Friday, December 23, 2011

‹‹አይሆንም ፤ አይደረግም›› እንበል

(አንድ አድርገን ታህሳስ 13 ፤ 2004 ዓ .ም)፡- እንደ 1999 ቆጠራ በአዲስ አበባ 3,384,569 ያህል ህዝብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ 82 በመቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ፤ 12.7 በመቶ የእስልምና ፤ 3.9 በመቶ  ፕሮቴስታንት ፤ 0.8 በመቶ ካቶሊክ ፤ 0.6 በመቶ ሌሎች የእምነቶችን ይከተላሉ ይላል የመጨረሻው የህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ ፡፡ እንደሚታወቀው አቶ ዐሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከተማ ማስተዳድር ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ 98 አዲስ የመስጊድ ቦታዎች መፅደቅ ችለውና መስኪድ ተሰርቶባቸዋል :: 82 በመቶ በላይ የሕዝብ ብዛት ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 131 ያልበለጡ የአምልኮ መፈጸሚያ ይዞታዎች ሲኖሩዋት በአንጻሩ ከ12.7  በመቶ የማይሞለው ሙስሊሙ ኅብረተሰብ 180 በላይ የአምልኮ መፈጸሚያ ይዞታዎች እንዲኖሩት ተደርጎአል ፡፡ 





 በባሌ በጅማ የተፈጸሙ ግፎችን  በዚች አምስት እና ስድስት ዓመታ ውስጥ መለስ ብለን ስናየው ከጊዜ ወደ ጊዜ ምን ያህል ሸክማችን እየከበደ ፤ ቀንበሩም ወገባችንን እያጎበጠው እየሄደ መሆኑን ያመላክተናል፡፡ በቅርቡ በስልጤ ዞን የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመንግሥት አካል ከለላ ሰጭነት በፈረሰው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ምን አይነት ሁኔታ ላይ እየኖሩ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል ፡፡ ‹የክርስትያን ድምፅ እና የውሻ ጩህት ›› መስማት አንፈልግም ብለውናል ፡፡  እዚች ሀገር ላይ ነገ ያላቸውን ሀሳብ ዛሬ በገሀድና በተግባር ፤ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያየነው እንገኛለን (ቪዲዮውን ለማየት ይህን ይጫኑ) ፡፡ የስልጤው ዞን እንደማሳያ አነሳን እንጂ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በፍራቻ የሚኖረው ክርስትያን ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ  ነው፡፡ ሰዎች የራሳቸውን እምነት በነፃነት  ማስኬድ የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየተደረሰ ያለበት ጊዜ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ጆሯችንን በቴሌቪዥን ያደነቆረን ‹‹የሀይማኖት መቻቻል›› የቱ ጋር ነው ያለው ? በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻል አለን

Islamist vision for Ethiopia



‹‹አይሆንም ፤ አይደረግም›› እንበል
ዛሬ ደግሞ ለመናፍቃኑ የአምልኮ መፈጸሚያ ቦታዎችን ከሕዝቡ የሃይማኖት ስብጥር ጋር ባልተገናዘበ መልኩ በየቦታው ከመስጠታቸውም በላይ በቤተክርስቲያናችን አፍንጫ ስር በመስጠት አይደለም ሰውን እንስሳን  የሚያስደነብረው የመናፍቃኑ የሞንታርቦ ጩህት የአምልኮ ሥርዓታችንን እንዲረብሽ በማድረግ ሆን ብለው ምእመኑ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመራ እየቆሰቆሱ ይገኛሉ::

ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ለመናፍቃን  ተሰጥቶ በሕዝቡ ተቃውሞ ተከልክሎ የነበረው የመናፍቃን ቤተ እምነት ሥራን በደረሰን መረጃ መሰረት እንደ አዲስ ለመሥራት በመንቀሳቀሳቸው የአከባቢው መናን በአሁኑ ሰዓት የተቃውሞ ፊርማ እያሰባሰበ ይገኛለል::

በገጠር የሚገኙትን አብያተክርስትያናትን መጠበቅና ማስጠበቅ አቅሙ ባይኖረን እንኳን እዚህ አጠገባችን የሚሰራውን ነገር መቃወም መቻል አለብን፡፡ ዛሬ ይህን ቆመን የምንመለከት ከሆነ ነገ ከቦታችን ቆርሰው ላለመስጠታቸው ምን ያህል እርግጠኞች መሆን እንችላለን ? ጊዜው ከውጭ ብቻ ሳይሆን የኛ የምንላቸው መሰሪዎች ሆዳቸው አምላካቸው የሁኑት ፈተናቸው የጠነከረበት ፤ መቆማችንን የሚገዳደሩበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ፡፡ ከአባቶቻችን የተቀበልነውን አደራ በአግባቡ መወጣት እንድንችል ሁላችን ስለ ቤተክርስያን እና ስለ ቤተክርስያን ብለን ዘብ መቆብ መቻል አለብን ፤ አይናችን እያየህ በዘመናችን በ10 ዓመት ውስጥ ከ98 መስኪድ ተሰርቷል ፤ ይህን መንግስት አይቶ እንዳላየ ማለፍን መርጧል ፤ አሁን ግን ከቤተክርስትያናችን በ50 ሜትር በማይርቅ ቦታ ላይ የመናፍቃኑን የሞንታርቦ ድምፅ ልጆቻችን እየሰሙ ቅዳሴ እንዲያስቀድሱ መፍቀድ የለብንም ፤ መንግስት ማለት ህዝብ ማለት ነው ፤ እኛም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሌላው የተሻለ የምዕመን ቁጥር አለን ፤ ለሚመለከተው ክፍል አቤት ልንልና ድምፃችንም ሊሰማ  ይገባዋል፡፡

ሀገሪቱ ሀይማኖት ያለውም የሌለውም የሚኖርባት መሆኑን እናውቃለን ፤ ነገር ግን የሀይማኖት ቦታም ሲሰጥ ሊላውን መረበሽ በማይገባ ቦታ መሆን አለበት እንጂ አጠገብ ለአጠገብ ቦታ ሰጥቶ ህዝቡን ወዳልሆነ መንገድ መምራት ተገቢ ነው ብለን አናምንም ፡፡ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያ ስር ሄዶ ቦታ መስጠት አውነት አዲስ አበባ ውስጥ ቦታ ጠፍቶ ነውን? በየክፍለከተማ በሊዝ ለመሸጥ የከተማ መስተዳድሩ ያወጣቸው አያሌ ክፍት ቦታዎች እያሉ ለምን እንዲህ አይነት ቦታ ላይ ለተቃራኒ ለእምነት ተቋም መስጠት አስፈለገ ? ይህ ሊመለስልን የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡

ሌላ ተቃውሞ

በሥፍራው የሚገኙ ነጋዴዎች መስተዳድሩ የነዋሪውን ቅድሚያ የማልማት መብት ሳይጠብቅ ያለ አግባብ ከቤታችን እንድንፈናቀል ተወስኗል፤ ይሄ ደግሞ የህግ አግባብ የሌለውና የእኛን መብት የተጋፋ ጉዳይ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለከተማው መስተዳደርና ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አቅርበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ /ቤትም ነሐሴ 6/2003 በተፃፈ ደብዳቤ፣ አመልካቾቹ የቅድሚያ ማልማት ጥያቄያቸውን ያቀረቡት ስፍራው ቤተክርስቲያኒቱ ከተሰጠ በኋላ መሆኑን በመግለፅ ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ 

የአካባቢው ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቦርድ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ቢያሰሙም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውንና ያለአግባብና ያለ አንዳች ምትክ ቦታ ሜዳ ላይ ሊጣሉ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡


ተሳስሮ ዛሬ ላይ የደረሰው ጉዳይ
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ ስፋቱ 2300 ካሬ ሜትር የሆነውን ቦታ፣ በአቶ አርከበ ዕቁባይ የቦርድ ሰብሳቢነት ከሊዝ ነጻ ቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰጥ አግባብነት የሌለው ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ያልቻለበትን ሁኔታ ሲገልጽ፤ የቦታው አገልግሎት ለቅይጥ አገልግሎት እንጂ ቤተክርስቲያን ያለመሆኑንና ቦታው በዋና መንገድ ላይ የሚገኝና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወንበት ስለሆነ በተፈለገው ፍጥነት ቦታውን ቤተክርስቲያን ማስረከብ እንዳልቻለ በመግለፅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን ደብዳቤ ፅፎ ነበር፡፡ በየጊዜው ከቤተክህነት በዚህ ጉዳይ ላይ የተፃፉ ደብዳቤዎችን በጥቂቱ ኣቅርበነዋል፡፡




ይህንኑ ውዝግብ ተከትሎም የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት /ቤት፤ ለክቡር አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሐምሌ 28 ቀን 2003 . በተፃፈ ደብዳቤ፣ ለኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሊሰጥ የታቀደው ቦታና የደብረ ፅጌ /ዑራኤል ቤተክርስቲያን ያለበት ቦታ እጅግ የተቀራረበ በመሆኑ፣ ካልጠፋ ቦታ የተለያዩ እምነት አራማጆችን በዚህ መልኩ ማጠጋጋት ቤተክርስቲያኒቱ ችግር ብቻ ሳይሆን የመንግስት አካላትንም የሚመለከት ስለሆነ መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስቡ ነበር፡፡ ሀገረ ስብከቱ አሁን ያለው ነገርን ማወቅ ባንችልም

የሚገርመው በጊዜው ሕዝቡ እንደተቃወመ የሚያውቁት ከንቲባ ራሳቸው በድጋሚ መፍቀዳቸው ነው ::እርሶም ለሌሎች መረጃ በማደረስና እውነተኛ የሃይማኖት እኩልነት እንዲረጋገጥ መንግሥት በባለሥልጣናቱ  በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚደርሰውን ተጽእኖ እንዲያስቆም ለማድረግ የበኩልዎን ክርስቲያናዊ ግዴታ እንዲወጡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን ::

የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ በእኛ ዘመን "ዳሩ ሲደፈር መሃሉ ዳር ይሆናል" እንዲሉ የማንም መዘባበቻ እየሆነ ነው፡፡   አባቶቻችን ያቆዩልን ድንበር በማስጠበቅ ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን :: ለዚህም ረድኤተ እግዚአብሔር የወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን

እኛም መረጃዎችን እናንተው ጋር በጊዜው ለማድረስ ቃል እንገባለን


5 comments:

  1. WHY Muslims did such bad omen activities?Though their Quran/book/ allowed to do bad omen activities,in my opinion the hand of the gov't is there.so I want to tell one thing for the gov't,i.e,please don't touch our blesses religion other wise not us rather God may dethroned you from ur power!

    ReplyDelete
  2. "ዳሩ ሲደፈር መሃሉ ዳር ይሆናል"

    Let us pray God to be with us, & do what we should

    ReplyDelete
  3. አቶ አሊ አብዶ ከስልጣን መውረዳቸው ብቻውን የመንግስትን ፍትሃዊነት አያመለክትም፤በስልጣን ዘመናቸው የተፈጸሙት ስህተቶች ሙሉ በሙሉ ሲታረሙ ብቻ ነው የህግን የበላይነት ማረጋገጥ የሚቻለው፡፡ ይህ እስከሚሆን ድረስም ማንኛውም እውነተኛ ኢትዮጵያዊ በግልም ሆነ በጋራ የሚያደርገውን ጥረት ልንደግፍ ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  4. ጎበዝ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የሠላም፣ የፍቅር እና የአንድነት መድረክ (ተምሳሊት) ናት። ይህም በመሆኑ ከአገር ውጪም ሆነ ከአገር ውስጥ እሷን ለማዳከም የማይጥር አካል የለም። በውጪ በኩል በዋናነት የሚጠቀሱት ሳዑዲ አረቢያ እና ኢራን (ከአክራሪ ሙስሊሙ ጎራ) ሲሆኑ፣ ከነሱ ባልተናነሰ መልኩ ደግሞ "ክርስትያን ነን" ብለው ራሳቸውን በተለያየ ስም የሚጠሩ የዲያቢሎስ መልዕክተኛ የእምነት ድርጅቶች ናቸው። በአገር ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት (ሕወሐት/ኢህአዴግ) በዋናነት ይጠቀሳል። የመንግሥት ሥልጣኑን በእጁ ባስገባበት ማግስት በኢትዮጵያ ታሪክ ሰምተን የማናውቀውን "የእስላም ንጉሥ አል ነጋሺ የተባለ ኢትዮጵያን ገዝቶ ነበር" በማለት ጆሮአችንን አደነቆሩት። እነርሱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ንን እና ምእመናኑን ለመበጥበጥ የፈጠሩት የበረሃ ታሪክ ነው።ይህንንም ጉዳይ በመሐል አገር እንዲያራግቡላቸው በቅድሚያ አቶ ተፈራ ዋልዋን፣ ከዚያም በመቀጠል አቶ ዓሊ አብዶን የአ/አ ከተማ አስተዳዳሪ አድርገው በመሾም እስኪሰለቸን ድረስ ተሳለቁብን።

    አቶ ዓሊ አብዶ በነገሠበት ዘመን በእርግጥ ብዙ መስጊዶች ተሠርተዋል። የመስጊድ መበራከት ግን የሙስሊሙን ቁጥር አይጨምረውም። በዚህ ሥጋት ሊገባን አይገባም። ከ15 ዓመት በፊት የብሔረ ጽጌ ማርያም ቤ/ን በመቃኞ መልክ ተሠርታ አገልግሎት መስጠት በጀመረችበት ወቅት ከየት መጡ ሳይባል በውድቅት ሌሊት ሙስሊሞች ከጎኗ መስጊድ ሠርተው አደሩ። ሲነጋም ክርስትያኑ ሁኔታውን በማስተዋሉ አላግባብ የተተከለችውን መስጊድ አፈረሷት። ሙስሊሙ ሕብረተሰብ አንድ የበዓላቸው ቀን አ/አ ስታዲዮም ሰግዶ ሲያበቃ በሎንቺና እየተጫነ ቤተ ክርስትያኗን ለማፍረስ ወደ ብሔረ ጽጌ ነጎደ። ሁኔታውን የተረዱ የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት ከሙስሊሞቹ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው ቤተ ክርስትያኗን ከመፍረስ አተረፏት። በዚህ ግጭት ሳቢያ አንድ ሙስሊም ተገደለ። የተቀሩት ቀሚሳቸውን እየሰበሰቡ “እግሬ አውጪኝ” አሉ። መንግስት ለግጭቱ መፍትሔ ለመስጠት ከአስፋልት ወዲያ እና ከአስፋልት ወዲህ በማለት ቦታ አከፋፈለ። ሁለቱም በተሰጣቸው ቦታ ላይ ሕንፃዎቻቸውን ገነቡ። ሙስሊሞቹም የገነቡት ትልቅ ሕንፃ ነበር። የሚገርመው ነገር ግን በየዕለቱ በውስጡ የሚሰግደው ሰው ብዛት ከ 10 አይበልጥም ነበር። በሌሎችም አካባቢ ከዚህ የተለየ ሁኔታ አይፈጠርም። እንደ ሕንፃ መብዛት ቢሆን ኖሮማ አውሮፓ የክርስትያኖች መናኸሪያ በሆነች ነበር።

    አረመኔው መለስ ዜናዊ በአንድነት ዙሪያ ማዳከም ያልቻለው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ንን ብቻ ነው። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ሕግና ሥርዓት ውጪ የራሱን ፓትርያርክ ሾሞ ቢያስቀምጥም እንኳ ዓላማው እስካሁን ሊሳካለት አልቻለም። እውነት እንነጋገር ከተባለ አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስትያኗን እንደ አባት ለመጠበቅ ወይስ የወያኔን ፖሊሲ፣ ውጥን፣ ዕቅድ፣ ዓላማ፣… ወዘተ ለማስፈጸም ነው የተቀመጡት? እሳቸው እኮ የእግዚአብሔር መንፈስ የራቃቸው የተሐድሶ አቀንቃኝ ናቸው። በሳቸው መልካም ፈቃድ አይደለም እንዴ በየቦታው መናፍቃን “አባቶች” በየአብያተ ክርስትያኑ የሚመደቡት? ይህቺን ቤተ ክርስትያን ለውርደት የዳረጓት እሳቸውና መሰሎቻቸው አይደሉም እንዴ? መልካም አባት ቢኖረን ኖሮማ ቤተ ክርስትያን አጠገብ መስጊድ ወይም “ጸሎት ቤት” እንዲሠራ መስተዳድሩ ፍቃድ ሲሰጥ በተቃወመ ነበር።

    ጎበዝ! “መንግሥት ማለት ሕዝብ ነው” የሚለው አባባል በዚህ ዘመን አይሠራም። መንግሥትና ሕዝብ ሆድና ጀርባ ስለመሆናቸው ምስክር አያስፈልገንም። እግዚአብሔርን ከማያውቅ መንግስት ጋር ያበሩ ወገኖችም ካሉ እነሱ አንደኛ እግዚአብሔርን የካዱ ናቸው (ለሁለት አምላክ መስገድ አይቻልምና)፣ ሁለተኛ፣ ለሆዳቸው እና ለጥቅማቸው ሲሉ ደሃውን ወገናችንን እና ኢትዮጵያን የካዱ ናቸው። እነርሱ ፍርዳቸውን በቅርቡ ከእግዚአብሔር ያገኛሉ።

    ከዚያ በተረፈ የዚህ ብሎግ አዘጋጆችን በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዙሪያ ለማሳሰብ የምፈልገው ነገር አለኝ። እሱም፣ እስልምናን እንደ ኃይማኖት ተቀብለው “አምላካቸውን” በሠላም የሚያመልኩትን ወገኖቻችን እና በውጪ ኃይሎች እየተደገፉ ኃይማኖቱን ለፖለቲካ መሣሪያነት የሚጠቀሙበትን አክራሪ ሙስሊሞች ለያይታችሁ ማየት ወይም ኢንፎርሜሽን መስጠት ይገባችኋል። የተለየ ዓላማ እስከሌላችሁ ድረስ! ሙስሊም ሁሉ አክራሪ አይደለም፤ አክራሪው ሁሉ ግን ሙስሊም ነው። ይህንን ልዩነት ያልተገነዘበ የዋሁ ወገን አላግባብ ሙስሊሙን ወገናችንን እንዲጠላ ያደርገዋል። በዚህም ሳቢያ አላስፈላጊ ግጭት ይፈጠራል። እንደዚህች ዓይነቷን አጋጣሚ ለመጠቀም አክራሪ ሙስሊሞቹ ገጀራ እና ቆንጨራ አዘጋጅተው እየተጠባበቁ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሆኗል።

    በመጨረሻ፣ በዘመናችን ይህ ሁሉ ነገር ሊፈጸም እንደሚችል አስቀድሞ ተነግሯል። እግዚአብሔር አምላክ ኃጢአታችንን እና በደላችንን ሳይቆጥርብን በቸርነቱ እና በምሕረቱ እንዲጎበኘን ወደ እርሱ እንጩህ። ኃጢአታችንን ለካህን ተናዘን፣ ንስሐ ገብተን፣ ሥጋ ወደሙ ተቀብለን ተዘጋጅተን እንጠብቀው። በአፋችን ሳይሆን ከልባችን እና ከነፍሳችን እንውደደው። በራሳችን አንመካ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትም አንተማመን። ልበ-አምላክ ዳዊት የዘመረውን መዝሙር እኛም እንዘምረው “እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፤ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና፤ ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው። እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ፤ማረኝም። የልቤ ችግር ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ። ድካሜንና መከራዬን እይ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ። ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፤ የግፍም ጥል ጠልተውኛል። ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር። አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።” መዝ. 24፡14-21 የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ!

    ReplyDelete
  5. You must first understand the meaning of the church. It is not physical building, but believers who are redeemed.

    'Nefitegna Asitesasebachiyu yalekekachihu, yezemenu fersawuyan, ewunetin yemitikawomu, yegehanim lijoch...' nisiha gibuna kesewu gar beselam nuru.

    Ende Haileselasie zemene mengist mengistin ejun temzizachu mazez yemitichilu yimesilachihal?

    Update yourself!

    ReplyDelete