አዲስ አበባ ነሃሴ 24/2004የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማህበር የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ
ዜናዊ አስከሬን በሙዚየም እንዲቀመጥና በህይወት ዘመናቸው የሰሩት አኩሪ ስራ እንዲታወስ ጠየቀ።
የማህበሩ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ከሸራተን አዲስ በመነሳት
አስከሬኑ ወዳረፈበት ቤተመንግሥት በማምራት ሃዘናቸውን ገልፀዋል።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ፋሲል ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ
ዜናዊ አገሪቱ ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገብ በአለም አቀፍ ተጠቃሽ እንድትሆን የጣሩ መሪ በመሆናቸውና በህዝቦች ተፈቃቅሮና
ተሳስቦ የመኖር ባህል በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ያደረጉ በመሆናቸው ማኅበሩ አስከሬናቸው ሙዚየም ይቀመጥ የሚል አቋም ይዟል።
አገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ዕቅድ ያወጡና ኢንዱስትሪው መሪ እንዲሆን ብቁ
አመራር የሰጡ በመሆናቸው ታሪካቸው ለትውልድ እንዲተርፍ አስከሬናቸው በሙዚየም እንዲቀመጥ የሚለውን ሃሳብ ህብረተሰቡ
እንዲወያይበት እንጠይቃለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በምዕተ ዓመቱ ያገኘችው ታላቅ መሪ በመሆናቸው ህያው ስራቸው ለትውልድ መትረፍ አለበት ያሉት
ፕሬዚዳንቱ አስከሬናቸው በሙዚየም ቢቀመጥ ስራቸው ህያው እንዲሆንና ትውልድ እንዲማርበት እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
አስከሬኑ በሙዚየም የሚቀመጥ መሪ ለአገሩ ትልቅ እመርታን ያስገኘ ነው ያሉት አቶ ፋሲል እኚህ ታላቅ
መሪ አገሪቱን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት ትልቅ ትግል ያደረጉና ትልቅ ዕቅድ ወይም መስመር የዘረጉ ባለ ራዕይ መሪ በመሆናቸው
ይህ ይገባቸዋል ብለዋል።
የአስከሬኑ መቀመጥ መጪው ትውልድ የእሳቸውን አርአያ በመከተል መልካም ጅምሮችን አጠናክሮ ለመቀጠል
የሚያስችል አቅም እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ገልፀዋል በአለም በድህነት የምትጠራን አገር አስከፊ ገፅታ የቀየሩና ለአገር መስራት ምን እንደሆነ ያሳዩ ብልህ
መሪ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በተለይ እኛ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማህበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን በሙዚየም ለማስቀመጥ በሚደረገው
ጥረት ሁሉ በቀደምትነት እንሰራን ብለዋል :: የአቃቂ ጋርመንትና ጂጂ ጋርመንት ስራ አስኪያጅና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ጌታቸው ቢራቱ በበኩላቸው
እንደተናገሩት የጥንት አባቶቻችን ''ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል'' ይላሉ እኛም ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳይርቁና የእሳቸውን
አርያነት እንድንከተል አስከሬናቸው በሙዚየም ይቀመጥ የሚል ሀሳብ አለን።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንትና ለዚች አገር ነፃነት የተዋደቁ፣ ዛሬ ላይ ልማቷን አፋጥነው በዕድገት ጎዳና
እንድትጓዝ ያደረጉና ለዚህች አገር የሞቱ በመሆናቸው የእኚህን ድንቅ መሪ አፅም አለም እንዲያየው ሙዚየም ቢቀመጥ ደስተኛ ነኝ
ብለዋል።
በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የተፈለገው ደረጃ እንዲደርስና ዘርፉ ያለበት ችግር
እንዲወገድ ሌት ቀን ከእኛ ጋር ሲሰሩ የኖሩ በመሆናቸውና በማለፋቸው ከፍተኛ ሃዘን ቢሰማንም ህያው እንዲሆኑ አስከሬናቸው
ሙዚየም ይቀመጥ የሚለው የማህበሩ አባላት ሃሳብ ነው ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንትና የሶሎኔስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ስራ
አስኪያጅ አቶ ይድነቃቸው ታዬ ናቸው
http://www.ena.gov.et
Oh great idea! Their request has to be accepted soon. Because of the following reasons:
ReplyDelete1. Meles Zenawi is the first leader who made his country and 80, 000, 000 people land locked (with out port)!
2. He is the first leader who gave 1700 km Ethiopian fertile boarder land freely to Sudan
3. He is the first leader who killed 200 innocent people in Addis Ababa in 2005 (1997EC)
4. He is the first leader who organised the killing of thousandth of innocents at Hawezin market
5. He is the first leader who splitted the country on ethnic lines and the cause for the death of many innocents due to ethnic clashes
6. He is the first leader who sold his own land to Arab, China, and Indian investors
7. He is the first leader who crowned/give power to 57 Tigrean Colonels and Generals out of 61. And almost all Minister positions to one Ethnic group.
8.He is the first leader who named his Flag as an ordinary cloth
9. He is the first leader who teft and sold 10,000 Tons of Coffee and take the money to his pocket. Finally said lets keep silent on this issue because our hands are involved in it!
10. He is the first leader who insult his people on TV, Radio or any media. Saying Yikoretal, Yigedelal, Yebesebese, Werada, Yewerada werada etc...
11. He is the first leader who arranged the killing of 78, 000 people at Bademe and finally said a fullish war.
12. He is the first leader who crowned a Patriarch of his village after chasing existing Patriarch
13. He is the first leader who brought Ahbash and force all Muslims to be ahbash
14. The first leader who sent Luci to America and made his country to loose the income from Tourists
15.The first leader who attack Monks and take away the land of the Waldba Monastery
16. He is the first leader who killed innocent Muslims including Imams at Awalia and many Mosques
17. He is the first leader to arrest innocent journalists and mistreat them in prison
etc.....
Therefore, yes he should not get buried at the Holy Trinity Cathedral. Better to take away his corp to Muzeum so as others learn from him.
Thanks,
Iwnet Menager Inilmed.Wushet Hatyat Newna.
Are you serious? You must be kidding me. I can't believe this. I have no doubt on you report but did they seriously believe it is necessary to put his body in musium? Good luck Hagere lela men yibalal.
ReplyDeleteየምኞታቸው ትርጉም እንደገባኝ ፣ አዲስ ድንበር ያበጀላትን ጀግና ፣ የባህር በር ያሳጣትንም መሪ ፣ በቆራረጣት ምድር ከመቅበር ፣ ያረፈበት ሥፍራ ለአሻራ ፈላጊ እንዳያስቸግር ሙዚየም ከናታችን ከሉሲ አጠገብ ይገትሩና ንፋስ ይወልውለው ማለት ነው ፡፡ አዬ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፣ ሲያልቅ አያምር ፡፡ ለመወደድ አቅዶ ፣ ወዲህም ያዘነ መስሎ በድናቸውንም እንኳን ሊያለፋና ሊቀጣ ሲከጅለው ፣ ቤተሰቡንም በሰቀቀን እያሰቃየ ሊያኖር የፈለገ የሞኝ የፍቅር መግለጫ ፣ ወዲያ ሲሉትም ለመበቀል የተመዘዘው ሰይፍ ነው ፡፡
ReplyDeleteድሮ ሁለት ጊዜ የሚበላውን ደሃ ሦስቴ እንድትበላ እናደርጋለን ብለውት ሲያበቃ ፣ ዛሬ ለአንዴውም የሚቀምሰው በየጉርሻ ቤት በመሰለፍና ፣ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ በመለቃቀም ፣ ግፋ ሲልም በዕርዳታና በምጽዋት ስም ከሚወረወርለት እህል ነው ፡፡
በስድሳ ብር ሙሉ ልብሱን ከነጫማው ይገዛ በነበረበት አገር ፣ ዛሬ አንድ ቁምጣ ሱሪ እንኳን መግዛት አይችልም ፡፡ በብር ሃያና ሠላሣ ይሸጥ የነበረው ዕንቁላል ፣ ዛሬ አንዷ ሦስት ብር ፣ አርባና ሰማንያ ብር የነበረ ኩንታል ጤፍ 14ዐዐ እስከ 18ዐዐ የደረሰው ፣ ሃያ ዓመት ሙሉ ያለማቋረጥ ባለጥንድ ቁጥር ዕድገት ባስመዘገበችና ብልጽግናዋ ለዓለም ህዝብና መንግሥታት በሚወራላት አገር ነው ፡፡
ይኸ የአገር ውስጥ አስከፊ ህይወትና ኑሮ አስመርሯቸው ፣ የተሻለ ለማግኘት ሲሰደዱ በየበረሃውና በየባህሩ ደማቸው ደመከልብ እየሆኑ የቀሩትን ፣ በየአረብ አገር የሚሰቃዩትን እህቶቻችንንና ልጆቻችንን ሁሉ አብረን ልናስታውስና ከሙዚየሙ በፊት መፍትሄ ልናገኝለት ይገባል ፡፡
ሃያ ዓመት ሙሉ ያለማቋረጥ በዕድገት ጐዳና የተጓዘች አገር ከእርዳታ ከረጢት ምግብ ዛሬም ካልወጣችና ልመናዋን ካላቆመች ፣ የሚወራው የብልጽግና ለውጥ ሁሉ ለህዝቡ ከጋዜጣዊ መግለጫ ያለፈ አይደለም ወይም ቀመር ሠሪታው ፣ ዓላማው ጆሮን መመገብ ብቻ ነው ማለት ነው ፡፡
ከዩኒቨርሲቲ የተመረቀው የቀን ሠራተኛ ድንጋይ አቅራቢ ፣ ባለዲግሪዋ ሴትም ጨለማን በመተገን ሽርሙጥናን መተዳደሪያ ባደረገችበት አገር ፣ እነርሱ ካንሰር እስከሚይዛቸው ሰላጨሱና ስለጠጡ ብቻ ህዝብ የጠገበ ቢመስላቸውና ፣ ሙዚየም ሊያኖሩ ቢመኙዋቸው አይገርምም ፡፡ ታሪክ ግን በየመልኩ ሆኖ ጊዜውን ጠብቆ መጻፉ አይቀርምና ሁሉንም ተጣድፈን ለማዳፈን አንሩጥ ፡፡
ቀደም አንድ ሠርቶ አደር በቀን ከስድስት እስከ አሥር ብር ተከፍሎት ፣ እንዳቅሙ ቤት ተከራይቶ ወይም ደባል ገብቶ ፣ ትዳርም ነገር መሥርቶ ይኖር ነበር ፡፡ ዛሬ በተገኘው ዕድገት የቀን ገቢው ሠላሣ ብር ቢደርስም ቤቱ ቀርቶበት ፣ ሆዱን እንኳን አጥግቦ ማደር አልቻለም ፡፡ ቀመረኞች ሲያታልሉት ታድያ ድሮ ስድስት የነበረው ዛሬ በብልጽግናችን ምክንያት ሠላሣ ይሉትና በመሃይምነቱ ይዛበቱበታል ፡፡ የአሁኑ ሺህ ማለት የድሮ መቶ መሆኑን ማን ባስረዳልኝ ፣ ለዚህ ለውጥ ያልተዘጋጁትን የመንግሥት ጡረተኞች እግዚአብሔር ያስባችሁ እላለሁ፡፡
አዲስ ዜና
እኛ ስለሙዚየሙ ስናወራ በደቡብ ክልል ብሔረሰቦች የሚገኙ ጥቅመኛ ካድሬዎች ደግሞ ሰውየውን ኢየሱስ ነው ብላችሁ እመኑ እያሉ ህዝቡን እየገረፉ ነው ማለትን ሰማሁ ፡፡ የሚያብራራው ካለና እውን ከሆነ ፣ ደርሰው ሳይገርፉን አጐንብሰን እንድንጠብቃቸው ለማለት፡፡ ጆሮ የማይሰማው የለም ፡፡ ራሴ ግን በምሰማው ትንግርት ሊፈነዳ ደርሷል ፡፡
i hate hodam asmsaye ayee ethiopia endzhe yale hezb yebkelbshe
ReplyDeleteene hezbu mene azim leqeqbet new yemilew. haset sidegagem ewnet meselena quch alelachihu. menew yehen yahel feri tewled metaben. abayen yalaye minch yamesegnal. ahun eko menchi yemibal negerm eko yelem. All the first tree Anonymous said it all. Unbleivable situation is going on. These guys are out of their mind or don't know nothing or are woyane buchiloch. Sooooooory for you.
ReplyDeleteHe was the best leader Ethiopia had in its History. You did not believe this and hear all the propogandas, enkuan zenbobish dirom teza nesh, Since you hate one Ethnic group, you believe what ever you hear. Above all, everything is accomplished with the help of God, Nothing will happen without the will of our God. What ever you talk, what ever you become racist, It is God who made everything happen, so i do not care for your bla bla.
ReplyDelete