Monday, December 5, 2011

የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በዋሻ ውስጥ ተገኝ


በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሰማነው እግዚአብሔር አሁንም  አብሮን እንዳለ በምህረቱም እየጎበኝን እያለ መሆኑን ነው፤ በጠላት ወረራ ጊዜ የተቀበረውን የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስትያ በማውጣት አሳይቶናል ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን:: እግዚአብሔር አልተወንም ፤ አይተወንም የሚያስብል ተዓምር ነው የተደረገው፡፡

ይህ ጥንታዊ ዋሻ በውስጡ አካቶ ይዟቸው የሚገኝው አስደናቂው ነገር ርዝመቱ በውል ያልታወቀ የግብር ቤትና ፤ የክርስትና ቤት በውስጡ የሚገኝ ሲሆን ፤ ከኢጣልያን ወረራ እና ከግራኝ መሀመድ በመሸሽ የተቀበረ ቅርስና ፅላት ተገኝቶበታል፡፡ ይህንን ጥንታዊ ዋሻ ያገኙት አባት በራዕይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅላት በውስጡ እንዳለ ተነግሯቸው ቁፋሮ ለመጀመር በሱባኤ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል፡፡ ሌላው አስደናቂው ነገር ከዋሻው መካከል ላይ የብርሀን መግቢያ የተፈጥሮ ክፍተት ያለው መሆኑ ድንቅ ያሰኛል፡፡ የዋሻው ጠረጋ ሲጀመር የአባቶች አፅም ፤ የብራና መፃህፍት ፤ የፅንአ ቁርጥራጭ ፤ የሰም ስብርባሪ በውስጡ እንደተገኝ ለማወቅ ችለናል፡፡ በተጨማሪም 
በዋሻው የውስጥ ክፍል ቅኔ ማህሌት ፤ ቅድስት ፤ መቅደስና ቤተልሔም ይገኙበታል ::
 ለመላው ህዝበ ክርስትያን በሙሉ አስደናቂውን እና ተዓምረኛውን የዋሻ ገብርኤል ቤተክርስትያን በአቃቂ ቃሊቲ ከቶታል ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሎ መብራት ሀይል ማዶ ላይ የተገኘውን የጥንት ዋሻ ቤተክርስትያን ብዙ ገቢረ ተዓምራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህውም በፀበሉ ፤ በእምነቱ ፤ በንፍሮ ውሀው ብዙ ህሙማና አጋንንት እየፈወሰ ስለሚገኝ በቦታ ተገኝተው ከበረከቱ እና ከገቢረ ተዓምሩ ተካፋይ በመሆን የቦታውን ታሪክም በአካል እንዲያዩ በቅዱስ ገብርኤል ስም ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ 
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከሳሎ ጊዮርጊስ ወረድ ብሎ መብራት ሐይል ማዶ ገላን ጉዳ መተሊ ቅዱስ አሮንና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን
 ለበለጠ መረጃ 0913-464936 ደውለው የተሻለ መረጃ ማግኝት ይችላሉ

 ‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››

9 comments:

  1. ሃሌ ሉያ_ ሁሉን የፈጠረ የሰማይ አባታችን እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን!!!ቅድስት ቤተ ክርስትያን ሆይ ደስ ይበልሽ!!ዛሬም በበደላችን ምክንያት ያልተወን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ይመስገን!!!!!!!!

    ReplyDelete
  2. በእውነቱ ይህንን ታሪካዊ ቅርስ በማግኘታችን እድለኞች ነን።

    ReplyDelete
  3. ይህንን ጠፍቶ የተገኘ ቅርስ ሙዚየም ብናስገባው ብዙ ገቢ ልናገኝበት እንችላለን።

    ReplyDelete
  4. ኤግዚአብሔር አሁንም ስራውን አየሰራ ነው
    የበለጠ አንድያሳየን አብዝተን አንፀልይ!!

    ReplyDelete
  5. አምላካችን ሆይ እንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን

    ReplyDelete
  6. Desi yemeli zena newi bewineti Egzabiheri yimesigeni. Abatochachini bemanignawimi gizie ke Egzabiheri yiweginalu beyadinimi beyasigedilimi. Ignasi lelawi kerito yegibire sodomawiyanini sibiseba lemezegebi inkuani ferani mikiniyatumi mini alibati yasasirali. Gini wineti igna ye abatochachini lijochi neni? " ingedehi ya abirehami lijochi neni maleti atijemiru . Egzabiheri kewedede....."

    ReplyDelete
  7. አቤት የሠራዊት ጌታ ቸሩ እግዚአብሔር ምን ይሣንሃል እኛ በደለኞችን እንደበደላችን ሳታይ እንደ ይቅርታህ ለአበዛህልን ፀጋ ክብር ምስጋና ይገባሃል፡፡ አቤቱ በአንተ አምነን በድልንግል ተማፅነን ለምንኖር ለኛ ለፍጥረቶችህ ይህንን ያሰማኸን ክብር ምስጋና ይገባሃል አሜን
    በፀበሉ እንድንፈወስ አድርግልን አሁንም መድሃኒታችን መድሃኒት ሁነንና እንዳንበት በፀበሉ

    ወለተ ገብርኤል

    ReplyDelete
  8. በእውነቱ የልኡለ ባህሪ እግዚኣብሔር ኣምላካችን ስም ለዘልኣለም የተመሰገነ ይሁን ግን እሩቅ ኣገር ለምንኖር ኣንድኣንድ ወገኖች ይህ ቅዱስ ቦታ መጥተን እስክናየው ድረስ ቪዲዮ የተቀረጸ ካለ እንድናየው ብታስገቡልን በጣም ደስ ይለን ነበር እግዚኣብሔር ይባርካቹ ረጂም የኣገልግሎት እድሜ ይስጣቹ

    ReplyDelete