Saturday, September 1, 2012

የፓትርያርኩ ቀብር ላይ ትልቁ ስህተት



(አንድ አድርገን ነሐሴ 27 2004 ዓ.ም)፡-ፓትርያርኩ ቅዳሴውን አቋርጠው ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዳሴውን አቋርጠው ከዚህኛ ዓለም ወደዚያኛው ዓለም ከሄዱ ቀናት ተቆጥረዋል ፤ ቤተመንግሰቱም ሆነ ቤተክህነቱ አስጨናቂ የሆነ የሀዘን ድባብ ወርሶታል ፤ የፓትርያርኩ አስከሬን ለ6 ቀናት አፈር ሳይቀምስ ሲቆይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ለ13 ቀናት ያህል ቆይቷል ፤ የፓትርያርኩን ሥርዓተ ፍትሐት ላይ የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ፤ የግብጽ ኦርቶዶክስ ፤ የአርመንና የህንድ ኦርቶዶክስም ጸሎተ ፍትሀት አድርገዋል ፤ ከእነዚህ አብያተክርስትያናት ጋር የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ እምነት የዶግማና የእመነት አንድነት ስላላት  ጸሎተ ፍትሀት ማድረጋቸው በስርዓተ ቤተክርስትያናችን ተቀባይነት አለው፡፡ 

በእጅጉ የሚገርመው ደግሞ የእመነትና የዶግማ አንድነት የሌላቸው ከእኛ ጋር የማይቀድሱና የማይቆርቡትንም የግሪክ ቤተክርስትያን ተወካይ መሪዎችን ጸሎተ ፍትሀት እንዲያደርጉ መጋበዙ ስርዓተ ቤተክርስትያንን ያፋለሰ ነው፡፡ በወቅቱ ለሚመለከታው ክፍሎች ጉዳዩ እንዲደርሳቸው ቢደረግም ግሪኮቹ እንዳያኮርፉ በሚል ሰበብ አንድ ኢትዮጵያዊ ሊቀ ጳጳስ አዘዋል ተባለ ፤ ይህ በጣም ያሳዝናል ያስቆጣልም ፡፡ በርግጥ ማንኛውም  ዓይነት ያለው ማህረሰብ ሁሉ ሀዘኑን በአግባቡ መግለጥ ይችላል ፤ ለምሳሌ የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤ ሼህ አህመዲን አብዱላሂ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በግላቸው የገለጹ ሲሆን በወከሉት ተቋም ስም ደግሞ የሀዘን መግለጫ አሰምተዋል ፤ ይህ በእጅጉ ትክክለኛ የሆነ አካሄድ ነው ፤ የሃይማኖቶችን ወንድማማችነት የሚያሳይ ነው ፤ የሃይማኖቶቹ መልካም መገለጫቸውም ጭምር ነው ፤ ጥቂት ሙስሊሞች በጊዜው ከክርስትያኑ እኩል ነጭ ቆባቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ደፍተው የአቡነ ጳውሎስ ቀብር ላይ ሲታደሙ መመልከት ራሱ ውስጥን ደስ ከማሰኝት በተጨማሪ ያላቸውን ቁርኝት ያመላክታል ፤   በተመሳሳይ የቫቲካን ቤተክርስትያን ፤ የኖርዌይ ቤተክርስትያን እና የመላው አፍሪካ አብያተክርስትያናት  ጽህፈት ቤትና የዓለም አብያተክርስትያናት ጽ/ቤት ተወካይ ያሰሙት የሀዘን መግለጫ ምንም እንኳን ትርጉሙ ለማህበረሰቡ ያስተላለፈ ባይሆንም  በቋንቋቸው እንደሰማነው የቅዱስ ፓትርያርኩን ዓለም ዓቀፋዊ ስብዕና የመሰከረ መሆኑን ብዙዎች በዕለቱ የመሰከሩት ነው፡፡

የግሪክ ቤተክርስትያንም ልክ እንደዚሁ ስለ ቅዱስነታቸው ምስክርነት እንዲሰጡ መጋበዝ ሲገባ ነገር ግን ጸሎተ ፍትሀት እንዲያደርሱ ማድረግ ከየት የመጣ ሥርዓት ነው ? በዚህ ሁኔታ ውስጥ አቡነ ጳውሎስ በህይወት ቢኖሩ ይወቀሱበት ነበር ፤ እሳቸው ግን ተያዙ ፤ ተገነዙ ፤ ያልተያዙት  በአውደ ምህረት አዘዙ  ፤ ተናዘዙ ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የእምነት ልዩነትና የግሪክ ክርስትያኖችን ልዩነት አለማወቅ ወይስ ትርጉሙ ምንድነው ? በሌሎች አማኞች ጸሎተ ፍትሀት እንዲደረግ ማድረጉ ትርጉሙ በሥጋ የተለዩንን ፓትርያርክ የሚመለከት ? ወይስ በሕይወት ያሉትን ሥርዓት አስፈጻሚ የሚመለከት ? ይህን ጥያቄ የሚመልስ ማነው ? ለዚህ ሁሉ ሊወቀስ የሚገባው ማነው ? 

ነፍሳቸውን ይማርልንና አቡነ ጳውሎስ ሲሾሙ ጀምሮ በስርዓተ ቤተክርስትያን መፋለስ ምዕመኑ ጉርምርምታ ነበረው ፤ አሁንም ገና ቀድመው የነበሩት ፓትርያርክ ይምጡ ወይም ቀጣዩ አባት  ሳይታወቁ ይህን የመሰለ ትልቅ ስህተት መስራት ተገቢ አይደም ፤ ከዓመታት በፊት መረጃዎች እንደ አሁኑ ጊዜ የመረጃ ቴክኖሎጂው ባልተስፋፋበት ጊዜ በሰሚ ሰሚ ነበር ተጨምረው ፤ ተቀንሰውና ዘግይተው ነበር ሰዎች ዘንድ የሚደርሱት ፤  አሁን ግን እንኳን የተደረገው ይቅርና ሊደረግ የታሰበው ነገር ምዕመኑ ዘንድ ለማድረስ በቀላሉ የሚቻልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል ፤ ስለዚህ ስህተት ሰርቶ መሸፋፈንም ሆነ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ስለማይቻል ወደፊት ያሉ ነገሮች እጅጉን ቢታሰቡበት መልካም ነው እንላለን ፤ የተፈጸመን ስህተት ለማንም ብለን አይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ መደበቅ አንችልም ፤ ምዕመኑ እንዲያውቀውና በወቅቱ ጥያቄ እንዲያቀርብ ከመጻፍም ወደ ኋላ አንልም ፤ በማንም ጊዜ ይፈጸም ፤ ማንም ይፈጽመው ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ የሆነን ነገር ዝም አንልም ፤ ችግሮች መፍትሄ እንዲኖራቸው ዳግምም እንዳይሰሩ ከተፈለገ ችግሮችን ለቅሞ ማውጣት ግድ ነው ፤ አሁንም ያለፍንበትን መንገድ ላለመሄድ ቁጭ ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡(ሌሎች በርካታ ችግሮችን አስተውለናል ነገር ግን ይህን ያህል ክብደት ስለሌላቸው ትተናቸዋል)






“ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።” 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1440  “የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።” ትንቢተ ሕዝቅኤል 44፤5 “የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው?” ኦሪት ዘዳግም 10፤13 “ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፥ በአባቱም በዳዊት ሥርዓት ይሄድ ነበር” መጽሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 3፤3 እኛም እንደ ሰለሞን አባቶቻችን ባስቀመጡልን ስርዓተ ቤተክርስትያን ለመሄድ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ቸር ሰንብቱ 

 መነሻ ሀሳብ ፡- ዕንቁ መጽሄት (ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ ከጻፈው ላይ የተወሰደ)

5 comments:

  1. You guys lack knowledge of the church teaching and the bible. I hope you a bishop supported by you will not be a patriarch. We need knowledgeable, long distance thinker, developed and spiritual father. Not antagonist like you. Do you know the difference between oriental and eastern orthodox? I hope God will give us a good father who will think wider.

    ReplyDelete
  2. Just so you know, although it's true that the coptic orthodox churches (Ethiopian, Eritrean, Syrian, Egyptian, Indian, and Armenian) are not yet officially in communion with the Eastern Orthodox Churches such as the Greek, our differences (which mainly encompassed of the nature of Christ) have been settled. Eccumenical council meetings have been taking place for many many years between the scholar fathers of these churches and they have come to an agreement that the Coptic dogma which clearly states that Christ's divinity & humanity are of ONE nature, and not two (the mystery of incarnation). They have accepted our dogma and what's remaining is for the scholars and church fathers from both sides to finalize the communion procedures between these churches. That being said, I do not believe it's absolutely ridiculous to invite the Greek fathers to pray for our late Patriarch Abune Paulos. It only strenths Orthodox brotherhood and communion which is already underway. Stay Blessed.

    ReplyDelete
  3. Just so you know, although it's true that the coptic orthodox churches (Ethiopian, Eritrean, Syrian, Egyptian, Indian, and Armenian) are not yet officially in communion with the Eastern Orthodox Churches such as the Greek, our differences (which mainly encompassed of the nature of Christ) have been settled. Eccumenical coouncil meetings have been taking place for many many years between the scholar fathers of these churches and they have come to an agreement that the Coptic dogma which clearly states that Christ's divinity & humanity are of ONE nature, and not two (the mystery of incarnation). They have accepted our dogma and what's remaining is for the scholars and church fathers from both sides to finalize the communion procedures between these churches. That being said, I do not believe it's absolutely ridiculous to invite the Greek fathers to pray for our late Patriarch Abune Paulos. It only strenths Orthodox brotherhood and communion which is already underway. Stay Blessed.

    ReplyDelete
  4. wow excellent view May GOD bless u all.

    የተፈጸመን ስህተት ለማንም ብለን አይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ መደበቅ አንችልም ፤ ምዕመኑ እንዲያውቀውና በወቅቱ ጥያቄ እንዲያቀርብ ከመጻፍም ወደ ኋላ አንልም ፤ በማንም ጊዜ ይፈጸም ፤ ማንም ይፈጽመው ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ የሆነን ነገር ዝም አንልም ፤ ችግሮች መፍትሄ እንዲኖራቸው ዳግምም እንዳይሰሩ ከተፈለገ ችግሮችን ለቅሞ ማውጣት ግድ ነው ፤ አሁንም ያለፍንበትን መንገድ ላለመሄድ ቁጭ ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡(ሌሎች በርካታ ችግሮችን አስተውለናል ነገር ግን ይህን ያህል ክብደት ስለሌላቸው ትተናቸዋል)

    ReplyDelete
  5. "ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ ከጻፈው ላይ የተወሰደ"
    የሚለው ቃል ነገሩን ሁሉ በዜሮ አባዛብኝ።

    ReplyDelete