ተጨማሪ ሁለት ገጾችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመነበብ
እንሞክራለን
(አንድ አድርገን ሐምሌ
25 2004 ዓ.ም)፡- በቀደምት ዘመናት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ነገስታት ሀገራቸው ላይ የተለያዩ ችግሮች በሚፈጠሩበት
ጊዜ በየአህጉረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ ገዳማት እና አድባራት “በጸሎታችሁ አስቡን” ፤ “በጸሎታችሁ አትርሱኝ” የሚል ደብዳቤ እንደሚጽፉ
የታሪክ መዛግብት ይናገራሉ ፡፡በጊዜው በቅርብም ሆነ በሩቅ ላሉ ገዳማትና
አድባራትም “አትርሱኝ” እየተባለ ይነገራል ፤ ይጻፍላቸዋልም ይህንኑም አጥብቀው ለህዝቡ እና ለአባቶች ማሳወቅ ጠቃሚ ስለሆነ በንጉሰ ነገስቱ ማህተም እየታተሙ ወደ ተለያዩ ገዳማት
ይላካሉ ፤ በጊዜው ከተላኩት ደብዳቤዎች ለማስረጃ ያህል የሶስቱን ግልባጭ ከዚህ ቀጥለን ለማሳየት እንሞክራለን….
ጊዜው ድርቅ ሆኖ ለሰብል የሚያሰጋ በመሆኑ
ዐዋጅ
ባለፈው ዘመን ሰብል መታጣት ስናዝን ይህው ዘንድሮም ጊዜው እንዳምናው ለመሆን የሚያሰጋ
ሆኗልና አሁን ስለ ድርቁም ወደ እግዚአብሔር እንዘን፡፡ መስኖም እያወጣህ እህል ዝራ ፤ አታክልት ትከል ፤ ዳኝነትና ውርርድ ፤
ሰማኒያ ፤ የስድብ መቀጫ የገባውንም የተሰደበውንም ሰው ከሚካሰው ካሳ በቀር እስከ መጋቢት ሥላሴ ያለውን ምረናልና መኳንንቱም ሹማምንቱም
ማርልን፡፡
መጋቢት 20 ቀን 1920 ዓ.ም መጋቢት 15 ቀን ተጻፈ
ሰንበትን በግዝት የተከለከለውን በዓል ስለማክበር
ዐዋጅ
በሰንበትና በግዝት በተከለከለው በዓል ቀን ሥራ እንዳይሰራ ተብሎ ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ
ዐዋጅ ተነግሮ ተከልክሎ ነበር ፤ አሁን ግን በተከበረው በዓል ቀን ይልቁንም ዕለተ ሰንበትን በመድፈርና ግዝትንም በመድፈር ፤ ግዝትም
ዐዋጅም ጥሰህ ስራ እየሰራህ በዚህ ምክንያት በየጊዜው መቅሰፍቱ አልታገስ አለን፡፡ አሁንም ሰንበትንና ከዚህ ቀደም የተከለከለውን
በዓል አክብር ፤ በተከለከለውም በዓል ቀን ስራ አትስራ ፤ በዚህ በግዝትና ባዋጅ በተከለከለው በዓል ቀን ሲሰራ የተገኝ ሰው ይቀጣል፡፡
ሀምሌ 16 ቀን 1920 ዓ.ም
ስለ ዘውድ በዓል አትርሱኝ
ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ
ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ
ይድረስ፡-
እግዚአብሔር ከስጋ ከምወለዳቸው ከቃል ኪዳን እናቴ ወደ ኋላ አስቀርቶ የንጉሰ ነገስቱን
ወራሽ ስላደረገኝ የዘውዱን በዓል ለማክበር አስቤ አለሁና በንጉሰ ነገስትነት በሚሰራ ስራ ሁሉ እሱ እግዚአብሔር ሰሪ ሆኖ መሳሪያ እንዲያደርገኝ ከዛሬ ዠምራችሁ እስከ ዘውዱ በዓል ድረስ
በጸሎት ምልጃችሁን ወደ እግዚአብሔር እንድታመላክቱኝ አትርሱኝ ብዬ እለምናችኋለሁ
1922 ዓ.ም ተጻፈ
ይህ ታሪክ የሚያሳየን እውነታ ቢኖር በዘመናት ይችን ሀገር እንደ አምላክ መልካም ፍቃድ
ያስተዳደሯት ገዥዎቻችን ሀገር በእርዛት ፤ በርሀብ ፤ በዝናብ እጦት በችግር እና በጦርነት ስትወጠር በየአህጉረ ስብከቶች ያሉ ገዳማትና
አድባራት ጋር “በጸሎታችሁ አትርሱኝ” የሚል ደብዳቤ እንደሚልኩ ማሳያ ነው ፤ ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔር ምህረቱን እንዲያወርድላቸው
ጸሎታቸውን እንዲሰማላቸው በእስር የሚገኙ ታራሚዎችን የመልቀቅ ልማድም ነበር ፤ ከታሪክ ጠቃሚውን ወስደን የማይጠቅመውን ብናስወገድ
መልካም ይመስለናል ፤ አሁንም ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ህመም የተነሳ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች ፤ በዚህ ጊዜ መንግስት
ይህን መልዕክት ለገዳም አባቶች ቢልክ ምን ይመስሎታል?
ጉዳዩ ፡- በጸሎታችሁ አስቡኝን ይመለከታል
ለ፡- ዋልልድባ ገዳም ማህበረ መነኮሳት
እንደሚታወቀው ላለፉት 21 ዓመታት ይችን ሀገር በጠቅላይ ሚኒስርነት መምራቴ ይታወቃል
፤ ከዚህ በፊት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስላደረስኩባችሁ በደል አባቶቼ ሆይ ይቅር በሉኝ ፤ ሆኖም በአሁኑ ሰዓት በያዘኝ የጭንቅላት
ህመም አልጋ ላይ ከጣለኝ ይህው ዛሬ 42ተኛ ቀኔን ቆጥሬአለሁ ፤ በዚች አጭር ጊዜ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም
የበዛ አምላክ መሆኑን አውቄአለሁ ፤ እግዚአብሔር ምህረቱን እንዲልክልኝ በጸሎታችሁ እንድታስቡኝ ወደ እግዚአብሔር እንድታመለክቱልኝ
አትርሱኝ ብዬ እለምናችኋለሁ፡፡
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ..
ሐምሌ 25 2004 ዓ.ም ተጻፈ
ቸር ሰንብቱ
ግብዓት፡- ከመጽሀፈ ዝክረ ነገር (ከብላቴ ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል)
We are praying for him, Ethiopians and for all people around the world. Thank God for reading this good news.
ReplyDeleteአድር ባዮች ተቃዋሚውን ከባህልና ከእምነታችን ውጭ በመሪያችን ላይ ክፉ ያወራሉ እያሉ ይወቅሳሉ ፡፡ እንዲምራቸው ጸሎትን ከማድረግ ይልቅ የስልጣን ክፍፍሉ እንዴት እንደሚሆን ተጨንቀዋል በማለት ጽፈዋል ፡፡ ይህች አድራሻ የያዘችውን ጽሁፍ አንብቡና ራሳችሁን ገምግሙ
ReplyDeletehttp://www.aigaforum.com/articles/on-meles-health-coverage.pdf
ክርስቲያን ሆነው የክርስቲያን ሥርዓት እንዳይፈጸም ፣ ወይንም ሙስሊም ሆነው የእስልምና ዱዓ እንዳይደረግላቸው ከሁለቱም የሉበትም ፡፡ ትንሽ የሚንገዳገድ የእምነት ፍሬ እንኳን ቢኖራቸው ፣ ያችን ምክንያት አድርጎ ህዝቡ ለጸሎት ይተጋላቸው ነበር ፡፡ ግን ከሁለቱም የእምነት ጐራዎች ውስጥ በአንዳቸውም አባል አይደሉም ፡፡ እንዲያውም ሁለቱም ክፍሎች የሚዳከሙበትን የተንኰል ማግ ሲያደሩላቸው ኖረዋል ፡፡ እንደ እኔ አሁን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና /ከተሃድሶ ጀርባ/ በእስላም መስጊዶች /ከአልሃበሽ ጀርባ/ የሚደረገው እሰጥ አገባ የዚሁ ስውር ሥራ ውጤት ነው ፡፡ በዘርና በጎጥ የተሞከረው ስላልሠራ በሃይማኖት ቋንቋ የተሸፈነ የመከፋፈል የቤት ሥራ የተሰጠንም ሆኖ ይሰማኛል ፡፡
እንደ ክርስቲያንነቴ ፤ ለመሪነት የሚያገለግል ጉልበትና ዕውቀት ባይሆንም ፣ ለንስሐ የሚያበቃ ትንሽ አቅምና ዕድሜ እንዲሰጣቸው ፣ ፈጣሪ እንዳላቸውም አውቀውና አገልግለውት እንዲሰናበቱን እግዚአብሔር ጤናቸውን ይመልስ በማለት እጸልያለሁ ፡፡ አርባ ዓመት ባልሞላ በደል ምክንያት ፣ ሲነጋም ሲጠባ ለዘላለም ሲለበለቡ እንዲኖሩ አልመኝላቸውም ፡፡
Cherenetu yemayalqebet amlak ewenet kelebachewu kelemenut yesemal. yeneseha leeb endisetachewu metseley yaleben degemo engha nen.
ReplyDeleteNo comment!
ReplyDeleteWow Ejeg Betam Betam Tiru Hasab newe,
ReplyDeleteIt must be done like that, that is why Ethiopia has stretch her hands to GOD,
ይህ ታሪክ የሚያሳየን እውነታ ቢኖር በዘመናት ይችን ሀገር እንደ አምላክ መልካም ፍቃድ ያስተዳደሯት ገዥዎቻችን ሀገር በእርዛት ፤ በርሀብ ፤ በዝናብ እጦት በችግር እና በጦርነት ስትወጠር በየአህጉረ ስብከቶች ያሉ ገዳማትና አድባራት ጋር “በጸሎታችሁ አትርሱኝ” የሚል ደብዳቤ እንደሚልኩ ማሳያ ነው
KKKKKKKK betam sakachihugn weyanen meselachihugn demo yihen zena feterachuh enide. mele motoal siol newu yalewu. kefelegachuh eziya hiduna gobignut.
ReplyDelete