(አንድ አድርገን ነሐሴ
9 2004 ዓ.ም)፡- አቡነ ጳውሎስ ከታመሙ ቆየት ብለዋል ነገር
ግን ህመሙ የከፋ ባይሆን ፤ ከዓመታት በፊት በደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል በየጊዜው ህክምና እንደሚከታተሉ እናውቃለን ፤ ከእድሜ ጋር
አብሮ የሚመጡ በሽታዎችም እንዳሉ ይታወቃል ፤ ባሳለፍነው የሁዳዴ ፆም ጊዜ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ጸሎተ ሀሙስ እለት የቅድሥት
ሥላሴን የውስጥ መረማመጃ ደረጃዎች መውጣት አቅቷው ሁለት ሰዎች ከግራና ከቀኝ ደግፈው ደረጃዎቹን ሲያወጧቸው ሲያወርዷቸው ተመልክተናል
፤ ከዚህ በተጨማሪም ከኃላ በምዕመናን ተገፍተው እንዳይወድቁ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከኋላ ደግፈዋቸው ነበር ፤ በጊዜው በአትኩሮት
ስንመለከት የነበረው ነገር ራሳቸውን ችለው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ነው ፤ ከዚያ በኋላ ትንሽ ተሸሏቸው ስለነበር አንጻራዊ
ለውጥ ይታይባቸው ነበር ፤ አሁን ግን አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ታመው ወደ ልደታ አካባቢ የሚገኝው ባልቻ ሆስፒታል
አምርተዋል፡፡
እግዚአብሔር ይማራቸው የንስሀ እድሜ
ይስጣቸው እንላለን
Dear Andadirgen bloggers, I know u guys are trying your best but , I am about to hate your blog b/c do u remember that you were so mad when other blogs use your news with out mentioning the source? I saw you for most of the time that you took news from dejeselam and o a little modification with a lot of type error and post as yours . Please I'm following yours and dejeselam , and other yeTewahedo blogs, and I dont expect this from you . At least startting from now mention the source and i would send this message for Dejeselam blog also. Come on be proffessional
ReplyDeleteBeterefe Bertu sirachu yakoral
እግዚአብሔር ይማራቸው።መልካም አድርጋችሁ ትህትና በተከተለ ትከክለኛ መረጃ እንደ ጥሩ ልጅ በማቅረባችሁ ትመሰገናላችሁ።ስድብና ጥላቻ በክርስቲና ህይወት ለሚኖሩ ሰዎች ሆነ ጸሐፍዎች አይገባም።ሰው ብታመም በሕይወቱ ላይ ስልጣን የእግዚአብሔር ስለሆነ መልካም መመኘትና መጸለይ የእኛ የክርስቲያኖተች ግደታ ነው ። ለሰው ሞቱ ብንመኝለት ሐጢአቱ ለእኛ ነው እንጅ በሰማያዊ አባታችን ፍት ዋጋ አያሰጠንም። የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎቷ ለታመሙት መጸለይ መርዳት ማብላት መጠየቅ የእለት ተእለት አገልግሎቷ ነው። እኛ ልጆቿ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን ምሳሌዎች መሆነ ይገባናል። ሁሉን ነገር መልካም ሆነ ክፉ ስራዎችን ለምሰሩ ሰዎችን ዋጋን የሚሰጥ አንድ እግዚአብሐር ብቻ ነው።
ReplyDelete"እግዚአብሔር ይማራቸው የንስሀ እድሜ ይስጣቸው ዘንድ እኔም እላለሁ"
ReplyDeleteበዚህ ዘመን ደግሞ የምን የቀንድ ተስቦ መጣ ?
ጐበዝ ኧረ አስፈሪ ጊዜ ላይ ነንና በጸሎት በርቱ ፤ ተጋገዙ ፤
በአገር ሰው አንቱ የምንለው ሰው ላይኖረን ነው እኮ፡
እግዚአብሔር እንዲቀርበን ፤ ይቅርታውንም እንዲሰጠን ፤
የታመሙትን ሁላ እንዲምርና ለንስሐ ይበቁ ዘንድ እንዲረዳቸው እንለምነው ፡፡
ለመሆኑ ጾም አድክሟቸው ይሆን ወይስ ሌላ የዘመኑ መቅሰፍት እሳቸውንም ደግሞ አገኛቸው ?
ሌላውን ሁሉ ብተወው መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስላሳተሙልን ከልብ እጸልይላቸዋለሁ ፡፡ ቀልዴን አይደለም ፤ እኔ ቀልድ አላውቅበትም ፡፡
ኧረ አዛኝቷ ተለመኛቸው ፡፡
Minch tikesu unless the same person is blogging which is unlikely true
ReplyDelete