Tuesday, December 13, 2011

ቀኖናውንና ስርዓተ ቤተክርስትያንን ያፈረሰው ማን ሆነና ?

በቅርቡ የደረሰን ደብዳቤ እንደሚያመለክተው አባ ፋኑኤል እኔ በሕጋዊ መልኩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወክዬ የመጣሁ ወኪል ነኝ ካሉ በኃላ፣ በመቀጠል በተለያዩ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለሚገኙ ይልቁንም በገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ ልከዋል፥ ደብዳቤው እንደሚያብራራው ‹‹እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን (ደብር) ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ ሃይማኖት እንዳይበረዝና ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ እንድንመካከር አብረን ተነጋግረን ልንሰራ የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት›› በሚል ይጀምራል። በመቀጠል ‹‹የደብራችሁ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን›› ይላል። ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ


ለመሆኑ አባ ፋኑኤል ሥርዓት ለማስጠበቅ እና ቀኖና እንዳይፋለስ ብለው የሚሉት የትኛውን ሥርዓት ነው ? ቀኖናውንስ ቢሆን ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ አይደለም እንዴ ሥራቸውን እየሠሩ ያሉት?  እስቲ እነዚህን ነጥቦች እናንሳና እንያቸው፡

. በመጀመሪያ ‹‹የየደብራችሁ መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ›› ብሎ ማቅረብ ምን ይሉታል? ይህ ነገር  በርሳቸው መዝገብ ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያን መመሪያዋም መተዳደሪያዋም ቃለ ዓዋዲዋ ነው ፤ ይሄንን ደግሞ ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባቸዋል።

፪. በደብዳቤያቸው ላይ እንደገለጹት "በመራራቅ ሳይሆን በመቀራረብ፣ በቅያሜ ሳይ በይቅርታ በጋራ እንሠራ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ" እንዳሉት ጥሪውን ለነማን ይሆን ያቀረቡት ? በእውነት ጥሪውን ለሁሉም አድባራት እና አጥቢያ አድርሰው ይሆን? እስከ አሁን ባለን መረጃ መሰረት ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት እራሳቸውም በገለልተኛ አስተዳደር ሥር ነን ለሚሉ አጥቢያዎች ብቻ ነው። ነገር ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተመሠረተው የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ 17 የሚጠጉ አጥቢያዎች ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረሳቸው ተረድተናል። ታዲያ አባ ፋኑኤል አላማቸው ምን ይሆን ? ገና በፊት እናት ቤተ ክርስቲያንን ብለው በሀገረ ስብከቱ ስር በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ ያሉትን አጥቢያዎች ወደ ጎን ትቶ በገለልተኛ አስተዳር ስር ነን ብለው ራሳቸው በሰየሙትና ከቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ውጪ የሆኑትን አድባራት ብቻ ኑና ልባርካችሁ ፤ አባት ልሁናችሁ ማለት ትክክለኛ አካሄድ ነውን? እሳቸው ተወከልኩ ያሉት ከቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ጥሪ እያቀረቡ ያሉት ደግሞ ለገለልተኞቹ እና ዋናውን  ሲኖዶስ ለማይቀበሉት ፡፡


. ገና ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመግባታቸው ራሴ የሰራሁት ቤቴ ነው ፤ ማንም ሊከለክለኝ አይችልም ፤ በሚል ፈሊጥ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደ ግል ንብረት ማየታቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ መንበረ ጵጵስናዬ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ነው ፤ ማለታቸው ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነው። አባ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናቸውን በደብረ ምሕረት ማድረጋቸው ባልከፋ ነበር፣ ችግሩ ግን ደብሩ ከምሥረታው ጀምሮ እራሱን በገለልተኛ አስተዳደር ስር ነኝ ከሚሉት አጥቢያዎች አንደኛውና ግንባር ቀደሙ እንደሆነ ይታወቃል እንደውም የገለልተኛ ዋናው መሥራቹና አቋቋሚው እርሳቸው መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ስለሆነ ወደ እዛኛው ርዕሰ ጉዳይ አንገባም፥ ታዲያ ይህንን አጥቢያ ይልቁንም የግሌ ነው የሚሉትን በገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ አስቀምጦ እኔን ግን ቅዱስ ሲኖዶስ የላከኝ ሕጋዊ ወኪል ስለሆንኩ መንበረ ጵጵስናዬ በገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ ባለው ደብረ ምሕረት ነው ማለት የት ድረስ ሊያስኬድ እንደሚችል አባ ፋኑኤል የሚያውቁት ጉዳይ ይመስለናል።

፬.  እስከ አሁን ባለን መረጃ መሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ ተልከው የመጡት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ምሥራቅ ሐረርጌ ከሚሄዱት ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አለማድረጋቸውስ? እንደ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑማ መጪው ሊቀ ጳጳስ፣ እንደመጣ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ተገናኝቶ ጅምር ሥራዎችን፣ እቅዶችን፣ ችግሮችን እና በመሳሰሉት ላይ ንግግር ካደረገ በኃላ ሌላ ሰው እማኝ ተደርጎ የጽ/ቤት እቃዎች እና ንብረቶች ዝውውር ይደረጋል ነገር ግን እንዲህ አይነት ሕጋዊ ሥራዎችን አባ ፋኑኤል የማይገልጉት ወይም ሥርዓትን ከሚያፈርሱ ወገን መሆናቸውን በግልጽ ያሳየ እንደሆነ እንገነዘባለን። 

፭.  በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ያለው "የውጪ ግንኙነት ክፍል" በመባል በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ትዕዛዝ የተከፈተው በአስቸኳይ ሥራውን እንዲያቆምና ከሕገ ቤተክርስቲያን አንጻር ኢ-ቀኖናዊ እንደሆነና እንዲዘጋ ቢወስኑም አባ ፋኑኤል ግን በተለመደው ማን አለብኝነታው አሁንም ከጽ/ቤቱ ጋር በቅርብ እየሰሩ እነደሆነ ጠቋሚ መረጃዎች ደርሰውናል። 

እንደ እስሳቸው አባባል ሥርዓት ልናስጠብቅ ቢሉም ነገር ግን ሥርዓት እያፈረሱ ያለበትን አካሄድ አጥብቀን እንቃወማለን፣ ቤተ ክርስቲያን መገለጫዋ ሥርዓቷ፣ ቀኖናዋ ፣ እና ትውፊቷ ናቸው ፡፡ ነገር ግን እነዚህን የቤተክርስቲያን መገለጫዎች የምንላቸውን ወደ ጎን እየገፉ ሥርዓት ልናስከብር ነው ቢሉን ራስን እንደማታለል ነው የምንቆጥረው።

በአዋሳ ሲያደርጉ እንደነበረው አሁንም በካሊፎርኒያ እና በዋሽንግተን ያሉትን ምዕመናን እናንተ ከኛ ወገን አይደላችሁ ፤ በማለት ሥራቸውን ጀምረዋል ነገር ግን መጨረሻቸውን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነት ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሚሆን ከወዲሁ ለማየት ይቻላል። ምክንያታቸውም አንድና አንድ ነው ፤ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት እና ቀኖና ማፍረስና የራሳቸው መጠቀሚያ፣ በክበሪያና መበልጸጊያ ለማድረግ የተነሱ ለመሆናቸው እነዚህ ከላይ የገለጽናቸው ነጥቦች በቂ ማስረጃ ይሆናሉ ብለን እናምናለን።

ቸር ይግጠመን

ከመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ የተወሰደ

10 comments:

 1. This seems jealousy! We know what he has been doing in Hawassa. Let's give Him another chance. This is a good start. please stop hair splitting and be optimistic! Who knows He might change!

  ReplyDelete
 2. ክርስቶስ አለምን የሰበከዉ በስድብ በመግድል በማንገላታት ነበር ወይ
  እዉነት የሚነገረዉ በቅንነት ብቻ ነዉ
  2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ2፥15
  የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ

  እዉነት ደግሞ ክርስቶስ ብቻ ነዉ
  የዮሃንስ ወንጌል14፥6
  ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም

  ይህንን የማይቀበል በትልቅ እስራት ዉስጥ ይኖራል

  የዮሃንስ ወንጌል 8፡ 32 እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።

  ስለክርስቶስ ሲነገር ስለምን ያንገበግባችሁሃል

  የዮሃንስ ወንጌል 8፥40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ
  8፥44
  እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም።

  ReplyDelete
 3. አንድ አድርገን ከምትሉ እንለያይ በሚል ስማችሁን ለውጡ። አለበለዚያ እናንተ ያልፈለጋችሁት ሁሉ የተወገዘ ነው ያለው ማነው? ስለቤተክርስቲያን አምላክ ጥላቻ ይቁም!

  ReplyDelete
 4. You guys! It looks unchristian to write such very biased and unfair blamings on other people. Abune Fanuel may have problems as it has been discussed previouly. But the way you write this article wrong. I don't know what is the target behind this article. It doesn't give me sense.

  ReplyDelete
 5. As to me nothing is behind of this article.I believe that, A man who is educated very well, adult or old enough,made mistakes knowingly for his purpose, advised by the responsible authority but didn't accept can never be changed.If u think Abune Fanuel didn't know kenona,dogma and tiwfit of EOTC,& i.e why he made mistakes, I will accept the above comments he is not baby he knows very well mistakes he did are wrong if he is a right father do u believe that he did these mistakes knowingly? but I believe that if such peoples are in side our church,the solution to protect our selves deviating from orthodox & the church from these peoples should be posted.

  ReplyDelete
 6. ለምን ይዋሻል?

  አንድ አድርገኖች ለምን ትዋሻላችሁ?

  ካቀረባችሗቸው ውሸቶች ውስጥ
  1 “የደብራችሁ መተዳደሪያ እንደተጠበቀ…አሉ” ላላችሁት ፣ በመሠረቱ እንዲህ ማለታቸው በቦርድ አስተዳደር ስር ያሉትን የሚያቀራርብ እንጅ እናንተ እንዳላችሁት ማራቅ አይደለም ። በውጭ ያሉትን ማቅረብ የሚቻለው እኮ በእንደዚህ ዓይነት አቀራረብ እንጅ ፡ “ዕኛ ያልነውን ካልተቀበልህ ገደል ግባ” በማለት አይደለም ። ለፖለቲከኞችና ለግል ጥቅመኞች መጫወቻ እንደሆኑ ይቅሩ ብሎ ማሰብም ከክርስቲያን ነኝ ባይ የሚጠበቅ ተግባር አይደለም ።

  2.ሀገረ ስብከታቸውን በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማድረጋቸው ያስመሰግናቸዋል እንጅ አያስነቅፋቸውም ። እኔን የሚገርመኝ ፡ የራሳቸውን ትተው ወደ ሌላው እሄዳለሁ ቢሉ ነበር ። ሰርተው ለቤተ ክርስቲያኗ ማስረከብ ደግሞ ያስመሰግናል እንጅ አያሰነቅፍም ። እኔ ሰራሁት አሉ እንጀ የኔ ቤት አላሉም ፡ ለምን የሰው ስም ታጠፋላችሁ ?

  3.የተሾሙበትን አባሪ አድርገው የላኩት የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤም፣ ለሁሉም ቤተ ክርስቲያኖች ደርሷል ፡ በቂ መረጃ ከሌላችሁ እንደገና ማጣራት ይኖርባችሗል ፡ ዝም ብላችሁ ስም ለማጥፋት ፈልጋችሁ ከሆነ ግን ፡ ሌላ ጉዳይ ነው ። ግን በእግዚአብሔር ስም መዋሸት ትልቅ ሃጢአት መሆኑን አትርሱ ። ራሳችሁን ከሚከፋፍላችሁ በቀር ፣ የቡድን ስሜት የትም አያደርሳችሁም ።

  4፣ “የውጭ ግንኙነት” ተብሎ የተከፈተውን ጽ/ቤትም ፡ ቅ/ሲኖዶስ ፡ ከሶስቱም አህጉረ ስብከት ጋር አብሮ እንዲሠራ እንጅ ፡ እንዲፈርስ አልተወሰነም ። ማንን ለማሳሳት ነው የምትሞክሩት?

  ስለ አዋሳ የምናውቀው ምንም ነገር የለንም ። እኛ ያለነው አሜሪካ ነውና አብረን ተቀራርበን እየተመካከርን ለመሥራት እንሞክራለን ። ከዛ የሁሉንም ውጤት በሂደት እናየዋለን ።

  ReplyDelete
 7. እውነትን እውነት በል ሀሰትንም ሀሰት በል፡ ይህ ነውና የኣባቶችህ ቃልኪዳን!!!

  ReplyDelete
 8. besimesilase ahadu amilak amen

  selam lehulachihu yihun

  mechem mereja lehizibu beyegizew madiresachihu balikefa nebere neger gin akahedachihu simeleketew yeselam sewoch atimesilinim mikiniyatum yeselam meniged bilich sil lemezigat new yemitirotut

  einide eiwunetu kehone beahunu seat siriate betekirisitiyanin eiyaferesu yalut abune abiriham nachew 20 ena 30 sew keye betekirisitiyanu genitilew yeeigiziabiherin tabot mekeleja eiyaderegut yalut eisachew naCHEW BENEGERACHIN LAYI ABUNE FANUELIN TIKIKIL NACHEW EIYALIKU AYIDELEM lemehonu abune abiriham ketezaweru behuwala leminidinew besew hagere sibiket betekirisitiyan yemikefitut ? abune fanuelin addis yetegeza betekirisitiyan yale hageresibiketachew bareku eiyalu sikesu nebere beanid eiras hulet milas malet yihe new

  lemehonu sinit amet lemenor new? yihini talak maeireg eiyakalelut yalut beeiwunetu leabatochachin liniseliyilachew new yemigebaw zare kenesugara tifozo honen abiren siriat yeminafalis hulu anid ken yeminiteyekibet einidehone binawukew tiru new

  yeselam amilak bemihiretu yimeliketen

  ReplyDelete
 9. Dis respecting a pop who is appointed by the holly synod is not only a sin but also is not a character expected from an Orthodox Christians. We are known for respecting people let alone our fathers. I think that there is an organized effort to make us disrespect our 'Tiwift' such as respecting our fathers. If we start insulting the pops how can we be sure that we will not insult saints tomorrow ? Let us all join together and pray to God to save our chruch!

  ReplyDelete
 10. አነድረግኖች ስም ጥፊዎች ክፋፋች እዚህ ራግቡ ራግቡ አሁን ድግሞ ዝምቱ ምን እግዚብሄር ታልብን ነክረሳዎች ናችሁ አባቶች ብርቱና ይህንን ጋኔል ክቤተ ክርስቲያን በጸሎት አውጡልን ህዝብሆይ እንጸልይ ይተወንም እና ጌታ

  ReplyDelete