራ ታጋባላችሁ፡፡ በአማርኛና የቤተክርስቲያኗን ትውፍት በጠበቀ ሁኔታ እንዘምራለን፡፡ የመዝሙር በታችሁ ገበያና የቡድናችሁ ተሰሚነት ስለቀነሰ ብቻ በቅናት መንፈስ ተነሳስታችሁ የሃይማኖት ተቆርቋሪ አትሁኑ፡፡ አምላክ ልቦና ይስጣችሁ፡፡ ትዕዛዛቱን ለመፈፀም ተጣጣሩ፣ ቤተክርስቲያን አፍራሽና ምዕመን በታኝ አትሁኑ!!!
ReplyDeletewey begashawe techawetkben egzabehaer ye serahen yestehe!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteSome people just don't get it. For example I never heard protestant's song, opening myself, on purpose. But since there is a chance of listening them when we pass by the song stores. From listening the songs again and again we get to know the song involentarily. So you can't say, "how did you know this is protestant song?". Even some of our church songs, I don't have the cassette but just by listening when I pass by the mezmur stores I just know them. So don't worry how people know it was protestant song. If we know it was copy--paste it is enough to isolate ourselves from this person's unity. .
ReplyDeleteስለ መረጃው በጣም እናመሰግናለን። ሁሉም በፍቅር ይሁን እንዲል ግለሰባዊ ልዩነቶችን ባላከተተ መልኩ ለመጻፍ ሞክሩ።ዲ/ን በጋሻው እና ግብረ አበሮቹ ብዙ ታሪክ አላቸው። ያንን ታሪክ ለሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በትክክል ለማድረስ ከፈለጋችሁ እባካችሁ አትሳደቡ። እስከማውቀው ድረስ ልጁ ዲ/ን ነው። ዲቁናውን ሽራችሁ አቶ የምትሉት እናንተ እነማን ናችሁ?? እሱን በምትከሱበት ክስ እንዳትወድቁ።
ReplyDeleteተዋህዶን ይጠብቅልን!
lebnet hateyat new
ReplyDeletebetam yigermal enante gna orthodox nachu gena ahuns eyateratergn meta mknyatum yenezi sewoch bota tesetachew hasabache ena melsache endinageru slal semanachew anferdachewum katefutn sra yibelt sewochun yetekemutn yibeltal atfredu frdun ye egziabhear new ena. enante enemanachu b egziabhea sifra honachu yemtferdu enezi sewoch tkkl kehonu egziabhear edme yistachew kalhonu degmo egziabhear lubona yistachew. yebedele sew asalfeh sayhon mekreh new yemtmelsew yenante gna betam yateratral lenantem lubona yistachu lehulachin mastewal yadlen.
ReplyDeleteAnd Adrgen - yihen yemesele mereja eske zare dires yet debqachihu new yihe hullu sew siTef. Ere ahunim lela kalachihu nigerun.
ReplyDeleteWela tehadso asteyayet biseT aygremachihu.mewchia megbia biaTa new.
Egziabher yabertachihu 1 adirgen
/3 God bless you!!!
ReplyDeleteIt is shamefull for begashaw and the singer to copy menafikan mezmur in the 21st century both in spiritual and secular perspectives.Egziabher lib yistachew!
ReplyDeleteThose of you who are blaming this bloger, for opening our eyes to see the secret actions of begashaw and his group, are not from EOTC. Begashaw &...were leading us to the protestant hall simply by pretending as orthdoxawian but conveying prtestant message and we were folloing them:
wherever they preach, sing
whatever amount they charge;
whatever message they deliver, blindly!
(Remember:
1. the content of begashw sibiket "Silassie Atibelu...")
2.Content of the mezmur he authored..
3.The way mezemiran of his group like Dagmawi, Jamping in our Owdemiret...)
However, this blog and some others are helping us to see the wrong direction we were gone following begashaw....So let us open our eyes/ears and see the facts,take what ever weighs right and pray for him and his group.
"Joro yalew mesmatin yisma"
Otherwise, your support does not bring them back nor cover their mistakes. So watch yourself!
Medihnu Abate
Is their any pricher like Megaby Haddis Begashew,Aseged,Berhyhun,tiztaw, and more. But MK are very jelous, because they have so many followers. They are gifted by God!!!!. Zemedkun is a dog of Mk. I know Zemedkun very well, he is in love with money, If devel comes and pay him maney I will assure he is ready to sell his wife for the devel.
ReplyDeleteABATU EGEZIABAHER HOW FETEHEN WADANA MALESE BATEHEN TABEK LEJOCHEHENM EREDA MANGADEHENEM MERAN !!!!
ReplyDelete1.በቃሉ ላይ መቆም እንጂ ለቡድኖች/religious groups መወገን ህይወት አይሆንም:: If the point here is about entrnal life and you are true christians at all.
ReplyDelete2. 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4 ቁጥር 11 ፡ ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር
ስለዚህ ሀሳቡ መሆን ያለበት እንደ እግዚአብሔር ቃል ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ መሆን አለበት፡፡
This a great jobs, pls keep itt up...there are many neophytes protestants inside the Orthodox tewahido church. We the true children of This holy Orthodox tewahido church lets come together and pray God will wipe them out for He will be not late for His promise.
ReplyDeleteI was so skeptical about Mr. Begashw and his team for I knew him from 1996 at HTTC, Holy Sillassie church .....anyways the time gave them the discourse ....will see more ,,,
1. http://www.youtube.com/watch?v=BcV2JrDm278&feature=related
2. http://www.youtube.com/watch?v=pxtncNsjHG8&feature=related
liju lemindinew kirkir yemifetir sira yemiseraw, betam metenat alebet
ReplyDeleteWhether it is right or wrong we have our own kenona and dogma so all things should be done with our frame work. Anything outside this is "Minfikina".
ReplyDeleteI think this blog is not intended to justify this is biblical or not the intention is to show that those groups are not our members, they belong to somewhere. Their teaching might be correct but they should present it publicly. They can be whatever they want but they should specify themselves and this should not be done by making our church a cover. That is the intention.
This is not personal issue, if someone is found of guilty about his faith and unable to repent the option that will follow should be to expose his identity so that he will no more mischief others. So perfect start and I can’t wait to hear more…keep it up…god bless u and our church.
12/09/11
ReplyDeleteበቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን አቀረባለሁ
ቀጥዬ ልጠቅሰው የምፈልገው የፍቅር የሰላም መልዕክት አስመ
ስላችሁ ሀሳባችሁን የምታዠጐደጉዱት ሁሉ ብዙዎቻችሁ የፕሮ
ቴስታንት ተሀድሶ ታጣቂዎች እንደሁናችሁ ስለምንረዳ በመሳም
አሳልፎ የሰጠውን እምነተኛ ወዳጆች መሳዮች እንዳሉ የሚዘነጋ
አይደለም፡፡ጋዜጠኛ ያገኘውን መረጃ ለአንባቢዎች ያቀርባል፡፡
የተሳሳተ መረጃ ደርሷቸው ከሆነ ለማስተካከል ተገቢውን መረጃ
መስጠት አዋቂነት ነው፡፡በስነፅሁፍ ህግም ሆነ ኤቲክስ የአንድን
የስራ ውጤት መዝረፍ ያስጠይቃል፡፡ካልሆነ ማስፈቀድና የተገኘ
በትን ምንጭ መጥቀስ ብልህነት ነው፡፡መፅሐፍ ቅዱስን የአፃፃፉን
ይዘት ተቀብላችሃል ላልከው የእንግሊዘኛውን ብትመለከት ኢትዮ
ዽያ የሚለውን ስም እንዳጠፉት፤ፕሮቴስታንቶች ቀላል አማርኛ
ብለው ስንት አሳፋሪ ተግባር እንደፈፀሙ እኛ የተዋህዶ ልጆች እናው
ቀዋለን፡፡ስለዚህ መታደስ ካስፈለጋችሁ ራሳችሁን ይዛችሁ ብትተዳደሱ
የግድ አኛን መረበሽ አለባችሁ፡፡የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ
ተብሎ የተፃፈው አለምክንያት አይደለም፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ተዋህዶን ይጠብቅልን፡፡
እርስበርሳችሁ ተዋደደዱ ወንድማችሁን አታሳዱ ስለፍቅርና ስለሰላም ብቻ ስበኩ፣ ከክርስቶስ የተማርነው መነካከስን ሳይሆን ፍቅርን ስለሆነ የክርስቲያን ሥነ-ምግባር ይኑራችሁ፡፡ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ሽፋን በማድረግ የግል ጥቅማችሁን ለማስጠበቅ ከመሯሯጥ ይልቅ በቤተክስቲያናችን ውስጥ ያለው መከፋፈል ቀርቶ አንድነት እንዲሰፍን ያገኛችሁትን አጋጣሚ በመጠቀም ወንጌልን ስበኩ፡፡ ይኸ ነው የክርስቲያን ተግባር፡፡
ReplyDeleteእናንተ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብሎ በፍፁም ሊታመን አይችልም. ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንዴት አሳልፋችሁ ለጴንጤዎች ትሰጣላችሁ?
ReplyDeleteታሳዝናላችሁ
EWUNET YIGELETAL! EGNAM NEKANNBACHEW!
ReplyDeleteENERSU BICHA TADIK HONUBN!
GENAM YIH DIBK SERACHEW YIWOTAL
MEREJAWOCHN TOLO LAKULN!
ወይ ጉድ! እንዲ ነው እንግዲ መረጃ ማለት፡፡
ReplyDeleteይሄ ዌብ ሳይት የተከፈተው ስለ በጋሻው ለማውራት ነው ወይስ ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ስራ ለማውራት
ReplyDeleteአብዛኛው ክፍል ላይ ያለው ስለበጋሻውና የጋሻው ሥራዎች ነው በጣም የሚገርማችሁ ነገር በአካል አላውቀውም ግን ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው እንዲህ የጠመዱት ብዬ እንዳስብ አደረጋችሁኝ... በኃዋሪያት ዘመን እኮ ወንጌልን እንዲሰማ ያደረጉት አንዳንዶች በፍቅር በመስበክ አንዳንዶች ደግሞ ለተቃውሞ ብለው በመናገራቸው ነው፡፡
ከዚህ ይልቅ ለእግዚአብሔር ወንጌል እንደተጠራ ራሳችሁን የምትቆጥሩ ከሆነ እናንተ ለህዝቡ ቅዱሱን መጻህፍ ብታስተምሩ ያ ለህዝቡ ክፉንና ደጉን የሚለይበት ይሆንለታል፡፡ አሊያ ግን አሁን እያደረጋችሁ እንዳላችሁት ስለ አንድ ሰዎች በግል የጠሉት ስለሚመስል ሰው ነው እየሰበካችሁን ያላችሁት፡፡ ለእናንተ ያለንን ክብር እንዲቀንስ እንጂ እንዲጨምር አያደርግም፡፡ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንጌልን እንጂ ሰውን አንስቶ ይሄን ያህል ጊዜ ፈጅቶ ማውራት ያን ያህል አያስኬድም፡፡ እኔንጃ ልክ ጥቅሙ የተነካ ሰው ነው የምትመስሉት፡፡ እግዚአብሔር ቀናውን መንፈስ በውስጣችሁ ያድስላችሁ፡፡
Ya web of Begashaw!!!
ReplyDeleteyigermal and aynet laba yalachewu wefoch andlay yiberalu aydel yemibalewu. inante protestantoch lebegashawuna meselochu bitikerakeru aygemenm neger gin betekristianachin serawun awukalech leteliko yeteselefutim afrewal. yekidusan tselot betekiristiyanin tebikual seytan angetun deftwal/afrwal. yetewahido lijochim des bilonal.
ReplyDeleteandairigenoch lemitesetun mereja egizabher yisitachihu, yetenekabet yinchacha inanite gin atisinefu bertu behymanot tegadelu iyandandua mereja lene lebetesebena leguadegnoche indet indetekemen.Tebareku ahunim be betekirstian wust tesegisigewu liatefuat likebiruat yetenesu bejua yebelu yegeza lijochua keyeakitachawu tenesitewal ina kiristianoch and inhun, Egizabiher ethiopian yitebikilin.
ReplyDeleteandairigenoch lemitesetun mereja egizabher yisitachihu, yetenekabet yinchacha inanite gin atisinefu bertu behymanot tegadelu iyandandua mereja lene lebetesebena leguadegnoche indet indetekemen.Tebareku ahunim be betekirstian wust tesegisigewu liatefuat likebiruat yetenesu bejua yebelu yegeza lijochua keyeakitachawu tenesitewal ina kiristianoch and inhun, Egizabiher ethiopian yitebikilin.
ReplyDeleteEbakachehu feriha Egziabeher blebachen yinur kesew yemishesheg ke Egziabeher ayisheshegimena
ReplyDeleteEbakachehu feriha Egziabeher belibachen yinur kesew yemishesheg ke Egziabeher ayisheshegimena
ReplyDeleteyemiyaderguten ayawekumena yiker belachew
ReplyDeleteበስመ ስላሴ አሜን።
ReplyDelete1. ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድን መጽሐፍ ከማንበብህ በፊት ጸሐፊው ማን ነው በል። ምክንያቱም መልካም ሰው በሃይማኖት የሚመስልህ ከሆነ ዘክረው ለሱ የገለፀ መንፈስ ቅዱሰ ላንተም እንዲገልፅ። ካልሆነ ግን አታንብብ አትምሰለው ይላል። ተግሳፅ በተባለው መጽሐፍ ክፍል 7 ላይ። ታዲያ አንድ ሰው በእምነት ከማይመሰለው ሰው ስራን ስጋዊ ድርጊቶችን ሊማር ይችል ይሆናል ምክንያቱም ሁላችንም በዚህ አለም ነውና የምንኖረው ነገር ግር ሃይማኖት አንዲት ናትና (ሌሎች ሃይማኖት በሚባል ስም የሚጠሩ አንጂ ሃይማኖቶች አደሉም)መንግስተ ሰማያትም አንዲት ናት ስለዚህ ከመናፍቃን የሚለየን በሰማይ እርስታችን ሲሆን በምድር ሃይማኖታችን ነው በሃይማኖት የማይመስል ሰውን ግጥም መኮረጅ ምን ያስብላል? የመናፍቅ አድናቂ፣ መናፍቅ ተከታይ፣ መናፍቅ፣ ከሃዲ፣ .............. ሌላም ሌላ ያስብላል። ከላይ አንድ ወንድም አንደገለጸው ከግጥሙ አንድ አይነት ሳይሆን እን እገሌን መከታተል ምንድን ነው።
2. ቤተ ክርስትያነ ባህረ ጥበባት ነው የምንለው "አንተ ታልቃለህ እንጂ የቤተ ክርስትያን ጥበብ አያልቅም ባህርን በእንቁላል ክርፍት ማለት ነው" ከሰማይ የመጣ ዜማ እያለ ከአንድ መናፈቅ የመጣ ምን ያደርግልናል። ከሊቃውንት ግጥም ጠፍቶ ነው እንዴ ከመጸህፍትስ(ከገድላት፣ ከስንክሳር፣ ከድርሳን፣ ከሊቃውን ቅኔ) ከአንድ መናፍቅ ግጥም የሚኮረጀው። ምን አለ ያ ባለ ቅኔ ማለት ይቻል የለም እንዴ።
3. ተመሳስሎ መኖር እስከ መከር ነው። እዚህም ብሎግ ላይ የቤተ ክርስትያን ሰው መስላችሁ ጴንጤ ምናም የምትሉት መናፍቅ ነበር ማለት ያለባችሁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው መናፍቅ የሚለውን ሲተረጉሙ፡- መናፍቅ ማለት ግማሹን ተላጭቶ ግማሹን ያጎፈረ ነው። መናፍቅ ማለት ከፍሎ ማመን ማለት ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው ይላሉ ትክክል (ጎፈሬው) ኢየሱስ አማላጅ ነው (የተላጨው)/ሎቱ ስብሐት ለተጻፈው/ ታዲያ ይሄንን ጎፈሬው አንበለው መላጣው። መልሱን ለአንባቢያን።
አንድ አድርገኖች በርቱ የናንተ ሃላፊነት መረጃ መስጠት ነው/ለእነርሱማ መጻህፍት አሉላቸው አንዲል/ የተቀረው ያንባቢ ውሳኔ ነው። በርቱ እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ።
ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ
4.
U know what impress me ሁል ጊዜ ስለሰው እና ስለቤተክርስቲያን ብቻ ከምታወሩ ለምን ስለውንጌል ሰው እንዲድን አትሰብኩም?
ReplyDeletewhile reading all the comments here, i sometimes came across with comments which reads like..."ሁል ጊዜ ስለሰው እና ስለቤተክርስቲያን ብቻ ከምታወሩ ለምን ስለውንጌል ሰው እንዲድን አትሰብኩም? "....
ReplyDeleteyes we all agree that gospel preach is a vital for our spiritual life in order to have/conquer the eternal life...but pleas don't forget that protecting our church,and making aware the fellow Christians about the WOLF and the WOLF CUBS (LIKE BEGASHAW AND HIS GROUPS) is also another way and means for Christians to communicate information like this inorder to stand still and safeguard their mother church and them selves,this is what our fore-fathers did,our fore-fathers had the patience for an insult about themselves and yes they kept silent,BUT an insult on their faith and their church they never ever keep quiet and just let the wolves to snatch a lamb ....so andeadirgens continue your effort of protecting your church,the only thing you should take care is that..make sure that you have the evidence to support your news,if you do that,i assure you that u r protecting ur eternal house(z church) and u r preaching the gospel.
weladite amlak tibeb ena masitewal tihunachu!!
"በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ::" (ትንሶፎ.1:9)
ReplyDeleteበጣም የሚያሳዝነው ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በዙሪያዋ ልትከላከለው የሚገባ የእስልምና ጨለማ እያለ በክርስቶስ ደም አንድ የሆኑትን ወንድማማቾችን እህትማማቾችን መዋጋት መቀጠሉአ ነው (እነበጋሻው ወይም ወንጌላዊ አማኞች) ማለቴነው እስቲተመልከቱ በየክፍለ ሃገሩ በእስልምና አክራሪዎች ቤተ/ክናት እየተቃጠሉ ምእመናን እየተገደሉ እጃቸው እየተቆረጠ ብዙ እየተገፉ ነው ምን ነው ስለ እነዚህ ምእመናን ግድብሎአችሁ አትጽፉም ይሄን መረጃ በhttp youtube ላይ ይኛል እባካችሁ ሊሰበክ የሚገባው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ጳውሎስ በእስር በነበረ ጊዜ በፊሊጵስዪስ እስራቱን ሊያበዙበት ክርስቶስን ይሰብኩ ለነበሩት ያላቸው እንዲህ ነው "ቁም ነገሩ በቅንነትም ይሁን በማስመስል በማንኛውም መንገድ ክርስቶስ መሰበኩ ነው"ፊል 1፡18
ReplyDeleteበጋሻው ግጥም ቢጽፍ ዘርፌ ብትዘምረው የተሰበከው ክርስቶስ ኢየሱስ ከሆን ምንገዶአችሁ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማክበር የምትፈልግው ለአለም መድሃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይደል? ይልቅ ብንነቃ ይሻላል እስልምናን በአንድነት ሆነን ሙስልም ውግኖቻችን ካሉበት ጨለማ ይወጡ ዘንድ የክርስቶስ ኢየሱስን ፍቅር በመስበክ በማሳየት እንቁአቁአም።
እግዚአብሔር ይርዳን 1ሰው ነኝ
ራሳችሁን "ቅዱሳን" እያላችሁ ሰይጣኖች
ReplyDelete"አንድ አድርገን" እያላችሁ ገነጣጥሎች
አቤት ስም ማውጣት እኮ ስታውቁበት!!!!
እስኪ ሁሉንም ጥላቻ ተውና ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጃትን አንድ መሆንን እንተግብረው:: እንዲህ ግንጥልጥሉ ሲወጣ አያሳዝናችሁም???
ብዙ ነገሮች በሁሉም በኩል መስተካከል አለባቸው:: ሰባክያኑ፣ ዘማርያኑ እኮ ሊመከሩ የሚችሉ ናቸው በፍቅር ብንሄድ የማንደርስበት አልነበረም::
ችግሩ እናንተም እነሱን ለማጥፋት፣ እነሱም እናንተን ለማጥፋት ሆነ እሩጫችሁ!!!
እናት ቤተ ክርስቲያን እናንተን በመሰሉ ልጆቿ ትቃጠላለች! እስከ መቼ??
ከእኔ በቀር ጻድቅ የለም እያልን ሌላውን እንኮንናለን::
ዲያቢሎስ በመላእክት ተሸንፎ እየወረደ ሲሄድ እሱ መላእክትን አሸንፎ ቅዱሳን መላእክት እሱን ፈርተው እየራቁ የሚሄዱ ነበር የመሰለው:: እናንተም ዛሬ እንዲህ እንዳትሆኑ!!!!!!!
ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!
ባጭሩ ጥያቄ አለኝ
ReplyDelete፩/ በዘመናችን ያሉ የሐይማኖት ሰባኪዎችን /መምኅራንን ሐዋርያ ማለት ይቻላልወይ ?
፪/ አማልክት ማለት ምን ማለት ነው ?
Men this is a fantastic information supported by tangible evidence!!! Go ahead to and show the reality to the confused people. May God bless you!
ReplyDeleteውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ብናስተውል መልካም ነው፡፡ አይሁድ የአለምን መድሀኒት ለመስቀል አሳልፈው የሰጡት ባለማስተዋል ነው፡፡
ReplyDeleteእኔ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻውን የማውቀው በስራዎቹ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ነው፡፡ አሉ የሚባሉትን የቤተክርስቲን መምህራን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ የማውቀውን ልናገር፣ልመሰክር ሀይማኖቴ የስገድደኛልና ይኸው እናገራለሁ፡፡
መልእክቴ ትድረስልኝ በተለይ በተለይ ማህበረ “ቅዱሳን”/ሰይጣን አሰልጥኖ በየስርቻው የቤተክርስቲን ሰዎችን ለመዋጋት የሰይጣን ሰይፍ አስይዞ አስታጥቆ ላሰማራችሁ፣ለላካችሁ የማህበረ ሰይጣን ሰራዊቶች በሙሉ፡፡ በአንድ ግለሰብ ላይ እንዲህ የመስቀል ጦርነት ይመስል እንድትዘምቱ ያደረጋችሁ ነገር ምንድን ነው? ዛሬ በየቤተክርስቲያኑ ያለውን ወጣት ማን የሰበሰበው መሰለህ? እናነተማ ውጣ እነጂ ግባ ብላችሁ አታውቁም፡፡ ይህ ግብራችሁ ነው፡፡
በእውነቱ ከሆነ እንደ ምናከብራቸው ቅዱሳን፣ ሐዋርት፣ ሰማእታት በዘመናችን ትልቅ ተጋድሎ እየፈጸመ ያለ እግዚዘብሔር የመረጠው እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአጭር ጊዜ ውስጥ አለምን ማለት ይቻላል በወነጌል ዳር እስከዳር ያናወጠ ትክክለኛ የወንጌል መምህር ማለት መጋቤ ሐዲስ ዲ/ን በጋሻው ነው፡፡ ሐዋርያት 72 ቋንቋ ተገልጾላቸው ዓለምን ያስተማሩት ዩኒቨርስቲ ገብተው 72 ቋንቋ ተምረው አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ስለገለጸላቸው ነው፡፡ በመማር ብቻ ሰው ሊቅ መሆን አይችልም፡፡ እንደ ሰሎሞን ከእግዚአብሔር ሲሰጥ እንጂ፡፡ የመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ጉዳይ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትክክለኛ ጸጋ መሆኑ ምንም የማይካድ ጉዳይ ነው፡፡ አሉ እኮ ስንት የሐዲስ፣የብሉይ እና የሌሎችም መምህራን የቤተክርስቲን አባቶች፡፡ ነገር ግን እነርሱ ብዙ ዘመናትን ወጥተው ወርደው ተምረው ነው ያገኙት፡፡ ሆኖም ቢማሩም በጋሻው በቆመበት አውደ ምህረት ላይ ቆመው የትኛውን ምእመን ነው በወንጌል ያረሰረሱት፡፡ በኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ኢአማንያን ዘነድ ልዩ ቦታ ያገኘ የዘመኑ ተጋዳይ የወንጌል መምህር ማለት መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ብቻ ነው፡፡ እኔ እንጃ በህይወት ዘመኔ እንዲህ ገኖ የወጣ ብዙ የወንጌል እንቅፋት የሆኑበት የወንጌል መምህር አላየሁም አልሰማሁም፡፡ በሀገራችን ታሪክ የተማረን፣ተቀባይነት ያለውን፣ህዝብ የሚወደውን፣ጥሩ ስራ የሰራን፣ቅን ሰውን በህይወት ሳለ አንድም ቀን አዘክራው አታውቅም፡፡ ሱማ ብዙም አይገርመኝም፡፡ ከክርስቶስ ጀምሮ፣ሐዋርያት፣ሊቃውንት እንዲሁ እንደ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ተሳደዋል፣ተገርፈዋል፣ስማቸው ተፍቷል፣ተገለዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጽና እንዳለው እኔ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ጽና ነው የምልህ፡፡ እኒህ የሚያሳድዱህ ሁሉ አንድ ቀን ወጋቸውን ያገኛሉ፡፡ ማንም የወንጌል መምሀር የመጋቤ ሐዲስ በጋሻውን ያህል እውቀት የለህም፡፡ ይህ በቃላት ሳይሆን በተግባር ታይቷል፡፡ ህዝበ ክርስቲያኑ ጠጠር መጣያ እስኪታጣ ድረስ መንገድ ዘግቶ ወንጌልን ሲሰማ ከመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ አውደ ምህረት የበለጠ በቤተክርስቲያናቸን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ሰይጣን ቀና ጠላት አስነሳ፡፡ እንደ ሐዋርያት ሊያስወግር፡፡ በጋሳ ቢያልፍም የሰራው ስራ ግን አያልፍም፡፡ ብዙወች ሲሉ እሰማለሁ፡፡ በጋሻው እኮ አልተማረም፡፡ አቋርጦ ነው የወጣው፡፡ ማድነቅም ያለብህ የህንን ነው፡፡ ሳይማር እንዴት ወንድሜ አንተን በለጠህ፡፡ እንዴት ከአንተ ብዙ ከተማርከው የበለጠ ታሪክ ሰራ፡፡ ምን ታደርገዋለህ፣ከእግዚአብሔር ስሰጥ እንጂ በመማር ብቻ አይደለም፡፡ ስንት የተማሩ የሚባሉ ግን ያልተማሩ ብዙ ሰዎች እንዳሉ አታውቅም፡፡ በአለማችን ድንቅ ድንቅ የተባሉ የፈጠራ ውጤቶች የተገኙት ባልተማሩ ሰነፍ ተብለው በሚጠሩ ሰዎች እንደ ሆነ ታውቃለህ፡፡ ወንድሜ እኔ ተምሬ፣ድግሪ ይዤ፣አቋቋም አውቄ እያልክ ስትጎራ ያልተማረ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተሰጠው መጣና አለምን አስደነቀ፡፡ ታሪክ ሰራ፡፡ አሁን ሙስሊሙም፣መናፍቁም፣ኦርቶዶክሱም፣ሚዲያውም ሁሉም ነገር የሚያወራው ስለአንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ አረ እናንት ይህ ሰው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው ይህ ሁሉ የሚነገርለት፡፡ ወንጌሉም፣መዝሙሩም፣ተገሰጹም ለአንድ ሰው ብቻ የተሰጠ እስኪመስል ድረስ አለም ሰለሱ ብቻ ታወራለች፡፡ አለም ድሮም እንደዚህ ናት፡፡ ደግሞ እኮ የሚገርመው ነገር ከየትኛውም ወገን የሚሰማው ተስተካክሎ ያገልግል አይደለም፡፡ ከኦርቶደክስ ይለይ ነው፡፡ አስገራሚ ነው፡፡ እኔ እማውቀው ከውጭ ያሉትን ማምጣት እነጂ በግድ አንተ ውጣ እኛ ብቻ ኦርቶዶክስ እንባል፡፡ አስገራሚ ነገር ነው፡፡ ምን ይደረግ የተማሩት ተዋጡ ያልተማረውን እግዚአብሔር አገነነው፡፡ እንደ ይሁዳ ታናሽ ሳለ መረጠው፡፡ አለምና መላው በእርሱ የወንጌል ትምህርት ስትናወጥ ሰይጣን አየና እንዴት አድርገን ይህን ደቀ መዝሙር ከቤተክርስቲያን እንለየው ብሎ ክፉ ሀሳብ አሰበ፡፡ እስቲ ማን ይሙት የየትኛው ደቀ መዝሙር የስብከት ካሴት ነው እንድ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው ብህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በመላው አለም እንደ ወረርሽኝ የተበተነው፡፡ እንዲያው የእርሱ ስብከት በሞባይሉ፣በኮምፒዩተሩ አድርጎ አንዴ አይደለም 1000 ጊዚ ድጋግሞ የላደመጠ፣የማያደምጥ እርሱ ማን ነው፡፡ በእውነት ከሰይጣን በስተቀር አርሱን የሚያሳድዱት ሁሉ እቤቱ ገዝቶ ያላዳመጠ፣ያላስደመጠ ማን ነው፡፡ ይህ ሁሉ ህዝብ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻውን የተከተለው ሌላ ምኑንም ብሎ ሳይሆን እንደ ኢሱስ ክርስቶስ ንጹህ የወነጌል ትምህርት በማስተማሩ ብቻ ነው፡፡ ዛሬማ በየመድረኩ የምንሰማው እንርሱን አትስሟቸው፡፡ እኛን ብቻ ስሙ፡፡ እናንተ በየቤተክርስቲን አውደምህረቱ የእግዚአብሄርን ቃል ሳይሆን የተጫናችሂትን ይዛችሁ እየመጣችሁ እነ መምህር በጋሻው እንዲህ አድርገው ህዝቡን ወደ ራሳቸው ወስደውት እኛን ደብቀውን ነበር፡፡ አሁን ይኸው መጣን፡፡ ተእንግዲህ አታስገቧቸው፡፡ የኛን መዝሙር፣ስብከት ብቻ ግዙ ትሉናላችሁ፡፡ የመምህር በጋሻው ስራዎች ግን ማንም በየአውደምህረቱ አንደናንተ ሳጮህ ህዝቡ ባለበት ቦታ ድረስ ሄዶ አሁን አሳተመ ወይስ አላሳተመም እያለ ገና ከማተሚያ ቤት ነው የሚያልከው፡፡ እናንተን ያስቀናችሁ ሌላ ምንም አይደለም ይህ ነው፡፡ ገንዘብ ዘንዘብ ያለ ያውቃል ተብሎ የል፡፡ እርሱ ግን ክርስቲያንና ቢስማር ሲወጉት ይጠብቃል እንደተባለው የበለጠ ነው ያገነናችሁት እንጂ ምንም አታደርጉትም፡፡ እዚህ ቦታ በኢህ ተመርቄ እያልክ አትደስኩርብን ወንድሜ፤ ዲግሪ አይደለም መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው ደሳለኝን ታላቅ ገድል እንዲፈጽም ያደረገው፡፡ ክርስትና በመማር ሳሆን በማመን ነው ወንድሜ ዝም ብለህ አትድከም፡፡ እንደ መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው እኔ ምንም አላውቅም በመማርማ ስንት አመት የሚበልጡኝ አሉ በል ዝም ብለህ፡፡ ነገሩ አይፈረድባችሁም ክርስትና ይኸው ነው፡፡ አልጋ በአልጋ ነው መንገዱ ምንግስተ ሰማት ሴሄዱ የሚል ጥቅስ የለም፡፡ እንኳን በወንጌል መምህሩ በእኛ በሰሚዎችም ላይ ያለውን ፈተና እኛ ነው የምናውቀው፡፡
በመጨረሻም መጋቤ ሐዲስ መምህር በጋሻው እየሆነ ያለው ነገር በሐዋርያት ላይ የደረሰው ግፍና መካራ ነውና እግዚአብሔር በተጋድሎ ያጽናህ ነው የምለው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡
ሰይፉ ነኝ
አዲስ አበባ,ልደታ
yap you are right the right bible is one, I think you get me what I mean the bible is one dat is the righ bible. but now day's there are lots of copies of 'bible's' which are published by different missionaries those who are integrated with with different goals the right Bible are the right meaning which doesn't have any fallacy with those booklets(parts of the bible) but those 'bible' which are ublished by different missionarises and religious groups have a huge gap between the words, ideas and otehr many staffs =====================================================================================================
ReplyDeleteso, the Bible is One which doesnot have any fallacy between the parts of it.
thank you!!!!!!!
kee JIMMA UNIVERSITY ምን አይነት ጉድ ነው እባካችሁ???
ReplyDeleteባሕረ ጥበባት በምትባል ቤ/ክ ሆኖ ሌብነት???
ያሳዝናል!!!!!!!!!!!!!!!!
bewnetu yemiberetata neger new ketilubet
ReplyDeleteke engdih yemademitewun mezmur yaredawi zemanetun mermerie yhonal!!!
and adirgen ayzoachihu bertu,,,e/hair kehulachin gar yihun
egziabhair hoy tebekin
Yegna Derasi Min Watew, Mezmur ena Zema Kesemay Siset New Yetebalew Hizibin Siyamogn Mehonu New. And ken Gin Egziabher Yiferdal Lehulum Libona Yistachew, Legenzeb Teblo Amita Yeweledechin, Welda Yasadegechin Enat Betekrstiyan Tut Menkes Agbab aydelem, Yizegeyal Enji Firdu Aykerim
ReplyDeleteምን ችግር አለው እግዚያብሔር ብቻ ከተወደሰበት
ReplyDeletethank you so much brother. you 100% right that is the truth. memhr begashew we love you and also we proud of you. keep going brother may God bleswe you with all your heart diser.
ReplyDeletebeyn
New York.
ለሰይፉ!
ReplyDeleteከላይ ሰይፉ በሚል ስም ስለ በጋሻውና ተያያዥ ጉዳዮች ሰፊ ማብራርያ ለሰጠኸን ወንድማችን ፤ ስለትጋትህና ስለትብብርህ ዘመሰግናለሁ፡፡ ነገርግን ወንድሜ ማስተዋል ያለብን ነገር ያለም ይመስለኛል፡፡ ቅ/ዮሃንስ በ1ና መልዕክቱ ምዕረፍ 4፡1 ላይ ‹‹...ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና...›› ይላል፡፡ ምን ማለት ፈልጌ መሰለህ ፤ ቅ/ቤ/ክርስቲያን ብዙ ፈተናዎችን አልፋ ነው እዚህ የደረሰችው ... አሁን ደግሞ ማወቅ ያለብህ በበጎ ብቻ ነገሮች መመለከት ሳይሆን መመርመርም ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር እንደነገረን በጎውና ክፉው ፤ እውነቱና ሓሰቱ ተደባልቆ ያለበት ስለሆነ ማለቴ ነው፡፡ አልመረምርም ዝም ብዩ እንደመጣ እቀበላለሁ ካልክ የምትጋጨው ከላይ ከጠቀስኩት ጋር ነው፤ በመጨረሻም ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ልትደርስ ትችላለህ፡፡ ይህን ስልህ ከላይ ስሙን የጠቀስኩት ግለሰብ ላይ እንዲህ ነው እዲ ነው ልልህ ፈልጌ ሳይሆን ፤ በቃ በትዕግስት ግን ቃሉም እንደሚነግረን ምናለ እውነት ይሆን ወይ ብለህ ብትመረምር!! አንተ ተከራከርክ እንጂ በሌላ እምነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ ምስጢሩን ያውቁታል፡፡ እነሱ ለዓላማ ስለሚሰሩ አይገዳቸውም ፤ አንተ በንጹህ ህሊና ላለኸው ወንድማቸውም አያዝኑም!! እባክህ ትንስ የመመርመር ልብ ይኑርህ ፤ እነዲህ ብታደርግ ምናልባት ካላስፈላጊ ትፋት ትድናለህ፡፡
ስለሰውዩው ጸጋ ከመንፈስ ቅዱስ ነው ብለህ መገመትህ ክፉ አይደለም ፤ ነገር ግን አንተ ምስክርነት ከመስጠትህ በፊት እስኪ አካሔዱን በቃለ እግዚአብሔር መርምረው፡፡ አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴ 7፡ 15-16 ‹‹ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ...›› ብሎናል፡፡ ሰውን ከፍሬው እነደጂ ከንግግሩ ማወቅ በእውነት ከባድ ነውና፡፡ አንተ በድፍረት በጋሻው ወጣቱን ወደ ሓይማኖት መለሰ አልክ ፤ በውኑ ምን ያህል እርግጠና ነህ ፤ እንዴት አንድ ሰው እንዲህ አደረገ ብለህ በድፍረት ትናገራልህ ካሄድከው ጥናት አለ ፤ በርግጥ ሰው የዋህ ስለሆነ የእርሱንና መሰሎቹን ስብከት ሲሰማ ታይ ይሆናል ፤ ነገር ግን መቼ ሰዉ ቀርቶ እርሱ ወደ ቤ/ክርስቲን መጣ፡፡ እስኪ ከልብ ሆነህ አንድ ጥያቄ መልስልኝ ፡ በውኑ በጋሻው አንድ ቀን ንሰሃ ገብቶ ያውቃል ፤ ከገባ ንሰሃ አባቱ ማን ይባላሉ ስጋ ወደሙስ ተቀብሎ ውቃል ... ተወው እርሱን በሰንበት አስቀድሶ ቤ/ክርስቲያን ገብቶ ያውቃል ...ዐረ ተወው እርሱን .. ነጠላ ለብሶ ያውቃል ወይ የቅ/ቤክርስቲን የጸሎት መጻህፍትን ይዞ ጸልዮ ያውቃል ወይ ... አዎ ውቃል ካልክ በቃ አንተ እርሱን አታውቀውም ማለት ነው ... እስኪ እባክህ ጠይቀውና ንገረኝ ... እኔ እርሱን ካንተ ይልቅ ጠንቅቄ አቅቀዋለሁና፡፡ ሌለው ምንፍቅነው ና በዚህ ብሎግና በሌላው ሚነገረውን ተወው.. በቃ እኔ ልኩህን ብቻ ስለማድረጉ ማረጋገጫ አምጣልኝ፡፡ በቃ ያን ጊዜ መነጋገር ሳሻል አይቀርም፡፡ ታድ ለራሱ ወደ ቤ/ክርስቲን ልመጣን ሰውዬ እንዴት ሌላውን አመጣ ብለህ ለመናገር ትደፍራልህ፡፡ ደግሞ የድፍረትህ ብዛት ከነ ቅ/ጳውሎስ ጋር ለማመሳሰል መሞከርህ አስገራሚና ስለመንፈሳዊነት ያለህ ግንዛቤ .... እነቅ/ጳውሎስ እኮ ከጌታ እግር ስር 3 ኣመት ከሶስት ወር ቁጭ ብለው ከተማሩ በኃላ ነው ለማስተማር ተሰማሩት ፤ ከየት የመታ ነው ሳማሩ መስተማር .. ሊውም በዚህ ዘመን.. ንት የምነግርህ ነበረኝ ፤ ነገር ግን አለ ቅ/ጳውሎስ .. ይቆየን!
አንተ ነህ እኮ የምታወራው እንደ ጥላ እየተከተልክ ከስር ከስር ባያስቀድስ ቢያስቀድስ አንተ እሱቤት ነው እንዴ ውሎህ በስንት ቀጠሩህ እነዛ ለዝና ገዳዮች ወንጌል አስተምሩን የሱ ምንፍቅና ካስተማርን እናንተ ደግሞ ቃላት እሰነጠቃችሁ ሳይሆን መዳኛውን እውነተኛውን ለምንድነው የማትገለጹልን እንደ መዥገር ሰው ላይ መጣነቅ እራሳችሁን ቻሉ ሰውን አትመርዙ የሄን ሁሉ ጊዜና መማማሪያ ሰአት ለተንኮልና ለስድብ ማዋል ምን ይባላላል ቸሩአባት ልቦና የስጣችሁ እንዴ ልጁ እኮ የሰራ ነው ስራውን እናንተ መርዛችሁን ስትረጩ በየሰንበት ት/ቤቱ ለጆቹንና ህዝቡን ግራ ማግባት ከተማው ሰፊ ነው ማን ይከለክለው መሰላችሁ አታድክሙት አምላኩን ፈርቶ ነው እንጂ ወሬያችሁ በጣም ነው የሰለቸው
Deleteአንተ ነህ እኮ የምታወራው እንደ ጥላ እየተከተልክ ከስር ከስር ባያስቀድስ ቢያስቀድስ አንተ እሱቤት ነው እንዴ ውሎህ በስንት ቀጠሩህ እነዛ ለዝና ገዳዮች ወንጌል አስተምሩን የሱ ምንፍቅና ካስተማርን እናንተ ደግሞ ቃላት እሰነጠቃችሁ ሳይሆን መዳኛውን እውነተኛውን ለምንድነው የማትገለጹልን እንደ መዥገር ሰው ላይ መጣነቅ እራሳችሁን ቻሉ ሰውን አትመርዙ የሄን ሁሉ ጊዜና መማማሪያ ሰአት ለተንኮልና ለስድብ ማዋል ምን ይባላላል ቸሩአባት ልቦና የስጣችሁ እንዴ ልጁ እኮ የሰራ ነው ስራውን እናንተ መርዛችሁን ስትረጩ በየሰንበት ት/ቤቱ ለጆቹንና ህዝቡን ግራ ማግባት ከተማው ሰፊ ነው ማን ይከለክለው መሰላችሁ አታድክሙት አምላኩን ፈርቶ ነው እንጂ ወሬያችሁ በጣም ነው የሰለቸው
Deleteandairigenoch lemitesetun mereja egizabher yisitachihu, yetenekabet yinchacha inanite gin atisinefu bertuበሃይማኖት የማይመስል ሰውን ግጥም መኮረጅ ምን ያስብላል? የመናፍቅ አድናቂ፣ መናፍቅ ተከታይ፣ መናፍቅ፣ ከሃዲ፣ .............. ሌላም ሌላ ያስብላል። ከላይ አንድ ወንድም አንደገለጸው ከግጥሙ አንድ አይነት ሳይሆን እን እገሌን መከታተል ምንድን ነው።
ReplyDelete2. ቤተ ክርስትያነ ባህረ ጥበባት ነው የምንለው "አንተ ታልቃለህ እንጂ የቤተ ክርስትያን ጥበብ አያልቅም ባህርን በእንቁላል ክርፍት ማለት ነው" ከሰማይ የመጣ ዜማ እያለ ከአንድ መናፈቅ የመጣ ምን ያደርግልናል። ከሊቃውንት ግጥም ጠፍቶ ነው እንዴ ከመጸህፍትስ(ከገድላት፣ ከስንክሳር፣ ከድርሳን፣ ከሊቃውን ቅኔ) ከአንድ መናፍቅ ግጥም የሚኮረጀው። ምን አለ ያ ባለ ቅኔ ማለት ይቻል የለም እንዴ።
3. ተመሳስሎ መኖር እስከ መከር ነው። በርቱ እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ።
የሁለተኛው መዝሙር የኦርቶዶክስ ነውያላችሁት የፕሮቴስታንት ነው ሁ ለተ ኘኛ ወው ሰስ ነን ኘኝ ሊነጋ ሲጀምር ሰማዩ ሲቀላ ያለበት አሰስተከካከሉ
ReplyDeleteyou guys have a problem when jesus christ our lord preached widely and deeply , i could not get a single mistake from begashews preaching . you andadirgen better shut up do not even try to split our church.
ReplyDeleteEgizhabher lehulachin mastewalun yisten , GOD keep Orthodox Tewahedo Churh
ReplyDeletelebonawn ystln lekehadi menafkan
ReplyDeletegelesebe masaded mefthe ayhonem
ReplyDelete