(አንድ አድርገን ጳግሜ 1 ፤
2004 ዓ.ም)፡- አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በደቡብ ኢትዮጵያ በሎሎ ወረዳ በ1980 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ምህድስና የመጀመሪያ
ድግሪ ፤ ፊንላንድ ከሚገኝ ዪኒቨርሲቲ ባገኙት ነጻ የትምህርት እድል በሳኒቴሽን ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ድግሪያቸውን አግኝተዋል ፤በአርባ
ምንጭ የውሃ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ13 ዓመት በዲንነት አገልግለዋል ፤ ከ14 ዓመት በፊት የኢህአዲግ አባልነት ከተመዘገቡ በኋላ
በ1993 ዓ.ም የደቡብ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል ፤ ኢህአዴግ በብቃት ማነስ ከተሸሙበት ቦታ ዝቅተኛ ቦታ
ሰጥቶ እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ፤ ከዓመታት በፊት በብቃት ማነስ ወደ ታች የተወረወሩት ዛሬ ሐገሪቱን ለመምራት ትልቁን ስልጣን ለመቆናጠጥ
፤ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ለመቀመጥ ከፊት ለፊት ቆመዋል ፤
ግላዊ ስብዕናው በተመለከተ ሀይለማርያም ቅንነትና ትህትና የሚታይበት ፤ ሰውን ሁሉ የሚያከብር ፤ የማይመጻደቅ ተግባቢ
ምሁር ፤ በራሱ የሚተማመን ፤ ስብሰባ ሲመራ የማያስፈራራና የማይደነፋ
፤ ተቃራኒ ሀሳብ የሚቀበልና በአግባቡ ምልሽ የሚሰጥ ፤ በአግብኦ(አሽሙር) ወይም በማሽሟጠጥ ጥያቄዎችን የማይመልስ ፤ የበታችነት
ወይም የበላይነት ስሜት የማይሰማው ፤ ፈገግታ የማይለየውና ለማነጋገርም የማይከብድ ሰው መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ይመሰክሩለታል፤
በተጨማሪ አቶ ኃ/ማርያር ትልቁ ስብእና የኢህአዲግ ባለስልጣን ይቅርና ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆንም ባይሆንም ራሱን ችሎ በሰላምና በነጻነት
ለመኖር እንደሚችል አስቀድሞ የተረዳ ሰው በመሆኑ አምባገነን ልሁን
ቢል እንኳን ለመሆን የማይችል ሰው ነው፡፡
በአጠቃላይ አቶ ኃ/ማርያም
ከመሪነት ይልቅ ወደ አስተዳዳሪነት የማድላት ተፈጥሮ ስላላቸው የዘር ፖለቲካ እየሸረቡ ፤ እሁድን ሰኞ ነው ፤ ድንጋዩን ዳቦ ነው
፤ ጨለማውን ብርሀን ነው በማለት በአፈ ጮሌነት በማስመሰል የሚኖሩ ሰው አለመሆናቸውን የቅርብ ሰዎች ይመሰክሩላቸዋል፡፡ ከሳምንት
በፊት አቶ መለስ የሞቱ ሰሞን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አቶ ኃ/ማሪያም ፕሮቴስታንት መሆናቸውን የሚናገሩ ዘገባዎች በአለማቀፋዊ
ድረ ገጾች(Los Angeles Times) ላይ ወጥቶ ነበር ፤ በመሰረቱ
በደፈና ሁሉንም ፕሮቴስታንት ካላልናቸው በቀር አቶ ኃ/ማርያም “በኢትዮጵያ ሃዋሪያዊት ቤተክርስትያን ” ወይም ONLY JESUS
የሚባለው የእምነት ተከታይ ናቸው ፤ በኢትዮጵያ ፍቃድ ከጠየቁ ከሺህ የሚበልጡ ተቋማት በአሁኑ ሰዓት ፍቃዳቸውን አሳድሰው የሚንቀሳቀሱት
178 መሆናቸው ይታወቃል፡፡
እንደ እነርሱ እምነት አምላክ አንድም ሶስትም ነው የሚለውን የሥላሴን ትምህርት የማይቀበሉ ሲሆን
አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም ኢየሱስ ነው የሚል እምነት አላቸው ፤ አንድ አምላክ አንድ አካል እንደሆነና በወልድና በመንፈስ ቅዱስ
አመለካከት የራሳቸው አስተሳሰቦችን ያራምዳሉ ፤ እኝህ ሰው የአቶ መለስ ሞት ለህዝብ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በነጻነት እንደ
አንድ ተራ ግለሰብ ያለ ጠባቂ ጎፋ ካምፕ አካባቢ የሚገኝው የእምነት ተቋማቸው ጋር በሳምንት 2 ቀን እንደሚሄዱና ፕሮግራም እንደሚከታተሉ
ቦታው ላይ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡
አቶ ኃ/ማርያም ጠቅላይ ሚኒስትር
ቢሆኑ ከበፊት ስብእናቸው ጋር የማይሄድ ስራ ይሰራሉ ተብሎ አይገመትም ፤ እርሳቸው ሀይማኖትን መሰረት አድርገው ከሚፈጥሩት ተጽህኖ
ይልቅ የእሳቸውን እምነት የሚከተሉ ሰዎች እንደ አንድ አይከን እሳቸውን በመውሰድ ብዙ ነፍሶችን ወደ አዳራሾቻቸው ለማስገባት የአባላትን
ቁጥር ለመጨመር ስማቸውንና ስልጣናቸውን በሀገሪቷ ላይ ተጨማሪ የእምነት ተቋም ለመገንባት ሊጠቀሙበት ይችሉ ይሆናል ፤ “ጌታን ተቀብዬ
ስራ ያዝኩኝ ፤ ጌታን ተቀብዬ ኮንዶሚኒየም ቤት ወጣልኝ” እያሉ የሚያስተምሩ ግብዞች የሰውየውን Public image በመጠቀም በዚህ
መሰሉ አካሄድ በመጠመድ ብዙ ነፍሳትን ወደ አዳራሾቻቸው ሊያኮበልሉ ይችላሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም በፖለቲካ ብዙ ተሰሚነትም ሆነ ተጽህኖ
ፈጣሪ ሰዎች ውስጥ ስለማይገኙ ቦታውን ቢያገኙት እንኳን እንደ ጋሪ ፈረስ ከኋላ ሆኖ የሚጋልባቸው ፓርቲው በመሆኑ ሌሎች እምነቶች
ላይ ተጽህኖ ለማሳደር እንደሚከብዳቸው በቅርብ የሚያውቋው ሰዎች ተናግረዋል፡፡
አቶ ኃ/ማርያም ጠቅላይ ሚኒስቴር
ቢሆኑ እንኳን የዋልድባን አይነቱን ችግርና ሙስሊሞች ያነሱት ጥያቄዎችን
መፍታት እና አግባብ የሆነ መልስ የመስጠት ብቃቱ የላቸውም ፤ ይህን መልስ መስጠት የሚችሉት እንደነ አባይ ጸሀዬ ፤ አቦይ ስብሀት
፤ በረከት ስምኦንና የፓርቲው የፖሊት ቢሮ ከፍተኛ አባላት እንጂ
ሌሎች ሊሆኑ አይችሉም ፤ ስለዚህ ኃ/ማርያምን ጥርስ የሌለው አንበሳ ሊያደርጓቸው ይችላሉ ተብሎ ይገመታል ፤ ብዙ ሰዎች እሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆኑ ኢትዮጵያ በታሪኳ
የመጀመሪያውን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውጪ የሆነ ሰው ሀገሪቱን እንደሚያስተዳድራት ይናገራሉ ፤ ነገር ግን ካለፉት ጥቂት ነገስታት
በስተቀር ማነው በህይወተ ስጋ ሳለ ስልጣኑ ሳያስኮፍሰው ኦርቶዶክስ ነኝ ብሎ ያለ ባለስልጣን ? 17 ዓመት ይችን ሀገር የመራው
መንግስቱ ኃ/ማርያም እምነቱ ምንድነው? ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በቤተክርስትያን ስለተቀበረ ብቻ ኦርቶዶክስ ነበር ማለት አይቻልም
፤ ለክርስትና በእናቶቻችን መዳፍ በ40 እና በ80 የምንመጣ ፤ ስንሞት ደግሞ ግብአተ መሬት ለማስፈጸም በሳጥን በሰዎች ተሸካሚነት
ወደዚች ቤተክርስትያን የምንመጣ ሰዎች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነን ብለን መናገር አንችልም ፤ ለቀብር ለቀብር ቅዱስ
ዮሴፍ ቤተክርስትያን ሙስሊሙም ፤ ፕሮቴስታንቱም ፤ እምነት የለሹም ሁሉም ሲሞት ይቀበራል ፤ ታዲያ እኝህ ሰዎች ኦርቶዶክስ ናቸውን
? ታምራት ላይኔ እግዚአብሔር የለም ብሎ የሚያምን ሰው ነበር ፤ ይህን አመለካከቱን በራሱ አንደበት ሲናገር ተሰምቷል ፤ ይህ ሰውና
መሰሎቹ በጊዜው ሲያራምዱት በነበረው አመለካከት ምክንያት ብዙዎችን መንገድ አስተዋል ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ቦታ የተከፈለው በእነዚህ
ሰዎች አማካኝነት ነው ፤ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔና ጓደኞቹ ይህን ሁሉ ስራ ሰርተው “እግዚአብሔር የለም”
ብለው ቢሞቱ የሚቀበሩት እዚችው ቤተክርስትያን ነው ፤ ፍትሃትም የሚደረግላቸውም በኦርቶዶክሳውያን ስርዓት ነበር(በአሁኑ ሰዓት ታምራት
ላይኔ ፕሮቴስታንት መሆኑ ይታወቃል) ፤ ጥቂቶችም ትግል አንድ ያድርጋቸው እንጂ የዚህ አመለካከት የሰረጸባቸው ሰዎች ነበሩ ፤
በጣም የሚገርመው ነገር በአሁኑ
ሰዓት በዋልድባ ገዳም መነኮሳትን መከራ እያደረሱባቸው የሚገኙት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሲሞቱም የሚቀበሩት እዚችው ቤተክርስትያን
ነው ፤ እነሱ ሲሞቱም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነበሩ እንላለን ? ስንቱን ደመከልብ ያደረጉ የደርግ ባለስልጣናትም በዘመናቸው
ህይወታቸው ሲያልፍ የተቀበሩት ኦርቶዶክስ ቤተክርስያን ነው ፤ “ኢትዮጵያ ትቅደም” እያሉ ያንን ሁሉ ደም ያፈሰሱ ሰዎች ፤ ቤተክርስትያንን
ሙዝየም ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ባለስልጣናት እነሱም ኦርቶዶክስ ናቸውን ? የሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል የአክሱም ሀውልት የተቀረጸበት
የላሊበላ ውቅር አብያተክርስትያነት የታነጹበት ፤ አብርሀ ወአጽብሀ የነገሱበት ፤ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ፤ ክርስትና የበቀለበት
ቦታ ሰው ቢወለድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነው ልንለው አንችልም ፤ ቦታው ላይ መወለድ ፤ እምነቱን ማወቅና ፤ በእምነቱ አምኖ መገኝት ሁሉም
ለየቅል ናቸው ፤ ስለዚህ አቶ ኃ/ማርያም የሚከተሉትን እምነት ፤ የሰውየውን ስብእና እና የሚቀመጡበት ወንበር ሁሉን ለያይተን ብንመለከት
መልካም ነው ፤ አንድን ሰው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው ለማለት መስፈርታችን ምንድነው ? ለዛውም የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝም
እምነታቸውን አውቀናል ፈሪሀ እግዚአብሔርም ያለባቸው ይመስላሉ የበፊት መሪዎቻችንን እምነት ግን አናውቅም . .(ያለፉትን በጠቅላላ በደፈናው ኦርቶዶክስ ነበሩ
አትበሉን)
ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በሰጠው ኢንተርቪው
“ንጉሥ ዳዊት የተከበረ በእግዚአብሔር ዘንድም የተወደደ በብዙ ነገር በጣም የተመሰገነ ንጉሥ ነበር፡፡ እስራኤልን የሚመስል ትልቅ ሕዝብ መግዛት የቻለ ዳዊት ግን ራሱን መግዛት አልቻለም ነበር፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ከተማን ከመግዛት ይልቅ ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው፡፡ ነገር ግን መጽሐፉ የሚመክረው ራስን ቤተሰብን መግዛት እንድንችል ነው፡፡ ከተማን በመግዛትህ ሁሉን እገዛለሁ አትበል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊ ሰብዓዊ ውድቀት ሊኖርብህ እንደሚችል አስበህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡” ምዕራፍ መጽሔት፣
ጥር 2003 ዓ.ም.
መልካም የሱባኤ ወቅት ይሁንልን
አንድአድርገን ብሎግ ላይ የሚወጡትን ጽሑፎች እና መረጃዎች በተደጋጋሚ ለማየት እሞክራለሁ ፡ የሚጠቅሙ መረጃዎች እንዳሉት ደግሞ የማይረቡም አይጠፉም፡ ግን በየጊዜው እንደ አንድ መካነ ድር መሻሻል ሲገባው ሲሻሻሉ የማላያቸው ነገሮች አሉ እነሱን ብጠቁም ምናልባት ይጠቅማሉ ፡
ReplyDelete- የቃላት/ፊደላት አጠቃቀም ችግር - ይህ ማለት አንድን ነገር ለመግለጽ የምትመርጡት ቃል ግዴታ ጠንካራ ተቃውሞን የሚገልጽ ብቻ መሆን የለበትም ግን ጥበብ የተሞላበት ቢሆን ይሻላል፤ ሌላው ግን እጅግ ተራ የሆነ ነገር ፊደላት ላይ የሚታዩት ናቸው ለምሳሌ አ እና ሀ በምን እንደሚለያዩና እንዴት እንደምንጠቀምባቸው መለየት ግድ ያስፈልጋል፤ ሃይማኖት/አይማኖት፡ ህልውና/እልውና ሚሉት ቃላት ስለለመድናቸው ብቻ ሳይሆን በአነባበብም እንደሚለዩ ማወቅ ይጠበቅባችኋል . . .እና ከመለጠፋችሁ በፊት እርማትና አርትኦት ብትሰሩ
- ሌላው ደሞ ወጥነት ያለው አገላለጽ ልትጠቀሙ ይገባል ለምሳሌ ስለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጻፋችሁት ላይ የእርማት ችግር እንዳለበት በግልጽ ይታያል ፤ አንቱታው (አንተ/አንቱ) ተቀላቅሎአል፡፡ የሚገባውን ባህላዊውን አክብሮት ለማንም ቢሆን አትሰጡም ብዬ አላስብም ግን ይህ በጽሑፍም ሊንጸባረቅ ይገባዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ ነገር መነሻ የሚሆነው ቤተክርስቲያን የሁሉ ዕውቀት መሠረት መሆኗ ሲሆን ይህን ለመመስከር የሚወጡ የትኞቹም የኅትመት ውጤቶች ይህን መሠረታዊ መግባቢያ ሊያከብሩ ይገባል የሚል እምነት አለኝ
አገልግሎታችሁን እግዚአብሔር ያከናውንላችሁ
It is good to see this way. But this is the failure of us to have a protestant PM in Ethiopia.
ReplyDeleteEven though the Tigirian autocrats are orthodox by birth most of them are non Christians. If I am correct it is only Seyoum Mesfin whom I heard was studying bible with Dn. Ashenafi as per my information years ago.
blachihu bilachihu keprotestant meTsehet tiTeqsulin jemer?
ReplyDeleteBetam des yelal telek genezaba new yasechebetachewen.Egiziabher yesetelen.Ena gen Menem Behone Orthodox Ethiopian bemera betam des yelegnal
ReplyDeletewhy " Ante " and " Antu " ; "esu" and "Esachew"???
ReplyDeleteውድ ዓንድ ዓድርገን ዓዘጋጆች እግዚኣብሄር ይባርካቹህ።
ReplyDeleteምጥን፤ግን ብስለት ና ጥልቀት ያለው ሃሳብ ነው የሰፈረው። ዓንዳዶች የወረደ የዘቀጠ ሃሳብ ሰፍሮባቸው የሰውየው ህይማኖት ከ ዊኪፒድያ ያለዊን ዓይተው ነው መሰል ብዙ ዓረመኔ ገዝወችን ኦርቶዶክስ ናቸው ይላሉ ። ማ መንግስቱ ፤ መለስ፤ ታምራት ፨
ዓንጀቴን ያራሰ ጥሁፍ ነው። ብዙ ነገራቹህ በጣም ጥሩ ነው በርቱ። የሰው ሃሳቢም (ዓስተያየት) ተቀባይ ናቹህ። ቢያሰድ (ዓድሎነትም) የለም ምናለ ደጀ ሰላሞችን ኮርስ ብትሰጡልን እና አንደናንተ በንጡህ ቢሰሩሉን ፤ ቤተ ክርስትያንም ብትጠቀም ።
እኔን የሚገርመኝ ነገር ዓገርቤት ያለው ኢቲቪ እያየ በሳል አና ሚዛናዊ ሲሆን፤ ውጭ ያሉት ስንት የበሰለ አና ሚዛናዊ ነገር እያዩ ማስተዋል ሲሳናቸው ይገርማል ።
በዓንድ ወቅት እዚህ ዊጪ ዓነገር የሆነ ዝግጂት ነበር ዓሉ። ካህናትም ነበሩና ካህናት ፊት ሁነው ነፍሳቸውን ይማርና ዓቶ መለስን ዓሳለሙ ። የቀረበዊን ቢፌ ግን ከቡራኬ ቀድመው እሳቸው ላጥ ብለው ጀመሩት ። የሚገርመው ጊን መለስ እኮ ተሳለመ ። ተሳለመ ። ተሳለመ። በሰው ከደስታ ጋር ቀለጠ። የሚገረመው ካህናት መስቀል ሲይዙ ዘር በል ሊል ኣይችልም ምን ጦስም አንዳለው ኣይጠፋውም ። ልብ በሉ ሰውየው እኮ በ ባድመ ጦርንት ወቅት ሰላም በጠሎት ዓይመጣም ያሉን ደፋር ናቸው። ቢያንስ የስንት ሚሊዮን ሂዚብ ስሜት ቢጠብቁ ምናለ። በሳቸው ፓርቲ ኦርቶዶክስ ስንት ጊዜ ነው ተዘለፈች ። የዋልድባንማ ኣምላክ ይቁጠረው።ፖለቲካ ዊሸት የበዛባት መድረክ አንደሆነም ኣያቁም። ከዛ በላይ በጌታ ፊት የኔ ቢጤ ዲሃ ይሁን መለስ በጌታ ፊት ዓንድ ናቸው ብሎ ማሰብ ዓቃተው ። ልብ ይስጠን አስኪ ።
AMEN LE HULACHNE
ReplyDelete"ቀድሞ" ማለት ምን ማለት ነው ወዳጄ? አንተ/ቺ ከተወለድኽ/ሽ ወዲህ የተነሡትን ደርግና ኢሐዲግን የቀድሞ ማደረግኽ/ሽ በምን ስሌት ነው? ረ ባካችኹ ዝም ብላችኹ አትሞንጭሩ።
ReplyDelete"የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝም እምነታቸውን አውቀናል ፈሪሀ እግዚአብሔርም ያለባቸው ይመስላሉ"? ኧረ? ታዲያ ፕትርክናውንም እንደርብላቸዋ!
ረረ ባካችኹ ዝም ብላችኹ አትሞንጭሩ!!!!awo atichekulu think before pick
DeleteSelam Andadirgen, I think your analysis is off the mark. Why did you go far, PM Meles was an self proclaimed atheist. But he was Baptized in the Tewahdo Church. That is not the point. Saul was also king of Israel but he was not loyal to God. Meles and Mengistu are like Saul. Hailemariam is different. He is not just not loyal to God and His mother our Blessed Mary, but he is in the service a foreign cult whose purpose in Ethiopia is to destroy the EOTC. Hailemariam may not have the fortitude to think and directly cause damage to the EOTC, but that doesn't mean that those who are in control of his mind will not guide him to our country's hurt. Simply put, in the blessed Mary's Ethiopia we have now a man who is baptized of enmity toward her. The guy has no regard to our colorful history. It is sad that we are going from one sorrow to another.
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን ድንቅ ዕይታ ነው:: አሉን የምንላቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማህበረ ቅዱሳንን ማሳደድ ለመጀመር ዕቅድ የነበረውን: ዋልድባን እንደ አንድ ተራ ገበሬ እርሻ ያረሰዉን: መለስ ዜናዊን: ክርስቲያን ነው ተብሎ ፍትሃት ተደርጎለት ቤተ ክርስቲያን ተቀበረ:: ይሄ እንግዲህ ''ሩጫውን የጨረሰ ታላቅ ክርስቲያን ነበር'' ተብሎ የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ይጻፍለታል እኛ ኦርቶዶክስ ነው የምንለው እንዲህ ያለውን ነው::
ReplyDeleteyetezeberareqe neger new yemtsifew minim ayigebam? minidnew aquamih
ReplyDeleteHailemariam said in the interview that His Mother is not still saved because she is orthodox. You know how he is small minded. And he could have some influence if he can. ስተኛ እናቴ አልዳነችምና ለወላጅ እናቴ በተለይ እጸልያለሁ፡፡
ReplyDeletehttp://news.yehabesha.com/801/
Selam wegenoch! kemeneshaw yehulunim meriwoch emnet yegeltse yemeselew zegeba ye kiribun comunist Melesin zelo yalmotew Mengisitu ga mehedu geremegn. Minew Melese eko motuwal ferachu enede euwnetun lemenager? esum eko emenet yelesh neber gin degimo simot beferedebat betekiristiyanachin beweg enediqeber yetederege? gin yeswe sira yesew bemehon kemayadalewu ena bezemed kemayaseraw Hayal Nigus Fit qeribuwal ahun, lib yalew lib yebele!
ReplyDeleteMelkam Addis Amet yehunlun!
when did evangelicalism start?
ReplyDeleteWhen did Orthodox Christianity start?
Who is saved first? Mother or Son?
Evangelicalism is a Protestant Christian movement which began in the 17th century and became an organized movement with the emergence around 1730 of the Methodists in England and the Pietists among Lutherans in Germany and Scandinavia. The movement became even more important—drawing far more members than in Europe—in the United States during the series of Great Awakenings of the 18th and 19th centuries. It continues to draw adherents globally in the 21st century, especially in the developing world.
It is a religious movement that de-emphasizes ritual and emphasizes the piety of the individual, requiring him or her to meet certain active commitments, including:
Orthodox Christianity became the established church of the Ethiopian Axumite Kingdom under king Ezana in the 4th century through the efforts of Abba Selama, Kesaté Birhan ("Father of Peace, Revealer of Light").
The Ethiopian christans saved from the day baptized by Philip the Evangelist one of the seven deacons:
Then the angel of the Lord said to Philip, Start out and go south to the road that leads down from Jerusalem to Gaza. So he set out and was on his way when he caught sight of an Ethiopian. This man was a eunuch, a high official of the Kandake (Candace) Queen of Ethiopia in charge of all her treasure. (Acts, 8:26-27)
The passage continues by describing how Philip helped the Ethiopian treasurer understand a passage from Isaiah that the Ethiopian was reading. After the Ethiopian received an explanation of the passage, he requested that Philip baptize him, and Philip did so.