Tuesday, September 18, 2012

‹‹… ሙሴ በድንጋይ ዘመን የገነነ አንድ እረኛ በመሆኑ ቢሳሳት አይገርምም…›› የበዕውቀቱ ስዩም የዕውርነት ፍሬ


 ቀሲስ  ወንድምስሻ   አየለ 
በዕውቀቱ ስዩም ደፋርና የራሱን የስነጽሑፍ ዘይቤ ለመፍጠር የሚሞክር ገጣሚና ደራሲ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፤ ብዙ የሚባሉ የወረቀትና የኤሌክትሮኒክስ ኅትመቶችን አዘጋጅቶ ያበረከተ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ የጻፋቸውን ግጥሞች ዋጋ ለክቶ በብልጫው መርጬዋለሁ ያለው ዓለምአቀፍ ድርጅትም በኦሎምፒክ ዋዜማ እንግሊዝ ሀገር ለንደን ወስዶት ግጥሙን አቅርቦና ሌሎችም መርሐግብሮችን አሳትፎ በቴምዝ ወንዝ አካባቢም አዝናንቶትሸኝቶታል፡፡ የሀገራችን የስነጥበብ ባለሙያዎችም ሲሄድ ተሰብስበው ሸኝተውት፣ ሲመጣም ከአቀባበል ጋር ልምዱን ተካፍለውታል፡፡ እንዲህ ነው የሀገር ልጅነት፡፡

የዛሬው መጣጥፌ የወጣቱን ታሪክ ለመተረክ ሳይሆን ከሌሎች በተለየ ደጉን ኢትዮጵያዊነት ደጋግሞ ከመተቸቱ አልፎ በፈጣሪ የተመረጡ በምእመናን የተከበሩ ቅዱሳንን በመዝለፍ እየታወቀ ሲሄድ ዝምታው ተገቢ ስላልሆነ፣ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ የከፈተውን አፍ ያዘጋውን ትችትና ምላሽ አላስተውል ብሎ ዛሬ ደግሞ ሊቀነቢያት ሙሴን መተቸት ውስጥ ስለገባ ለወደፊትም ትምህርት ቢሆነው፣ ሊከተሉት ለሚፈልጉ /እንዳሉ ስለማውቅ/ መንገዳቸውን እንዲያቀኑ ለመጠቆም፣ ምናልባት ከመከራ በፊት ከተመከረ ለራሱና ለሀገር የሚጠቅሙ መጣጥፎችን ያበረክት ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡

የማየት ፍሬ
እንግሊዝ ደርሶ ሲመጣ ያጋጠመውን ነገር ‹‹ የማየት ፍሬ›› በማለት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ጳጉሜን ሁለተኛ ክፍል ጽሑፍ ሲያቀርብ ‹‹ድህነት ጠፍንጎ ይዞን ነው እንጂ አበላሉንስ እናውቅበት ነበር›› በማለት እንግሊዞች ስለሚመገቡት ጥንቸል ያገኘውን ‹‹ዕውቀት›› ሊያካፍለን ይተጋል፡፡ ይህ ባልከፋ፤ ጥንቸልን እንድንበላ በጎ ስጦታዎን አብዝቶ ቢጽፍ ለማሳመን እንደሚበቃው ስለማያምን ነባሩን ባህላችንን ሊተች ሲሞክር የባህሉን ተገቢነት የሚያየው ከመብላት ፍላጎትና ካለው የገንዘብ ድህነታችን አንጻር ብቻ ሆነ እንጂ፤ ሳይተች ለማሳመን ያልሞከረው በሀሳብ ጥራት ማሸነፍ ሳይሆን በማሸማቀቅ ተቀባይነትን ማግኘት የዘመኑ ‹‹ምሁራዊ›› ‹‹ፖለቲካዊ›› አማራጭ ተደርጎ በመወሰዱ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከወታደር ቤተሰብ የተወለደ መሐንዲስ ጓደኛዬ አንድ ወቅት ስለዚህ አመጋገብ ሲያስረዳኝ እኔ ተጸይፌ እንዳልጨነቅ ያደርገው የነበረውን ጥንቃቄ ሳይለውጥ በውትድርና ሕይወት አባቱ ያጋጠማቸውንና ሌላውም ቢመገብ ይጠቅማል ብሎ የሚመክረውን ከራሱ ተሞክሮ ጋር እያጣቀሰ እንዴት ሲነግረኝ እንደነበረ ሳስታውስ ከበዕውቀቱ ይልቅ ምን ያህል ጨዋ መሆኑን አደነቅሁኝ፡፡

 
መቼም ምንም የሚስተካከል ነገር የለንም ባልልም ‹‹ባህል›› ተብሎ ግን የተያዘን ነገር መተቸት ስሕተት ስለሆነ መንግሥታዊና መያድ ተቋማት እን£ ‹‹ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች›› ይሏቸዋል እንጂ ‹‹ጎጂ ባህል›› ማለትን ትተዋል፤ መሠረታዊ የነገረ ስያሜ /ተርሚኖሎጂ/ ስህተት ስላለበት ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ሃይማኖታዊ ቀኖናዎችን ለመተቸት መድፈር ‹‹የወረቀት ላይ ጀግና›› ከመሆን ካለፈ ‹‹የእርጎ ዝንብ››ነት ነው፡፡

 
የዚህ መጣጥፍ ዓላማ ‹‹ድንጋይ ዘመኑ›› ሙሴና ‹‹ICT›› ዘመኑ በዕውቀቱ ማን እንዳየ ወይም ማን እንደታወረ መዳሰስ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አዲስ አድማሶች ከወራት በፊት በብዕር ስም የላክሁላቸውን ከበዕውቀቱ የተሸለ ወቅታዊ ጽሑፍ ስላላወጡልኝ ይህንንም ያወጡልኛል ብዬ ስለማልጠብቅ ነው በዚች ማኅበራዊ ማዕድ ያቀረብኩት፡፡ አዲስ ነገር ጋዜጣ በመጨረሻ አካባቢ እትሟ እንዳለችው፣ ጋዜጠኛው ወንድሜም በሙያዊ ትንታኔው እንዳረጋገጠልኝ ‹‹የራሱ ዓላማ/ዝንባሌ የሌለው መገናኛ ብዙኃን ስለሌለ›› ለምን ነጻ ሆና የበዕውቀቱን ዝርክርክ ጽሑፍ እያስተናገደች የእኔን የተለፋበት ጽሑፍ አስቀረች አልልም፤ ስህተቱ የእኔ ሳይሆን አይቀርምና፤ ወደ ሐተታዬ፡፡

ሕገ ሙሴ
ከሙሴ ሕግ በፊት በኢትዮጵያ የተለያዩ የሥጋ አመጋገብ አማራጮች እንደነበሩ በዕውቀቱ ማስረጃ ያደረጋቸው ‹‹የሙሴ ድምጽ በማይደርስበት ቦታ ተሸሽገው የኖሩ እንደ ነገደ ወይጦ ያሉ ጥንታዊ ሕዝቦች…››  በማለት ነው፡፡ የ፫ኛ ዓመት የሳይኮሎጂ ተማሪ እያለ ፈጣሪውን የካደው በዕውቀቱ ቅዱሳንን ቢሳደብ፣ ሕገ ሙሴን ቢነቅፍ ላይገርም ይችላል፡፡ ነገር ግን ያመነበትን ሳይንሳዊ ሕግ ተከትሎ ታሪክን መተንተን ግን ግዴታ መሆኑን መዘንጋት ‹‹የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ፤ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ›› እንደሚባለው የሆነበት ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የኦሪቱን ባህል ይዘው የቀሩ እንዳሉ ማስረጃ ያለ ሲሆን ከኦሪት በፊት ሌላ የአመጋገብ ባህል የነበራቸውና በዚያው አመጋገብ የሚገኙ እርሱ እንዳለው  ዓይነት ብሔር የለም፤ ለዚህን ያህል ዘመን የሙሴ ሕግ የአደባባይ፣ የእነሱ ኑሮ ደግሞ የሽሽግ መሆን አያስፈልገውም፡፡ ጥቂቶች በልዩ ልዩ ችግር ጊዜ የተገኘውን በመብላት ራሳቸውን ካዳኑ በኃላ ለምደው የቀሩ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ በጥንቃቄ ተማምለውና ወስነው በጦርነት ጊዜ የተዉትን የምግብ ምርጫ ሥርዓት ከጦርነት በኃላ ይዘው ቀጥለዋል፡፡ ለምሳሌ እጅግ ቅባት የሚበዛባት ጃርት የምትወደድ ምግባቸው የሆነችላቸው በሸካና ካፋ ውስጥ አባል ጎሳ የሆኑት መንጃዎች በዚህ ሥርዓት አፍራሽነታቸው ከሕዝቡ ተገልለው እራሳቸው እንደ ርኩስ ይቆጠራሉ፡፡ በደቡብ ክልል እንደ ብሔር ሳይሆን የብሔር አባል የሆኑ ጎሳዎች ተመሳሳይ ሁኔታ አለ፡፡ የሸካ ብሔር ግራኝ አሕመድን ለመዋጋት ሲወጣ በጦርነት ውስጥ ያገኘውን ለመብላት መገደዱ ስለማይቀር ‹‹ቁርፌ ቁጶ›› በተባለ ሥርዓት ‹‹ቁርባኔን አላረክስም›› በማለት   ላለመርከስ ቁርባኑን በምራቁ ምሳሌ ለወንዝ አደራ ሰጥቶ ተዋግቶአል፡፡ የቆረበ በመሆኑ ክርስቲያን፣ ስለርኩሰት በማሰቡ ኦሪት ዐዋቂ ያደርገዋል፡፡ ጦርነቱ ሲፈጸም ደግሞ ሌላው ጎሳ ሁሉ ወደ ቀደመ ሥርዓቱ ሲመለስ የመንጃ ጎሳ ግን የበላው ተስማምቶት በዚያው አመጋገብ ቀርቶአል፡፡ እንግዲህ ጉዳዩ ይህንን መሰል ታሪክ አለማወቅ ጥሩ ጸሐፊ ለመምሰል ከመቀባጠር ያድናልና ጸሐፊ ብቻ ሳይሆን አንባቢም መሆን ግድ ነው፡፡
በነገራችን ላይ እኔም እንደ በዕውቀቱ በምህንድስና ሙያዬ ዲዛይን ላይ ድፍረት አበዛ እንደነበረ የገባኝ ፪ኛ ዲግሪዬን ስማር ነው፡፡ እያንዳንዱ ምሁራዊ ውሳኔ ከብዙ ንባብ፣ ምርመራና ንጽጽር በኃላ የሚመረጥና የሚተች እንጂ እንዳገኙ የሚሳለቁበት ነገር አለመኖሩን፤ በተለይ ኢትዮጵያዊ ጉዳዮች ላይ ለመጻፍ ደግሞ ‹‹ታሪክን በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ፣ ጥንታዊ ቋንቋና ስነቃልን /ፊሎሎጂና ፎክሎር/ በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ መውሰድ ብዙ እንደሚያበስልህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ከነዚህ አንድ ሁለቱን ተማር እባክህ›› ብዬ ልለምንህ፡፡ ከሠፈርህ የበቀሉትን ሐዲስ ዓለማየሁንና ዮፍታሔ ንጉሤን ካወቅሀቸው ደግሞ ጥንታዊ የሃይማኖት ትምህርት ምን ያህል በዕውቀት እንደሚያበለጽግ አለመረዳትህ አለማየት ወይም ማየት መሳን/ዕውርነት ያጋጠመህ ይመስላል፡፡

ሳይንስና ሳይንሳዊነት
ሳይንሳዊነት ብዙውን ነገር ‹‹ሳላይ አላምንም/ ማየት ማመን ነው›› ወደሚል ተጠራጣሪነት የሚወስድ የእምነት ተቃራኒ ሲሆን ሃይማኖት ግን ‹‹ሁሉን ዐዋቂ›› መሆን ያለበት ተመላኪ/አምላክ/ የሰጠውን መመሪያና ዕውቀት ‹‹ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዐን ናቸው›› በሚለው ሕግ ተቀብሎ በከለሩ እንደማይታወቀው ብርቱካን / በዕውቀቱ እንደነገረን ፖርቹጋላዊው ብርቱጋል-ብርቱካን/ ‹‹እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁት›› በመባሉ በምግባርና ትሩፋት፣ በአምልኮና ተጋድሎ አፈጻጸም እርሱን ወደማወቅ የሚወስድ መንገድ ነው፤ ሃይማኖት፡፡ በዕውቀቱ ስለምግብ ምርጫ የነገረን ቅድም እንዳልኩት ሆዳችንን መሙላት እንደቸገረን ‹‹ረሀብተኞች፣ ድሆች፣…›› የተባልንበት ታሪክ እንዲቀየር ካለው ጽኑ ፍላጎት ይመስላል፡፡ ሳይንሱ በላብራቶሪ ወይም ሳይንሳዊ አመክንዮ /ሎጂክ/ እስኪያስረዳ ድረስ ማንኛውንም ክስተት ወይም ኅላዌ በጥያቄነት የሚይዘው ሲሆን በሃይማኖት ግን ሁሉም ጥያቄዎች በመጀመሪያ የማመን ቅጽበት ተመልሰው በዕድሜ ውስጥና ኋላም በመንግሥተ ሰማያት እስኪገለጡ ልብ የሚያርፍባቸው ናቸው፡፡አሁን በድንግዝግዝ እናያለን…› እንዲል፡፡ ሳይንሳዊውን ምስክርነት ከማቅረቤ በፊት እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉትን የሚያተጋቸው የዕውቀቶች ሁሉ ምንጭ የሆነው ግእዝና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ምንጭ የሆነው ኢትዮጵያዊው የቁጥር ስሌት ዘዴ መሆኑን ሳስታውስህ ቀድሞ ያስመሰከረውን ሥልጣኔ ዛሬም እንዲደገም ‹‹ ሕዳሴ›› መባሉን በማስረጃነት በመጥቀስ ነው፡፡ እንዳንተ ያሉት ተናጋሪዎች ኢትዮጵያን የ፻ ዓመት ታሪክ ‹‹ባለክብር›› ቤተክርስቲያንን የቅኝ መግዣ መሣሪያ ከመሆን ጋር የኋላቀርነትና የሥልጣኔ አድኃሪነት ማዕከል አድርገው ከብሔረሰቦች ልብ ውስጥ ለማውጣት ሤራ የጎነጎኑት ኢሕአዴጎች ሳይቀር ‹‹ንስሐ ገብተዋል እንዴ;›› በሚያስብል ደረጃ ነባር ሥልጣኔ የነበረንና በታሪክ አጋጣሚ ያጣነውን ማንነት ዳግም የምንፈልግ የሕዳሴ ሠራዊት እንድንሆን ሲሰብኩን፣ ለፕሮፓጋንዳውም ማካሄጃ ‹‹የሕዳሴ ድልድይ፣ የሕዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያን ሕዳሴ እናበስራለን›› ወዘተ ሲሉ ምንያህል ገብቶአቸው እንደሆነ አላውቅም፡፡ ማጣቱም ማግኘቱም ከማያረካው ምዕራባዊ ከምትቀላውጥ በአንድያ ምርጫው ብቻ ልቡ ያረፈውን ኢትዮጵያዊ ጠባይ አክብር፤ በፈጣሪ ማመን፣ መታመን፡፡
ለነገሩ ‹‹ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ነው›› ይባል የለ፤ አለቃ ገብረሐና የነገሥታቱ አማካሪ ለመሆን ያበቃቸውን መጽሐፋዊ ዕውቀት ከያዙ በኃላ ለራሳቸው አድናቆትን፣ ለሕዝቡም ፈገግታን የሚያጎናጽፉ ቀልዶችን ሲያዘወትሩ ከርመው በሞታቸው መቃረቢያ ሐዲሳቱንና ብሉያቱን /መጻሕፍቱን/ሰብስበው ‹‹ተሳልቄባችኃለሁና ይቅር በሉኝ›› እያሉ ሲያለቅሱ እንደነበረ ታሪካቸው ይናገራል፡፡

መንፈሳዊውን ኢትዮጵያዊ ባህል መተቸት ትቶ ሳይንሳዊውን እውነታ ቢቃኝ የሚከተለውን እውነት ያረጋግጥ ነበረ፡፡ በሊ// ሙሴ የተከለከሉትና የተፈቀዱት እንስሶች ያላቸውን የጥቅም ልዩነት በሚቀጥለው ምንባብ ያስተውሉ፡፡ በዚያ ላይ አሁንም ሳይንሳዊ ሆኖ ለተጠራጠረ የተጠቀሱትን ምንጮቼን እንዲቃኝ ልጋብዝ፡፡

‹‹
መጽሐፍ ቅዱስና የሕክምና ሳይንስ›› በተባለ መጽሐፉ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ሠፊ ትንታኔ ምንጮችን ጠቅሶ ያቀረበ ሲሆን በአጭሩ ለመጥቀስ ያህል፡- እንዳይበሉ የተከለከሉት እንስሳት፣ አዕዋፋትና ዓሣት ለጤና ችግር በማጋለጥ፣ ራሳቸው ለበሽታ በመዳረግ፣ ለሌሎች ፍጥረታት ዕድገት መገታት ምክንያት የሆኑ ፈሳሾችን ከሥጋቸው በማፍሰስ ጎጂነታቸው በሳይንስ ምሁራን የተረጋገጠ መሆኑን በስፋት ገልጾል፡፡ /‹‹መጽሐፍ ቅዱስና የሕክምና ሳይንስ›› መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ፳፻፬ ገጽ 27-31 ሩሴል 1994 ገጽ 76-77 What does the bible teach about clean and unclean meats? What does Jesus eat? ገጽ 49-50 ibid], www.Gnmagazine.org/booklets/cu/matterofhealth.htm)
ከብዙ ጥናቶች ግንዛቤ በኃላ / ዊሊያም ‹‹… በመሆኑም ሰው አስቀድሞ ይኸንን ሕያው የኾነ የእግዚአብሔርን ቃል አስቀድሞ ቢያውቅና ቢረዳ ኖሮ ብዙ ችግርና ጉዳት ሳይደርስ በፊት አስቀድሞ መቆጣጠር በተቻለ ነበር›› ብለዋል፡፡ /Coder p.49, Modern Science & Christian Faith, 1948 p.191/ ለምርምሩ ቀረቤታ ያላቸው እንዲያጤኑት ዴቪድ አይ ማችት የተባለ ምሁር ከተለያዩ እንስሳት የትኩስ ጡንቻዎችና የሥጋ ጭማቂና በሰውነት ውስጥ የያዙትን የሚገኘውን የጨው መጠን በመጨመር ‹‹የሉፒነስ አልበስ›› የበቆልት የሥር ዕድገትን በመቶኛ ማወዳደር የሞከሩትንና ከግኝታቸው ጥቂቱን ለአብነት የሚከተለውን ሠንጠረዥ አቅርቤዋለሁ፡፡ የምርምር ዘዴያቸው በዘርፉ ‹‹ከዕፅዋት መድኃኒት የማውጣት ዘዴ›› በእንግሊዝኛው Phyto-pharmacology የሚባለው ነው፡፡

በዕውቀቱ ምራቁን የዋጠባት ጥንቸልን በተመለከተ ለአብነት ብናነሳ ሥጋቸውን መብላት ብቻ ሳይሆን ሲሞቱ መንካት እን£ ‹‹ቱላሬምያ›› በተባለ ገዳይ በሽታ ለመጠቃት አምስት በመቶ ያጋልጣል፡፡ የበሽታው መተላለፊያ ተሐዋስያን ልብስንም ለመውረር ጊዜ ስለማይወስድባቸው ከነኩዋቸው በኃላ ፈጥኖ ሰውነትንም ልብስንም መተጣጠብ ግድ ይሆናል፡፡

ታዲያ ማን ዐየ ወይስ ማን ታወረ ትላላችሁ? ሙሴማ ይህን ካወቀ እነሆ በዕውቀቱ $ ትውልድ ነው፡፡ ‹‹ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሶች የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው። ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።›› ብሏልና ዘሌ 01:-9-$ የርኩስና ቅዱስ ነገር ደግሞ በትጉሀኑ ይነበብና ፍረጃውን ይከተል፡፡


ማስታወሻ
መቼስ ሥርዓት አልባነት የሚያመጣው ስህተት ብዙ ነውና /የተ// አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን የጎነጠበትን፣ ሳይንቲስቶቹን ያመሰገነበትን፣ ኢትዮጵያዊነትን ያፈረበትን ሁሉ ብነካካ ደስ ባለኝ፤ አይመለከትህም ከሚለኝ በላይ ለማንበብ የሚደክመው ያሳዝነኛልና ልተወው፡፡ ‹‹አልፎ ሂያጁን ሁላ እንዲህ ለጋስ ያደረገው ምን ነበረ? እንደ ኤሊ በድንጋይዋ ሥር ተሸሽጋ የምትኖር ኢትዮጵያዊ Superiority Complex አለች›› ያልከው ተራ ሳንቲም ለቃቃሚ እንጂ ለጋዜጣው አንባቢ የማትጨነቅ መሆንህን ያረጋግጣል፡፡ እንዳንተ ያሉት ናቸው በፖለቲካቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያልደገፏቸውን ሁሉ ሞታቸውን እንዲመኙ የሚጠብቁና ሕዝቡ ከልቡ አዝኖ ሲወጣ ቅኑን ኢትዮጵያዊ አንዴ ፖለቲከኛ፣ ሌላ ጊዜ አላዋቂ፣ ካድሬዎች ደግሞ በእነሱ ጥረት ያዘነ ይመስል በሆቴል ቤት እን£ ከዓላዋቂ ሳሚው ሬድዮና ቲቪ በቀር እንዳይሰማ ሲከለክሉና በለቅሶ ፕሮግራሞች ሰዓት ሥራቸውንና ድርጅታቸውን እንዲዘጉ ሲያስገድዱ የነበሩት፡፡ ከጽንፈኛና ሁለት ብቻ ከምትሉት አማራጮቻችሁ ውጪ ሌላ አማራጭ እንዳለ የሚያስብ ልብ እንድታገኙ ብዙ እንድታነቡ/እንድትማሩ እያሳሰብኩ እጸልይላችኃለሁ /ከቻልኩ/፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴማ በሙስሊሙም ሙሳ ተብሎ በዓለም ደረጃ ትምህርቱ ለ፴፭፻ ዓመታት የዘለቀ መከበር ያለው፡- ‹‹ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ነው፤ ላጥፋውና በሌላ ታላቅ ሕዝብ ላይ እሾምሀለሁ›› ሲባል ‹‹ ሕዝብህን ከምታጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍህ ደምስሰኝ›› ያለ የመሪዎች ምሳሌ መሥዋዕት /ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስቴራችን አደረጉት እንደሚባለው/፣ አስቦና ዐቅዶ ከሚሠራው ጀምሮ በቸልተኝነት እስከሚፈጸመው፣ ከወንጀል ነክ እስከ ፍትሐ ብሔር፣ ከፍትሕ መንፈሳዊ እስከ ፍትሕ ሥጋዊ ድረስ የሚያካልሉ ሕግጋትን ያዘጋጀ የሕግ ላይብረሪ፣ ምድራዊ ሁሉ መርምሮ ያልደረሰበትን ዕውቀት ፈጽሞ ‹‹ወነበቦ፣ ወነበቦ›› እያለ 570 በላይ የእግዚአብሔርን እስትንፋስ ጽፎ ያኖረና ኋላም ስለሰው ፍቅር ሰው የሆነውን ክርስቶስ በባሕርይ ክብሩ ለማነጋገር የተመረጠ የደብረታቦር የባሕርዩ ምስክር፣ ‹‹የፈርዖን የልጅ ልጅ መባልን ሳይሆን ከወገኖቹ ጋር መከራን መቀበልን መረጠ›› የተባለለት ሀገርና ሕዝብ ወዳድ ምሁር፣
‹‹
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል›› ያለውን ኢትዮጵያዊ ካህን ዮቶር ሳይንቅ መሪ ሳለ ምክር የተቀበለና የፍትሕ ሥርዓቱን ያሻሻለ ትሑት ባለሟል ነው፡፡

 
በናባው ተራራ ባረፈበት የካቲት 17 ቀን በየዓመቱ ስንዘክረው ‹‹ርሑቅ ሕይወት እምኃጥአን …›› እያልን በሌሊቱ ምስባክ መድኃኒት ከኅጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና። አቤቱ፥ ቸርነትህ እጅግ ብዙ ነው፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ። ያሳደዱኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፤ ከምስክር ግን ፈቀቅ አላልሁም። ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።
‹‹
አርአየ ፍናዊሁ ለሙሴ…›› እያልን በጉን ክርስቶስን በምንሰዋበት የቅዳሴ ምስባክ ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን። እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ።ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም። እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
 …
እያልን ትምህርቱንና ሕይወቱን እናስባለን፡፡ የማልዋሽህ ግን ታላቁን መምህር እንዲህ ስትዳፈር ነፍሴ እንዴት እንደተቆጣች ብታይ ምንያህል ታግሼ ጽሑፍ ለማዘጋጀት እንደተጋሁ ትረዳኝ ነበረ፡፡ አያያዝህ ግን ነውረኛ ነውና ከዚህ በኋላ በሌሎች ቅዱሳን ላይ እንዲህ ያለ ድፍረት እንዳትሞክር ማስጠንቀቅ ሳይኖርብኝ አይቀርም፡፡ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን ፈጽሞ በአደባባይ ስሟን እንዳትጥራ፤ አደራ ታስቀይመኝና አስቀይምሃለሁ፡፡ በዐለትነቱ ሥር በተሸሸገችው ኢትዮጵያ እየኖርክ ‹‹በባህርዩ ክቡር ክርስቶስን ብትንቀው ‹‹በዐለቱም ላይ ለሚወድቅ፣ ዓለቱም ለሚወድቅበት›› ይቀጠቅጠዋልና ለድንጋይ አስተሳሰብህ የመዳን ውሀ ከምንጩ እንዲያጠጣህ የድንጋይ ያይደለ የሥጋ ልብ ግዛ፡፡

 
ምክር
ለአቅመ መናቅ ‹‹ደርሰህ›› የናቅሀቸው እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ እንዳሉት ‹‹በኢትዮጵያ ላይ ክፉ አትናገር፤ ክፉ አትስማ፤ ክፉ አታስብ››  ለኢትዮጵያ ገና ምንም ሳታደርግላት ባለውለታዎን አታዋርድባት፤ ከዓለም ወደኃላ የቀረች ቢመስልህም አንተን ጨምሮ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነች ሀገር ነችና ዕድሜህን ሳትፈጅ በወጣትነትህ ዕወቃት፤ ኋላ በማይጠቅም ሰዓት ባንነህ እንዳትጸጸት፤ አደራ፡፡

ከሔኖክ ጀምሮ በሙሴና በሌሎችም ነቢያት በተተነተነው የቁጥር ስሌት መሠረት ፳፻፭ ዓም ብዙ የሚበላበት የጥጋብ ዓመት ስለሆነ በምታውቅበት አበላል በደንብ ተዘጋጅ፡፡ በእኔና በአንተ ጥፋት በታሪክ እጅግ የከፋው ረሀብ የሚከሰትበት ዓመትም ይኼ ዓመት ሊሆን እንደሚችል ሳረዳህ -Superiority Complex- ታግሰህም ቢሆን ገንዘብ ለማጠራቀም የምትሽቀዳደም ስለሚመስለኝ ራስ ወዳዶች በዚህ ዓይነት ዘመን የበለጠ ትከፋላችሁና ታስፈራላችሁ፡፡

እስኪ ቸሩ ፈጣሪ እንደምሕረቱ ብዛት ይቅር ብሎ አዲሱን ዓመት ወደልባችን የምንመለስበት፣ ሀገራችንም ቤተክርስቲያናችንም መሪዎቻቸውን በሰላም የሚሾሙበት ያድርግልን፡፡

18 comments:

  1. በሕይዎቴ ብዙ ደናቁርትን አይቻለሁ፡፡ አንተን የመሰለ ደንቆሮ ግን ገጥሞኝ አላውቅም፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. the only dormant on the planet is you and only you so far,u saw such dormant on your life spane but they are much -much better than you,so the only thing what i advise you like and adrgen,you have to reconsulat your self ,you have eye but u are totally blined and u have ear but u can't leasson then u are totaly deaf that is why and adrgen told u the reality.but i can promisse u that we are pray for you for ever but u have to learn from your failer.

      Delete
  2. Bezu eweroch alu gobezz andeadrigen!
    lemsale sele Germany Abayatkerstyanat gude ena germany yalu Krstyan nen Kahen nene Menkosat nen Diakonat Nen yemilu bezu eweroch alu
    ezih laye yemeleketut!

    http://ewenetaw.blogspot.de/2012/09/blog-post.html




    thanks

    ReplyDelete
  3. ቀሲስ ወንድምስሻ - መልካም ጽሁፍ ነው። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎ።

    በእውቀቱ ስዩም የሚባለውን ጋዜጠኛ/ ገጣሚ አንዳንድ ጽሁፎቹን አነበብኩ። እሱ ወጣት በመሆኑ የሚጠቅም እና የማይጠቅመውን ገና ለይቶ ያወቀ አይመስልም። ለሱ የመንደር አሉባልተኛነት በመንደር አድናቂዎችን ስላፈራለት ሙያ አድርጎ ሊይዘው ያሰበ ይመስላል። እንደ እሱ አይነት ብዙ ወጣቶችን አውቃለሁ። እኔ ያዘንኩት ግን አእምሮ የጎደላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን በመኖራቸው ነው። ብዙዎች እንክርዳዱን ከስንዴ መለየት የማይችሉበት ዘመን ደረሱ ወይ? ጋኖች አለቁና እንድሚባለው ሆነ እኮ።

    ሃገራችን “ከዓለም ወደኃላ የቀረች ቢመስልህም አንተን ጨምሮ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነች ሀገር ነችና ዕድሜህን ሳትፈጅ በወጣትነትህ ዕወቃት፤ ኋላ በማይጠቅም ሰዓት ባንነህ እንዳትጸጸት፤ አደራ፡፡” ያሉት ጥበብ ያለው ምክር ነው። በውቀቱ ስዩም ምክርዎትን ሰምቶ ልብ ቢገዛ ይገነባበታል።

    ReplyDelete
  4. ደስታ ወገኛውSeptember 19, 2012 at 4:28 AM

    በፌስ ቡክ የሰጠኋቸውን አስተያየት እዚህም ላይ ማስቀመጥ ፈለግኩ:: የአንድ አድርገን ጦማሪ ተገቢ ነው ካላችሁ አውጡት:: ካላመናችሁበት የእናንተን መስፈርት ስለተላለፍኩ አስቀርታችኋል ብዬ ራሴን ከወዲሁ አሳምናለሁ::


    "የእርስዎም ምላሽ አልገባኝም :: በድፍረትም ልናገርና ትክክል አይደለም:: "አውቃለሁ" ባይና ብዙ ቅድመ ዝርዝሮችን ከመሰንዘር ያለፈ አንኳር ነጥቡን አልገለጹም:: "ከኃይማኖት ጋር ፍቺ ገጥሜአለሁ" ከሚል ሰው ጋር ይህን ያህል መዛለፍም እምብዛም ተገቢ ነገር አልነበረም:: ያም ሆኖ የእርስዎ አጻጻፍ እንዲያውም ስሜታዊነትና ማስፈራሪያ እጅግ ገንኖ ይንጸባረቅበታል:: ከስሜታዊነትዎትም የተነሳ አንዳንዶቹ አገላለጽዎት እየተጣረዙ መጡብኝ ወደ መጨረሻው አካባቢ::
    ለምሳሌ እጠቅሰዋለሁ:-
    "ከሔኖክ ጀምሮ በሙሴና በሌሎችም ነቢያት በተተነተነው የቁጥር ስሌት መሠረት ፳፻፭ ዓም ብዙ የሚበላበት የጥጋብ ዓመት ስለሆነ በምታውቅበት አበላል በደንብ ተዘጋጅ፡፡ በእኔና በአንተ ጥፋት በታሪክ እጅግ የከፋው ረሀብ የሚከሰትበት ዓመትም ይኼ ዓመት ሊሆን እንደሚችል ሳረዳህ ከ-Superiority Complex-ህ ታግሰህም ቢሆን ገንዘብ ለማጠራቀም የምትሽቀዳደም ስለሚመስለኝ ራስ ወዳዶች በዚህ ዓይነት ዘመን የበለጠ ትከፋላችሁና ታስፈራላችሁ፡፡"

    እዚህ ላይ የኢትዮጵያው ፳፻፭ የጥጋብ ዘመን ነው እያሉ እጅግ የከፋ ረሃብም ይከሰታል የሚል ተቃራኒ ነገርም አንጸባርቀዋል:: ይህንን ያሉበትን ምክንያት የሚያብራራ አስተማሪ መልዕክት ቢያካትቱበት አንድ ነገር ነው አለበለዚያ ከስሜት ሳይወጡ እየጻፉ ነው ማለት ነው::

    ከካድሬና ከዘመኑ ፖለቲካ አራማጆች ጋርም እጅግ የተጣሉ ይመስላሉ:: ብዙ ያነበቡና ብዙ ያወቁ ቢመስሉም መግለጹን አልቻሉበትም በእኔ ሚዛን::ቅዱሳንን የመሳደብ ክፋቱን ከመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ከኃይማኖትዎት አንጻር ምክር አዘል መልዕክት ጋር ቢያብራሩ ለእኔ አሳማኝ ነው:: እንደ ክህነትዎና እንደ እምነትዎ ጸሎት አደርግለታለሁ የሚሉትን ሰው የማስተማር ፍላጎት ሳይሆን ለመሞገት ሙከራ ያደረጉ ነው የሚመስለው የእርስዎ ጽሑፍ:: በዕውቀቱ አንዴ አልሰማም ብሎ የመጣለትንና ያመነበትን (እኔና እርስዎ የማናምንበትን) የሚጽፍ በዚያም የምድራዊ ኑሮውን የሚመራ ሰው መሆኑን በገሀድ እየተናገረ የእርስዎ አገላለጽ ደግሞ “ካህን ይሳዳባል እንዴ?” የሚያስብል ነው::

    ሌላው በዕውቀቱ ያላወቀው አንኳር ነገር ነበረ:: ጥሩ ምሳሌ ግን ባለፈው ሊቢያ ላይ የሞቱት የአሜሪካው አምባሳደር “the innocence of muslim” የሚለው የሙስሊሞቹን “ነብዩ ሙሐመድ”ን ያንኳሰሰ ፍልም መሆኑን የሰማ አይመስለኝም:: ያም ሆኖ በዕውቀቱ ለምን ጻፈ ልንለው አንችልም፤ የዩትዩብ ድረ ገጽም “the innocence of muslim” የሚለውን አላነሳም ያለው “የመጻፍ መብቱ ነው (freedom of speech)” ብሎ እንደሚሟገተው ሁሉ:: እኔም ለእርስዎ ያለኝ ነጥብ ኃይማኖቱ ውስጥ እንዳለ ሰውና የኃይማኖቱ አስተማሪ እንደመሆንዎት መጠን (ቄስ ነዎትና ) የበዕውቀቱን ሃሳብ በማስረጃ እየገለጹ ቢያቀርቡ እሱን ሊሞግት እኔንም ሊያስተምር ይችላል::

    በዕውቀቱ ስዩም የሚጽፈው በአማርኛ ነው:: ፊደላቱን ያገኘው ግን እነዚያን እሱ የሚያንቋሽሻቸውን ከሚታዘክር ቅድስት ቤተክርስቲያን ነው:: እነዚህን መሰል ምሳሌዎች እያነሱ ያልዎትን ዕውቀት እያጣቀሱ እንደመጻፍ ብዙ የሚያሳዝኑ ቃላቶችን ተጠቀሙ እርስዎ:: እርሱን መሞገት እንጂ አንባቢዎትን ያከበሩ አይመስለኝም::

    የእኔን ቃላት አጠቃቀም ሳይሆን የአስተያየቴን መልእክት ቢረዱ ደስ ይለኛል:: አመሰግናለሁ::"

    ደስታ ወገኛው ነኝ::

    ReplyDelete
  5. wow Kesis Wendemsha
    It excellent way of explanation well done. Excellent response, Egziabhere endenate yale Abat Ayasatan.

    ለአቅመ መናቅ ‹‹ደርሰህ›› የናቅሀቸው እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ እንዳሉት ‹‹በኢትዮጵያ ላይ ክፉ አትናገር፤ ክፉ አትስማ፤ ክፉ አታስብ›› ለኢትዮጵያ ገና ምንም ሳታደርግላት ባለውለታዎን አታዋርድባት፤ ከዓለም ወደኃላ የቀረች ቢመስልህም አንተን ጨምሮ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነች ሀገር ነችና ዕድሜህን ሳትፈጅ በወጣትነትህ ዕወቃት፤ ኋላ በማይጠቅም ሰዓት ባንነህ እንዳትጸጸት፤ አደራ፡፡

    እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉትን የሚያተጋቸው የዕውቀቶች ሁሉ ምንጭ የሆነው ግእዝና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ምንጭ የሆነው ኢትዮጵያዊው የቁጥር ስሌት ዘዴ መሆኑን ሳስታውስህ ቀድሞ ያስመሰከረውን ሥልጣኔ ዛሬም እንዲደገም ‹‹ ሕዳሴ›› መባሉን በማስረጃነት በመጥቀስ ነው፡፡

    ReplyDelete
  6. Dear Kesis Wendmisha Ayele

    Every one can understand what u wrote,
    u pass ur message to us, tanx for that.

    Be Eweketu , started his way of explanation by eating rabbit is a good way of habit, በዕውቀቱ ምራቁን የዋጠባት ጥንቸልን በተመለከተ ለአብነት ብናነሳ ሥጋቸውን መብላት ብቻ ሳይሆን ሲሞቱ መንካት እን£ ‹‹ቱላሬምያ›› በተባለ ገዳይ በሽታ ለመጠቃት አምስት በመቶ ያጋልጣል፡፡

    The next he insult የማልዋሽህ ግን ታላቁን መምህር እንዲህ ስትዳፈር ነፍሴ እንዴት እንደተቆጣች ብታይ ምንያህል ታግሼ ጽሑፍ ለማዘጋጀት እንደተጋሁ ትረዳኝ ነበረ፡፡ አያያዝህ ግን ነውረኛ ነውና ከዚህ በኋላ በሌሎች ቅዱሳን ላይ እንዲህ ያለ ድፍረት እንዳትሞክር ማስጠንቀቅ ሳይኖርብኝ አይቀርም፡፡ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን ፈጽሞ በአደባባይ ስሟን እንዳትጥራ፤ አደራ ታስቀይመኝና አስቀይምሃለሁ፡፡ በዐለትነቱ ሥር በተሸሸገችው ኢትዮጵያ እየኖርክ ‹‹በባህርዩ ክቡር ክርስቶስን ብትንቀው ‹‹በዐለቱም ላይ ለሚወድቅ፣ ዓለቱም ለሚወድቅበት›› ይቀጠቅጠዋልና ለድንጋይ አስተሳሰብህ የመዳን ውሀ ከምንጩ እንዲያጠጣህ የድንጋይ ያይደለ የሥጋ ልብ ግዛ፡፡
    Please I have send u the link which the western called themselves professor , Doctor , look what they come up today's idea , very very sad , I am afraid "Beewkwtu u are going to follow the same way as ur western freinds.

    http://nz.news.yahoo.com/a/-/world/14893067/early-christians-believed-jesus-wed-harvard-expert/
    'Wife' of Jesus theory attracts scepticism

    ማጣቱም ማግኘቱም ከማያረካው ምዕራባዊ ከምትቀላውጥ በአንድያ ምርጫው ብቻ ልቡ ያረፈውን ኢትዮጵያዊ ጠባይ አክብር፤ በፈጣሪ ማመን፣ መታመን፡፡
    ለነገሩ ‹‹ከታሪክ የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ነው›› ይባል የለ፤

    'Ejig Meremir yadersal kemot'Be Ewketu becareful, becareful for urself and for ur soul , pls don't mix religion with advancement .

    VATICAN CITY (AFP) - A US professor has caused a sensation in Rome where she spoke about an ancient papyrus fragment that refers to the "wife" of Jesus, but the theory that Christ could have been married is seen with great scepticism in the Vatican and by historians.

    Professor Karen King, who teaches at Harvard Divinity School, spoke about the existence of an ancient Coptic Christian scroll from the fourth century measuring 3.8 centimetres by 7.6 centimetres which contains the words: "Jesus said to them, my wife."

    During a congress on Coptic studies she put forward the theory that some early Christians believed Jesus was married.

    She added that this "doesn't prove that Jesus was married" but hinted that the question was being raised at the time, even though Christian tradition assumed as a fact that Jesus was not married.

    ReplyDelete
  7. "From the very beginning, Christians disagreed about whether it was better not to marry, but it was over a century after Jesus' death before they began appealing to Jesus' marital status to support their positions," she added.

    The professor also cautioned that the authenticity of the document still had to be verified with tests on the ink.

    Contacted by AFP, Vatican spokesman Federico Lombardi refused to call into question King's competence as a historian but said that "we do not really know where this little scrap of parchment came from."

    "This does not change anything in the position of the Church which rests on an enormous tradition, which is very clear and unanimous" that Jesus Christ was not married, he said.

    "This changes nothing in the portrayal of Christ and the gospels. This is not an event that has any influence on Catholic doctrine," he said.

    A professor at the Protestant Faculty of Theology in Paris, Jacques-Noel Peres, pointed out the text was from a relatively late period.

    "I have never read texts from any preceding period which spoke about the veracity of Jesus being married," Peres said.

    The professor added that in the language of the time "wife does not necessarily mean spouse."

    He quoted the famous phrase from the Bible in which Jesus spoke to his mother at the marriage at Cana saying: "Woman, why turn to me?" underlining that the reference could come from this passage.

    Some historians said the script could come from gnosticism -- a doctrine that was popular in the second century -- which was very marginal and in disagreement with the Church and whose texts were exaggerated.

    The editor of the Vatican's official daily Osservatore Romano, Professor Giovanni Maria Vian, a specialist in the history of the early Church, said he doubted the authenticity of the fragment which could be a fake sold as a genuine article to get a higher price since "the theme raises popular interest."

    "There is a business in fakes in the Middle East," Vian said, adding that in the United States there had been "an attempt to create a buzz around this case."

    Citing expert observations, he said that the writing on the papyrus is "personal writing" whereas a Codex would have been written in a "very rigid" way resembling a printed text.

    "Church tradition has no mention of a wife of Jesus. All the historical indications are that Jesus was unmarried. It is clearly said that Saint Peter was married. So why hide this for Jesus?" Vian said.

    Vian said that if the text were indeed from that period it could be a fragment from an apocryphal gospel inspired by gnosticism translated into the Coptic language.

    The apocryphal gospels, which were presented as coming from the entourage of Jesus Christ, flourished in the early centuries of Christianity.

    Sorry for my way of writing just to pass my message.

    ReplyDelete
  8. "From the very beginning, Christians disagreed about whether it was better not to marry, but it was over a century after Jesus' death before they began appealing to Jesus' marital status to support their positions," she added.

    The professor also cautioned that the authenticity of the document still had to be verified with tests on the ink.

    Contacted by AFP, Vatican spokesman Federico Lombardi refused to call into question King's competence as a historian but said that "we do not really know where this little scrap of parchment came from."

    "This does not change anything in the position of the Church which rests on an enormous tradition, which is very clear and unanimous" that Jesus Christ was not married, he said.

    "This changes nothing in the portrayal of Christ and the gospels. This is not an event that has any influence on Catholic doctrine," he said.

    A professor at the Protestant Faculty of Theology in Paris, Jacques-Noel Peres, pointed out the text was from a relatively late period.

    "I have never read texts from any preceding period which spoke about the veracity of Jesus being married," Peres said.

    The professor added that in the language of the time "wife does not necessarily mean spouse."

    He quoted the famous phrase from the Bible in which Jesus spoke to his mother at the marriage at Cana saying: "Woman, why turn to me?" underlining that the reference could come from this passage.

    Some historians said the script could come from gnosticism -- a doctrine that was popular in the second century -- which was very marginal and in disagreement with the Church and whose texts were exaggerated.

    The editor of the Vatican's official daily Osservatore Romano, Professor Giovanni Maria Vian, a specialist in the history of the early Church, said he doubted the authenticity of the fragment which could be a fake sold as a genuine article to get a higher price since "the theme raises popular interest."

    "There is a business in fakes in the Middle East," Vian said, adding that in the United States there had been "an attempt to create a buzz around this case."

    Citing expert observations, he said that the writing on the papyrus is "personal writing" whereas a Codex would have been written in a "very rigid" way resembling a printed text.

    "Church tradition has no mention of a wife of Jesus. All the historical indications are that Jesus was unmarried. It is clearly said that Saint Peter was married. So why hide this for Jesus?" Vian said.

    Vian said that if the text were indeed from that period it could be a fragment from an apocryphal gospel inspired by gnosticism translated into the Coptic language.

    The apocryphal gospels, which were presented as coming from the entourage of Jesus Christ, flourished in the early centuries of Christianity.

    Sorry for my way of writing just to pass my message.

    ReplyDelete
  9. Bewuketu kezihe befit Tsadiku Tekilehaymanotin bemezilefu and wetat beTekilye kelid alawukim bilo endemetaw sinager semichewalehu, yihn kaweke sewun bemaskotat masitemar aychalimna, Haymanotawe yehonu gudayoch lay gebito kemezebarek yilik be Mahiberawe gudayoch lay atikoro yetesetewun yesinetsihuf tsega bitekemibet hagerinm rasunm yitekimal biye aminalehu.

    ReplyDelete
  10. Hi Bewketu, you are always happy of insulting those who are blessed with God. This is the habit of people whose heart and mind is occupied with Devil. I recommend you to repent soon. If you continue to insult saints and our church your punishment will be heart breaking. Lib Yistih!

    ReplyDelete
  11. ለቄሱ መልስ የሰጠህ መስሎህ ከደንቆሮ ጋር ልትገሰጽ የተጋኸው ደስታ ወገኛው ሆይ ምነው ቄስ ቄስ ማለት አበዛህ፣ቄሱ ከካህን አንደበት ሊወጣ የሚገባውን ቅንአት እና ትሕትና የተሞላበትን ተግሳጽ አበርክተዋል።አንተም በወገንህ በመሐመድ ላይ የነቀፋ ፊልም የሰሩ እና ሊቀ ነቢያት ሙሴን የዘለፉ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው እንዲከበር ብለህ በልማደኛው አደናጋሪ ብዕርህ ሞጫጭረሃል ያንተን በዚህ ላብቃው እና ደንቆሮው በውቀቱ ሆይ ደንቁርና የዕውቀት ተቃራኒ ሆኖ ሳለ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የደነቆረውን ሰው በውቀቱ ብሎ ከመጥራት በግብርህ ደንቆሮ ብሎ መጥራት ተገቢ ነው፣ይልቅ የደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ወጣቶች ያበረከቱልህ የዲሲፒሊን ትምህርት ክፍል ሁለት እንደሚያስፈልግህ ይታየኛል።
    ሳምሶን ነኝ ከካናዳ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ውድ Anonymous አንተም መጻፍህ ልክ ነው:: ነገር ግን ከምንገለገልባቸው የመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ የአዋልድ መጻሕፍት አንድብ ቦታ ላይ የሰውን ልጅ ተሳደብ የሚል ነገር ብትጠቅስልኝ ደስ ይለኝ ነበረ:: እኔ ለቄስስ ወንድምስሻ የሰጠሁት ምላሽ ስድብ የለበትም::አለመስማማቴን መናገር የግል አገላለጽ እንጂ የስድብም አይደለም:: ተመልሰህ ማንበብ ትችላለህ:: አንተ እንዳልከው "ቄስ ቄስ. . ."ም ብዬ ልኮንናቸው አልሄድኩም፤ "ቄስ ቄስ" ብላቸውም ክህነታቸው ነውና የሚያኮራ እንጂ የሚያስነቅፍም አይደለም (የታደለ ሰው ነውና ለዚያም የሚመረጠው):: እንዳንተ ግን እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ሰው "ደንቆሮ" ብዬ አልሳደብም:: እንደምረዳው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታይ ነህና ከመቼ ወዲህ ነው በዚህ ኃይማኖት ውስጥ እንደዚህ የስድብን አንደበት የተማርከው? የትኛው የቤተክርስቲያኒቷ ስርዓት ውስጥ ነው ይሄ ዘለፋ ያለው? አንተስ ብትሳደብ ከተሳዳቢው በምን ተሻልክ? የገደለ ይገደል ዓይነት ስሜታዊነትህን ትተህ ትምህርቱን አጣቅሰህ የበዕውቀቱን ጥፋት በአሳማኝ አነጋገር ብትገልጸው በደንብ ታሳምነኝ ነበረ:: አሁን ግን የዕውቀት ማነስ ውስጥህን ሰቅዞ ስለያዘው ግልፍ ብለህ ወደ ስድብ ትሮጣለህ:: አዋቂ ሰው ጽፎ ለሰሚ ያደርሳል እንጂ "ድንቆሮ" ብሎ ግን አይሳደብም:: አዋቂ ሰው ደንቆሮን ማስተማር ይችላል:: ደንቆሮን ከተሳደበ ግን ያው እሱም አብሮ ደንቁሯል ማለት ነው:: እናም የእኔ ወንድም ወደድንም ጠላንም መጻፍ መብት ነው:: መሞጫጨረ ከደነቀህ ቢያንስ አንተ ጋ መድረስ ችያለሁና በመጻፍ መብታችን መነጋገር ችለናል ማለት ነው:: ኃይማኖትህን ሳታውቅ ከኃይማኖትህ አስተምሮ ውጪ የሆነ ነገር አታድርግ:: ወንድማዊ ምክሬም ነው::

      Delete
    2. መልካም ነው ቀሲስ ጥሩ መልእክት ነው እኔ ደግሞ በማትረባው እውቀቴ አንድ ነገር ልበል
      የሰቱን ት/ት መልካም ሁኖ እያለ ትንሽ ስሜታዊነት ያለበት ይመስለኛል እንደ አባት ቀስ አድርገው አባታዊ ምክር /ተግሳጽ
      ቢሰቱት መልካም ነው

      Delete
  12. but why bewketu nevet write anyththing about muslim leaders like muhammed?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Nice question which I should ask myself too.

      Delete
  13. wow betam egziabeher yakbereh ategabi yehone mels new. endante ayenetu 1,2 echi hager binorat yet bederesen neber,,,egziabeher yakbereh

    ReplyDelete
  14. Wndeme be ewenet egziabeher yakberelegn ende ante ayenet bezu ethiopiawi yasfelegenal enam endezih ayenet temesasay yehonu tsehufochen betawtalen des yelenal beteley ende bewketu ayenet betekeretianachen lay yetenesuten sewoch asfelagiwen melash endetesetelen fekadh yehun ahunm bedegami egziabeher yakberelen

    ReplyDelete