Wednesday, December 21, 2011

‹‹ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ምንም አይነት ድርድር ውስጥ አታስገቡ ›› ብፁእ አቡነ አብርሀም


ለብፁእ አቡነ አብርሀም የሽኝት ፕሮግራም
በሕግ አክባሪነታቸው፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በመጠበቅ እና በማስጠበቅ እንዲሁም በብዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ የሚወደዱት እና የሚከበሩት ብፁዕ አብነ አብርሃም የምሥራቅ ሐረርጌ እና የጅጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሰየሙበት ካለፈው የጥቅምት ፳፻፬ ዓ.ም. በኃላ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሔድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገልጿል። ብፁዕ አብነ አብርሃም ከአሜሪካ መዲና ከሆነችው ከዋሽንግተን ዲሲ ሲነሱ በርካታ ካህናትና ምዕመናን በእንባና በልቅሶ ሸኝተዋቸዋል። ብፁዕነታቸው በበርካታ የአካባቢው ምዕመናን እና አድባራት በአይነቱ ልዩ የሆነ የመሸኛ ምሽት አዘጋጅተውላቸው እንደነበር ከቦታው የደረሰን ሪፓርት ይገልጻል። ብፁዓን አባቶች፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ካሕናት፣ ሰባኪያነ ወንጌል፣ ዲያቆናት፣ እንዲሁም በርካታ ከተለያየ ጠቅላይ ግዛት የመጡ ምዕመናን በዚህ የመሸኛ ምሽት ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል። ብፁዕነታቸውም በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ የዋሽንግተን እና አካባቢውን ምዕመናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ምንም አይነት ድርድር ውስጥ ማስገባት እንደሌለባቸው እና ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አባት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚችለው በሕገ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ተናግረዋል። እንደሚታወቀው በዚሁ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ  አነጋጋሪው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እንደገቡ የሚታወቅ ሲሆን በዚሁ ለብፁዕ አቡነ አብርሃም በተደረገ የመሸኛ ምሽት እለት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው የራሳቸውን ስብሰባ እያደረጉ እንደነበር የደረሰን ሪፓርት ጨምሮ ይገልጻል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸውም በፊት ብፁዕ አብነ ፋኑኤል ነባሩን ሀገረ ስብከት ወይም ሥራዎች ለማየት እና ለመረካከብ ፈቃደኝነታቸውን ባለማሳየታቸው እንደገና እንደ አዲስ የተለየ ሀገረ ስብከት ሊመሠርቱ እና ሊሰሩ እንዳሰቡ በስብሰባው ላይ የተገኙ ምዕመናን የነገሮችን ብልሽትሽት ያለ አካሄድ እያነሱ ሲያማርሩ ተሰምቷል። እንደምንጮቻችን አነጋገር ከሆነ በስብሰባው ላይ የነበሩት ጥቂት ተሰብሳቢዎች፣ የተስፋ መቁረጥ እንዲሁም የመሰላቸት ስሜት ይታይባቸው እንደነበር ተነግሯል ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልም የአካባቢውን ምዕመናን ስደተኛውንም፣ ገለልተኛውንም፣ መጻተኛውንም በጋራ በአባትነት እመራለሁ ሲሉ መሰማታቸውንም አንዳንዶች በግርምት ተመልክተውታል። 


ከመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

5 comments:

 1. ልብንና ኩላሊትን የሚመረምረው እግዚአብሔር ብቻ ነው። የአቡነ አብርሃምን እና የአቡነ ፋኑኤልንም እንዲሁ። በእናንተ መንገድ ያልሄደ ሁሉ ሕገ-ወጥ ነው። የተለያየ ድሪቶ ስም ይለጠፍለታል። ሌላው የሚያቀርበው መስዋዕት ወይም የሚፈተተው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ "ፋንድያ" እንደሆነ ያለ ሐፍረት ይገለጻል። "ዘማሪት እከሌ፣ ዲያቆን እከሌ "ገለልተኛ"ው ቤተ ክርስትያን ስላልሄዱ የተባረኩ ናቸው" ይባልልኛል። "ገለልተኛ" የምትሏቸው አብያተ ክርስትያናት እኮ እንደ እናንተ ከፋፋዮች አይደሉም። የተለያዩትን አባቶች ለማስታረቅ ደፋ ቀና የሚሉት ከእነዚሁ "ገለልተኛ" ከምትሏቸው አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ ምእመናን እና ካህናት ናቸው። ወሬ እና አሉባልታ መንግሥተ ሰማያት ቀድሞ አያስገባም። እስኪ ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተውለት። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን!

  ReplyDelete
 2. ልብንና ኩላሊትን የሚመረምረው እግዚአብሔር ብቻ ነው። የአቡነ አብርሃምን እና የአቡነ ፋኑኤልንም እንዲሁ። በእናንተ መንገድ ያልሄደ ሁሉ ሕገ-ወጥ ነው። የተለያየ ድሪቶ ስም ይለጠፍለታል። ሌላው የሚያቀርበው መስዋዕት ወይም የሚፈተተው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ "ፋንድያ" እንደሆነ ያለ ሐፍረት ይገለጻል። "ዘማሪት እከሌ፣ ዲያቆን እከሌ "ገለልተኛ"ው ቤተ ክርስትያን ስላልሄዱ የተባረኩ ናቸው" ይባልልኛል። "ገለልተኛ" የምትሏቸው አብያተ ክርስትያናት እኮ እንደ እናንተ ከፋፋዮች አይደሉም። የተለያዩትን አባቶች ለማስታረቅ ደፋ ቀና የሚሉት ከእነዚሁ "ገለልተኛ" ከምትሏቸው አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ ምእመናን እና ካህናት ናቸው። ወሬ እና አሉባልታ መንግሥተ ሰማያት ቀድሞ አያስገባም። እስኪ ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተውለት። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጠን!

  ReplyDelete
 3. Aye Gashe Ameha Yabeyen Wedemeye.

  ReplyDelete
 4. ብፁዕ አቡነ አብርሀም ምዕመናን "ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ምንም አይነት ድርድር ውስጥ ማስገባት እንደሌለባቸው እና ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አባት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚችለው በሕገ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ተናግረዋል።"

  ይህ አባባል ጥቅል ነው:: እንደ አባትነታቸው በግልጽ መናገር ይገባቸው ነበር:: ይኸውም አቡነ ፋኑኤል የዛሬ አምስት አመት ወደ ዋሺንግተን ተልከው ሲመጡ ምዕመኑ አይድረሱብን ብሎ መልሶ ልኳቸዋል:: የአዋሳና የድሬዳዋ ምዕመናንም እንዲሁ:: ሀገር ቤት ሄደው ጵጵስና እንዴት እንዳገኙ ሁሉም የሚያውቀው ነው:: በዋሺንግተን የሚገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ኢ/ኦ/ተ/ቤ ወደ ሃገረ ስብከቱ እንዲገባ አድርጌአለሁ በማለት በውሸት አስጨብጭበው እንደነበር እናውቃለን:: ይህ ሁሉ ከአንድ አባት የማይጠበቅ የሸፍጥ ሥራ ነበር:: ታዲያ አሁን እንደገና ቅዱስ ሲኖዶስ ሹማቸውልና ተቀበሉ ነው የሚባለው? በእውነተኛው መመዘኛ ከሆነ መቀበል የለባችሁም ብለው ለምን በግልጽ አልተናገሩም:: ዳር ዳር ማለት ጥቅሙ ምንድን ነው? ብዬ ነበር ለማለት ካልሆነ በስተቀር:: ብቻ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መሪዎች ትክክለኛ አመራር ይገኛል ብሎ ከመጠበቅ ምናልባት አሳማ ክንፍ አውጥቶ ይበራል ማለት ሳይቀል አይቀርም::

  ReplyDelete
 5. ወልዳ ለተዋህዶDecember 26, 2011 at 7:17 PM

  ብጹ (ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ምንም አይነት ድርድር ውስጥ ማስገባት እንደሌለባቸው እና ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አባት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚችለው በሕገ ቤተክርስቲያን) እንደሆነ ተናግረዋል ይበል እንላለን ግን አንድ ጥያቄ አለኝ ለመሆኑ የቤተ ክ/ያንን አባት በስርኣተ ቤ/ያን ሊመዝን የሚችል አካል ማነው?ሲኖዶስ ወይስ ምእመናን? ይህ አባባል ግልጽ ስላልሆነልኝ ነው ምእመናን ካልን ሲኖዶሱን ወደ ጎን መተው:ይህ ደግሞ ቀኖናችንና ስርአታችን ወይም አካሄዳችን ሊመረመር ይገባዋል እላለሁ:ሲኖዶሱ ካልን ደግሞ የሲኖዶስ መሪ እ/ር መንፈስ ቅዱስ ነውና የሲኖዶሱን ውሳኔ ማክበር የሚጠበቅብን ይመስለኛል በሌላ መልኩ ደግሞ ማናችንም ስርዓተ ቤ/ያን ሲጣስና ሲናድ ወይም ፈለገ አበውን የማይከተልና የማያስጠብቅ አባት አንፈልግም ግን ይህን የማድረግ መብትና ግዴታ ስልጣንም ያለው ቅ/ሲኖዶስ እንጂ አንድ ግለሰብ ወይመ ፍጡርን የሚያመልክ አካል እንዳልሆነ መገንዘብ ያልብን ይመስለኛል ይህ ካልሆነ አካሄዱ ስለ ቤ/ያን ሳይሆን ስለ ራሱ ጥቅም እንዲሁም የራሱን ጠማማ አካሄድ የሚደግፍ አባት ፍለጋ እንዳይሆን እሰጋለሁ ስለዚህ ስለ አሃቲ ተዋህዶ ጥቅምና ጉዳት ይህንን ቃል ብንተረጉመው እላለሁ

  ReplyDelete