(አንድ አድርገን ነሐሴ 7 2004 ዓ.ም)፡-ባሳለፍነው ሳምንት ዓርብ ቀን ማታ በለንደን ኦሎምፒክ የሴቶች
5ሺህ የፍጻሜ ውድድርን ለመመልከት በሚሊየን የሚቆጠሩ አይኖች ቴሌቪዥኖች ላይ አፍጥጠዋል ፤ በጊዜው ከፍተኛ የማሸነፍ ግምቱ
የተሰጣቸው ጥሩነሽ ዲባባ እና ኬኒያዊቷ ቪቪያን ቺሮት ነበሩ ፤ ነገር ግን በጊዜው ብዙም ግምት ያልተሰጣት መሰረት ደፋር
በአሸናፊነት ውድድሩን ካጠናቀቀች በኋላ የእመቤታችንን ስዕል በማውጣቷ እና ረዳትነቷን መመስከር በመቻሏ ጥቂቶች ደስ እንዳልተሰኙ
በሚሰጡት አስተያየት መመልከት ችለናል ፤ መሰረት ደፋር ምኑ ነው ጥፋት ሆኖ የተቆጠረባት ፤ እሷ ያመነችበትን ለዓለም ህዝብ
በቀጥታ በሚተላለፍ ስርጭት ላይ ማሳየት መቻሏ ነው ወይስ ምንድነው? መሠረት የእመቤታችንን ሥዕል እንዳሸነፈች በማሳየቱ፣ ብዙ ሰዎች ሃይማኖት ጎራ ከፍለው ሲከራከሩ አንዳንዶች አጸያፊ ስድብ ሳይቀር ጽፈው በመለጠፍ fb አጨናንቀውታል፡፡ በተለይ እመቤታችን የሚጠሉ ሰዎች “የጥላቻ ሃይማኖታቸው” ይፋ አድርገዋል፡፡ ግን መሰረት በልቧ የምታመነው በአደባባይ ገለጸች፡፡ መቼም አምልኮ አልፈጸችም፡፡ ራሷንም መካድ አልቻለችም፡፡ የሌላውን መብትም አልነካችም ፤
ባለፈው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ኢብራሂም ጀይላን 10ሺህ ሜትር ሲያሸንፍ “አላህ ዋክበር” እያለ ደስታውን መግለጽ ችሎ ነበር ፤ ታዲያ ይህ ሰው እሱም የሚያምንበትን ነገር መግለጽ መቻሉ ችግሩ ምኑ ላይ ነው? የሌላውን እምነት አላንቋሸሸም የራሱን እምነት ግን መግለጽ ችሏል ፤ ብዙዎች የ ኢብራሂም ጀይላን እምነት ላናምንበት እንችላለን ነገር ግን የእሱን የእምነት ነጻነት ግን መግፈፍ አንችልም ፤ ኢብራሂም ጀይላን የሚያምንበትን መግለጽ መቻሉ ተፈጥሮያዊ መብቱ ነው ፤ አላህ ዋክበር አትበል ብለን አፉን መያዝ መብታችን አይመስለንም ፤ ስለዚህ መሰረትም ወላዲተ አምላክን ሩጫው ላይ ስላደረገችላት ውለታ ፤ ስለሰጠቻት ጉልበት ማመስገን መብቷ ነው ፤ ይህ ደግሞ ላመነው ክርስትያን ብርታትን ያላብሰዋል ፤ በጣም የሚገርመው ስርጭቱን ደጋግመው ለማሰራጨት ያልታከታቸው ሰዎች እያሉ እኛ እዚህ ተቀምጠን መከራከር መቻላችን ነው ፤ እውነት ነው መሰረት ሀገርን ወክላ ነው የሄደችው ታዲያ ሃገር ወክሎ የሄደ ሰው ማንነቱንና እምነቱን ቢገልጽ ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ? ፡፡ ግራ የሚገባው ነገር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እምነታቸውን የሚገልጹበት ነገር ማከራከሪያነቱ እየጨመረ መቷል፤ ይህ ተቃውሞ የሚብሰው ከመናፍቃኑ እና የወላዲተ አምላክ ስም ሲጠራ ጆሯቸውን የሚያሳክካቸው ፤ ምስሏን ሲያዩ አይናቸው የሚቀላባቸው ሰዎች ዘንድ ነው ፤ እመቤታችን አምላክን ለመውለድ ተመርጣለች ፤ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለእኛ አማላጅ አንድትሆነን እናት አድርጎ ሰጥቶና ፤ ድንግልን ከልጇ ከመድኃኔዓለም ጋር ይዞ ማን አፈረ ? እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክርስቲያኖች መተማመኛ፣ የሩጫችን አጋዥ፣ ሲጠማን የምታጠጣ፣ ሲደክመን የምታበረታ፣ ስንታወክ የምታጽናና፣ እግዚአብሔር የሰጠን የእግዚአብሔር ለመሆናችን መለያ ምልክታችን ናት!!!+የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን!
የመሰረት ደፋር ታላቅ ምስክርነት ሁሌም እናደንቃለን ፤
.- Ethiopian athlete Meseret Defar provided one of the most emotional moments of the London 2012 Summer Olympic Games when she crossed the finish line in the 5000 meter race to win the gold.
She then pulled a picture of the Virgin Mary out from under her jersey, showed it to the cameras and held it up to her face in deep prayer.
An Orthodox Christian, Defar entrusted her race to God with the sign of the cross and reached the finish line in 15:04:24, beating her fellow Ethiopian rival Tirunesh Dibaba, who was the favorite to win.
A teary-eyed Defar proudly showed the picture of the Virgin Mary with the Baby Jesus that she carried with her for the entire race.
Throughout the event, Defar kept pace with three other Ethiopian runners and three from Kenya, until speeding past them on the homestretch to win gold.
The silver medal went to Vivian Cheruiyot of Kenya and the bronze to Dibaba.
Defar is also a two-time world champion in the 3000 meters. In Athens in 2004 she won the gold in the 5000 meters and in Beijing in 2008 she won the bronze.
On June 3, 2006 she broke the world record for the 5000 meters set previously by Turkish runner Elvan Abeylegesse, with a time of 14:24:53.
She then pulled a picture of the Virgin Mary out from under her jersey, showed it to the cameras and held it up to her face in deep prayer.
An Orthodox Christian, Defar entrusted her race to God with the sign of the cross and reached the finish line in 15:04:24, beating her fellow Ethiopian rival Tirunesh Dibaba, who was the favorite to win.
A teary-eyed Defar proudly showed the picture of the Virgin Mary with the Baby Jesus that she carried with her for the entire race.
Throughout the event, Defar kept pace with three other Ethiopian runners and three from Kenya, until speeding past them on the homestretch to win gold.
The silver medal went to Vivian Cheruiyot of Kenya and the bronze to Dibaba.
Defar is also a two-time world champion in the 3000 meters. In Athens in 2004 she won the gold in the 5000 meters and in Beijing in 2008 she won the bronze.
On June 3, 2006 she broke the world record for the 5000 meters set previously by Turkish runner Elvan Abeylegesse, with a time of 14:24:53.
If You Love me Respect My Faith
ENKUANS AMLAKN YEWELEDECH YE EMEBETACHN S-EL ETHIOPIAWIAN HULU YALAMENUBET MN-NETU YALTAWEKE KOKEB YALEBET BANDIRA YALEBSUACHEW YELE, DEG ADEREGSH MESEE SEW BCHA SAYHON BESEMAY HULU DESTA HONUAL YANCHI MSKRNET.
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalin...Thank you Andadirgenoch. This is true. We never complained when Mohamed said alahwakibr, why they complain when meseret show Dingil Mariam's picture? Whoever is not happy with what she did,...forget them. She did not force anyone to be Christian. She just showed who helped her through the race. Yedingil bereket kehulachin gar yihun.
ReplyDeleteከክርስትናና ከድንግል ክብር እስልምና ስለሚቀርባቸውና ስለሚስማማቸው ነው ፡፡
DeleteThe problem with Ethiopian Protestants is they are uneducated and extremist. They don't know to respect other faith. Anyone can show what he believes in. And she as an orthodox Christian knows that the baby Jesus and Virgin Mary can help. So what is wrong thing? Nothing......
ReplyDeletePlease people don't be extremests think broadly... European Christian (protestants) don't insult the Muslim champion for showing his faith. While Ethiopian uneducated protestants insult the hero for showing icon of Mary our beloved mother.
Go and Educated yourself!!!!!!!!!
I love meseret defar
ReplyDeleteWe the son of Orthodox are proud of our sister, she showed to the world her strong foundation and her love of our Mother.
ReplyDeleteድንግልን ከልጇ ከመድኃኔዓለም ጋር ይዞ ማን አፈረ?
Don't worry the son of snake is always snake we never expect to be a sheep.
We know who hate his/her own mother but Virgin St. marry loves all.
Meseret, We love you! you are our religious preacher and national hero!
God bless you believe more than this!
በሉቃስ ወንጌል እንደተጻፈ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጣ እንዲህም አለ ሉቃ 1:28:
ReplyDelete'መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።'
በዚሁ ወንጌል ሉቃ 1:41-43 ደግሞ እንዲህ ይላ:
'ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?'
በዚሁ ወንጌል ሉቃ 1:48 ላይ ደግሞ እመቤታችን እንዲህ አለች 'እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል'
በወንጌል የተጻፈ እውነትን መመስከር ጽድቅ ሲሆን ይህን እውነት መካድ ግን ኃጢአት ነው:: እህታችን መሲ ያደረገችው ታላቅ ጽድቅ ነው! ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አንቺ ከሴቶቸ መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሎ ያመሰገናትን እመቤታችንን: ቅድስት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱሰ ተሞልታ አንቺ ከሴቶቸ መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ በላ ያመሰገነቻትን እመቤታችንን: ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ብላ በመንፈስ ቅዱስ የተናገረች እመቤታችንን: ከፍ አድርጋ ብጽዕት ነሽ የተባረክሽ ነሽ ብላ የእርስዋንና የተወደደ ልጅዋን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ምስል ከፍ አድርጋ ለዓለም አሳየች! ከፍ አድርጋ መሰከረች! እግዚአብሔር ይባርክሽ መሲ! በወንጌል የተጻፈውን በዓለም ሁሉ ፊት መስክረሻልና የእመቤታችን ክብር ነገር ግራ የገባችሁ ሁሉ ስለ ክብርዋ ቅዱስ ገብርኤልን ጠይቁት አንቺ ከሴቶቸ መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሎአልና ሉቃ 1:28!!! ቅድስት ኤልሳቤጥን ጠይቁ አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብላለችና ሉቃ 1:41-43!!! ቅዱሳንን ጠይቁ! መጽሐፍ ቅዱስን ጠይቁ!
በጌታችን ዳግም ምጽአት ጊዜ የአምላክ እናትን ክብር ስታዩ በዚያን ጊዜ በማትጠቀሙበት የጸጸት እንባ ከምትታጠቡ ከአሁኑ ወደልባችሁ ተመለሱ! ጆሮ ያለው ይስማ!
እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ይህን እንድመሰክር ስለረዳሽኝ ክብርና ምስጋና ይድረስሽ! ከተወደደ ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምሕረትን ለምኚልኝ አሜን!
ገብረ ማርያም
ቃለህይወት ያሰማልን በእህታችን ደስብሎናል
DeleteWe love you Meseret! You did right! It is your Natural Right!
ReplyDeleteBye the way, we need to appreciate whatever the faith she has. Remember Gelete Burka a few years ago, she showed " Eyesus Geta new" on her T-shirt while she won 1500m. No one complains. But these Protestant followers actually not all, there are some fair ones, are really narrow minded. They believe Christianity is insulting saints who God honors. ye Egna hager pentewoch meche mayet ena mastewal endemijemiru alawukim. shame on you Protestants. Le Enesu Hayimanot malet Orthodoxin Mawaredina mesadeb, Kidusanan Mawaredina mesdeb new. Yemigermew eko ersi bersachew kidus kidus eyetebabalu new yemiteraru.
we love you Meseret we recpect our faith they have too.
ReplyDelete