Monday, December 12, 2011

አሁንም ተሀድሶያውያኑ አልተኙልንም

 • አባ” ናትናኤል ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ከቤተክህነት ተሾሙ፡፡
(አንድ አድርገን ታህሳስ 2 2004)- ከጥቅምት ሲኖዶስ መጠናቀቅ በኋላ በተሀድሶነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አቀንቃኞች በደረሰባቸው የምዕመናኑ ተቃውሞ ድምፃቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ አሁን በደረሰን ወሬ ግን በአዋሳ ምዕመናን እንደተዘጋጀና በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ለብፁዐን አበው በነጻና በስፍራው ለተገኘው ምዕመን በአነስተኛ ዋጋ ያተሰራጨው ቁጥር አንድ ቪሲዲ ካሴት ላይ ሦስቱ ወፎቹ ተበለው ከተጠቀሱትመነኮሳትአንዱ የሆነውና በወቅቱ የአዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንአስተዳዳሪየነበረውአባናትናኤል በዕለተ ሰንበት እሁድ 01/04/2004 . ቀን በአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አለቃ ሆኖ ከቤተክህነት ተሹሞ ፓትርያርኩ ሹመቱን አፅድቀውለት ቢሄድም የሰንበት /ቤቱ ወጣቶች የሰበካው ጉባኤው እና የአካባቢው ምዕመን በነበራቸው መረጃ መሠረት
ግለሰቡ የሃይማኖት ሕፀፅ ያለበት ሐዋሳ ላይ ከእነ በጋሻው ጋር ግሩፕ በመፍጠር ‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም ብሎ በመስበክ ፤ ሰውን ለአመፅ ያነሳሳ እና በከፍተኛ ሁኔታ የገንዘብ ምዝበራ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ እንደዚህ ዓይነት ሰው መመደቡ ለቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ አሁኑኑ እንዲመለሱ እንዲደረግ በማለት ለሕዝቡ አስፈላጊው መግለጫ ከተደረገ በኋላ ሕዝቡም የ‹‹አንፈልጋቸውም›› ድጋፉን በእልልታ በመግለጹ ቅዳሴው እንደተፈፀመ በመጡበት እግራቸው በሰላም ሌላ ብጥብጥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከመከሰቱ በፊት ግለሰቡን ሸኝተዋችዋል

ህዝቡ ለቤተክርስትያን መቆርቆሩ ጥሩ ሆኖ ሳለ ፤  አባ” ናትናኤል ላይ በጊዜያዊ ስሜታዊነት ሌላ ችግር እንዳይፈጥሩበት በቤተክርስትያኒቱም ውስጥ ሌላ አላስፈላጊ ነገር እንዳይከሰት ተብሎ በማሰብ ጥቂት ሰዎች ምዕመኑን እንዲበተን ካደረጉ በኋላ ከአካባቢው በሰላም ለመሸኝት ኮንትራት ታክሲ ተኮናትረውላቸው አብረዋቸው ከመጡ ሁለት መነኮሳት ጋር ከቤተክርስትያን አስወጥተው ሊሸኟቸው ችለዋል ፤ ሶስት ሆነው ቤተክርስቲያኒቱን ለማስተዳደር ምንፍቅናቸውን ለመዝራት ሀዋሳ ላይ የሰሩትን ለመድገም ህዝበ ክርስትያን ለማወክ በእግራቸው ቢመጡም ምዕመኑ ግን በኮንትራ ታክሲ ሸኝተዋቸዋል፡፡

አባ ናትናኤል(የሀዋሳ ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩ ) እና አባ ጊዮርጊስ (የሞኖፖል ተክለ ኃይማኖት እና የቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ) በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት አራማጆች(ተስፋ ኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው )ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ሁለቱ ናቸው፡፡በጊዜው ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ለአውደምህረት የማይመጥኑ ትምህርቱ የሌላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ካደረኩ ሰዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ አሁንም በሰሩት ስራ ንስሀ እንደመግባት ከእኩይ ስራቸው ሊማሩ ባለመቻላቸው አሁንም ከአቡነ ጳውሎስ ተልከው ለአስተዳዳሪነት በአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን መጥተዋል፡፡

አባ ናትናኤል ሲኖዶሱ ባቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ በጊዜው እንደ ስራቸው ተመዝነው በፊት ከተሸሙበት ቦታ ተነስተዋል:: አባ ናትናኤል ‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም›› ብለው በአውደ ምህረት ላይ የሰበኩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለሌላ ብጥብጥ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ እኛም መዝገባቸውን ከፍተን ለምዕመን ከማድረስ ወደ ኋላ አንልም  እነርሱ ቤተክርስትያኒቷን ለማፍረስ እንዳልተኙ ሁላ ፤ እኛም ሁላችንም ነቅተን መጠበቅ ይገባናል፡፡


ከአንድ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ስካን ተደርጎ የተወሰደ

የአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን  አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መሸሻ በቅርቡ የሰንበት /ቤቶች /መምሪያ ሓላፊ ተደርገው ከተዘዋወሩ ጊዜ ጀምሮ ደብሩ ያለ አስተዳዳሪ 2 ወር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህችን ቀዳዳ በመጠቀም አይናቸውን በጨው አጥበው አባ ናትናኤል ከአቡነ ጳውሎስ ተሹመው መምጣታቸው ለእኛም ገርሞናል፡፡እንደ አየር ጤና ምዕመናን ሁላችንም በየአካባቢያችን ያለውን ደብር የመጠበቅ ሀላፊነት እንዳለብን ልንዘነጋ አይገባም ፤ እኛ ሀላፊነታችንን ከተወጣን ቤታችን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሰላም ይሆናል፡፡

‹‹ከኛ የሚያመልጥ እርስዎ ጋር የማይደርስ መረጃ የለም››

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅልን››

 

24 comments:

 1. egezyabehyer betwunena lejochun yetebek!!!!!
  AMEN!!!!!

  ReplyDelete
 2. Somebody said MK will not stop fighting its enemies unless they are dead...even will not give them a chance for repentance.

  ReplyDelete
 3. Egziho malet becha manen enemen

  ReplyDelete
 4. '...manen enemen...' Yemishalewima Abatochin ena tikikilegnawin yebetkrstian lisanat bicha mesmat...betbarari wore alemerebesh...

  ReplyDelete
 5. እኔ በበኩሌ ከሁለቱም ቡድን አይደለሁም፡፡ ነገር ግን እያየሁት ያለው ነገር በጣም አሳዝኖኛል፡፡ ለምን ቢባል የክርስቲያን ሥራ እየተሠራ ስላልሆነ፡፡ ቤክርስቲያን መበጥበጥ፣ ምዕመኑን መለያየትና መከፋፈል፣ ወንጌል ከማስተማር ይልቅ አድማ ማስፋፋት ለምን እንዳስፈለገ አልገባኝም፡፡ በእውነት ለቤተክርስቲያን ከመቆርቆር ነው ወይስ ለግል ጥዝምና ዝና ሲባል፡፡ ሕዝቡ ማስተዋል አለበት፡፡ ቅስቀሳ ስለተደረገ ብቻ አጨብጭቦና እልል ብሎ አንድ ሰው ላይ መነሳት ያለበት በትክክል ቅስቀሳው እውነት መሆኑን በትክክለኛ መረጃ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ አባቶችን መሳደብ፣ ማዋረድና በየደረሱበት እያሳደዱ ማባረር ለማንም የሚጠቅም አይመስለኝም፡፡ ይህን ነገር ግርግር ከመፍጠር ባሻገር እንደ ክርስቲያን ቆም ብላችሁ አስቡበት፡፡ ዝም ብሎ ተሃድሶ የሚባል ሽፋን ስለተሰጠ የግለሰቦች መጠቀሚያ ከመሆን መፀለይና ቆም ማሳብ ያስፈልጋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. you are right. our fathers solved everything through prayers but this generation is not doing the right thing. What is the benefit of 'kiskesa'.We should ask God daily to solve our problems not blame our fathers. Don't forget we will be judged with what we are judging. Be careful and be watchful.

   Delete
 6. Have you heard about the three priest that work in "Hawassa kideste selasye dabre" "Ya getachene ya medanitachene ya eyasusu kebure sega ena dame (dafu or through to garbage)tabelo selatadgadute kahenate yetetara maraja kalchu betakafelune yeheme andu ya thadeso andu magalacha nawe ena". Egzio meharena kerestose!

  ReplyDelete
 7. Hi ande adergane woche. Ba egziabehere selameta endamene karamachu! I have found the second edition of "Kesatye berehane" the book published by "Ethiopia Church reunion" being distributed in the "pentye or protestant" church. It say that Ethiopia orthox church is wrong on many part showing false history. If you have found the book you should post all the thing that are wrong on this material because it's one method of movement of "Tehadeso" bezi matsehafe yetenesa bezu sawe lisasate yechelae. As soon as you can post all the info you got on this book or I can eamil you.
  "Egziabehere Byete kerestyanene yetadagate"
  Wasebehate la egziabehre la waladitu dengele"

  ReplyDelete
 8. anonnymous @ December 12, 2011 6:13 AM ,
  do you understand what is being said at all? This guy , has minfikina.

  እኚህማ ካህን ናቸው ምንም አትናገሯቸው እያልን በተደጋጋሚ ተጫወቱብን ምናልባት አንተ ይሄ ስላልደረሰብህ ይሆናል እስከአሁን ካህን ስለሆኑ ምንም አትናገሯቸው የሚባል ነገር ያልለቀቀህ ነገር ግን እኛ ግን በቃን አንድ ሰው መናፍቅ ከሆነ መናፍቅ ነው፡፡ ምንም መሸፋፈን አያስፈልገውም፡፡ ካህን ሆነ ምዕመን ሆነ ዘማሪ ሆነ ለመናፍቅ ቅንጣት ታክል ትግስቱ የለንም፡፡ጉዳቱ የደረሰብን እኛ እናውቀዋለን፡፡እንደዚህ አይነቶቹን በጊዜ መሸኘት ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ የሚሽር ወይም ለጥርጥር በር የሚከፍት በአደባባይም ይሁን በምስጢር ለማስተላለፍ የሚጥ'ርን ሰው ገና ለገና የቤተክርስቲያን ሰላም ይደፈርሳል፡ መለያየት ይመጣል በክብር ልንጠብቀው አይገባም። ማጣራቱ እንዳለ ሆኖ፡ በፀሎቱም እየተጋን፡ ትምህርተ ወንጌሉን አጥብቀን እየተከታተልን መለየት ያለበትን ካልለየን አደጋው የከፋ ይሆናል።

  ReplyDelete
 10. beretu ewnetuen neger eyfwlfelaheu asawekun

  ReplyDelete
 11. አንድ አድርገን እያሉ የመከፋፈልን ወሬ ማውራት ብዙም አያስኬድም፡፡፡ እርስ በርሷ የምትከፋፈል መንግስት.... ነው የሚለው ቃሉ፡፡ ጌታ ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ አንዱን ሊፈልግ እንዲሄድ ... ከህንጻ ቤተክርስቲያን ይልቅ ግድ የሚለው ሰዚያ ስለሚጠፋው ስለ አንዱ ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም "አንዱ ስለሁሉ ሞተ" ነው የሚለው ቃሉ... ዛሬ እንዲህ የምናብጠለጥለው ሰው እኮ ጌታ እየሱስ ክርስቶ በመስቀል ላይ የደም ዋጋ የከፈለለት ነው፡፡ ያ ያጠፋውን ሰው ሰብስቦ መምከር፣ መገሰጽ እና መመለስ ነው እንጂ እሰጥ እገባ ማለቱ ለማንም አይጠቅምም....እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ ለእግዚአብሔር ቤት ነው ለስሜታችን እየሰራን ያለነው?... አንዱ ባንዱ ሲስቅ... እንዳይሆን ነገሩ

  ReplyDelete
 12. አንድ አድርገን እያሉ የመከፋፈልን ወሬ ማውራት ብዙም አያስኬድም፡፡፡ እርስ በርሷ የምትከፋፈል መንግስት.... ነው የሚለው ቃሉ፡፡ ጌታ ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ አንዱን ሊፈልግ እንዲሄድ ... ከህንጻ ቤተክርስቲያን ይልቅ ግድ የሚለው ሰዚያ ስለሚጠፋው ስለ አንዱ ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም "አንዱ ስለሁሉ ሞተ" ነው የሚለው ቃሉ... ዛሬ እንዲህ የምናብጠለጥለው ሰው እኮ ጌታ እየሱስ ክርስቶ በመስቀል ላይ የደም ዋጋ የከፈለለት ነው፡፡ ያ ያጠፋውን ሰው ሰብስቦ መምከር፣ መገሰጽ እና መመለስ ነው እንጂ እሰጥ እገባ ማለቱ ለማንም አይጠቅምም....እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ ለእግዚአብሔር ቤት ነው ለስሜታችን እየሰራን ያለነው?... አንዱ ባንዱ ሲስቅ... እንዳይሆን ነገሩ:::masreja enfelgalen asteyayetu temechitognal yetgnaw metset new silenesu yaweraw?

  ReplyDelete
 13. የማይመስላችሁን አባራችሁ ቤተክርስቲያኗን በቁጥጥራችሁ ሥር ለማድረግና የፈለጋችሁን ለመሾምና የጠላችሁትን ለመሻር ብሎም ለማባረር የሚትፎክሩት ለመሆኑ ቤተክርስቲያን የግለሰብ ቤት አይደለችም!! የራሷ ህግና ሥርዓት ያላት ናት ለእናንተ እንደፈለጋችሁ የመሆን ሥልጣን ማን ሰጣችሁ፣ ሌላውን እንጀራ ልጅ ያደረገው ማነው፣ ቤተክርስቲያን ለሁሉም የራሷ አማኞች እኩል ናት፡፡ እናንተ መረዳት ያቃታችሁ ይህን ይመስለኛል፡፡ እስቲ ወደ ልባችሁ ተመለሱ፡፡ ከቲፎዞና ከቡድንተኝነት ስሜት ተላቃችሁ እውነተኛ ክርስቲያን መሥራት ያለበትን ሥራ ለመሥራት እንድትችሉ እግዚአብሔር እንዲራችሁ በርትታችሁ ፀልዩ!!

  ReplyDelete
 14. የማይመስላችሁን አባራችሁ ቤተክርስቲያኗን በቁጥጥራችሁ ሥር ለማድረግና የፈለጋችሁን ለመሾምና የጠላችሁትን ለመሻር ብሎም ለማባረር የሚትፎክሩት ለመሆኑ ቤተክርስቲያን የግለሰብ ቤት አይደለችም!! የራሷ ህግና ሥርዓት ያላት ናት ለእናንተ እንደፈለጋችሁ የመሆን ሥልጣን ማን ሰጣችሁ፣ ሌላውን እንጀራ ልጅ ያደረገው ማነው፣ ቤተክርስቲያን ለሁሉም የራሷ አማኞች እኩል ናት፡፡ እናንተ መረዳት ያቃታችሁ ይህን ይመስለኛል፡፡ እስቲ ወደ ልባችሁ ተመለሱ፡፡ ከቲፎዞና ከቡድንተኝነት ስሜት ተላቃችሁ እውነተኛ ክርስቲያን መሥራት ያለበትን ሥራ ለመሥራት እንድትችሉ እግዚአብሔር እንዲራችሁ በርትታችሁ ፀልዩ!!

  ReplyDelete
 15. ሃዋሳ ላይ ለተነሳው ብጥብጥ ተጠያቂ ከሆኑ እና ጥፋተኝነታቸው ከታወቀ ወደ ሕግ መሄድ ሲገባቸው ወደ ሹመት ይገርማል:: ጥፋቱ ግን የሳቸው ይመስላችኋል? ለኔ አይደለም:: ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ ሲኖዶሳችን ሰብሳቢ አድርጎ የሾማቸው አባት ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለግለሰብ ለእውነት ሳይሆን ለሃሰት ለእድገት ሳይሆን ለውድቀት ለሰላም ሳይሆን ለብጥብጥ ለአንድነት ሳይሆን ለመለያየት ለተዋሕዶ ሳይሆን ለተሃድሶ የሚሰሩ በመሆኑ ጥፋቱ የሳቸው እንጅ የሌላ የማንም አይደለም:: አሁን እኮ የለየለት ነገር ከፊታችን ቁጭ ብሏል:: መታገል ያለብንም ዋናውን ነው:: የሳቸው እስትንፋስ የሆኑት አባ ገሪማ ( ይገርማል) ደግሞ ለጀርመናዊቷ ያን የመሰለ የመሳለቂያ ፊልም እንድሰራ ፈቃድ ሰጥተዋል:: ከዚህ በላይ ምን እንደምንጠብቅ አይገባኝም እኒህን እንደት አባት አባት እንደምንል አይገባኝም አባት እኮ ለልጁ ብዙ ነገር ነው:: መቼ ነው አባት በልጁ ቤት ውስጥ አውሬ አስገብቶ ልጁን አደጋ ላይ ሲጥል ያያችሁት ካደረገ አባትነቱ የት ላይ ነው::ነው ወይንስ እበትም ትል ይወልዳል አይነት ነው? ለኔ ግን አባት ማለት ስለልጆቹ ረሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው " ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች" አይደል ተረቱስ::

  ReplyDelete
 16. sinodosin lemetemzez eyetederege yale rucha new aba yawlos eyaderegut yalew yemot shiret torinet mehonu gilts new. ahunem mk yemtilu sewoch yebete kirstiyanina yemahiber guday leytachihu iweku mejemeriya lib yistachihu mk baynor betekirstiyanin lemeshet ej yesetachihu yemenafik mirko nachihu. be mk sim betekirstiyanin lematfat chigir yalebachewn eyemeretu yemishomu sewye mastewal aktuchihu new weyis yeleyelachihu menafik honachihu miemenun behasab lemeleyet new hasabachihu ? egziabher yefekedew new yemihonew wugiyawm keegziabher gar new ke MK GAR aydelem please if ur orthodox. from hawassa be strong brothers

  ReplyDelete
 17. Kifuwch Yemisebesebubat musengoch yekebebuwat atifitewu yebedelutn hizib yikir saylu yemishomubatin betekrstian asitedader kelay gemiro matsidat yasfelgal. Enih sew hizbin yekefafelu ena bebetekrstian audemihret betenagerut bizuwoch tedebdbewal, tesedewal lemenafikanu yeliblib endisemachew adirgewal silezih Yemimerutin hizb eskiyawuku dires benisiha Yikoyu

  ReplyDelete
 18. ምን ሆናችሁ ነው እስካሁን የተጎዳነው ይብቃል ማለት ማን ምን ጎዳችሁ እናንተ ያላችሁት ካልሆነ ተጎዳቸህ ማልት ነው ባዳራሸ የዘልሉት ሌሎች አሁን በሽፋን የምታቀርቡት ሌሎችን እናንተ ላይ ያለው ጋኔል በተክረርስቲያንን ሊከፋፍል ስለሆነ የተነሳው በሐሜት ፣ሐሰት፣ በመናፍቅነት የተጠናወታችሁ ስለ ሆነ ጌታን የሰቀሉት እኮ ብብሉ በትቱ ማግስት ነው እኮ የካዱት መንፍቅ ከሆነ ብቃ የጣል ከግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው የጤና መንፈስ አይመስለኝም ሰዎች መርምሩ ተጠንቀቁ ጸልዩ መናፍስት ገብተዋል በቤተክርስቲያን እግዚዎ ማሀኀረነ ክርስቶስ ይቅርበለን ይቅርበለን ይቅርበለን ጌታሆይ

  ReplyDelete
 19. ምን ሆናችሁ ነው እስካሁን የተጎዳነው ይብቃል ማለት ማን ምን ጎዳችሁ እናንተ ያላችሁት ካልሆነ ተጎዳቸህ ማልት ነው ባዳራሸ የዘልሉት ሌሎች አሁን በሽፋን የምታቀርቡት ሌሎችን እናንተ ላይ ያለው ጋኔል በተክረርስቲያንን ሊከፋፍል ስለሆነ የተነሳው በሐሜት ፣ሐሰት፣ በመናፍቅነት የተጠናወታችሁ ስለ ሆነ ጌታን የሰቀሉት እኮ ብብሉ በትቱ ማግስት ነው እኮ የካዱት መንፍቅ ከሆነ ብቃ የጣል ከግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው የጤና መንፈስ አይመስለኝም ሰዎች መርምሩ ተጠንቀቁ ጸልዩ መናፍስት ገብተዋል በቤተክርስቲያን እግዚዎ ማሀኀረነ ክርስቶስ ይቅርበለን ይቅርበለን ይቅርበለን ጌታሆይ

  ReplyDelete
 20. እኔ በጣም የሚደንቀኝ ነገር አንድ መፅሐፍ ቅዱስ እያነበብን ለአንድ የእግዚአብሔር መንግስት እየሰራን ይህን ያህል የሃሳብ ልዩነት ፈጥረን አንዳችን ሌላችንን ስንተች ዘመናችን መፍጀታችን ነው፡፡ አባቶች እንደሚያስተምሩንና እኛም እንዳነበብነው ክርስቶስ ሰምራ ጨርሶ የማይሞከር እርቅ አስባ ነበር፡፡ በሰይጣንና በእግዚአብሄር መካከል ….. እኛ ግን ለአንድ መንግስት እየሰራን ልዩነታችንን ብቻ እየነቀስን ስንከራከር ስንት ዘመን አለፈ? ያልጠፋነው እኮ ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ ወገኖቼ በክርክራችን እግዚአብሔር አይከብርም ፡፡ ያላመኑ ወገኖች ከእኛ ምን ይማራሉ ? እግዚአብሔር. ሆይ አንድ አድርገን፡፡ ማስተዋልን ስጠን ፡፡
  ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል፡፡
  ወስብት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 21. እኔ በጣም የሚደንቀኝ ነገር አንድ መፅሐፍ ቅዱስ እያነበብን ለአንድ የእግዚአብሔር መንግስት እየሰራን ይህን ያህል የሃሳብ ልዩነት ፈጥረን አንዳችን ሌላችንን ስንተች ዘመናችን መፍጀታችን ነው፡፡ አባቶች እንደሚያስተምሩንና እኛም እንዳነበብነው ክርስቶስ ሰምራ ጨርሶ የማይሞከር እርቅ አስባ ነበር፡፡ በሰይጣንና በእግዚአብሄር መካከል ….. እኛ ግን ለአንድ መንግስት እየሰራን ልዩነታችንን ብቻ እየነቀስን ስንከራከር ስንት ዘመን አለፈ? ያልጠፋነው እኮ ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ ወገኖቼ በክርክራችን እግዚአብሔር አይከብርም ፡፡ ያላመኑ ወገኖች ከእኛ ምን ይማራሉ ? እግዚአብሔር. ሆይ አንድ አድርገን፡፡ ማስተዋልን ስጠን ፡፡
  ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል፡፡
  ወስብት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 22. tehadiso is one of the strategiy pland by protestant....but Christian Orthodox will Live forever since founded by boold of Juses christ our true God !!! ....በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም (matewos 16.18)

  ReplyDelete