Thursday, December 8, 2011

የታፈኑ እውነቶች

  • ከ10 ዓመት በፊት አቶ አሊ አብዶ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሀላፊ አድርጎ መንግስት ከሰየማቸው ጊዜ ጀምሮ እሳቸው ከስልጣን እሲኪወርዱ ድረስ በእሳቸው ቦታ ፈቃጅነት 98 የሚያህሉ መስኪዶች አዲስ አበባ ውስጥ እንደተሰሩ ያውቁ ኖሯል? 
  • እኛ  መስኪድ አይስሩ አያስፈልጋቸውም እያልን አይደለም እኛ አራት አብያተ ክርስትያናት ስንሰራ እነሱ ደግሞ 98 መስራታቸው በጣም ስለገረመን ስለደነቀንም ጭምር ነው እንጂ፡፡
  • አንድ መስኪድ አዲስ አበባ ላይ በሰሩ ቁጥር በ100ሺዎች የሚቆጠር ብር ከሳውዲ አረቢያ መንግስት አንደሚለቀቅላቸው 
  • (ለኢቲቪ የቀረበበት ክስ) 
  • መንግስት በ2004 ህዳር ወር ላይ የተካሄደውን ታላቁ ሩጫ ላይ 4ሺህ ያህል የደህንነት አባላቶችን ከህዝቡ ጋር አብሮ በመቀላቀል አስሩጦ ፤ ‹‹ሳንፈልጋችሁ 20 ዓመታችሁ›› በማለት የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙትን ወጣቶችን በማፈስ እስር ቤት ለማገባት ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፤ ነገር ግን በህዝቡ ላይ ለ10 ዓመት ያህል እንዲህ አይነት የመስኪድ መስራት ወረራ ሲካሄድ ዝም ማለቱ .........
  • አክሱም ላይ መሲኪድ መስራት ይፈቀድልን ?
  • ‹‹ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር የሙስሊም ማህበረሰቦች›› ብለው ይፅፋሉ እንጂ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ›› ብለው የመፃፍ መብቱ የላቸውም ነበር፡


ጦር ሀይሎች የእስልምና ምክር ቤት ህንፃውን ከለላ በማድረግ ያለፍቃድ የተሰራ መስኪድ

    ከETV ሾልከው የወጡ ወሬዎች
    (አንድ አድርገን ፤ ህዳር 29 ፤ 2004 ዓ.ም) ፡- ጊዜው ከወራት በፊት ነው ፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰቦች በዓላቸውን ለማክበር ከህፃን እስከ አዋቂ ፤ ወጣቶች ፤ ሽማግሌዎች ሴቶች ፤ ወንዶች አንድ ሰው ከቤቱ ቀረ በማይባል መልኩ በዓላቸውን ለማክበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተዋል ፤ ስታዲየሙ አከአፍ እስከ ገደቡ ስለሞላ ስታዲየም ዙሪያ የእምነቱ ተከታዮች ለስግደት ተሰብስበው የሚሰገድበትን ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ቁጭ ብለው ይታያሉ ፡፡ ኢቲቪ ይህን በዓል ለዓለም ህዝብ ቀጥታ ለማተላለፍ በተለያዩ የስታዲየም ቦታዎች እና በስታዲየም ዙሪያ ባሉ አንበሳ ህንፃ ፤ ቤተዛታ ላይ ካሜራቸውን አስተካክለው የፕሮግራሙን ጅማሬ በመጠባበቅ ያገኙትን ምስል ለማተላለፍ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ ፡፡ በዚህ ጊዜ ያልታሰበ ችግር ተከሰተ ፤ ኢቲቪ ይህን ሲሰራ ከተለያየ አቅጣጫ ሊያነሳ ካዘጋጃቸው ካሜራዎች 3 ያህሉ ቴክኒካዊ ችግር ተፈጠረባቸው ፤ ፕሮግራሙ ተጀምሯል ኢቲቪ ግን እየቀረፀ አይደለም ፤ እንዳሰቡት ሳይሆን እንዳላሰቡት ፕሮግራሙ እየተከናወነ ነው ያለው ፤ ከተለያየ ቦታ መቅረፅ ስላልቻሉ አንዱን ምስል ደጋግመው ፤ ደጋግመው ለማሳየት የተገደዱ ይመስላል ፡፡ በበዓሉ ቀን ‹‹ኢቲቪ የሰራው ስራ አሳፋሪም አሳዛኝም ጭምር ነው ፡፡ ለዓለም ህዝብ የቁጥራችንን ብዛት ለማሳየት የምንጠቀምበት አጋጣሚ እንዳይሆን አድርጎ ያበላሸው ለምንድነው?›› የሚል ጥያቄ በጥቂት ሰዎች ቀስቃሽነት ተነሳ ፡፡


    ከቀናት በኋላ ለኢቲቪ የቀረበበት ክስ
    የሆነውን ነገር የኢቲቪን ስህተት ሰዎች ወደኋላ መለስ ብለው ተነጋገሩበት ፤ ጥቂት ሰዎች ይህ ችግር ያጋጥማል ብለው ማለፍ ቢሞክሩም አብዛኛው ሰው ግን ‹‹አይደለም ይህ የእኛ እምነት ላይ ሆን ተብሎ የተሰራ ሴራ ነው›› በማለት የኢቲቪ ባለስልጣናትን ለማነጋገር እና የተፈጠረበትን ምክንያት ማወቅ ፈለጉ፡፡ ከእስልምና ምክር ቤቱ ጋርበመተባበር ይዘውት የሄዱት ደብዳቤ እንዲህ የሚል ነበር
    እኛ የሙስሊም ማህበረሰቦች በዓላችንን በምናከብርበት ጊዜ ሆን ተብሎ የክርስትያን ካሜራ ሰዎች በሰሩት ስራ በስታዲየሙ ተገኝቶ የነበረውን ህዝባችንን ለዓለም ህዝብ ማሳየት አልቻልንም ፤ ይህም የሆነው በኢትዮጵያ ላይ ያለን ቁጥር ትንሽ መስሎ እንዲታይ የተደበቀ ሴራ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ይህን በሰሩት ሰዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን ይላል፡፡
    ሰዎች ይህን ክስ ተራ ክስ አድርገው ማየት ይችላሉ ፤ ለእኔ ግን ተራ እና አትኩሮት የማይስብ ወሬ አይደለም ፤ ይህ ጥያቄ የዘመናት ጥያቄያቸውን በትንሹም ቢሆን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ፤ የወደፊት ፍላጎታቸውን ፤ አላማ እና ግባቸው በመነሳት እንጂ የዚያን ቀን ስህተት ብቻ የወለደው ጥያቂ አይደለም ብዬ ለራሴ ወስጄዋለሁ፡፡ ብዙ የማውቃቸው እውነት አዘል መረጃዎች ስላሉኝ ከእነሱ ጋር እያወጣው እያወረድኩ ፍላጎታቸውን ለማየት ፈልጌ ብፅፈው ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ ስለመጣልኝ ባወኳቸው ያህል እዳስስላችኋለሁ::

    የኢቲቪ ውሳኔ
    ኢቲቪም በጊዜው የተቀረፀውን ፊልም በኮሚቴ አባልነት በተመደቡ ሰዎች ተመልክቶ የጠየቁት ጥያቄ ተገቢ አይደለም እንዳይል ፤ የሚታይ ነገር አለ ፤ የራሱ ባለሙያዎች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ መቶ በመቶ አስረግጦ የሚያስረዳ ክስ ስላልሆነ ፤ከበስተጀርባው ሌላ ነገር ስለሚያመጣ ሀላፊዎቹ የሚያደርጉት ግራ ገባቸው ፤ በመጨረሻ ግን አዎን ይህን የሰሩት ክርስትያን  የካሜራ ሰዎች ሆን ብለው ሌላ አላማቸውን ለማንፀባረቅ አሰበው ነው በማለት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተፅፎ ሲሰጣቸው ፤ እነርሱም በበኩላቸው ይህ እኛ ሆን ብለን ያደረግነው ነገር አይደለም የቴክኒክ ችግር ተፈጥሮብን ነው ፤ ይህን ደብዳቤ አንቀበልም ሊሉ ችለዋል ፡፡ ይህን ጉዳይ ባለጉዳዮቹ ሲመላለሱ ባለስልጣኖቹም መልስ ሳይሰጡ በደፈናው ‹‹ወደ ላይኛው አካል ሄዷል›› ብለው ነገሮችን አደባብሰው ጊዜው ሲሄድ ሊረሳ ችሏል፡፡ ዋናው ጥያቄ ከክርስትያኑ እንድናንስ ተደርገናል ፤ የእጅ አዙር ስራ ተሰርቶብናል የሚል ነው ፡፡ እውን እነርሱ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በሀገር ደረጃ ከእኛ ይበልጡ ይሆን? ወረድ ስንል እናየዋለን (ምንጭ በጊዜው የነበረ የካሜራ ሰው)፡፡

    ምኞት
    የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ይህን በአል በማክበር ሂደት ላይ አንድ የሙስሊም ጋዜጠኛ ስለ በዓሉ የሚቀጥለውን ነገር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ተናግሮ ነበር፡፡‹‹ ዛሬ በሚከበረው በዓል ላይ 1.6 ሚሊየን የሚጠጉ ሙስሊሞች በቦታ ላይ እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል›› ብሎ ሌላ በዚህ በኩል ብዙ ማብራሪያ ሲሰጥ ተመልክቼ በጣም ነበር የገረመኝ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር እንደ ህዝብና ቆጠራ ስሌት ከሆን 3.2 ሚሊየን ይጠጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ አሁን ይህን የዘገበው ሙስሊም ጋዜጠኛ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከሁለቱ ሰው አንዱ ሙስሊም ነው እያለን ነው ያለው፡፡ ወይንም ከ50% በላይ የሚስሊም ማህበረሰብ አዲስ አበባ ይኖራል ብሎ እየነገረን ነው ያለው ፡፡ ቁጥራቸው በሶስት ቢባዛ እንኳን 1.6 ሚሊየን አይደርሱም ፤ ኢቲቪ ይህን የመሰለውን ታስቦ የተገባበት ሴራ ፤ መረጃን በማዛባት ሰዎች ጋር ማድረስን በምን አይነት መልኩ እንደሚመለከተው አላውቅም፡፡ ስታዲየሙ ይይዛል ተብሎ የሚገመተው 35 ሺህ ሰዎችን ነው ፡፡ ስታዲየም አካባቢ እንኳን 10 የስታዲየም ቦታ ላይ ቢያርፉ ከ350ሺህ ሰው የሚዘል አይሆንም ፤ በስታስቲክስ ኤጀንሲ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አዲስ አበባ ውስጥ 13% ያህል ሙስሊሞች ይገኛሉ ብሎ ነው ያስቀመጠው ፤ ታዲያ ይህ ሰው እውን ይህ መረጃ ሳያውቅ ተሳስቶ ነው ? ወይስ ሆን ተብሎ የተሰራ ስራ? ወይስ የቅርብ ጊዜ ምኞታቸው ነው ? መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡

    ስታስቲክስ ኤጀንስ ባስቀመጠው ስሌት መሰረት ወደ 400 ሺህ በላይ ሙስሊሞች አዲስ አበባ ይገኛሉ ይላል ፤ 1.6 ሚሊየን ለመድረስ 1.2 ሚሊየን ሰዎች ይጎላሉ ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርቡ በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ያለው መረጃ ኦርቶዶክስ 43.5 በመቶ ማለትም 32 ሚሊየን አካባቢ ከጠቅላላው ህዝብ  ቁጥር አላት ፤ ሙስሊም 33.9 በመቶ ማለትም 25 ሚሊየን አካባቢ ህዝብ ብዛት አላቸው ብሎ በወጣው ሪፖርት ላይ ‹‹የተሳሳተ ቆጠራ ነው እኛ ብንበልጥ እንጂ አናንስም›› ብለው መጠየቃቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ይህ ጥያቄ የተጠየቀው በፓርላማ ደረጃ መሆኑን ሲያውቁት ደግሞ አላማቸው ምን እንደሆነ ፍንትው ብሎ ነው የሚታየው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሰጠችው ስሟን አሁን የማላስታውሰው የኤጀንሲው የበላይ ሀላፊ ሙስሊም ወ/ሮ መረጃው ትክክል እንደሆነ ብዙ የተሰራበት ፤ ብዙ ብር የፈሰሰበት ቆጠራ ስለሆነ ይህን ጥያቄ ኤጀንሲው እንደማያስተናግድ አስታውቃቸው ነበር፡፡


    እንዳለኝ መረጃ መሰረት በደርግ ጊዜ ከእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የሚወጣ ደብዳቤ ራሳቸውን እንደ እንግዳ ነበር የሚቆጥሩት ፤ ትክክል ነው እነርሱ ለዚች ሀገር እንግዶች ናቸው ፤ የሀበሻ ሀገር ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ፤ የራሳቸው ነብይ ነበር የላካቸው ፤ በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ ንጉስም ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ታሪክ ይነግረናል፡፡ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስ እና በደርግ ሰዓት ከስርዓቱ ጋር ህጋዊ ደብዳቤ ሲለዋወጡ ‹‹ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር የሙስሊም ማህበረሰቦች›› ብለው ይፅፋሉ እንጂ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ›› ብለው የመፃፍ መብቱ የላቸውም ነበር፡፡ ይህ ተፅፎ የተቀመጠ ማስረጃ እንጂ የፈጠራ ወሬ አይደለም ፤ እድሜ ለኢህአዴግ መንግስት ይበሉ ሙሉ ኢትዮጵያዊነትን ላጎናጸፋቻ ፤ ይህን መረጃ ስመለከት በጣም ነበር የገረመኝ፤ ታዲያ ማረፊያ አጥተው ብናስተናግዳቸው እነርሱ ደግሞ ‹‹ ወርቅ ላበደረ አመድ›› እንዲልህ ብሂሉ በጅማ ፤ በምስራቅ ሀረርጌ ፤ ከቀናት በፊት በስልጤ ወረዳ ከአክራሪ ሙስሊሞች የሚደመሩ ሰዎች ህዝበ ክርስትያን ላይ መከራ እያበዙበት ፤ ቤታችንን ወደ አመድነት እየቀየሯቸው ይገኛል፡፡

    ‹‹ኢትዮጵያ የአረብ ሀገር አባል ትሁን›› ጥያቄ
    ደብዳቤው የተፃፈው ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ነው ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ ደብዳቤዋች ከተለያየ አካል ይፃፋሉ መልስ ግን የላቸውም የሚል ትችት በቅርብ ጊዜ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ አንብቤአለሁ ፤የደብዳቤው ይዘት ከሞላ ጎደል ‹‹ ከ50 በመቶ በላይ በቁጥር የምንመዝን የሙስሊም አማኞች በኢትዮጵያ ውስጥ እንገኛለን ፤ እንደ ቁጥራችን መጠን ለመንግስት የምንጠይቀው ጥያቄ ፍትሀዊ መልስ ይሰጠን ዘንድ ግድ ነው ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት አባል ብትሆን ለእኛም ሆነ ለሀገሪቱ መልካም  ስለሆነ ፤ መንግስት ቁጥራችንን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት አባልነትን እንዲጠይቅ ስንል እንጠይቃለን›› ይላል፡፡ ጥያቄው ሲነሳ ከ50 ከመቶ በላይ ነን ይላል ፤ ለዚህ ጥያቄያቸው መንግስት ምን አይነት ምላሽ ይስጣቸው አላቅም ፤ በተጨማሪም ከዚህ ጋር በተያያዘ  አክሱም ፅዮን አካባቢ  መስኪድ ለመስራት ጥያቄ እንዳቀረቡም ለማወቅ ችያለሁ ፤ አክሱም ፅዮን ውስጥ አይደለም መስኪድ ሙስሊም እንኳን ቢሞት እዛ አካባቢ የመቀበሪያ ቦታ እብደሌላቸው ፤ የሀይማኖት እኩልነት የሚያውጀው ህገመንግስ በአግባቡ እየተተረጎመ እንዳልሆነ ጠቅሰው ነበር የጠየቁት፡፡ እውነት ነው ፅዮን ታቦተ ሙሴ መገኛ ናት ፤ ለእኛ ልዩ ቦታችን ናት ፤ መንግስም ይህን ጥያቄ ኦፊሺያል በሆነ መልኩ የሰጣቸውን መልስ የለም፡፡ በተባራሪ ወሬ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ እኛ መካ ላይ ቤተክርስትያን እንድንሰራ ከፈቀዳችሁልን እኛም አክሱም ፅዮን ላይ እንድትሰሩ እንፈቅዳለን›› ብለዋችዋል ይባላል ፤ አዎን ለእነርሱ መካ መዲናቸው ፤ ለእኛ ደግሞ አክሱም ቢበልጥ እንጂ አያንስም ፤

     98  ለ4

    ከ10 ዓመት በፊት አቶ አሊ አብዶ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሀላፊ አድርጎ መንግስት ከሰየማቸው ጊዜ ጀምሮ እሳቸው ከስልጣን እሲኪወርዱ ድረስ በእሳቸው ቦታ ፈቃጅነት 98 የሚያህሉ መስኪዶች አዲስ አበባ ውስጥ እንደተሰሩ ያውቁ ኖሯል? አሁን ላይ ከቤተክርስትያናችን በ100 ሜትር ርቀት ላይ የቆሙ መስኪዶች ሁሉም ከ10 ዓመት በፊት በአሊ አብዶ ፍቃድ የተሰጣቸው መሬት ነው፤  ይህ ቁጥር የተጋገነነ መስሎ አይሰማዎ  ፡፡ በጊዜው በርካታ ሰዎች ይህን መስፋፋታቸውን አይተው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ቢያቀርቡ የሚሰማ ጆሮ ሊያገኙ ፤ መፍትሄ የሚሻ አካል አቤት ሊላቸው ግን አልቻለም ፤ በብዛት እነዚህ መስኪዶች የተሰሩት በኮልፎ ቀራንዮ  ፤ አየር ጤና እና አስኮ  ባለው አካባቢው ላይ ነው፡፡ ይህን ድርጊት ከጊዜ በኋላ የተመለከተው መንግስት እንደ መመዘኛ በመውሰድ አሊ አብዶን ከስልጣን  እስካስወገደው ጊዜ ድረስ የመሬት ሽሚያው እና መስኪድ የመስራት ተልዕኮን የሚያስፈፅሙ በርካታ ሰዎች በየአካባቢው ነበሩ፡፡ መንግስት ለእኛ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ሰግቶ ትንሽ አካሄዳቸውን ገታ ባያደርገው አሁን ላይ በሺህ የሚቆጠር መስኪድ በሰሩና ባጥለቀለቁንም  ነበር፡፡ መንግስት በ2004 ህዳር ወር ላይ የተካሄደውን ታላቁ ሩጫ ላይ 4ሺህ ያህል የደህንነት አባላቶችን ከህዝቡ ጋር አብሮ በመቀላቀል አስሩጦ ፤ ‹‹ሳንፈልጋችሁ 20 ዓመታችሁ›› በማለት የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙትን ወጣቶችን በማፈስ እስር ቤት ለማገባት ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ነገር ግን በህዝቡ ላይ ለ10 ዓመት ያህል እንዲህ አይነት የመስኪድ መስራት ወረራ ሲካሄድ ዝም ማለቱ ከምን የተነሳ እንደሆነ አላውቅም፡፡

    ይህ ሁሉ ሲደረግ አዲስ አበባ ላይ የታነፁት አብያተ ክርስትያናት ግን 4ብቻ መሆናቸውን ስንገነዘብ በጣም ያናዳልም ያበሳጫልም ፡፡ አንድ መስኪድ አዲስ አበባ ላይ በሰሩ ቁጥር በ100ሺዎች የሚቆጠር ብር ከሳውዲ አረቢያ መንግስት አንደሚለቀቅላቸው ውስጥ ውስጡን ይወራል ፤ ተጨባጭ ዶክመንት ባላገኝም ፤ ከተሰሩት 98 መስኪዶች  ውስጥ ከ50 በላዮቹን ለማየት ችያለሁ ፡፡ የተሰሩበት ቦታ ጥቂት መንገድ ዳር ቢሆኑም አብዛኞቹ ግን የሰው ግቢ ውስጥ ከ300 - 1000 ካሬ ቦታ ባላቸው ቦታ ላይ ያረፉ ናቸው፡፡  ….. ይህን ማን አስተዋለ ? ነገሮች ሲመቻችላቸው ሁኔታውን አይተው እድሜ ለአረብ ሀገራት ገንዘብ በደንብ አድርገው ይሰሩታል፤ እኛ አይስሩ መስኪድ አያስፈልጋቸውም እያልን አይደለም እኛ አራት አብያተ ክርስትያናትን ስንሰራ እነሱ ደግሞ 98 መስራታቸው በጣም ስለገረመን ስለደነቀንም ጭምር ነው እንጂ፡፡


    በዚህ ዙሪያ ላይ ተኝቶ አልነቃ ያለው ቤተክህነት ምንም  መረጃ ሳይኖረው ቀርቶ አይመስለኝም ፤ ነገር ግን ‹‹አውቆ የተኛ ›› ሆነ እና ነገሩ በጊዜው ዝምታን ነው የመረጠው ፤ ለነገሩ እኔም ከእነሱ ምንም የምጠብቀው ነገር የለኝም ፡፡ በተሻለ ሁኔታ አነፍንፈው መረጃ የማግኝት አቅም አላቸው ብዬም አላስብም ፤ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ካለቀ በኋላ ሰዎች አፍ ላይ ነገሩ ሲመላለስ እነርሱም ይሰማሉ እንጂ ነቅቶ ህዝበ ክርስትያንን እና ቤተክርስትያንን የመጠበቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው እንኳን የሚያውቁ አይደሉም ፤ የእኛ አብያተክርስትያናት በጠራራ ፀሀይ በሚቃጥሉበት ሀገር ላይ ፤ የእነርሱ መስኪድ ህግ ባለበት ሀገር አዲስ አበባ ህገወጥ ፍቃድ በማውጣት እየሰሩ ይገኛሉ ፤ እኛስ ህጋዊነቱን መጠየቅ መብት እንዳለን እናውቃለን ? የመንግስት መሬት ማለት የህዝብ መሬት ነው ፤ የህዝብ ከሆነ ደግሞ እኛም የህዝቡ አንዱ አካል ነን ፤ 

    ለምሳሌ ከጦር ሀይሎች ተነስተው አጠና ተራ እስኪደርሱ ድረስ በግራ እና በቀኝ የሰፈሩ መስኪድ ቁጥሮች 9 ይሆናሉ ፤ የእኛ ቤተክርስትያን ግን እየሱስ ገዳም  ብቻ ነው ያለው ፤ ሁሉን ፎቶአቸውን ከነ ስማቸው ማስቀመጥ እችላለሁ ፤ የእኛ አብያክርስትያናት ትልቅ ተደርገው ስለሚሰሩ ያሉበትን ቦታ ማወቅ አስቸጋሪ አይደለም ፤ የእነርሱ መስኪድ ግን ከ300 ካሬ ቦታ ላይ ተነስተው ስለሚሰሩት ጎረቤት ያለ ሰው እንኳን የሚያውቀው ጨረቃ ሲሰቀልበት እንጂ በሌላ መንግድ አይደለም ፡፡ ቀራንዮ አካባቢ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሶስት ብቻ ናቸው ፤ መድሀኒአለም ፤ ቅዱስ ገብርኤል እና እመቤታችን ነገር ግን የእነርሱ መስኪድ ግን 7 ናቸው፡፡ ጦር ሀይሎች ጋር የእስልምና ምክር ቤት ህንፃ አጠገብ ከዓመት በፊት ህንፃውን ከለላ በማድረግ ጨረቃ እና ኮከቧ ዝቅ ብለው ያለ ፍቃድ ነበር የተሰቀሉት ፤ ሲሰቅሉት ከዋናው ቀለበት መንገድ 30 ሜትር በማይርቅ ቦታ ላይ ከፊት ለፊቱ ህንፃ ስላለ ማንም ያስተዋለው የለም ፤ ወራት ካለፉ በኋላ ትንሽ ከፍ አድርገው ሰሩት ፤ እርግጠኛ ነኝ የዛሬ ዓመት ትልቅ መስኪድ ቦታው ላይ ተሰርቶ እንደሚያልቅ አና መቼ ነው ደሞ ይሄ የተሰራው?  ብለን ራሳችንን እንደምንጠይቅ ፤ በአዲስ አበባ ብዙ ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያለው ፤ መስኪድ አይስሩ የሚል አቋም የለንም ፤ እምነታቸውን የሚያካሄዱበት ቤታ ያስፈልጋችዋል ፤ ነገር ግን በእንደዚ አይነት አካሄድ ነው ብለን አናምንም ፤ 
     የእስልምና ምክር ቤት ህንፃ አጠገብ ህንፃውን ከለላ በማድረግ ያለፍቃድ የተሰራ መስኪድ
    ህንፃውን ከለላ በማድረግ ያለፍቃድ የተሰራ መስኪድ

    ቀራንዮ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን በ1826 ዓ.ም እንደተመሰረተ ይነገርለታል ፤ ይህው እስከ አሁን ድረስ ከመድሀኒአለም አንስቶ 178 ዓመት ታሪክ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉት ደብሮች ከ131 አይበልጡም ፤ እርሱ ግን አጋጣሚውን ተጠቅመው እኛ በ170 ዓመት ቆይታችን የሰራነውን በ10 ጊዜ ውስጥ ሊሰሩ ችለዋል፡፡ አገረ እግዚአብሔር በምትባል ኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ላይ የቤተክርስትያኖች ቁጥር ከመስኪድ ያንሳል ቢባል ማን ያምናል ?


    ይችን ጨረቃ አውርዱ
    ይህ የሆነው ኮልፌ መብራት ሀይል የሚባለው ቦታ ነው ፤ አንዱ ቤት በትምህርት ምክንያት ብዙ ሰዎች በዝተው መታየት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል ፤ በኢማሞቻቸው አማካኝነት ያለ ፍቃድ ፤  በቤታቸው ውስጥ ብዙ ሰው እየመጣ ይማራል ፤ ይሰግዳል ፤ ለካንስ ውስጥ ውስጡን ነገሩ አልቆ ኖሯል  ፤ ባልታሰበ ቀን ረዥም እንጨት ላይ ስፒከር በአራቱም አቅጣጫ ሰቅለው ለሊት 11 ሰዓት ላይ ‹‹አላህ ዋክበር›› ሲሉ ጎረቤቶች ሰምተው ማመን ነው ያቃታቸው ፤ ጎረቤታሞች  ወጣቶች ተሰበሰቡ ‹‹ እዚህ ቅርብ መስኪድ አላችሁ ፤ በዚህ ምክንያት 25 ዓመት በኖርንበት አካባቢ በነጋ በጠባ ቁጥር መበጥበጥና እንቅልፍ ማጣት አንፈልግም ፤ ይህን ስፒከራችሁን ዛሬውኑ አውርዳችሁ ካላደራችሁ እኛው ራሳችን እናወርደዋለን ፤ ፖሊስም መጥራት አያስፈልገንም እናወርደዋለን›› ብለዋቸው ሄዱ ፤ በመጀመሪያ ቤቱን ለመስኪድነት ባለቤቱን አስማምተው አሽጠውታል ፤ ሁለተኛ ካለ መንግስት ፍቃድ መስኪድም ሆነ ቤተክርስትያን መስራት አይቻልም ፤ እነርሱ ግን ሀሳባቸው አንድ ጊዜ ከሰቀልን በኋላ አውርዱ ብንባል ፤ ሌላ ጥያቄ አንስቶ ነገሩን ወደ አልሆነ አቅጣጫ የመውሰድ ሀሳብ ነው የነበራቸው፡፡ የሙስሊሙን ህዝብ መንግስት መስኪዳችንን አፈረሰብን ብለው ቢነሱ እውነታውን የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው አይኑን ጨፍኖ እንደሚከተላቸው እርግጠኞች ነበሩ፡፡ እንዲህ ተብለው ካበቁ በኋላ ወጣቶቹ ለሚመለከተው አካል የሰሩትን ስራ አቤት አሉ ፤ ሳይወዱ በግዳቸው ጨረቃዋን በሰቀሉ 24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አውርደው ሊያድሩ ችለዋል፡፡ ስንቶቻችን ነን ዛሬ ህገ ወጥ ነገር ሲሰራ እኔም ይመለከተኛል ብለን በግለሰብ ደረጃ ጥያቄ የምናነሳው? ስንቶቻችን ነን ለሚመለከተው አካል አቤት ብለን ውሳኔውን የምንከታተለው ? ስንቶቻችን ነን የዛሬው ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የመስኪድ ስራ ነገ የሚያመጣውን ተፅእኖ ከግምት የምንከት ? ስንቶቻችን ነን አዲስ አበባ ካለው የቤተክርስትያ ቁጥር የመስኪዶቹ ቁጥ እንደሚበልጥ የምናውቅ? አዲስ አበባ ላይ ከ82% በላይ ያህል ቁጥር አለን ፤ እነርሱ ግን ከ13 በመቶ አይበልጡም ነገር ግን የኛ ቤተክርስትያኖች ቁጥር ከእነርሱ መስኪድ ቁጥሮች እጅጉን ያንሳሉ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? አዎን ስለቤተክርስትያናችን ግድ የሚለን ከሆነ ቤተክርስትያን ከመመላለስ በተጨማሪ በዙሪያዋ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ማጤን ይገባናል ፤ በአካባቢያችንም እየተሰራ ያለውን ነገር ማስተዋል ግድ ይለናል  ፤ ነገ ልጆቻችን ‹‹አላህ ዋክበር›› የሚለውን ቃል ከቅዳሴ ጋር እኩል አንድ ላይ መስማት የለባቸውም፡፡ 

    የመናፍቃኑ መስፋፋት
    አንድ አባት ‹‹መናፍቅ›› የሚለውን ሲተረጉሙ የማያምን ማለት አይደለም እምነት የጎደለው ማለት ነው ብለውናል፡፡ እነዚህኛዎቹ በ1987 ዓ.ም 5.4 ሚሊየን ህዝብ ቁጥር ነበራቸው ከ10 ዓመት በኋላ ግን ወደ 13.7 ሚሊየን ሊጠጉ ችለዋል ፤ እኛ በተኛንበት ዘመን እነርሱ ቢሰሩ የሚያስደንቅ አይደለም ፤ የእነዚህኛዎቹ አካሄድ እንኳን ከእነዚያ ይለያል ፤ ብዙዎች አማኞች ከእስልምና የሄዱ ሳይሆኑ ከእኛ አያያዝ ችግር በትንንሽ ምክንያቶች ጠላት ውስጣቸው እንክርዳድ በመዝራት ያኮበለላቸው ናቸው ፡፡  እነዚህኛዎቹ አዲስ አበባ ላይ ከ50 የሚበልጡ እምነቶች ሲሆኑ ፤ የበጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበራዊ ኤጀንሲ በሀይማኖት ተቋምነት  እውቅና የተሰጣቸው አካላት ናቸው፡፡  እየተሰነጣጠቁመም ፍቃድ ማውጣቱን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል ፤ ህዝቡንም ግራ እያጋቡት ይገኛሉ ፡፡ ከዓመታ በፊት ብዛታቸው 50 እያለ አውቃለሁ ፤ አሁን ግን  ምን ያህል አዲስ እምነት እንደጨመሩ መረጃ የለኝም፤  ነገር ግን የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ግንቦት 13 2002 ዓ.ም በአንድ ቀን ለአራት የመናፍቃን ድርጅቶች መንግስት እውቅና የሰጠበት ማስረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ያሳወጁበት  እጄ ላይ አለ ፡፡ ይህን ይመልከቱ

    አስቡት በአንድ ቀን 4 የእምነት ተቋማት ፍቃድ ሲጠይቁ ፤ይገርማል ፤ ቢያንስ በወር አንድ የእምነት ተቋም ፍቃድ ቢሰጠው በዓመት 12 የምንፍቅና ድርጅቶች እየተቋቋሙ ይሄዳሉ ማለት ነው፡፡ በሁለት ዓመት ደግሞ 24 …..  የእነዚህን ማን ምን ያህል ቤተክርስትያ እንዳለው ለማወቅ ብዙ ጥሬ ነበር ፤ በአጋጣሚ አንድ ቦታ ስሄድ አዲስ ስም አያለሁ ፤ ሌላም ቦታ በከተማው ስንቀሳቀስ እንደዛው ፤ እንደ አሸን ነው የሚፈሉት መሰል ግራ አጋብተውኛል ፤ አንድ ላይ ደምረነናቸወው በደፈነናወው ካላየናቸው ቆጥረን እና አውቀን የምንዘልቃቸው አይደሉም ፤  ብዛት  ከሙስሊሞቹም በእጥፍ ይበልጣል እንጂ አያንስም ፤ እነዚህ ከቻሉ ቦታ ይገዛሉ ካልቻሉ ደግሞ ባዶ ቦታ በመከራየት ቦታው ላይ በቆርቆሮ አዳራሽ ይሰራሉ ፤ አካሄዳቸው ይሄ ነው ፤ የአማኛቸውንም ብዛት ጭምር ለማወቅ እፈልግ ነበር ፤ ነገር ግን አንዱ ምዕመን ደስ ሲለው ሙሉወንጌል ፤ ሌላ ቀን መካነ እየሱስ ፤  ወይም FBI (Faith Bible International) ፤ ወይም አንዱ ጋር ይሄዳል እንጂ ቋሚ እምነቱ ይህ ነው የሚባል ሰው መሀከላቸው ትንሽ ነው ፤ ሰው ሁሉ ወደቀረበው ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ማወቅ እንደማይቻል ለማወቅ ችያለሁ ፤ ሁሉም መናፍቅ እንበላቸው እንጂ መሰረታዊ ልዩነት የለባቸውም ፤ መዝሙራቸው ሰባተኛው ቀን ፤ ነፃነት ፤ ሬማ ፤ የትንሳኤ ምስክሮች ጋር ሁሉም ጋር ይሸጣል ሁሉም ጋር ይደመጣል ፤ የእኛም መዝሙሮች ሁሉን ያማከለ እያደረጉ እየሰሩልን ያሉ የዛሬ ዘማሪያን በመካከላችን አሉ ፤ የዘርፌ ካሴት መናፍቃኑ አዳራሽ ከፍተው ይጠቀሙበታል ፤ ይሄ ምን ማለት ይሆን ? የአንዱ እምነት ሰባኪ ሌላው ጋርም እየተጋበዘ ከዚህ ቤተክርስትያን ነው እየተባለ እንደሚሰብክም ከእምነቱ ተከታዮች ለማወቅ ችያለው:: ይችን አካሄድ አሁን መስበክ የተከለከሉት የኦርቶዶክስ ሰባኪያን አዳራሻቸው ሄደው ባይሰብኩ እንኳን ሁሉም ፕሮቴስታንቱም ፤ ሁሉም ሙስሊሙም ፤ ክርስትያን የሆነውም ያልሆነውም እንዳይቀር እያሉ በክፈለ ሀገር የሚገኙ ቤተክርስትያናችን እንዲመጡ በሞንታርቦ የቀሰቀሱበት ጊዜ ነበር ፤ ይህ የመሰለ አካሄድ ከእነርሱ የመጣ ይሆን ? ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡  ይህን ሁሉ ለማወቅ መፈለጌ ሀጥያት ነው ብዬ አላስብም ፤ መረጃ ከሆነ የፈለኩት ከወዳጅ ይልቅ ጠላት ጋር እንደሚገኝ አውቃለሁ :: 


    ለማንኛውም የመናፍቃኑን የመስፋፋት ሂደት ፤ የሚጠቀሙባቸውን መንገዶች ፤ በውስጣችን ስላሰማሯቸው ጡት ነካሾችና በአዲስ አበባ በባቡር ጣቢያ ውስጥ ስላለው ህገወጥ መስኪድ ፤ ቦታውን ማን ሰጣቸው ? የመንግስ ቦታ ላይ መስኪዱ ሲሰራ የከተማ መስተዳድሩ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መስተዳድር ጩህት ፤ የመንግስት ዝምታ….የአይናችን ፕሮግራም ሙሉ ያልሆነ ዘገባ ፤ እንነግሮታለን ፤ በሌላ ጊዜ እመለስበታለው

    ‹‹ የምንፈራው እውነት የለም ››


    ‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››

    16 comments:

    1. ገና ምንታይቶ በቤታችን ጣሪ ላይ ጨረቃና ኮከብ እንስቀል ይላሉ ሀይ ካልተባሉ እነሱ በመንደራቸው ቤተክርስቲያን ያቃጥላሉ እዚህ ደግሞ መንገድ ያጣብባሉ ልብያለው ልብይበል እየተስተዋለ ብንከባበር ይሻላል እግዚያብሄር ኦርቶዶክስንና ኢትየጵያን ህዝቧን የጠብቅ አሜን!!!!

      ReplyDelete
    2. ባጎረስኩ ተነከስኩ!
      ዛሬ እና ትናንትን እኔ እየኖረኩኝ ያለሁት ለየቅል ሁኖብኛል፡፡ትናንት ቢያንስ እምነቴን ተስፋ አድርጌ ባገኝ በልቸ ባጣ ጠጥቼ ፈጣሪየን አመስግኘ አድር ነበር፡፡ዛሬ ግን ተስፋየን የሚሸረሽሩ፤ነገን በዕሩቅ አሳቢነት እንዳልኖር የሚያደርጉ ነገሮች በመብዛታቸው ሁሉ ነገር እሬት እሬት እያለኝ ነው፡፡ ሰው ምንም ይሁን ምን በእምነት ካልኖረ ምን ቢሰራ፤ምን ቢለፋ ውጤቱ የሚሆነው ሆድን በጎመን የመደለል ያህል ነው፡፡ለምን ይሆን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን እና እምነቱን ሌሎች የሚተናኮሉት?የሚያስገኝላቸው ጥቅም ምን ይሆን?ተከባብሮ እና ተቻችሎ ለመኖር ሲፈለግ ይህ መሰል ሰደድ እሳት እንዳይስፋፋ መንግስትስ ምን እየሰራ ነው?
      አንድ አድርገን ብሎግ የምታወጡት መረጃ እጅግ ጠቃሚ ነው እና በርቱልን፡፡ግን መረጃውን ማሰራጨት ብቻ ሳይሆን የመፍትሄ ሀሳብ የሚሆኑ ነገሮችን ጠቁሙን፡፡ሰ/ት/ቤቶች ይህ አይነቱ መረጃ ሊደርሳቸው የሚችሉበትን መንገድ አመቻቹ፡፡እኛም ምዕመናን የበኩላችንን መወጣት አለብን ባይ ነኝ፡፡
      መረጃችሁን በአንድ ቋት ብቻ/ማለትም በኢንተርኔት/ ለመላው ምዕመን ማዳረስ አትችሉም ብየ ስለምገምት ሌሎች መንገዶችንም ምረጡ፡፡ከመረጃ እጥረት የሚመጣ ኩዋሾከር ወጣት ክርስቲያኑን ስለያዘው እንጂ ቀድመው አባቶቹ ከውጭ እና ከውስጥ ጠላት እየጠበቁ ለዚህ ያደረሱለትን ሐይማኖት ለመጠበቅ እንደማያንቀላፋ እርግጠኛ ነኝ፡፡እናም ወጣቱን በመረጃችሁ ከጫት ገረባ ቀስቅሱት፡፡ሐይማኖቱን እንዲጠብቅ፤ትውፊቱን አሳልፎ እንዳይሰጥ የት ነህ ያለህው በሉት ወጣቱን፡፡ሰው ካወቀ፤መረጃ ከኖረው፤የአስተሳሰብ አድማሱ ይሰፋል፡፡እናም እባካችሁ በመረጃችሁ ወጣቱ እንዲማር ጥረታችሁን ቀጥሉ፡፡እኔ ግን በበኩሌ አሁን እየተሰማኝ ያለው ስሜት ከበድ የሚል ሆኖብኛል፡፡ለካንስ ሰው ሲያነብ ነው መጥፎ እና መልካሙ ነገር ፍንትው ብሎ የሚታየው፡፡በእውነት በዚህች ሐይማኖት ላይ እየተሰራ ያለው ደባ እጅጉን ያሳዝናል፤ያሳፋራልም፡፡እናም ከመሞት መሰንበት የሚለው የአገሬ ብሂል ለሐይማኖቴ የማይመጥን በመሆኑ ይህንን መሰል ድርጊት የሚሰሩ ሰዎችን መረጃ ካገኘሁ ለሚመለከተው በማሳሰብ የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት ወደ ኋላ አልልም፡፡
      በርቱ በርቱ በርቱ!

      ReplyDelete
    3. hulachenenem liyasasebene yemigeba hasab newe.

      Egiziyabeheare silehayemanotachen endenecheneqe yeredan!!

      ReplyDelete
    4. yemigermegn yemeles new alamudin yesudan asmat asdergobetal yibalal enem gira agabagn. yihin hulu iyaye ahunim yemishomew yemishrew enesun new gelew resaw lay endemikomu biyasib melkam new endih aynetu sefata ayawatahim p/r mele

      ReplyDelete
    5. I know it was about 150 mosques bro. keep countin. hte mosques around addis in his time.

      ReplyDelete
    6. goodjob bro!!!.berta bizu yemaytawk sera ale....

      ReplyDelete
    7. This why as an Ethiopian Orthodox Tewahedo Christians we should be united instead of getting divided on minor issues that will be solved overtime, but from what I have been observing for the past couple of years. what we have done is create blogs and website to confuse followers of our church. Think for a second people, how many people have left our church because of our daily arguments on blogs and magazines on various issues which the general public doesn't understand? So we should all stop this nonsense accusations and we should fight for the unity of our church and our people. For Bloggers and website owners this should give you a clear message on which way things are going.This is an article I read on a http://www.thetrumpet.com/?q=8901.7669.0.0
      "reason we can tell Ethiopia and Eritrea will soon fall to Iran".I am not saying all I have read is true in the article but there is some truth in it. So Pleas Please Please lets stop on accusing each other and lets unite for the sake of our believers and our church

      ReplyDelete
    8. Sorry I am cofused that my brother covert to Islam recently, meaning that he is not an Ethiopian man ????? please let us be rational. now time to fact , proof and evide. you are telling me all religions have right to buid church, mosque and so on because they are ethiopians and the same time this one is guest, that one is immigrant, or new, tahadso and so on. nowadays people have many sources of information and they follow proof and rational reason. we should change this emotional style.

      ReplyDelete
    9. ጥሩ መረጃ ነው ወንድማችን!
      ከተወሰኑ ወራት በፊት የሰማሁት፡-
      እዚሁ አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ከብዙ አመታት ጀምሮ ካህናት የሚያጥኑት ቦታ (ታቦትም ያለ ይመስለኛል) በፍርድ ቤት ክስ የተያዘ ቦታ... ምዕመናን ከዛ ቦታ ሲሄዱ ብዙ በደል እንደሚፈጸምባቸው ሰምቻለሁ፡፡ ቦታውም በፖሊስ ይጠበቃል---እንግልቱ መገፍተሩን ችለው ግን የሚያጥኑ እንዳሉ አንድ ለዕምነቱ ቀናዒ የሆነ ሰው ነግሮኝ ነበር፡፡ ምናልባት ከቻልኩ መረጃውን እንደገና ጠይቄ ለማስረዳት እሞክራለሁ... በአገሩ ባዳ፡፡ እግዚአብሔር ያስታግስልን፡፡

      ReplyDelete
    10. fear, fear and fear. it is just a nonsense article. i mean come up with any thing new and stop fabricating lies. if there are Muslims in an area then they should have a place to worship. if what your saying is true, what ali did is good since Muslims were neglected from the main stream society for long and now they are regaining their identity and place in the society. what about protestants? they are building church in every village in addis and also the country side. what can you say about them? i say to you they have a right as you have a right to build churches.do you believe there are only 2 or so million people in addis? don't you think it is fabricated? and final comment to you , there is no going back. fear not Muslims but fear itself.

      ReplyDelete
    11. እናንተ እየተከፋፈላችሁና እየተወጋገዛችሁ በአደባባይ አፍ ስትካፈቱ ከቀን ቀን እየመነመናችሁ ትሄዳላችሁ እነርሱ ግን የዉስጥ ችግራቸዉ ከኛ የባሰ ቢሆንም ልዩነታቸዉን አቻችለዉ የመስኪድ ቁጥር በማብዛት( ሳይኮሎጂካል ጫና መፍጠር)፣ ሴቶቻቸዉን ለክርስቲያን ወንዶች ሚስት አድርገዉ በመስጠትና በተጠና ሁናቴ በማሰለም( በቁጥር ለመሸፈንና የእስላም ሐገር ለማስባል)፤ ብዙ ገንዘብ በመስጠትና በስራ በማሰማራት ማሰለም፤ በተቻለ መጠን የመንግስትን ስልጣን በመያዝ የመሮጫ መንገዱን ማመቻቸት ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡ እናንተ ግን እነ በጦሩ፣ በጋሻዉ …..እያላችሁ ተነካከሱ

      ReplyDelete
    12. Islams are trying to take others using various strategies and EOTC are chasing out people with silly mistakes. We know how to push people out of the church and they know how to fish people...that is the main reason...I TELL YOU WILL DIMINISH MORE UNLESS WE HAVE STRATEGIES TO SOLVE OUR INTERNAL PROBLEMS BY FAR BETTER THAN CHASING PPL OUT!

      ReplyDelete
    13. አረ ሰዎች የምናልመውና የምናደርገው እኩል ይሁን፡፡ ርእሳችሁ አንድ አድርገን የሚል ነው የምታስተላልፉት ግን ለያየን የሚል ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሁሉም የሰው ልጅ እኩል ነው እና አደራ፡፡ የሚለያይ ነገር ባታስተላልፉ፡፡

      ReplyDelete
    14. What is written here is revelation of truth. None of what is said is wrong. It is not fair to be emotional about the article and say it is a lie. The fact of illegal or unfair construction of mosques is supported by evidences. We should work for revealing hidden agendas of those religious institutions who try to mask the truth.

      ReplyDelete
    15. ሰላም ለእናንተ "አንድ አድርገኖች" ስላስቀመጣችሁት መረጃ እግዜር ይስጥልኝ በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው፡፡ በተለይ በእስልምናው ጉዳይ ላይ የሰፈረው ማለቴ ነው እንደው ፈቃደኞች ብትሆኑ እና አንድ አስተያየት ሰጪ እንደጠቆመው መፍትሄ ሊሆን የሚችሉ ሃሳቦች ቢጤ ለመሰንዘር ነው እንግዲህ (አድሚኖች) ገምግማቸሁ ታሳልፉታላችሁ ወደ ዋናው ሃሳቤ ልግባና በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእስልምናን ጉዳይ ቀረብ ብዬ ለማየት(ለማጥናት) እየሞከርኩ ነው ለዚህ ጠቃሚ ሆኖ ያገኘሁት የእነሱኑ መጽሐፍ ምን እንደሚል ማንበብ እስላም ምን? እንደሆነ መሐመድ ማን? እንደሆነ ማወቁ አስፈላጊ ነው የሙስሊሞች ችግር መጽሐፋቸው እና መሐምድ እንደሆን ተግንዝቤአለሁ እንደኔ እንደኔ እናንተ አድሚኖች የእስልምና አክራሪዎች ይህን አደረጉ ይሄን ሰሩ ከምትሉ ስለ እስልምና እውነተኛ ገጽ ምእመናንን አስተምሩ ምነው እነሱ በየ መስጊዳቸ ክርስትናን እና ክርስቶስን እያጣመሙ ያስተምሩ የለ? ለዚህ ጠቃሚ የሆነ መረጃ ያለው በአማርኛ የተዘጋጀ የመጽሐፍቅዱስ እውቀት ባላቸው እስልምና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሆነ በክርስቶስ እየሱስ ላይ ለሚያነሳቸው ማንኛውም ጥያቄ ተገቢ መልስ የሚሰጡበት ድረ ገፅ ልጠቁም እወዳለሁ http://www.answering-islam.org/amargna.html (ለእስልምና መልስ) የሚለው ገጽ ነው፡፡
      ሌላ ለማለት የምፈልገው ነገር የእስልምናን አይዲዮሎጂ ለመቃወምም ሆነ ለመዋጋት መፍትሄው ኦርቶዶክሳዊያኑ ወንጌላዊ አማኞችን መናፍቃን በመባባል የትም አይደረስም በነገራችን ላይ ሁሉም ክርስትያኖችም አይሁዳውያንም አምላክ የሌላቸውም ሁሉ ለቁርአኑ አላህ ከሃዲዎች እምነት የለሾች እንደሆኑ ታውቃላችሁ እስኪ የራሳቸው መጽሐፍ ምን እንደሚል ተመልከቱ "ቁርአን (አል-ተውባህ) ምዕራፍ 9፡ 29“ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን አላህ እና መልእክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው”
      ተመልከቱ እኛኑ ከሃዲ አምላክ የለሽ የተባልነውን ነው አላህ ተዋጉአቸው ብሎ ያዘው ድግሞስ ዛሬ አክራሪ ተብለው የሚጠሩት ከሃዲዎችን ቃፊሮችን እንዲገድሉ ፈቃድ እንደሰጣቸው እንዲህ ይላል "12. Mohammed said, "No Muslim should be killed for killing a Kafir" (infidel). Saih Al Bukhari Volume9 book 83 Number 50."ከሃዲዎችን(ቃፊሮችን) የሚግድል ሙስሊም ሊሞት አይገባውም" እንግዲህ ለእስላሙ ኦርቶዶክስ ይሁን ፕሮቴስታንት ወይም ተሀድሶ ወይም ካቶሊክ ወይም ባህላዊ ሃይማኖት ተከታይ ሁሉም ከሃዲ ነው(ቃፊር ነው)፡፡ "ክርስትያኖች፣ አይሁዶች እና ጣዖት አምላኪዎች በመሐመድና በቁርአን የማያምኑቱ በሲዖል ውስጥ ለዘላለም ይቃጠላሉ እነሱም በምድር ላይ ካሉት ፍጥረታት ይልቅ እጅግ በጣም አስከፊዎቹ ናቸው 98.6፡፡" እነዚህ እንግዲህ ከላይ ያነሳሁአቸው ለምሳሌ እንዲሆኑ ነው ስልዚህም ወዳጆቼ የመሐመድ ተከታዮች ኦርቶዶክስ ወንጌላዊ አማኝ ወይም ሌላብለው ለይተውሳይሆን በአንድ አይን እንደምንታይ አትርሱ ሁለችንም ለእነሱ(ቃፊሮች)ነን፡ በኦርቶዶክስ፣ በወንጌላዊ አማኞች፣ በኦቶዶክስ ተሃድሶ በካቶሊክ መሰረታዊ የክርስትና እውነቶች ያስማሙናል እና ልዩነታችንን በመወያየት እናጥብብ እላለሁ በሌላ አስተያየት እስክምንገናኝ ሰለም ሁኑልኝ፡፡
      አንድ ሰው ነኝ

      ReplyDelete
    16. let us stop blaming each other

      ReplyDelete