Wednesday, December 21, 2011

አስኬማው የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን (የትዝታው ሳሙኤል ግሩፓች)


የሥርዓት አልበኞቹ ግሩፕ ፊት አውራሪዎች

(አንድ አድርገን ታህሳስ 11 ፤ 2004)፡- በዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ህገወጥነት እና ስርዓት አልበኝነት በፊት እነ በጋሻው ደሳለኝ እና ትዝታው ሳሙኤል ባስመረጧቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን በስራ ላይ የሚገኝውን የሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና በምትኩ ህዝቡ ይሆኑኛል ፤ ቤተክርስትያኗን ለማተዳደር እውቀቱም ሆነ ብቃቱ አላቸው ያላቸውን ሰዎች እንዲመርጡ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተፃፈ ደብዳቤ ከሳምንት በፊት በእጃቸው ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩም ሆነ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አያገባቸውም በሚል እሳቤ ሰውን ለሌላ ብጥብጥ ለማነሳሳት የቤተክርስትያ አስተዳዳሪው የኛ የሚሏቸውን ሰዎች  እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡

በፊት የነበረው ሰበካ ጉባኤ በእነ በጋሻው እና ትዝታ ሳሙኤል ገፋፊነት እነርሱ ያቀረቧቸውን ሰዎች ያስመረጡ ሲሆን ቀድሞም ቢሆን አካሄዱ ትክክል ስላልሆነ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፡፡ ለእነሱ አላማ የሚያስፈፅም ቃላቸውን የሚሰማ ፤ ተግባራቸውን የሚያደርጉ ሰዎችን ነበር ማስቀመጥ የቻሉት ፡፡ ለዘመናት ዲላ ሚካኤል ላይ አውደ ምህረቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲከለክል እነዚህ አባላት በመፍቀድ ሲያስፈነጩበት ከርመዋል፡፡ የህዳር የቅዱስ ሚካኤል ጉባኤ የመላእኩን ስም ሰውን አስረስተውት የትዝታው ጉባኤ እስከመባል ደርሶ ነበር ፡፡ አሁን ግን ስራቸው ተመዝኖና ፤ ግራ ቀኙ ታይቶ የቤተክርስያኑ ሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና አዲስ ሁሉ ምዕመን በተገኘበት የምርጫ ፕሮግራም እዲደረግ በደብዳቤ መልክ ከሀገረስብከቱ ቢደርሳቸውም ፤ ‹‹ቤተክርስትያኗ የምትተዳደረው በህዝቡ እንጂ በማንም አይደለም›› በማለት በግብር የሚመስሏቸውን ሰዎች ሰብስበው በመነጋገር የጋራ አቋም በማስቀመጥ ፤ እምቢተኛነታቸውን በቃለጉባኤ በማስደገፍ ተሰብስበው ተፈራርመዋል፡፡

በስብሰባ ላይ ከተገኙት ምግባርም ሆነ ስርአተ ቤተክርስያንን የማያውቁ ሰዎችና መናፍቃን ፤ ‹‹ቆቡ የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን›› ብለው ሲናገሩ አርፍደዋል፡፡ በሌላ በኩል እነዚህን ሰዎች የሚቃወሙ ስርአተ ቤተክርትያን ይከበር የሚሉ ሰዎች ፤ የሀገረ ስብከቱ ትዕዛዝ እንዲከበር አጥብቀው እየተሟገቱ ሲሆን ፤ ጉዳዬ መፍትሄ እንዲያገኝ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት መምጣቱን ለማወቅ ችለናል፡፡


በጣም የሚገርመው በቤተክርስትያኑ አጥር ውስጥ ይህን ስብሰባ ያደረጉት ከመካነ ኢየሱስ ፤ ከሙሉ ወንጌል ፤እና በተሀድሶነት በየጊዜው ስማቸው የሚነሳ ሰዎችና ፤ የሌሎች እምነት ተከታዮች ሲሆኑ እኛን ወክለው መሰብሰባቸው ነው፡፡  የመፈራረሚያ ሰነዱ ላይ ያልፈረመ ሰው 30 ብር እንደሚቀጣ በማስጠንቀቅ አስፈርመው ፤ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር አድርገው ወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊልኩ ችለዋል፡፡

አቡነ ፋኑኤል የሀረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ በ፳፻ ዓም ባስተላለፈው ውሳኔ ሰባኪያኑ እና ዘማሪያኑ ሁኔታዎች እስኪጣሩ በየትኛውም የቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ እንዳይሰብኩ እና እንዳይዘምሩ የተላለፈውን ውሳኔ፣ አቡነ ፋኑኤል በኔ ሀገረ ስብከት ዲሞክራሲ ሞልቷል በሚል ማንም ሊከለክላችሁ አይችልም በማለት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማናለብኝነት ሽረው ሰባኪያኑን እና ዘመሪያኑን የልብ ልብ ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ያደረጉ አባት መሆናቸው አይዘነጋም፥ በወቅቱም ከፓትሪያሪኩም ሆነ የቤተ ክህነቱ ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ አስተያየት ስላልቀረበላቸው በተመሳሳይ ማናለብኝነት ሥራቸው ይህው እስከ ዛሬ ቀጥለውበት ይገኛሉ።

አሁን ስራውን እንዲያቆም የተወሰነበት ሰበካ ጉባኤ የምርጫው ሂደት ላይ ራሳቸው ተመራጭ ፤ ራሳቸው ፔቲሽን ሰብሳቢ ፤ ራሳቸው ቆጣሪ ፤ ሆነው ነበር ምርጫውን ያከናወኑት፡፡ በቦታ ላይ ብዙ ተከታይ ያላቸው የእነ በጋሻው ግሩፕ የተቀነባበር የምርጫ ትርኢት ነበር፡፡ አሁን ግን በቃችሁ ሲባሉ ‹‹አይበቃንም ፤ ማንም ከህዝቡ ውጪ ስለቤተክርስትያኗ የሚያገባው የለም›› የሚል ፤ ከስርአተ ቤተክርስትያን ያፈነገጠ አካሄድ ይዘው የሚመጣውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

12 comments:

  1. weye gude derome eko yetaweqe newe enanete addis yehonebachehual endea?

    gena menu teyazena zelalem sibetebetu yenoralu...zare be asechekuaye mefetehea kaletesetachewe.

    yeleboche gubayea hulegizea yaderegalu

    ReplyDelete
  2. ሀ/ሚካአኤል ዘ ዲላDecember 21, 2011 at 10:26 AM

    kezih befite yeediru abelet sim tiri kee and mezgeb yenebere sihon bee ahunu sibeseba gin eyandandu abelal bemizoraw attendance lay kelfereme 30 birr tiketalechihu bilaw bemesfereret kesferemu bohala shegn/cover page/ lay yeresechawun yee amets hasab bemesfer bee edir mehatem leteqilay beta kihinet likawal.
    Betem yemigermew neger dagmo yelela emnet teketay/protestant ,mekeneyasus ,kelehiwot/yehonut bee sebasebut firmiya wust meketatu new.
    Silazih sawochu lee genezeb ayinachew yetewera ena kidist haymanotachinin leleloch aselifaw lemestet yetezegaju mehonachewun enditawuqu enelalen
    ገ/ሚካኤል ከዲላ!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  3. EGZIABEHER LAYKEBEREBET BEMEBETABET ANDENET SELAM FEQER LAYMETA MENEW BANJAJAL!

    ReplyDelete
  4. ebakachihu sewoch yedir papas mehon yalchale yekdstitu lijoch yehiyaw ye Egziabher shumamintn mehon yichalal yemiasbil yenufro tigabegna bedilla Kidus Michael tahisas 8 2004 E.C kisfetun abesere Kidus Michael yifaredew.

    ReplyDelete
  5. ebakachihu sewoch yedir papas mehon yalchale yekdstitu lijoch yehiyaw ye Egziabher shumamintn mehon yichalal yemiasbil yenufro tigabegna bedilla Kidus Michael tahisas 8 2004 E.C kisfetun abesere Kidus Michael yifaredew.

    ReplyDelete
  6. ebakachihu sewoch yedir papas mehon yalchale yekdstitu lijoch yehiyaw ye Egziabher shumamintn mehon yichalal yemiasbil yenufro tigabegna bedilla Kidus Michael tahisas 8 2004 E.C kisfetun abesere Kidus Michael yifaredew.

    ReplyDelete
  7. ኧረ መ/ር ሰሎሞንን ከዚህ አውጡት ይሄኮ ኢየሩሳሌም እንዳጋጣሚ የተነሳው ፎቶ ነው እንጂ በፍፁም ከነሱ ጋር ምንም ኅብረት የለውም! ግን ሁላችሁም እንደምታውቍት ክባድ ከሀዲ ነው በተለይ ብፁዕ አቡነ ሣሙኤልን......ወደፊት በዝርዝር ከመረጃ ጋር እመለስበታለሁ.ለማታውቊት ከቀኝ ወደ ግራ ሁለተኛው አይ ቀሲስ /አሀዱ አብ..የማይል ፡ኪዳን.. የማይደግም /ቄስ እየተባልክ ከሚሳቅብህ ሙዳዬ ምጽዋት ዘረፋህን እና ወደላይ /ስም ልጥራ እንዴ/ጉቦ ማቀበልኅን ትተህ እባክህ ተማር....ለዛሬ በቃኝ ፎቶህን ሳየው ደግሞ ምክሬን እቀጥላለሁ።

    ReplyDelete
  8. "Ye Dilla hizb hoy yaladeregnilih min ale" ale Yared bebetekrstian medirek lay komo

    Min Yidereg Enersu shumet legash Enersu kelkay honew betekrstianin endefelgu siyadergu kermew ahun degimo‹‹ቆቡ የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን›› lemalet beku

    kebahitawi Amiha jemirew Ye Dillan hizib gira siyagabu ena hizbun sikefafilu Yeneberut drgit ke ahun behuwala liyabeka yigebal Enitagel

    ReplyDelete
  9. abune paulos ke dilla lay ejachewn yansu. drom goremsochn lezih yabeku esachew nachew. betekristian selam aggnta efoy alech sibal lela mekera abekelulat. tiglna mekera yteykal enji yhe ye wushet drbrbosh nege ynadal. yeedr dagnam and ken wede edru ymelesal kob yelenm enji yalewm yekfatu medebekia kalhone yekdsna yalemehonun ye gil hywetu yasawqal. genzeb kagegne lemanm hedo ho ylal.

    ReplyDelete
  10. ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የላትም ማለት ነው ?በጋሻው ምን ስለሆነ ነው ቤተክርስቲያኑን የሚበጠብጠው እውነት ወንገል ከገባው እንዲ ነው የሚለው ቃሉ በጣም ያሳዝናል 1 23 የሚሆኑ ሰዎች ትልቁን ቤተክርስቲያን ሲበጠብጡ ሲያፈርሱ ማንም ያልደፈራትን በነዚህ ተኩልዎች ምን ይባላል ለነዚህ እ/ር ይበቀላቸው። ሌላ ምን ይባላል በጋሻው በጋሻው በጋሻው አትባረክ እ/ር ያዋርድህ አልሳደብም እንጂ.....

    ReplyDelete
  11. ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የላትም ማለት ነው ?በጋሻው ምን ስለሆነ ነው ቤተክርስቲያኑን የሚበጠብጠው እውነት ወንገል ከገባው እንዲ ነው የሚለው ቃሉ በጣም ያሳዝናል 1 23 የሚሆኑ ሰዎች ትልቁን ቤተክርስቲያን ሲበጠብጡ ሲያፈርሱ ማንም ያልደፈራትን በነዚህ ተኩልዎች ምን ይባላል ለነዚህ እ/ር ይበቀላቸው። ሌላ ምን ይባላል በጋሻው በጋሻው በጋሻው አትባረክ እ/ር ያዋርድህ አልሳደብም እንጂ

    ReplyDelete
  12. ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የላትም ማለት ነው ?በጋሻው ምን ስለሆነ ነው ቤተክርስቲያኑን የሚበጠብጠው እውነት ወንገል ከገባው እንዲ ነው የሚለው ቃሉ በጣም ያሳዝናል 1 23 የሚሆኑ ሰዎች ትልቁን ቤተክርስቲያን ሲበጠብጡ ሲያፈርሱ ማንም ያልደፈራትን በነዚህ ተኩልዎች ምን ይባላል ለነዚህ እ/ር ይበቀላቸው። ሌላ ምን ይባላል በጋሻው በጋሻው በጋሻው አትባረክ እ/ር ያዋርድህ አልሳደብም እንጂ

    ReplyDelete