Tuesday, December 27, 2011

አክራሪ ሙስሊሞች የወራቤ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥሉ ሲሉ ተያዙ‹‹ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ››

(አንድ አድርገን ታህሳስ 17 2004 ዓ.ም) ፡-የቤተክርስትያናችን ፈተና መልኩን እየቀየረ መጥቷል ፤ ፈተናችንም ከብዷል ፤ የዛሬ አንድ ወር ገደማ አክራሪ ሙስሊሞች የቅድስት አርሴማን ቤተክርስትያን ሲያቃጥሉብን ፤ ሀዘናችን ከልባችን ሳይወጣ ፤ መንግስትም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ሄዶ ፍትህ ሳናገኝ ፤ ሌላ ትንኮሳ ተካሂዶብናል ፤ ፤ የሙስሊም ማህበረሰቦች ያሉበት አንዳንድ ቦታ ላይ ቤተክርስትያን መስራትም ሆነ በተሰሩት ላይ አምልኮተ እግዚአብሔር መፈፀም እየከበደ ነው፡፡

በስልጢ  ዞን  የምትገኘውን  አርሴማ  ቤተ ክርስቲያን  ያቃጠሉ  ሙስሊሞች  ዛሬ ሌሊት 16/04/2004  በስልጢ  ዞን  በዋና  ከተማ  ወራቤ  የሚገኘውን  የወራቤ  ደብረ  ኃይል ቅዱስ  ሩፋኤል ቤተክርስቲያን  ሊያቃጥሉ ሲሉ በቤተክርስቲያኑ  ጥበቃ  በተከፈተ  ተኩስ ለጊዜው ሊያመልጡ ችለዋል፡፡  በጊዜውም በበረንዳው  ላይ እሳት  ሲለኩስ  የነበረ  አንድ  ሰው  በጥበቃ ፤ በካህናቱና በአስተዳዳሪው የተያዘ  ሲሆን ፤ጥያቄ ሲጠየቅ ‹‹ ሁለት ሰዎች ወደ መስጊድ ስሄድ ክብሪትና  ማቃጣጠያ  ሰጡኝ ›› ብሏል፡፡ ተኩሱን  ሰምተው  የመጡ  የፖሊስ  አባላት   ይዘውት ወደ ጣቢያ ሄደዋል፡፡  ይህ ሰው ከዚህ በፊት  በከተማው  እራሱን እንደ እብድ አድርጎ የሚኖር እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ 

አዎን የባለፈውን የቤተክርስትያን ቃጠሎ ቪዲዮ ፤ ኦዲዮ ፤  የሰው ፤ የፎቶ ማስረጃ ፤ ከፌደራል ጉዳዮች መንግስት መድቧቸው ለመጡ ሰዎች ተሰጥቷል ፤ ጉዳዩን ግን ፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔ ሊያስወስኑልን ፤ ፍትህን ሊሰጡን አልቻሉም ፤ መንግስት ፍትህ አለመሰጠቱ  ሰዎቹን የልብ ልብ እንዲሰማቸው ያደርጋል ፤  ላደረሱት አደጋ ተመጣጣኝ የሆነ ፍትህ ቢሰጣቸው ኖሮ ዛሬ ደግመው ይህን ባላሰቡት ነበር ፤ አስበውም ባልተገበሩት ነበር ፤ እነርሱ ምን ያድርጉ ? እንደ ፓርላማ አባል ያለመከሰስ መብትን ከመንግስት አግኝተዋል መሰል ፤ በህግ ፊት ሁሉም እኩል ከሆነ አሁን ፍትህ ለማሰጠት ጊዜው የረፈደ አይመስለንም፡፡ ያለበለዚያ የት ሄደን አቤት እንበል ? አንድ የማይገባኝ ነገር የቤተክህነቱ ዝምታ ነው ፤ መንግስት ዝም ቢል እንዴት ቤተክህነቱ ጉዳዩን ዝም ይላል ፤ ባለቤት የሌለው ቤት አስመሰሉት እኮ ፤ ይሄኔ ሹም ሽር ቢሆን ኖሮ እስከ ደም ጠብታ ድረስ ሲሟገቱ ይውሉ ነበር፡፡ ምእመኑም እየተደረገ ያለውን ነገር ማወቅ አለበት የሚል እምነት አለን ፤ ለምን ቢባል ነገ የሚመጣውን በማሰብ ራሱንና ቤተክርስትያንን የመጠበቅ ሀላፊነት ስላለበት ጭምር ነው፡፡
እኛም ይህን አይነት በቤተክርስትያናችን ላይ የሚደረግ እኩይ ምግባርን በጊዜው ህዝብ ዘንድ በማድረስ ፤ ምዕመኑ ቤተክርስትያንን እንዲጠብቅ የተሻለ መነቃቃት እንፈጥራለን ፤ በተጨማሪ መንግስትም ጉዳዩን ከቁብ በመቁጠር ሌሎች ይህ አይነት አደጋ ይከሰታል ብሎ የሚሰጋበት አብያተክርስትያናት ላይ ጥበቃውን ያጠናክራል ብለን እናስባለን፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ሁላችን ስለ ቤተክርስትያናችን አጥብቀን ብንፀልይ ፤ እግዚአብሔር እንዲጠብቃት ብናሳስብ የተሻለ ነው ብለን እናምናለን፡፡


ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት ያደረግነው ጥረት ሊሳካ አልቻለም ፤ ፖሊስ ይችንም መረጃ ለማንም እንዳይተላለፍ ጥብቅ ማጠንቀቂያ መስጠቱን ለማወቅ  ችለናል ፤ ፖሊስ እንዲህ ቢልም መረጃው ከእኛ ሊያመልጥ አልቻለም ፤ ከቀናት በኋላ  አጣርተን የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል፡፡


ከእኛ የሚያመልጥ እርሶ ጋር የማይደርስ የቤተክርስትያናችን ጉዳይ አይኖርም፡፡ 

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅልን››

18 comments:

 1. ወይ ጉድ! ግን ምን ነካቸው? ከእግዚአብሔር ጋር ትግል መግጠም አያዋጣም ተው በሏቸው:: ዝም ማለትም ፍርሃት አይደለም ሕይወት(ክርስቲያናዊ ምግባር) እንጂ!

  ReplyDelete
 2. ወይ ጉድ! ግን ምን ነካቸው? ከእግዚአብሔር ጋር ትግል መግጠም አያዋጣም ተው በሏቸው:: ዝም ማለትም ፍርሃት አይደለም ሕይወት(ክርስቲያናዊ ምግባር) እንጂ!

  ReplyDelete
 3. enough is enough!other wise they will get what they are eat!

  ReplyDelete
 4. “ባለቤቱ የተማመነ በግ ላቱን ውጭ ያሳድራል” ነው ነገሩ፡፡
  መንግስት ቤተክርስቲያን የሚያቃጥሉትን፣ክርስቲያኖች የሚያርዱትን፣ታሪክን የሚለውጡት ፤እርምጃ ከመውሰድ ስለተቆጠበ! ለምን አያቃጥሉ!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. እነሱ ምን ያርጉ:: መንግሥት በዘር የጠመደው ቦምብ አልፈነዳ ሲለው የኃይማኖትን መጠቀም መፈለጉ ነው እንጅ:: አልገባውም እንጅ እሳቱ መጀመሪያ እሱን እንድበላው አላወቀም ያንጊዜ እኛም አናውቀውም:: ለእስማኤላውያኑ ግን እረፉ በሏቸው አይጠቅማችሁም የአረብ መሳሪያ መሆኑ አይጠቅማችሁም:: ራሳችሁን ሁኑ::

  ReplyDelete
 6. may God keep our church in his care

  ReplyDelete
 7. ቤተ ክህነት ማለት አራት ኪሎ የተከማቸው የወንበዴዎች ግሩፕ ሳይሆን የእኛ የምእመናን ህብረት ብቻ ነው!!!

  ReplyDelete
 8. እገዚአብሄር ቤተክርስቲያንን የተብቅ

  ReplyDelete
 9. PLease watch this:http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=qT6sdABiCzk

  ReplyDelete
 10. Hi! Let us work for unity among Christians. We can overcome such problem by making unity among us.

  ReplyDelete
 11. እግዚአብሔር ይጠብቓት!!!

  ReplyDelete
 12. ይስማላ ጊዎርጊስJanuary 4, 2012 at 4:35 PM

  እግዚያብሄር ልቦና ይስጣቸው

  ReplyDelete
 13. ይስማላ ጊዎርጊስJanuary 4, 2012 at 4:37 PM

  እግዚያብሄር ልቦና ይስጣቸው ሌላ ምን ይባላል

  ReplyDelete
 14. wendimoch ye mengist fird gizawina midirawi new gin midirawina semayawi king of king erasu yemiferdew yibelital (gib kifu neger bisera min ehonalew bilo le kebero " kebero degmo ante ema minim atihonim le lig ligh new enji alechiw" ende min agebaj sile lig lige bilo keberowan libelat araratat tilik enchew hodu wist geba anchi kebero "minim atihonim alalishignm ende silat" ye kebero melis "antem ye ayatih kifat yihonal alechiw yibala silezi just pray u will see soon just do like rahel crying and we will see "litsedik biye bazilat tentelitila kerech new linitsedik bilen binasitegachew yaw hone melisu GOD blesss Ethiopian orthodox

  ReplyDelete
 15. ወይ መድኃኒዓለም ታረቀን እባክህ። እስራኤላውያን እንደታደግህ እኛንም ታደገን ስለ እናትህ ብለህ።

  እኔ ግን ያልገባኝ እስከመቼ ነው ዝም የምንለው።
  ዝምታ እኮ ፍርሀት አይደለም። ምዕመናን ለምን የነሱንስ አናጋይም?
  ለምነውን ገብተው ባስተናገድናቸው?
  ቤተክህነት ስሙ ነው ያለው እሱን እርሱት ::
  እንደ እኔ አመለካከት አባ ጳውሎስ እንደሆነ ለጥፋት የታዘዙ ናቸው።
  ምዕመኑ እስከመቼ ነው ዝም የምንለው መሞትም ካለብን እንሙት እኛ እኮ ሰይፍ አንፈራም
  ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕቷ ኢየሉጣን ቅዱስ ቂርቆስ ዝምታ አላስተማሩንም።
  ወገን እንንቃ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምዕመናኑ ስለኃይማኖቱ በጣም ደንታ የሌለው እየሆነ ነው፡፡ ሙስሊሞቹ በየመድረሳ ቤት አንዴት አድርገው ክርስትናን ማጥፋት አንዳለባቸው ሲያልሙና ሲያውጠነጥኑ የኖራሉ እኛ ግን በጀርባችን ተንደላቀን እንደጠገበ አህያ እንተኛለን…..ኦርቶዶክሶች ከልመና መጥተን በሙስሊሞት የተወሰደብን የኢኮኖሚ የበላይነት መልሰን መንጠቅ ያገባናል፡፡ እኛው በሰጠናቸው ሀብት መልሰው ሊያጠፉን ያልማሉና….

   Delete
 16. BEGAMO GOFA ZONE BE ZAYDA WEREDA NOV 29,2004 E.c. ANID BETEKIRSTIYAN MULUBEMULU BE PROTESTANT EMNET TKETAYOCH TKATELE. WEDE BOTAW YEHAGERESIBIKETU L/PAPAS ENA YEMAHBERE KIDUSAN YEARBAMINCH MAKEL TEGUZEW ATSINATEW TEMELSEWAL.
  ENAM MEREGAWN WESDACHU POST BITADERGUT

  ReplyDelete