Wednesday, December 14, 2011

ነገሩ ወዲህ ነው


‹‹ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ። ››


ትንቢተ ኢሳይያስ 621

ስለ አክሱም ፅዮን የESAT ዘገባ.. 

በዚህ ዘመን የሰሚን ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ብዙ ክስተቶች  እየተከሰቱ ነው። በተለይ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ፤ ይልቁንም ባለፉት ፳ ዓመታት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የተለያዩ አስደንጋጭ ክስተቶች ተከስተዋል፣ የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት አስደፍቷል፣  ለምን  በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን በቤተክርስቲያን ላይ ይህ ሁሉ ፈተና በዛባት? ፈተናውስ ከየት መጣ? እንደሚታወቀው በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን ብዙ ክፍተቶች፣ ግድፈቶች፣ ቀኖና ጥሰቶች፣  አፈናዎች፣ ስም ማጥፋቶች፣ እንዲሁም ብዙ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎችና ሙስናዎች ተፈጽመዋል ፡፡ እነዚህ ሁሉ ግፎች እና በደሎች ሲፈጽሙ ከጥቂት የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ወይም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ውጪ የተቃውሞ ድምጽ ያሰማ የለም፡፡ በዙሪያቸው የከበበቧቸው ሰዎች "ይደልዎ" ከማለት በስተቀር ምንም ዓይነት ተቃውሞ አላቀረቡም ፤


በዚህ ዓመት የተለያዩ ሚዲያዎችን የተለያዩ ዜናዎችን ተመልክተናል ፤ ብዙ ግር የሚያሰኙ ነገሮችን ለማየት ችለናል ፤ እንዴት ሊሆን ይችላል ? በማለት ብዙ ጥያቄዎችን ፈጥሮብናል፤ የተወራው የሚወራ ሁሉ እውነት ነው ብለን ባንቀበልም ፤ ሁሉም ነገር ደግሞ ውሸት ነው የሚል እምነት የለንም ፤ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ቅርሶች አውሮጳ ውስጥ የሚገኙት እንደሚበልጡ ምን ያህላችን እናውቃለን? ከእጃችን በስጦታም ይሁን በዘረፋ የወጡትን ማስመለስ ባንችል እንኳን በእጃችን ላይ የሚገኙትን መጠበቅ ታሪካዊ ግዴታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፤ እንደ እድልም አድርጎት ከአባቶቻችን ሲገላበጥ የመጣው የቤተክርስያኒቱ ቅርሶች ለሚቀጥለው ትውልድ ማስረከብ መቻል ግድ ይለናል፤ በአሁኑ ሰዓት በታቦተ ፅዮን ዙሪያ መረጃዎች እየተንሸራሸሩ ይገኛሉ ፤ ከሞላ ጎደል ኢሳት የዘገበውን እኛም እናውቀዋለን ፤ እኛ የምናውቀው ግን ኢሳት(ESAT) እንዳወራው አይደለም:: መረጃዎቻቸውን ሁላ በዝርዝር ለማቅረብ ሞክረዋል ነገር ግን ያቀረቡት ሁሉ አሳማኝነት ይጎድለዋል የሚል ሀሳብ አለኝ:: 


አስቲ አስቡት በሉሲ ጀምሮ ወደ ታቦተ ፅዮን ዘገባ መሸጋገር ምን ይሉታል ? ሉሲና ታቦተ ፅዮን ለእኛ ምንና ምን ናቸው? ፤ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምራብያውያኑ ራሳቸው በሰሩት መሳሪያ ፤ ምርምር አድርገው ሉሲን ከ1.2 ሚሊየን በላይ ዓመት ኖራለች ብለውናል ፤ ይህ ደግሞ ለእኛ ክርስትያኖች ተቀባይነት የለውም፡፡ የሰው ዘር ተፈጠረ ብለን የምናምነውን ዓመት እና እነርሱ ደግሞ ድንቅነሽ ኖራለች የሚሉን እድሜ የሰማይና የምድር ያህል እርቀት አለው፡፡ ስለ ሉሲ አውርተው ቢጨርሱ መልካም ነበር፡፡ ምዕራብያውያኑ ይህን ለማለት የሚጠቀሙበት መሳሪያን የተነሳበትን ጥያቄ መመለስ አልቻሉም፤ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ፤መንግስት የሚሰራውን ስራ ለመንቀፍ ያመቻቸው ዘንድ ፤ ወቀሳ ለመሰንዘር ከድንቅነሽ ወደ ታቦተ ፅዮን ባልተዘረጋ ድልድይ ሀሳባቸውን መሰንዘር ተገቢ ነው ብለን አናምንም፡፡  
 በ1991 ዓ.ም 70ሺህ ኢትዮጵያውያን ከ19 ሺህ በላይ ደግሞ ኤርትራውያን እንዳለቁበት የሚገመተው የኢትዮ- ኤርትራ የእርስ በእርስ ጦርነት ጊዜ ከ50 በላይ የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ጦርነቱ የሚያመጣውን ጥሩ አጋጠሚ ወይም  ክፍተት ተጠቅመው ታቦቷን ወደ ሀገራቸው ለመውሰድ በአክሱም እና በተለያዩ የምስራቁ ክፍል ለአርኪዎሎጂ ቁፋሮ ነው በሚል እሳቤ በቦታው ላይ ነበሩ ፤ ይህን እኛም እናውቃለን ፡፡  ምዕራባውያን አይደለም ጦርነት ተከፍቶ ጦርነት ሲታሰብ ወደ ሀገራቸው ለመሄድ አየር መንገዶችን በር እንደሚያጨናንቁ ነበር የምናቀው ፤ የእስራኤላያኑ የአክሱም ቆይታ ግን የሚገርም ነበር፡፡ ሀገር ባልተረጋጋችበት ወቅት ሰው ሀገር ምን ሊሰሩ ቆዩ?  ምንስ የተደበቀ አላማ አላቸው? ፤ ታቦተ ፅዮን በእግዚአብሔር መልካ ፍቃድ እንደመጣች ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንደምትሄድ ያስተዋሉ አይመስልመ ነበር ፡፡ ለማንኛውም ይህ ሁሉ ነገር አዲስ ለሚሰራው ሙዚየም ጋር አላፈላጊ ነገር እንዳይፈጸም የማቂያ ደውል አድርጌ ወስጄዋለሁ ፤ አቡነ ሳሙኤል የጥቅምት ሲኖዶስ ላይ እንዳሉት ስለ ሙዚየሙ ስራ አንስተን መወያየት መቻል ያለብን ይመስለኛል፡፡ ማነው ሙዚየሙን የሚሰራው ? 8.5 ሚሊየን ዩሮ ማን ሊለግሰን ቻለ? ከየት የተገኝ ብር ነው ሙዚየሙን የሚያሰራው ? ለምንስ ለጋሾች ለሙዚየሙ ማሰሪያ ሊረዱን ቻሉ? በቃልኪዳኗ ታቦት ዙሪያ የሲኖዶስ ሀሳብ ምንድነው ? የአባ ጳውሎስስ ሀሳባቸው ምንድነው ? በሚሉት ዙሪያ ህዝቡ መወያየት ቢችል መረጃ ቢኖረው ጥሩ ነው እላለሁኝ፡፡ ሁሉ ነገር እንዳለ ሆኖ ያለ እግዚአብሐር ፍቃድም የቃልኪዳኑ ታቦት ምንም እንደማትሆን ሙሉ እምነታችን ነው፡፡


ሌላም አለ ያድምጡ‹‹አሁንም እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››


9 comments:

 1. Ende Egziabher Fekad inji endegna fekad ayihun

  ReplyDelete
 2. minew yeminsemaw hulu merdo hone. yemisirach yeminisemaw meche new ? woy zemen !!

  ReplyDelete
 3. ኦሪት ዘሌዋውያን
  20፥9
  ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፥ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና ደሙ በራሱ ላይ ነው።
  ይልቁንም እርሱ በቀባቸው አባቶች ላይ ተባራሪ ወሬዎችን እያነሳችሁ የስድብ ናዳ የምታወርዱት ላይ ቅጣቱ እንዴት ይከብድ
  እገዚአብሔር ተነሳሒ ልቦና ስጣችሁ
  ለክፋታችሁ መሸፈኛ አድርጋችሁ የምትጠቅሱት ማኅበረ ቅዱሳንን ግን ለቀቅ አድርጉት፡፡
  የናንተን ክፉ ጥላቻ የሚያስተናግድበት ጊዜ ለውምና ፡፡
  እውነታውን ከ ፈለጋችሁ ግን የማኅበረ ቅዱሳንን ድረ-ገጽ ተመልከቱ፡፡
  የቤክርስቲያን አሳቢ በመምሰል ዘመኑ ያለፈበት ፖለቲካችሁን ባትደሰኩሩብን መልካም ነው፡፡
  ከክርስቲያን ይቅርና ከማንም ሰው የማይጠበቀውን የዘቀጠው ስነ ምግባራችሁም በእገዚአብሔር ዘንድ እንደሚያሰጠይቃችሁ በመረዳት
  መዝ 141፥3
  አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።

  በማለት አንደ ልቤ ከተባለለት የእሴይ ልጅ ቅዱስ ዳዊት ጋር ልመናችሁን በማቅረብ የተጋባባችሁ የስድብ ጋኔንን እንድታስወግዱ ምክሬን በመለገስ አዚሁ ልቋጭ፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ፡፡

  ReplyDelete
 4. though you are the same to them the comment was sent to you by mistake!
  sorry

  ReplyDelete
 5. Please lets pray to God he will give answer for all.

  ReplyDelete
 6. Geta Egziabher begowen Yaseman yale Amlak fekad menem lihon aychlemena hulun lersu enasaseb, ebakachehu abzeten entseley!!

  ReplyDelete
 7. Selame
  Endhe ayenate Zegabawochen kamzegabachew Befit mane Zegabew lemen zegabew belachew mayet betam asfalagi new bakachew Teru yemtezegbuten yahel sew endayamenachwe atadergu yemebalew propoganda new

  ReplyDelete
 8. BETERARA TSEHAY BETEKIRSTIAN TEKATELECHI!!! yehe yediabilos ye gibr abatachew and ye giragn ahmed sira new, ahunen giragn ahmed bimitim bewektu bewestu yenebere erkus menfes ahunin weldochu lay adro KIDIST BETEKIRSTIANIN eyateka new egna bicha sile hatiyatachin eyalekesin EGZIO MAREN ENEBEL SEYIFIN YEMIMEZU HULU BESEYF YITEFALUNA. AMLAKACHIN MEDANITACHI EYESUS KIRISTOS YASTEMAREN TIEGISTN NEW ESU ERASU MELAEKUN LIKO LIYATEFACHEW YECHALEWAL. EGZIO ENBEL KELIBACHIN ENALKIS YE ANDEBET BICHA AZENETA AYHUN KELIB WEDE AMLAKACHIN ENCHUH. ERGIT NEW BEZEMENACHI MERI ABAT ATITENAL EGZIO YEMIYASBIL ABAT ATNENAL!!! SILEMIHONUT NEGEROCH HULU ENE ALEW YEMIL SEMAET ENA MELKAM AMABT ATITENAL. EBAKACHU WEGENOCHIE YEMETAWEN FETENA EGZIABHER ENDIMELISEW ENALIKIS, NESEHA ENGIBA. BE'EWNET YIHIN EYADEREGU YALUT SEWOCH BE 650 G.C LAY EKO KEMOT YATEREFECHACHEW EKO HAGERACHIN NECH BAGORESKU TENEKESKU HONENA NEGERU AHUN BE ADEBABAY BETEKIRSTIYANIN MAKATEL KEJEMERU SENEBABTEWAL. MENGISTM BIHO HIGE MENGISTU YASKEMETEWEN YE HAYMANOT NETSANET EYASKEBERE NEW WEY!!!! ERASUN YITEYIK!!! YEHE EKO BE ALEXANDRIA BETEKIRSTIAN LAY YETEKESETEW HUNETA LIDEGEB AYIGEBAWEM, BARBEROCH (AREBOCH YIHININ NEW YADEREGUT. BAKACHU WEGENOCHE AHUN YALENIBET GIZE SEITAN BEGILTS WEGIYAWEN YASFAFABET ENA BIZUWOCHIN EYASATE YALEBET GIZE NEW, ENASTEWEL AHUN EKO MENAFKUM, AREMAWIWEM, ME'ERABAWEYANUM, ZEMENAWINETUM, GIBRESEDOMAWINETUM, GENZEB WEDAJINETUM, NUFAKEWEM, YENURO WEDENETUM ENA ENEZIHIN YEMESASELUT HULU DIABILOS BEKENACHIW HAYIMANOT ENDANTSENA YAMETACHEW FETENAWOCH NACHEW. LININEKABET YASFELIGAL AHUNIM ANTE SEITAN HID KEZIH WEGID KEATEGEBACHIN LINELEW YASIFELIGAL. BEFETENA YEMITSENA ESU YETEBAREKE NEW TEBLUAL AHUNEM LINASTEWEL YEMIGEBAW BETEKIRSTIANACHIN FETENA YEBEZABAT NETSUH ENA EWNETEGNA SILEHONECH NEW. LIBACHIN AYITAWEK LINTSENA YASFELIGAL WEGENOCHE, TINISH GIZE NEW YEH HULU CHACHATA HUKATA KELIBACHIN ENEMELES EGZIABHEREM YEMELESILINAL MAEBELUNM TSET YADERGAL. YE EGZIAHBER CHERNET ENA ERHRAHE KEGNA GAR YEHUN, YE ENATU YEDINGIL MARYAM REDE'ET ENA MELJA EAYILEYEN YE KIDUSAN MELAEKT ENA TSADKAN SEMAETAT REDE'ET KEGNA GAR YEHUN. AMEN. MENGISTE SEMAY KERBALECHINA NESEHA ENGIBA.

  ReplyDelete