Monday, August 13, 2012

ድንግል ማርያም ነኝ ባይዋ “ጣሪያ ቀድጄ እወጣለሁ” አለች


  • በደብረሊባኖስ በቁጥጥር ሥር ውላለች
  • የያዘችውን ህፃንእየሱስ ነውብላለች

ሦስት ልጆቼን የወለድኩት በመንፈስ ቅዱስ ነው በሚል ተከታዮች በማፍራት ለፈፀመችው የማታለል ወንጀል እና ተከታይዋ የነበረችውን ትዕግስት አበራ፣ ምንነቱ ያልታወቀ ባእድ ነገር በማጠጣት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ ተከስሳ /ቤት የቀረበችው / ትዕግስት ብርሃኑ፤ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለቷ ክሷን እንድትከላከል ተወስኖ ምስክሮቿን ያሰማች ሲሆን  ጥፋተኛ ነች አይደለችም የሚለውን ለመበየን /ቤት ለነሐሴ 10 ቀን 2004 . ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

ተከሳሿ የዋስትና መብቷን አስጠብቃ ከእስር ከወጣች በኋላ ድንግል ማርያም ነኝ በማለት ሠላሳ ተከታዮቿን ይዛ ደብረሊባኖስ በመሄድ አብሮአት ያለውን አቶ /ገብርኤል የተባለ ግለሰብ፤እሱ ገብርኤል ነው ብታምኑ ትድናላችሁ ባታምኑ ትቀሠፋላችሁበማለት ቅስቀሳ ስታደርግ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ / ትዕግስት በተጨማሪም የያዘችውን ህፃን ልጅእየሱስ ነው፤ ንኩት ትፈወሳላችሁበማለት ሁከት በመፍጠሯ፣ የአካባቢው ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላትና በደብረ ጽጌ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ ታውቋል፡፡ ተከሳሿ ማረሚያ ቤት ከገባች በኋላምበተአምር ጣሪያ ቀድጄ እወጣለሁ፤ የሚይዘኝ የለም፤ መንፈሴ ከተቆጣ ሁላችሁም ትሞታላችሁእያለች በእስረኞች ላይ ሽብር እየፈጠረች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

2 comments:

  1. ወንድሞቼ የዚህች ሴት ችግርን ማንም ሊረዳላት አልቻለም ፡፡ በሃይማኖት ቋንቋ ስለምትናገር ብቻ ፣ በዛ ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶት ፊልም እየተሰራባት ፣ ጽሁፈ እየተጻፈባት ነው ያለ ፡፡ ሴትየዋ የአእምሮ በሽተኛ ስለሆነች መፍትሄው የሚገኘው ደግሞ ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት ሳይሆን ፣ የአእምሮ በሽተኞች ሆስፒታል ነው ፡፡ እኛ የአእምሮ በሽተኛ የምንለው ጨርቁን የጣለ ፣ አላፊ አግዳሚውን በድንጋይ የሚማታ ፣ በየሥፍራው የሚጮህ ...ሰው አድርገን ነው ፡፡ ነገር ግን የአእምሮ የጤና ችግር የተለያየ ዓይነትና መገለጫ ባህርይ እንዳለው ከጠበብቱ ጠይቆ መረዳት ይቻላል ፡፡ ብዙዎች አእምሮአቸው ከተጎዳ በኋላ ራሳቸውን የሚረዱት /የሚያውቁት/ በህክምና ከታገዙ በኋላ ነው ፡፡ የምታሳየው delusional disorder የሚሉትን ይመስላል ፡፡

    The Diagnostic and Statistical Manual of Mental Disorders defines six subtypes of the disorder characterized as erotomanic (believes that someone is in love with him/her), grandiose (believes that he/she is the greatest, strongest, fastest, richest, and/or most intelligent person ever), jealous (believes that the love partner is cheating on him/her), persecutory (believes that someone is following him/her to do some harm in some way), somatic (believes that he/she has a disease or medical condition), and mixed, i.e., having features of more than one subtype. Delusions also occur as symptoms of many other mental disorders, especially the other psychotic disorders.

    አንዳንዱ ከፎቅ ዝለል ብሎኛል ብሎ ራሱን ፈጥፍጦ እስከ ወዲያኛው ይሰናበታል ፤ ሌላው ደግሞ ግደል ግደል ብሎኛል ብሎ ሰውን ለመጉዳት የሚያደባና የሚታገልም አለ ... እናም ተከታዮችዋንም ሁሉ ከጥፋት ለመታደግ ሃኪም ቢያያትና ዕርዳታ ቢደረግላት መልካም ነው ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. መጽሐፍህን ስላካፈልከን እናመሰግናልን፤
      ግን አንተ ከየትኛው ክፍል ነህ?

      Delete