Thursday, December 1, 2011

‹‹ሐጥያታችንን አጽድቁልን›› ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ


 • አዲስ አበባ ላይ ሊደረግ የታሰበው ስብሰባ ያለምንም እንቅፋት እንደሚካሄድ ለማወቅ ችለናል::
 • አዲስ አበባ ቢሮ ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው ሁላ ሰምተናል፡:
 • መንግስትም ይህን ሁሉ በማድረግ ረብጣ ዶላር ከምዕራባውያኑ በብዙ መልኩ ሊያገኝ ይችላል::
የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል የግብረ ሰዶም ሕጋዊነት መጽደቅ ምክንያት በማድረግ  ህዝባዊ ፌሽታ

(By Zelalem Mengestu ):- የሰውን ዘር በእግዚአብሔር ቁጣ ያስጠፋው፤ከኃጢያት ሁሉ የከፋው ኃጢያት፤ለባሕሪ የማይገባ ፤የእግዚአብሔርን የቁጣ ጽዋ ቶሎ የሚሞላ፤ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው በተሰጡ ሰዎች የሚፈጸም የኃጢያት ቁንጮ፤የዘመናችን ሕጋዊ ኃጠያት እየሆነ ከመጣ ዘመናትን ያስቆጠረ ቢኖር ግብረሰዶማዊነት ነው። ዛሬ ዛሬ በአለማችን ስለግብረሰዶምነት ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ማህበራት፤የሃይማኖት አባቶች ነን ባዮች፤ፓለቲከኞች..ብዙ ብዙ..ተፈልፍለዋል።በዚህ ዘመን በአንዳንድ አገሮችና አብያተ ክርስቲያናት ለምሳሌ በአለምና በተለያዩ አገሮች ያሉ የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተሰይጣን ውስጥ ያሉ ምእመናን መሪዎቿ በዚህ ተግባር ውስጥ ተሳታፊ መሆናችውና እውቅና እየተሰጣቸው መምጣቱን ምን ያህል አለም እንደረከሰች እናያለን።


ብዙ ወንዶችና ሴቶችም በተለያዩ ሀገራት በአደባባይ ላይ ያለ ኃፍረት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፤ለመንግስታትንም ኃጢያታቸውን እንዲያጸድቁላቸው አቤት ብለዋል፤ተማጽነዋል።በዚህ ትግል በአንዳንድ ሀገራት ድምጻቸው ተሰምቶ መንግስት እስከ ማጽደቅ ደርሷል።ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ካነሳሳኝ ነገሮች አንዱ ታሪካዊ የሆነችው የኒውዮርክ ከተማ ይህንን ኃጢያት በአደባባይ እንደፈቀደችና እንዳጸደቀች ካየሁኝ በዋላ ነው።ወትሮም ቢሆን በብዙ ቱሪስቶች የምትጎበኘውና ሁልጊዜም የቀለጠችው ከተማ የምትባለው ኒውዮርክ ከትናትና ሌሊት ጀምሮ ግን አዳሯም ሆነ ውሎዋ የተለየ ሆኖ ነበር።ከራቁት ባልተናነሰ ትንሽ ጨርቅ ሰውነታቸው ላይ ጣል ያደረጉ ሴቶች፤በየጥጋጥጉ እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሳሳሙት ወንዶች፤ኸረ ስንቱ....... ከተማዋን በጩኸትና በጭፈራ ሲያቀልጧት ነበር።ይህም ለብዙ ግዜ ሲያከራክር የቆየው የግብረ ሰዶም ሕጋዊነት መጽደቅ (መታወጁ)ምክንያት በማድረግ ነው።ከ52ቱ የአሜሪካ ግዛቶች ኒውዮርክ ግብረ ሰዶምን በማጽደቅ 6ኛውን ደረጃ ይዛለች። New York moves to become 6th state to legalize gay marriage ይህን ሳይ ነበር በአንድ ወቅት አንድ አዝማሪ ያለችው በእምሮዬ የመጣው

''የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
አለህም እንዳልል እንዲህም ይደረጋል".

ግብረሰዶም የቃሉ ፍቺ እንደሚያስረዳው የሰዶማውያን ሥራ ማለት ነው።ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ሲሆኑ አብርሃምና ሎጥ በአገልጋዮቻቸው ምክንያት ለመለያየት ሲወስኑ ሎጥ ወደ ሰዶም እንዳቀና በሰዶምም እንደኖረ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።በሰዶም ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በዝሙት ኃጢያታቸው የሚታወቁ ሲሆኑ በተለይም ደግሞ ወንድ ከወንድ ጋር ይገናኙ ስለነበር ግብረ ሰዶም የሚለው ስያሜ ከዚህ መጣ፤ሰዶማዊነት ወንድ ከወንድ ጋር ሴት ከሴት ጋር የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ነው።በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ይህቺን የኃጢያት ከተማ በዲን እሳት አጥፍቷታል (ዘፍ18-19)
.
የሰዶም ኃጢያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ የተወገዘ ኃጢያት ነው(ዘፍ19-1-29)ይኸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ የሆነ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ነው።ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ላይ ይህን ተግባር ''እስነዋሪ''..''ለባሕሪ የማይገባ'' እንዲሁም ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ በማለት ይገልጸዋል።(ሮሜ 1-24-48) ዛሬ ግብረ ሰዶም ለሚፈጽሙ ሰዎች የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ እሳት ከሰማይ በመላክ ሳይሆን የማይገባቸውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ(ለፍትወት)አሳልፎ በመስጠት ነው።...''ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሰሩ....የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም..''(1ኛቆሮ 6-9-11)

ክርስቲያኖች አለማችን በሚያሳዝኑ ተግባሮች እንደተሞላች ስንቶቻችን አስተውለን ይሆን? ዛሬ ሰዶምና ገሞራ የሚባሉት እነዛ ስማቸው ገኖ የነበሩት ከተሞች ለሕዝብ የሚታዩ አይደሉም።በሙት ባሕር ደቡባዊ መጨረሻ ላይ እንደተቀበሩ አርኪዎሎጂስቶች ይናገራሉ።እናሰተውል ይህ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ተግባር ያለውን ጥላቻና በተመሳሳይ ጊዜ ፍርድን ለማስተላለፍ ያለውን ትዕግስትና ፈቃደኝነት በግልጽ ያሳየናል።አለም ዛሬ በዚህ ተግባሯ ምን ያህል ከእግዚአብሔር ጋር ቅራኔ ውስጥ እንደገባች ተመልከት።...ስለዚህ.ሰውነታችንን ከሚያረክሱ አለማዊ ምግባሮች አርቀን አንደ ሎጥ ነፍሳችንን ከኃጢያት ጋር ሳንተባበር ለጽድቅ አስጨንቀን፤ሁልጊዜ ልባችንን ለእግዚአብሔር መንፈስ ሰጥተን እንኑር፤በአለማዊ ሕይወት የተስተካከለ ሕይወት መምራት የሚቻለው ይህን ስናደርግ ብቻ ነው።
መዓቱን በምሕረቱ
ቁጣውን በትዕግስቱ ያስታግስልን
 ዲ/ን ዘለዓለም መንግሥቱ
(አንድ አድርገን ህዳር 22 2004)፡- አሁን እኛ ባለን መረጃ መሰረት አዲስ አበባ ላይ ሊደረግ የታሰበው ስብሰባ ያለምንም እንቅፋት እንደሚካሄድ ለማወቅ ችለናል ፤ ድንገት ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ግን ላይካሄድ ይችላል የሚል ወሬ አለ ፡፡ መንግስትም ምንም አይነት የህዝብን ተቃውሞ ላለመስማት ጥበቃውን ከህዝቡ በሚበልጡ ፌደራል ፖሊሶች ለማስጠበቅ ፤ ያለእንቅፋት እንዲከናወን ወገቡን ታጥቆ እየሰራ ይገኛል፡፡ በእኛ ሀሳብ የዘመናችን መጨረሻ መጀመሪያ ይመስለናል ፡፡ 

 በቂርቆስ አካባቢ ያለው ፖፑላሬ ፖሊስ ጣቢያ ወንድ ልጆቻችን ተደፈሩብን የሚል ክስ በየጊዜው ይደርሰዋል ፤ አደረጉ የተባሉትን ሰዎች ግን እጅ ከፍንጅ ለመያዝም ሆነ ጠርጥሮ ፍርድ ቤት ለማቅረባ ሳይችል እንዲህ ናቸው ብሎ ያሰባቸውን ሰዎች በማስፈራሪያ ከማለፍ ውጪ ምንም ተጨባጭ አስተማሪ የሆነ ነገር ሲሰራ ለማየት አልቻልኩም ፡፡ ይህን ምግባር ፍርድ ቤት ድረስ እንዳይሄድ የሚያደርገው አንዱ አክል ደግሞ ልጆቹ ነገ የሚኖራቸው ስብዕና ላይ የሰዎች መጠቋቆሚያ እንዳይሆኑ ቤተሰብ ከፍተኛ ፍራቻ ስላለው ጭምር አደጋው ደርሶባቸው እንዳልደረሰባቸው ዝምታን የመረጡ እናቶች መብዛት ነው፡፡ ድርጊቱ በየክፍለ ከተማው ያሉ የፖሊስ መዛግብትን ለአንድ ሰሞን አጣቦት ነበር ፤ ለመክሰስም ለመከሰስም የማያመች አጸያፊ ተግባር መሆኑን ከአቃቢ ህግ ሰዎች ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ችግሩ በስፋት አለ ፤ መፍትሄው ግን ምን ሊሆን እንደሚችል ማንም ያመላከተን ማንም ያሳወቀን የለም

 የዛሬ አመት አዲስ አበባ ላይ ያሉትን ራቁት ዳንስ ቤቶች የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጸጥታ እና ደህንነት ጋር በመተባበር በአንድ ቀን አሰሳ በማድረግ ውስጥ የተገኙትን ሰዎች የማፈስና የማሰር ሂደት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እነዚህ ቤቶች ውስጥ እንደተገኙ እና ከፖሊሶች ጋር ትንሽ ግብግብ እንደፈጠሩ የዘሬ አመት ትውስታችን ነው፡፡ አሁንም የዚህ የግብረ ሰዶማውያን ስብሰባ ፍላጎት የፈረንጆቹ ብቻ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ የኛዎቹም ባለስልጣናት እዚህ አስነዋሪ ሀሳብ ውስጥ የሉበትም ፤ ደርሶም አይነካካቸውም ብዬ በሙሉ አፌ መናገር አልችልም ፤ ስብሰባው በሰላም ይካሄዳል ፤ የአቶ በረከት ስምኦን ቢሮ አልተካሄደም ብሎ የለመደውን ማስተባበያ ይሰጣል ፤ የነገ ሰው ይበለን ሁሉን የምናየው ነገር ነው ፤ ከባለስልጣኖቻችን ውስጥ ማን ተወክሎ ስብሰባውንም እንደሚካፈል ለማወቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ይበቁናል ፡፡

 ከዚህ ስብሰባ በኋላ ግብረሰዶማውያኑ አዲስ አበባ ቢሮ ለመክፈት እቅድ እንዳላቸው ሁላ ሰምተናል ፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን እኛ ላይ ለመጫን ስለሆነ አላማቸው የሚሰሩበት ቢሮ ግድ ይላቸዋል ፤ ነገሩን መሬት ለማውረድ ፤ አፈጻጸሙን ለመከታተል ፤ ህገመንግስታችን ውስጥም ሊከቱልን ስለሆነ ሀሳባቸው ቅርንጫፍ መስሪያ ቢሮ ያስፈልገናል ብለዋል ፡፡ መንግስትም ይህን ሁሉ በማድረግ ረብጣ ዶላር ከምዕራባውያኑ በብዙ መልኩ ሊያገኝ ይችላል ፤ ይህን ሀሳብ ከዴሞክራሲ ጋር በማቆራኝት ይህ የሰዎች የግል መብታቸው ነው ብለው ያስባሉ ፤ ይህ ሂደት ግን ከባድ ተቃውሞ ይገጥመዋል ብለን እናስባለን ፤ እኛም ሳንቀንስ ሳንጨምር የሆነውን የተደረገውን ፤ የታሰበውን ፤ ሁሉ እናንተ ጋር እናደርሳለን፡፡

9 comments:

 1. ይህ ድርጊትከተፈጸመ መሆን ያለባቸውን እንደሚከተለው ልበል
  ስብሰባው ላይ የተገኘውን ባለስልጣን መለየት ከዚያም በእርሱ እና በቤተሰቦቹ ላይ የማግለል ስራ መስራት
  የጤና ሚኒስትሩን እስካሁን በጤናው ዘርፍ በተለይም በጤና ኤክስቴንሽን ሰፊ ስራዎች ቢያሰሩም በአንድ ቀን ውድቀት በቃ ሊባሉ ይገባል
  መንግስት ለእኛ ለኢትዮጲያዉያን የቀረንን ነገር-በባህላችን መኩራት ላይ ውሃ ሊቸልስበት በመነሳቱ በቃህ ሊባል ይገባዋል፡፡በተለይ ስንራብ፤ስንጠማ ምንም ያላልንውን ይህ አጸያፊ ድርጊት ከተፈጸመ ግን ዝም የሚል አዕምሮ እንደማይነ ቀድሞ ይወቀው፡፡አሸባሪነት ከዚህ መሰል አጸያፊ በደል ይመነጫል፡፡

  ReplyDelete
 2. ‹‹አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈን በመአትህ አትገስጸን…›› እኛ ኢትዮጵያውያን እኮ ሃይማኖት ያለን ባይሆን እንኳን ምርጥ የሆነ ስብዕና ያለን ህዝቦች ነን እንዴት ነው መንግስት እንደዚህ ያለ ነገር ሲደረግ ዝም የሚለው! ይህ ምን አልባት የዝቅጠቱ መጨረሻ እንዳይሆን ቢጠነቅቅና ቢያስቆም የተሻለ ይመስለኛል፡፡ አለበለዚያ ሊመጣ ያለው ነገር አደገኛ ይሆናል መንግስት ቢያስብበት ይሻላል ፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆነ ከኛው አብራክ የወጣ መንግስት ከሆነ በእርግጥ ይህንን ነገር ይቃወማል እንጂ አይደግፍም! ስላሰብንም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን፡፡ ከሆነ ግን …
  አብነት ከሆሳዕና
  ‹‹አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈን በመአትህ አትገስጸን…›› እኛ ኢትዮጵያውያን እኮ ሃይማኖት ያለን ባይሆን እንኳን ምርጥ የሆነ ስብዕና ያለን ህዝቦች ነን እንዴት ነው መንግስት እንደዚህ ያለ ነገር ሲደረግ ዝም የሚለው! ይህ ምን አልባት የዝቅጠቱ መጨረሻ እንዳይሆን ቢጠነቅቅና ቢያስቆም የተሻለ ይመስለኛል፡፡ አለበለዚያ ሊመጣ ያለው ነገር አደገኛ ይሆናል መንግስት ቢያስብበት ይሻላል ፡፡ ኢትዮጵያዊ የሆነ ከኛው አብራክ የወጣ መንግስት ከሆነ በእርግጥ ይህንን ነገር ይቃወማል እንጂ አይደግፍም! ስላሰብንም እግዚአብሔር ይቅር ይበለን፡፡ ከሆነ ግን …
  አብነት ከሆሳዕና

  ReplyDelete
 3. ለጥቂቶች ሲባል ማንነታችን እንዲህ ይዋረድ?

  ReplyDelete
 4. ይህ ክርስትያን ሆነ እስላም የሀይማኖት አባቶችን ይመለከታለ አባቶች ባካችሁን ዉጥ ለምነታቹ ሙት

  ReplyDelete
 5. yegnawe meriwoche lalemehonachewe wastenaw menedenewe

  ReplyDelete
 6. ቸሩ፡አምላክ፡ከዚህ፡ሁሉ፡ይሰውረን፡፡እነዚህን፡የዲያቢሎስን፡ግብር፡የሚያራምዱትን፡በሙሉ፡ካገራችን፡ነቅሎ፡ያውጣልን፡፡ኢትዮጵያ፡አገራችንን፡ይጠብቅልን፡፡
  እባካችሁ፡የተቃውሞ፡ድምጻችንን፡የምናሰማበት፡መንገድ፡ካለ፡ብትገልጹልን፡፡
  እመቤታችን፡ተራጂን!!!

  ReplyDelete
 7. Sbsebaw Betebaberut yemesebsebiya adarash be room no.6 eyetekahede new yalew. Zare bequtr berket blew ymtu enji pre conference teblo yetejemerew 01 Dec.2012 new. Yejemeru elet mnm aynet tbeqa alneberachewm, betlantnaw elet gn mengst 2 dehnnet medbo siyastebq neber. Dehnnetochu metew meqomachewn enji, mann endemitebqu enka ayawqutm. Zarem yradio communication yalew 1dehnnet eyetebeqachew new. Eskahun gn andm Ehiopiawi besbsebaw lay aletegegnm.

  ReplyDelete
 8. set gulbet alatena ebakachun yebaleseltan mistoch yehenen hatiyate askumelen aleya yemimetawe kuta anameltemena new!!! nebx

  ReplyDelete
 9. lehatian yemeta letsadik yiterfal yemibalew neger ewenet new silezi wendimoch ehitoch enezih gena kahunu matifat new enji ende sodom gomora esatina din kesemay esikizenb meteberk yelebinim

  ReplyDelete