Saturday, December 3, 2011

ስለተቃጠለው ቤተክርስቲያን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ


በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በስልጤ ዞን በስልጤና ሀድያ ሀገረ ስብከት የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተቃጥላ ሙሉ በሙሉ መውደሟን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቆሙ፡፡ እንደምንጮቻችን ገለፃ፤ ቤተክርስቲያኒቷ ህዳር 18/2004 ከሁለት ትምህርት ቤቶች በመጡ ወጣት የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋዝ ተርከፍክፎባት ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች፡፡

ቀደም ሲል ሥፍራው የጥምቀት ማክበሪያ ቦታ ስለነበር ቤተመቅደስ ለመሥራት ፈቃድና ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰጣት ቤተክርስቲያኒቱ መጠየቋንና የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትም እንደተሰጣት ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የግንባታ ሥራ መከናወን እንደ ጀመረ የተናገሩ ምንጮች፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሥፍራውን ለመኪና መገጣጠሚያና ክሬሸር ሥራ ለመሥራት ጠይቀው በነበሩ ባለሀብትና በቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር መካከል አለመግባባት ተከስቶ ሁኔታው ወደ ፍርድ ቤት መቅረቡን አስታውሰው፤ ሥፍራው የቤተክርስቲያኒቱ ህጋዊ ይዞታ መሆኑ ተረጋግጦ ውሳኔ እንደተሰጠና የቤተመቅደሱ ግንባታ ተጠናቆ ምዕመኑ የእምነት ሥርዓቱን እየፈፀመበት እንደቆየ ገልፀዋል፡፡ ህዳር 18 ቀን 2004 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጋዝ ተርከፍክፎባት የተቃጠለችው ቤተክርስቲያኒቱ፤ በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደሟን የጠቆሙ ምንጮች፤ ድርጊቱም የምዕመናንን ቁጣ እንደቀሰቀሰ ተናግረዋል፡፡ በነጋታው በስፍራው የተገኙት የአገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሥራ ኃላፊዎች፤ ህብረተሰቡ ያሳየውን ትዕግስትና እርጋታ በማድነቅ የወረዳው መስተዳድርና ፖሊስ ድርጊቱን የፈፀሙትን ሰዎች በአስቸኳይ ይዞ ለፍርድ እንዲያቀርብ ባሳሰቡት መሰረት የችግሩን መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ምርመራው መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

 በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና ዕምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፤ የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ታዲዮስ ሲሣይ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀን፤ በሥፍራው የደረሰውን ችግር ተከትሎ ግጭቱ እንዲበርድ፣ የግጭት አስወጋጅ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን ጠቁመው፤ የድርጊቱ ፈፃሚዎችም ለህግ እንዲቀርቡ የሚደረግበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ግጭቶችን ለዘለቄታው ለማስወገድ የሚያስችል አሠራር በዳይሬክቶሬቱ ተጠናክሮ እንደሚሰራበትም አቶ ታዲዮስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

2 comments:

  1. እግዚአብሔር ታጋሽነው እንደሰው ፈጥኖ ብድራቱን አይሰጥም፣ ጊዜው ይረዝማል እንጅ የሥራቸው ይከፈላቸዋል፡፡

    ReplyDelete
  2. God told us. But we didn't hear him.This may happen widly because of our sin.So, he started punishing us. Do not worry, we pray for our sin. Otherwise, his punishment may continue.Now adays Muslims are strong.Why? because our sin. God revange by them. Please read the history of Ethiopia and Israel. God bless Ethipia.Amen

    ReplyDelete