Friday, August 17, 2012

የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ቀን ይፋ ሆኗል



(አንድ አድርገን ነሐሴ 11 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በመንበረ ፓትርያርክ የሀዘን የክብር መዝገብ ተዘጋጅቷል ከ12/12/2004 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያ በብጹ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እረፍት የተሰማውን ስሜት በጽሁፍ ማስፈር ይችላል ተብሏል፡፡ 

የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት እለት ነሐሴ 17/2004 ሀሙስ ከቀኑ 6.00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መሆኑ ተገለፀ:: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቋሚ ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ:: ቅዱስነታቸው 16/12/2004 ረቡዕ ከሰባት ላይ ከባልቻ ሆስፒታል ወደ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስከሬናችው ይሄድና ፍትሃት ሲደረገ አምሽቶ ወደ 11፡00 ላይ በዛኑ ቀን በሰረገላ አስከሬናቸው ሆኖ በብፁዓን አባቶች አጃቢነት ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይገባል ፤ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዚያው ቀን ያድራል ፤ በነጋታውም ከሌሊቱ 11፡00 ጀምሮ በብፁዓን አባቶች መሪነት ቅዳሴ ይደረጋል፤  ከጠዋቱ 300 ላይ የቅዱስነታችው አስከሬን ወደ ውጪ በመውጣት የሽኝት ፕሮግራም ይደረጋል በዚህም ወቅት የተለያዩ እንግዶች እንደየደረጃቸው ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል በመጨረሻም ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖት ከተቀበሩበት አጠገብ ሥርዓተ ቀብራቸው ይፍፀማል፡፡

የቅዱስነታቸውን ነፍስ በመንግስተ ሠማያት ያሳርፈው አሜን !!

4 comments:

  1. You guys why do not use PDF I can't read it your article

    ReplyDelete
  2. You guys why don't use PDF because I can't read your articles

    ReplyDelete
  3. setewokrochew newrachhu zare nefese yemere this is gume

    ReplyDelete
  4. Anid Adirgen Melkam zegeba new Andand bilogoch Kemotu Behalam siwekisuna sitechu yitayalu Abune Pawlos 20 Ametat Mulu Befetena -Bemekera Aslifew Alfewal Ahun Layimelesu Hedewal Menegager yalebin Wedefit silemimetsaw New Metsenkekim Silewedefitu new Beteley Anid Adirgen Zegebachihu Yismamagal yemetsinal wekesa-zelefa-masaded bizu ayitayibachihum Bertu

    ReplyDelete