Friday, September 7, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ያረፈበት 300 ካሬ ሜትር የሚሆን ቦታ ታጠረ





  • “መለስ የራሱ ሀውልት እንዲሰራለት አይፈልግም ፤ የእሱ ምስል ያለበት ሬክላም እንዲሰቀልለትም አይፈልግም”  ወ/ሮ አዜብ መስፍን

 (አንድ አድርገን ጳግሜ 2 2004 ዓ.ም)፡- የጠቅላይ ሚኒስትሩ  ግብዓተ መሬት ከተፈጸመ እነሆ 5 ቀናት አለፉ ፤ አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ከዚህ በፊት የማንም አስከሬን ያላረፈበት ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በስተ ግራ በኩል ይገኛል ፤ በቴሌቪዥን እንደተመለከታችሁት የውስጡ ግድግዳ በሴራሚክ ተነጥፎ ሳጥኑ በክብር አፈር እንዳይበላው ታስቦ አስከሬኑ አርፏል ፤ ሳጥኑ ላይ ወደፊት ሙዚየም እንደሚሰራ ታሳቢ በማድረግ ብዙ ድንጋይ እና አፈር ሊያሸክሟቻ አልወደዱም ፤ ባይሆን ትንሽ ባዞላ ቢጤ ከላይ በማስቀመጥ ክፍተቱን በሲሚንቶ በመሙላት ከላይ የኢትዮጵያ ባንዲራን አልብሰዋቸዋል ፤  
በቀብር ስነ ስርዓት አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የተቀበረበት ቦታ አፈር መመለስ የተለመደ ቢሆንም ይህ ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ላይ አልተደረገም ፤ ስርዓተ ቀብሩ ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ በርካታ ፊደራል ፖሊሶች እና የመከላከያ ሃይሎች በቦታው ይገኛሉ ፤ አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ላይ 2 ሜትር በ 3 ሜትር የሆነ ቤት በአሁኑ ሰዓት ተሰርቶበታል ፤በሩ መግቢያው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለው ባለ 5 ኮከብ አርማ አርፎበታል ፤ ሰዎች አሁንም የተቀበሩበት ቦታ ድረስ እየሄዱ ሲያለቅሱ ተስተውለዋል ፤ ያረፉበትንም ቦታ ለማየት እስከአሁን ድረስ በርከት ያሉ ሰዎች ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲመጡ ተስተውሏል ፤ ቦታው ላይ ምን ለመስራት እንዳሰቡ ባናውቅም መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችል ሸክላዎች ፤ ሲሚንቶዎች ፤ በርካታ ትላልቅ ብረቶች ፤ እንጨቶችና የተለያዩ መሳሪያዎች በቦታው ላይ እየተራገፈ ይገኛል ፤ አስከሬናቸው ሙዝየም ውስጥ ከተቀመጠ ለምን ይህን ሁሉ ነገር ይደረጋል? ሲሉ ሰዎች ሲያወሩ ይደመጣሉ ፤ ባሳለፍናቸው 4 ቀናት ውስጥ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ባይኖርም አሁን ግን አስከሬኑ ያረፈበትን  በአማካይ 300 ካሬ የሚሆን ቦታ በላስቲክ የማጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ፤ ሀውልቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ነው እንዳይባል አስከሬናቸው ሌላ ቦታ ያርፋል ተብሏል ፤ ታዲያ ለምን ይህን ያህል ቦታ ማጠር አስፈለገ ? 4 ካሬ የማይበልጥ ቦታ ላይ ያረፈን አስከሬን ስራ ለመስራት ይህ ያህል ቦታ ማጠር አስፈላጊነቱ አልታየንም ፤ ወደፊት ይህ ቦታ የታጠረው ላስቲክ ተነስቶ ለቤተክርስትያኒቱ ምዕመናን የቀድሞውን ቅዳሴ የማስቀደሻ ፤ በዓል ማክበሪያ እና መሰል አገልግሎቶችን ይሰጣል ብለን አሁን መናገር አንችልም::

የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ያለበት ሸራ የቀብራቸው እለት በቤተክርስትያኑ በስተግራ በኩል መሰቀሉ ይታወሳል ፤ ከሁለት ቀን በኋላ ግን የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ተነስቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶ በግራም በቀኝም ቦታ በጣም በትልቁ ተሰቅሏል ፤ መጀመሪያ እኛ የአቡነ ጳውሎስን ፎቶ ሰቅለን ባናሳያቸው ኖሮ እነርሱም ፎቷውን ለመስቀል ጥያቄ ባላቀረቡ ነበር  ፤ መሰቀሉን ለምን? እያልን ሳይሆን የተሰቀለበት ቦታ ግን አግባብ ነው የሚል ሀሳብ የለንም ፤ ፎቶው ዛሬ ከተሰቀለ 7 ቀን ሞልቶታል እስከመቼ እንደሚቆይ አይታወቅም ፤ የጥላሁን ገሰሰ ፎቶ የሞተ ሰሞን በእጁ ማይኩን ይዞ በትልቁ በግቢው ውስጥ መሰቀሉ የዛሬ 3 ዓመት ትውስታችን ነው ፤ የጥላሁንን ፎቶ ማይክ ይዞ በግቢው ውስጥ የተመለከቱ ጥቂት ሰዎች በሁኔታው ደስተኛ አለመሆናቸው በጊዜው ሲገልጡ ነበር ፤ ለምን ? ብለው ቢጠይቁም መልስ የሚመልስ ሰው አይገኝም ፤ ቤተክርስትያን ውስጥ በትልቁ እንዲህ አይነት ፎቶ መመልከት ለአማኙ ምን አይነት መንፈስ ውስጥ እንደሚያስገባው ማወቅ አይከብድም ፤ በጊዜው ጥቂት ወጣቶች “ኮንሰርት ያለበት ነው የሚመስው” እያሉም ሲቀልዱ ተስተውሏል ፤ ስለዚህ የቤተክርስትያንን ግቢ እኛው መደረግ ያለበትንና የሌለበትን ለይተን ማወቅ መቻል አለብን ፡፡ 

5ኪሎ ቅድስት ማርያም በሩ ላይ ቆመው ሲሳለሙ ከፊት ለፊት ያለው የአቡነ ጳውሎስ ፎቶ ይመለከታሉ ፤ አሁን ደግሞ ቅድስት ሥላሴ ሄደው እጅዎትን ወደላይ አንስተው ለማማተብ ሲሉ ከፊት የሚታይዎት ሌላ ነገር ነው ፤እነዚህ ነገሮች ከጊዜ ወዲህ የመጡ ተለጣፊ ነገሮችን እየለመድናቸው መጥተን ወደፊት ሌላ ነገር እንዳይፈጥሩ ፍራቻ አለን ፤ ከዓመታት በፊት የአቡነ ጳውሎስ በየቤተክርስትያኑ የተሰቀሉት ፎቶዎች ቅዱስ ሲኖዶስ ይነሱ ብሎ መወሰኑ የሚታወቅ ነው ፤ ማንሳት ሲያቅተን ለአእምሯችን ተገቢ ነው ብለን ነግረነው ካበቃን በኋላ አሁን ብናያቸውም ባናያቸውም ምንም ላይመስለን ይችላል ፤ ነገር ግን አግባብ አለመሆኑን ግን ማወቅ አለብን ፤ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፎቶም ቢሰቀል አግባብ የሚሆነው አስከሬናቸው ያረፈበት ቦታ ቢሆን መልካም ነው ፤ እንደ አሁኑ ተደርጎ መሰቀሉ ግን አግባብ ነው አንልም(ከተሳሳትን እንታረማለን)፡፡

ቸር ሰንብቱ

19 comments:

  1. Please remove the photo plus there is no way to give 300 M2 to give one person. Ethiopia has lost many people in its lifetime many of whom have done a lot for their country. There is no way of giving this much land for Meles. Please end the game now. It may be ok until the family gets some relief but this shall not be forever.

    ReplyDelete
  2. Thanks Andadirgen. It is nice observation. I am really surprised. 300m^2 is almost the same as an international basket ball field (28m by 15m).

    Andadrigen, the information you provide us is very important, but I am not sure if all such messages can reach the responsible person (or organization, in this case The Cathedral's office). So always you should find a way to reach those people (like Bete Kihinet). Otherwise, what you saying is just only for information to people (who have access to Internet).

    ReplyDelete
  3. Tazabi,

    Gobez... ere zares wedet enigba? Yihe hulu Aba Pawolos tilewlin yehedut kentu widase trafi new. Algeban endehone enji eko ...they are saying "I am a born-again believer & my religion is Meles Zenawi" Enkichun eko negerun Aiga Forum. please SEE- http://www.aigaforum.com/articles/There-is-nothing-left-for-me-to-say.pdf

    Ahun wedfit ketilew... they will say " You all are born-again believer & your religion is Meles Zenawi"

    Aye Habesha - Minew ergum fitret bezabet keto

    ReplyDelete
  4. ere mereren leman abet yibalal ..beyegizew bebete kirsetiyan lay yemitayew neger hulu eyebase new yemihedew yalew ..gobez manew ezich betekrstiyan lay azim yaderegebat ..melese zenaw mekeberem alineberebetem silasea bete kerstiyan yeresa metaya aydelechem yehiyawan bet enji yihe sew eminetem alineberewm yebete kerstiyanem telat neber ,,,mekeberu alibeka belo demo lesu photo yihew tuwat mata eyesegedin new yalenew yasazenal abatoch tebyewchem minem tesfa yemitalibachew aydelum ...min madreg endalebin ahunes gera geban ...tekatelin

    ReplyDelete
  5. Thanks Andadirgen. It is nice observation. I am really surprised. 300m^2 is almost the same as an international basket ball field (28m by 15m).

    Andadrigen, the information you provide us is very important, but I am not sure if all such messages can reach the responsible person (or organization, in this case The Cathedral's office). So always you should find a way to reach those people (like Bete Kihinet). Otherwise, what you saying is just only for information to people (who have access to Internet).

    ReplyDelete
  6. በበጎ እዩት ለቤተክ/ ክብር ነዉ የኢት/ መሪዎች ኦርቶዶክሳዊነት ክብራቸዉ እንደሆነ ይዩት ይህ ከሰዉ አይደለም ከእግዚአብሄር ነዉ ሰዉዬዉ ሳናዉቀዉ ክፉዉን ብቻ እያየን መቃወም ተጠናዉቶን ነዉ እንጂ ካሳለፍነዉ ከሱዘመን በፊት ሲነጻጸር ለቤተክ/ ወርቃማ ዘመኗ ነዉ እግዚ የለም የሚል ትዉለድ ወደ ቤ/ክ የተመለሰበት ለቤ/ክ ንብረቶቿን የተመለሰበት እነ ራእጉኤል መናፈሻ ደብረአሚን ተክ/ሓ መናፈሻ ሌላም ሌላም ያሁሉ ህንጻዎቿ የመለሰ የቅድስት ሥላሤ በር የከፈተ አማኞቿ ስለእምነታቸዉ እንዲማሩ ኮሌጓን የመለስ ከአብዮት አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የመለሰ ከፈረስ ማሰልጠኛ ወሰዶ ጥምቀተ ባህሯን ጃልሜዳን የመለሰ ሥላሤዎች ባወቁ ባሥከፈተዉ በር ሥላሤዎች እንማርበት ዘንድ ክብሩን አበዙለት ብትሉ ምንአለበት እኛ አማኞቿ ከላይ እስከታች መስራትአቃተን እንጂ ተዉ ባካችሁ ጌታን ሰቅላችሁ በርባንን አትፍቱብን

    ReplyDelete
    Replies
    1. lela lenawin enteweeina ena yemeles photo betekrstiyan yisekel eyalk/sh new weyis mindinew?

      Delete
  7. endih yalewin difiret Mengistu H/MARIAM enkuan almokerewim. beteqedesew bota lay mutanin endinamelk yeseqelachihu sewoch yenante mot qerboalina ansulin. 20 ametat mulu betekrstianin endegil nibiretachew photo, hawilit eyaqomu limeleku simegnu yeneberutin betibebu anesalin. ahun degimo yihinin amtito yedeneqerew sew yihichin betekristian sirat alba yewenbede washa adirgewatalina jirafun meliso endianesa hizibe krstian bemulu liazinina litseliy yigebawal. leaynachew yeteluat betekrstian simotum wusituan lemeberez minew enqilif atu? Abetu yehonebinin asib!!!

    ReplyDelete
  8. አቶ መለስ በጣም ብልህ ናቸው። ዛሬ ድንበራቸውን ሰፋ አድርገው የያዙት ለምክንያት ነው።
    አቶ ኢሳያስ ሲሞቱ መቶውን ስኩየር ሜትር በቀላሉ ቆርሰው ይሰጧቸዋል። እረፍትን ስለናፈቁ ሌላ የድንበር ጦርነት አይፈልጉም።
    ባንዲራውንም ለብሰውት የተኙበት ምክንያት "ባንዲራ ጨርቅ ነው"፤ ምስጥ እንዳይበላቸው ጨርቅ ፈልገው ነው። okay?

    ReplyDelete
  9. 1 Abune Merkorewosin Patiryarik Adirgo Yeshomachew Manew ?
    2 Abune Pawlosin Patiriyarik Adirgo Yeshomachew Manew ?
    3 Abebaw Yigozaw Yebete Kihinet Sira Asikiyaj Kemehonu Befit Yeti Nebere?
    4 Abebaw Yigizawn Sira Asikiyaj Adirgo Yeshomew Manew ?
    5 Memire Meazan Merkato Ragueil Church Yegedelachew Manew ?
    6 Merkato Ragueil Gibi Dewel dewayun Yegedelew Manew ?
    7 America Yalutin Abune Melketsdekin Papas Adirgo Yeshome Manew
    Anid Adirgen kelay Yekerebewn Hasab Kentu Atadirgut Yastezazibal Melsun Zegibulin Wede Patiryarik meshom Kemehedachin Befit Hulunim Neger mawek Yasfelgal Abune Pawlos Zerega Neberu Abune merkorewos Yibeltsalu Enkan Ethiopia America Sayiker Yegonder Kahin kalhone alakorbim gondere yalhone Miemen Meskel Alasalimim Bilewalna new

    ReplyDelete
  10. ሰፊ አጥር የሠሩበት ምክንያት አቶ መለስ ከተቀበሩበት ህዝብ ከማያውቀው ቦታ አውጥተው ነሐሴ 27 ቀን ከተቆፈረው ህዝብ ካየው ጉድጓድ ሊጨምሯቸው ነው። አቶ መለስ የሞቱት ሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓም ሲሆን የተቀበሩት በድብቅ ነበር። ነሐሴ 15 ቀን ሞቱ የተባለው አንድ ወር ከአንድ ሳምንት ጥቂት አመራሮች እንዴት እናድርግ የሚል ዝግጅት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ነው። ወይዘሮ አዜብና ልጆቻቸው እንባ ሲወጣቸው ያላየነው ከአንድ ወር በፊት ለቅሷቸውን ስለጨረሱ ነው። ነሐሴ 27 ቀን የተቀበረው ሬሳ የሌለው በእንጨት የተሞላ ሳጥን ነው። እንደ አባ ጳውሎስ ፊት እያሳዩ ያልቀበሩበት ምክንያት አቶ መለስ ከተቀበረ ከወር በላይ ስለሆናቸው ነው። የሆነ ሆኖ ግን ነሐሴ 27 ቀን ሳጥኑ ሲቀበር ከሱ ጋር አብሮ ኢትዮጵያን ለአርባ ዘጠኝ አመታት ሲያንገላቷት የኖሩት ሰይጣናዊ መጤ ፍልስፍናዎችና ሥራዎች በሰነደቅ አላማው ላይ ኢህአዴግ ካስቀመጠው ፔንታግራም የኮኮብ ምስል (ፔንታግራም የዲያቢሎስ አርማ መሆኑን ብዙ ኢትዮጵያውያን አያውቁም ምእራባውያን ግን ያውቃሉ) አብረው ተቀብረዋል። አሁን ሰፋ ያለ አጥር ያጠሩበት ምክንያት የአቶ መለስ ሬሳ ቀደም ብሎ በሚስጢር ከተቀበረበት ጉድጓድ አውጥተው ህዝብ ካየው ጉድጓድ ውስጥ ለማስገባት ነው።

    ReplyDelete
  11. መለስ ዜናዊም ሆነ ኢህአዴግ የአገርም የቤተክርስቲያንም ጠላቶች እንደሆኑ ከጫካ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የሰሩትንና እየሰሩ ያሉትን ማንም ያውቀዋል ለዚህም ብዙ ማስረጃ ማሳየት ቢቻልም እስኪ ለአብነት ያህል August 26, 2012
    የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል በሚል ርዕስ ስር ደጀ ሰላም ብሎግ ላይ የተጻፈውን በእጭሩ እንመልከት
    የኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተው “ፖለቲካዊ ትንታኔ” ገና ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ፈር በያዘ መልክ የተጠናና አቋም የተያዘበት እንደሆነ የህወሐት መሥራች አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባደረጉት የምርምር ሥራቸው (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia/ Amsterdam 2008) ላይ ጽፈውልናል። የፓርቲው ሃይማኖትን በተመለከተ የያዘው ይህ አቋም በተለይም ነባሮቹን የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና እስልምናን የተመለከተ መሆኑን፣ ኮሚኒስታዊ ፓርቲዎች ሁሉ ባላቸው “የጨቋኝ - ተጨቋኝ” ትንታኔ መሠረትም እነዚህ ሁለቱ ቤተ እምነቶች በተለያየ ጎራ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን፣ ክርስትና ጨቋኝ፣ እስልምናም ተጨቋኝ ተብሎ መፈረጁን አንብበናል።

    ዶ/ር አረጋዊ ባብራሩት የኢሕአዴግ ትንታኔ መሠረት “ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞቹ መንግሥታት ጋር “በነበራት ቁርኝት” ከገዢው መደብ ጋር የተሰናሰለ የጥቅም እና የጨቋኝነት ግንኙነት ነበራት። በነዚህ ረዥም የጭቆና ዓመታት ከተጨቆኑት መካከል ደግሞ ሙስሊሞች” ይገኙበታል፤ ስለዚህም ኢሕአዴግ ይኼንን የጭቆና ቀንበር “ለመስበር” እና እኩልነትን ለማስፈን የተከተለው ፖሊሲ፣ “ቤተ ክርስቲያንን ማምከን/ፍሬ ቢስ ማድረግ” እና “ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ” ("neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) ነው። (ገጽ. 300)

    እንደ ዶ/ር አረጋዊ ገለጻ ከሆነ “በኢህአዴግ እና በቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረው ..... ( ሙሉውን ከደጀ ሰላም ላይ ያንብቡ) ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ የቤተክርስቲያናችንና የአገራችን ጠላቶች ግን ዛሬም ለቤተክርስቲያን “ወርቃማ ዘመኗ ነዉ” ይሉናል ለማስመሰልና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ወይም ሕዝቡን ግራ ለማጋባትም ሊሆን ይችላል የቤተክርስቲያኗን ንብረቶች መንግስት ቢመልስም በርካታ በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያኗን ቦታዎች በመንጠቅ ለኢንቨስተሮች ቸብችቧል ያም አልበቃ ብሎት አይኑን በጨው አጥቦ ዋልድባን ያክል ቅዱስና ታላቅ ገዳም እያጠፋ ይገኛል ለዚህም ዋጋውን እያገኘ ነው የመንግስትን እኩይ ተግባር የምንደግፍ ሁሉ ከሰውም ከእግዚአብሔርም ዋጋችንን እናገኛለን

    ReplyDelete
  12. Negeru Hulu Eyalefe New tagesu Meleyayetin Awgizu- Andinetn Sibeku -Sewin lensiha Abiku- Yesewn Maninet Atimezigibu -Sim Matsifatin Akumu -Yesewn Sira Yemimeleket Egiziabher Newna Lehulum Eindesiraw yikefilewalna

    ReplyDelete
  13. አቶ መለስ በሕይወታቸው የቤተክርስቲያንን ይዞታ ሲቀሙ እንደኖሩት ሁሉ አስከሬናቸውም 300 ካሬ ይጠቀልል ገባ? ይስሩት መፍረሱ ግን አይቀርም

    ReplyDelete
  14. SENDEQ ALAMA not bandira. Please take note. Even woyanes called it SENDEQ ALAMA in their proclamations. I think we could do better.
    http://chilot.me/2011/04/10/flag-and-emblem-laws-of-ethiopia/

    ReplyDelete
  15. ህዝብ ለማደናገር ለፖለቲካ ትርፍ ለምንም ይሁን በመሰረቱ ህዝብን የሚያባብል ፖለቲካ ከተገኘ ህዝብን አከበረ /ፈራ ነዉ ሚባለዉ ይህ ደግሞ ጥሩ ነዉ በሳህን የተጣሉትን ሁሉ ሰምተን መደናቋር ያለብን አይመስለኝም አንድ አድርገንም ባካችሁ በእርግጥ ሀይማኖታዊ ብሎግ ከሆነ በፖለቲካ ትኩሳት በጭፍን ጥላቻ የሚጻፉትን ባታስተናግዱ እንደዚሁም ከህይማኖትም ከፖለቲካ ከባህልም በምንም ቢመዘኑ ፍጹም ከስንምግባር ዉጭ ዉጪ የሆኑት ፍሬ ቢስ የሆኑ እንደዚህ አይነት ሰዎች ባያነቡልኝ ይሻላል የሚያሰኙትን አስታያተቸዉን ባትለጥፉ

    ReplyDelete
  16. weyani tewenji bezu naweqalen eshi ketenager enaleqalen belen new zem yalenew kefelegh zemedeh yetsafewn aneb weyane dedeb
    ኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተው “ፖለቲካዊ ትንታኔ” ገና ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ፈር በያዘ መልክ የተጠናና አቋም የተያዘበት እንደሆነ የህወሐት መሥራች አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባደረጉት የምርምር ሥራቸው (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia/ Amsterdam 2008)

    ReplyDelete