Sunday, December 25, 2011

ፌደራል ፖሊስ መረጃ ሰጥተዋል ያላቸውን ሰዎች ከቤተክርስትያኗ ውስጥ እያሰረ ነው

(አንድ አድርገን ታህሳስ 15 2004 ዓ.ም) ፡- በደብረዘይት ከተማ የሚገኝው ታቦት ማደሪያ በአቡነ ጳውሎስ ቀጭን ትዕዛዝ ቤተክርስያናችን ካለት የመሬት ይዞታ ላይ ተቆርሶ ለባለሀብት በመሸጥ ሪዞርት እየተሰራበት መሆኑንና የሚሰራው ሪዞርት ላይ ትንኮሳ እንዳይፈጠርበት በማለት ቀን ከለሊት በፌደራል እና በከተማው ፖሊሶች እየተጠበቀ ይገኛል፤ ዛሬ ለጥምቀት ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ መሸጥ ከጀመሩ ነገ ከዚህ የከፋ ነገር እንደማያደርጉ ምን ማረጋገጫ አለን? ፡፡ለመሆኑ የቤተክርስትያኗ መሬት ላይ የማዘዝ ስልጣን ያለው ማነው? ፓትርያርኩ መሬት መሸጥ ይችላሉ እንዴ ? በማለት መዘገባችን ይታወቃል መንግስት ይህ ነገር አሳስቦት ማነው ይህን ዜና ሚዲያ ላይ እንዲወጣው መረጃ የሰጠው እንዴት በሚስጥር የተያዘው ነገር ሾልኮ ቀናት ሳይሞላው ድህረ ገፅ ላይ ወጣ? ማነው ይህን ያደረገው? በማለት ሰዎችን ከደብረዘይት ባቡጋያ አካባቢ ከሚገኝው መድሀኒአለም ቤተክርትያን ውስጥ ፌደራል ፖሊስ እያሰረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ይህ ጉዳይ የማንም ጉዳይ አይደለም የእኛ ጉዳይ ነው ቤተክርስትያናችን ላይ የሚደረገውን ነገር ማንም አደረገው ማን አይተን የምናልፍበት አይን የለንም መረጃ እስክናገኝ እስክናረጋግጥ ዝም ያልናቸው ነገሮች ብዙ ናቸው፤ እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት እንኖራለን ብለን አናስብም በተሰጠን እድሜ ግን ቤተክርስትያን ላይ የሚደረገውን ነገር ሁሉ ከመፃፍና ለሰዎች ከማሳወቅ ወደ ኋላ አንልም ፤እውነቱ ይሄ ነው ‹‹ ቦታው ተሸጧል ፤ ሪዞርትም እየተሰራበት ነው››

ሰዎችን በማሰር እና በማዋከብ መረጃ ለማግኝት መጣር የሞኝ ስራ ነው ፤ በመጀመሪያውኑ ሰዎች ጥያቄ እንዳይጠይቁ ህግን አግባብ አድርጎ መስራት የተሻለ ነው ብለን እናምናለን ፤ የቤተክርስትያናችን መሬት መሸጥ የለበትም ፤ በዚህ የቦታ እጠረት ባለበት ጊዜ ላይ ከዓመታት በኋላ ለጥምቀት ታቦት ማሳደሪያ ለምን ታሳጡናላችሁ ? ይህ መረጃ ማንም ይናገረው ፤ ማንም ይፃፈው ፤ ማንም ያድርገው ነገሩ እውነት ነው ፤ አሁን  የነገ ፍራቻችን ባዶ ቦታ   መሸጥ መለወጥ አይደለም ፤ ስጋታችን ከፍ ብሏል ፤ አቡነ ጳውሎስ ለሚሰሩት ስህተት እንደ ፓርላማ አባል ያለመከሰስ መብት ከመንግስት ከለላ እያገኙ ይገኛሉ ፤ ታዲያ እኛ የት ሄደን አቤት እንበል ፤ ስራቸውን መቃወም አንድ መንገድ ሆኖ ሳለ ከስራቸው መግታት አለመቻል ደግሞ ስራችን ውሀ ወቀጣ ያደርገዋል፡፡
 እኛ እንደ አውራምባ ጋዜጠኛ ዳዊት ‹‹ይች ሀገር የማናት›› ብለን አልፃፍንም ፤ ይሄ እኛ እየሰራን ያለነው ነገር ፖለቲካ አይደለም ፤ ደብረዘይት ባቡጋያ አካባቢ የሚገኝው መድሀኒአለም ቤተክርትያን እየተሰራ ያለውን ስራ መረጃ ነው ሰዎች ዘንድ ያደረስነው ፤ እውነት ነው የተናገርነው ፤ የሆነነና የተደረገ ነገር ነው ያቀረብነው ፤ ስለዚህ ስለቤተክርስያናችን ነው የፃፍነው ፤ ሆዳቸውና ጭንቅላታቸውን መለየት ያቃታቸው ሰዎች ቀላቅለውት ሊያስቡ ይችላሉ ፤ እንደፈለጉ ቢያስቡ በእነሱ ጭንቅላት እኛ ማዘዝ አንችልም ‹‹እነሱነታቸውን ለአመለካከታቸው አሳልፈን ሰጥተናል›› 
ከነካኩን ይህም አለ
በአሁኑ ሰዓት በባህልና ቱሪዝም ውስጥ ምን እየተሰራ እንዳለህ የውስጥ ሚስጥር ነው ፤ የሀገሪቱ አብዛኛው ቅርሶች የቤተክርስትያናችን መሆኑ እሙን ነው ፤ ይህን መስሪያቤት እየመሩት የሚገኙት ሙስሊሞች ናቸው ፤ በአሁኑ ጊዜ የግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተብሎ የተሾመው መሀሙድ ድሪል ለብዙ ዓመታት ማስተዳደር ችሎ ነበር ፤አላማው ከበስተኋላ ነውና እሱ ወደ ካይሮ ሲያቀና በምትኩ ሌላውን ሙስሊም አጭቶ እና አሹሞ ነው የሄደው ፤ በአሁኑ ሰዓት በደንብ አድርገው መዋቅሩን እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ ፡፡ የብራና መፋቅ ስራ እና የራሳቸውን አስመስለው በመፃፍ እኛም ታሪክ አለን ለማለት ትላልቅ ቋጥኞችን እየፈነቀሉ ይገኛሉ ፤ የኛ የሆኑት በ14ተኛው ክፍለ ዘመን የተፃፉት ተዓምረ ማርያም ፤ በአማርኛ እና በግዕዝ የተፃፈው ዳዊት እነርሱ እየጠበቁልን ይገኛሉ ፤ ይህን ነገር ከማስረጃ ጋር ወደፊት እመለስበታለሁ ፡፡ አላማቸው ጥልቅ ነው ፤ ጉዟቸውም ረዥም ይመስላል ፡፡ እውነት ስለሆነ እንናገራለን እንፅፈዋለን ፤
 ሌሎች
  • ኢቲቪ አይናችን በቅርቡ አቅርቦት የነበረው ያለ አግባብ በጉሙሩክ ውስጥ ስለተደረገው የመሬት ወረራ ሲዘግብ ለምን ግቢ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ስለተሰራው መስኪድ ዝም አለ?
  • የብራና መፋቅ ስራዎቻቸው
  • አስመስሎ በአረብኛ የተፃፉ ብራናዎች ከየት የመጡ ናቸው ?
  • በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣኞቻችን እና ቤተክርስያን ላይ ስለሚያደርጉት ጫና እና የመንግስ ዝምታ
  • በአክሱም አካባባቢ አገኝን ስላሉት አዲስ የድንጋይ ላይ የአረብኛ ፅሁፍ (ማነው የፃፈው ? ማንስ ነው ያፃፈው?
  • ሌሎች  ያልተሰሙ ብዙ ሴራዎችን እንናገራለን ፤  ‹‹የምንፈራው እውነት የለም›› 
ከቀናት በፊት የተቃለችውን ቤተክርስትያ ምንም ፍትህ ሳይሰጥ መንግስት ጉዳዬን ታቅፎት እንደ እሳት እየሞቀው ይገኛል ፤ በአይን ያዩ ሰዎች መስክረዋል ፤ ማን እንዳቃጠለው ታውቋል ፤ ለፍርድቤት እንዲያመቻቸው ቪደዮው ኢንተርኔት ላይ ከመለቀቁ በፊት ለአጣሪ ኮሚቴው በእጃቸው ተሰጥቷቸዋል ፤ ቦታው ድረስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሄደው ተመልክተዋል ከዚህ በላይ ምን መረጃ እንስጣችሁ?  እና ታዲያ ጊዳዩን ፍርድ ቤት ይዞ ሄዶ ለምን ሰዎች አይጠየቁልንም? ጥያቄያችን ይሄ ነው፡፡ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ዝም ብሎ ለማለፍ አስቦ እንጂ ይህን የመሰለ ድርጊት ፍርድ ቤት አቅርቦ ለማስወሰን 7 ቀናት ብዙ ናቸው ፤ አሁን ግን ጉዳዩ ወር አልፎታል፤ 



በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና ዕምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፤ የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ታዲዮስ ሲሣይ በሥፍራው የደረሰውን ችግር ተከትሎ ግጭቱ እንዲበርድ፣ የግጭት አስወጋጅ ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን ተናግረው ነበር፤  የድርጊቱ ፈፃሚዎችም ለህግ እንዲቀርቡ የሚደረግበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ግጭቶችን ለዘለቄታው ለማስወገድ የሚያስችል አሠራር በዳይሬክቶሬቱ ተጠናክሮ እንደሚሰራበትም አቶ ታዲዮስ አሳስበውም ነበር ፤ ይህ ሁሉ ወሬ እንጂ ምንም እስካሁን የሰሩትን ስራ በአይናችን ማየት አልቻልንም ፤ መንግስት ጉዳዩን ከምንም አልቆጠረውም ፤ ይሄኔ ያልሆነ ነገር የፃፈ አንድ ጋዜጠኛ ቢኖር አሳዶ ከሀገር ለማባረር የማይፈነቀል ድንጋይ አይኖርም ነበር፤ ቤተክርስትያናችን ሲቃጠል አይቶ እንዳላየ ማለፍ ሌላ ነገር ነው


‹‹የምንፈራው እውነት የለም››

7 comments:

  1. May God be with you

    ReplyDelete
  2. አይ መንግሥት! አሸባሪ ያላቸውንና ለራሱ የሚፈራቸውን ቅዳሜና እሁድ ሣይቀር ፍርድ ቤት ያቀርባል የእኛን በመረጃ የተደገፈ በደል ግን ታቅፎ ይሞቀዋል አይደል !ይሄ በደል በመሸከም ጫንቃው የተላጠ ኦርቶዶክሣዊ ያመረረ ዕለት እኔን አያድርገኝ "ይኲን ሰላም በኃይልከ"አይደል መጽሐፉ የሚለው።

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ዝም አይልም፡በርቱ

    ReplyDelete
  4. Bertu Adega lay nen

    ReplyDelete
  5. Egziabehere Kgna gare yehun.

    ReplyDelete
  6. Ayzoachihu bertu. People who live outside of Ethiopia didn't have an opportunity to know trustworthy news about our country or church. I am happy that you are here now to deliver the true stories about our church. It is good because we may organize ourselves and be helpful to our church one day. Temesgen.

    ReplyDelete
  7. lemin animotim lezich hayimanot; menigist=Islam=Protestant=catholic= silezih 8,000 geberie gonder lay yalekelat haymanot yizen egnam enilek. egna ketenesan egiziabher yiferdal=menigistim yiwedikal=Islamim angetun yidefal. Meles zenawi le hager lewegen gid yelewum.Betekihinet banit ken Yiselimal ke samsati paulos jemiro.

    ReplyDelete