Read by PDF
መከራ ሲመጣ አይነግርም ዐዋጅ
ሲገሠግሥ አድሮ ቀን ይጥላል እንጂ
(አንድ አድርገን ነሐሴ 13 ፤
2004 ዓ.ም)፡- ይህ ዓመት አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊን ከ40 ዓመታት የፕትርክና ዘመን በኋላ አቡነ ጳውሎስን ደግሞ ከ20 ዓመት የፕትርክና ዘመን በኋላ በሞት የተለዩበት
ዓመት ሆኗል ፤ የአቡነ ሺኖዳ ሞት ሲሰማ ዓለም አዝኗል ፤ በተለይ
በግብጽ ውስጥ የሚገኙት የመንፈስ ልጆቻቸው እና በርካታ የእስልምና ተከታዮች በእርሳቸው ሞት ክፉኛ አዝነዋል ፤ ግብጽ በጣም ቁልፍ
የሆኑ አባትን በወሳኝ ሰዓት ማጣቷን የሀገሪቱ መንግስት መስክሯል ፤ የአቡነ ሺኖዳ ሞት ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ ግብዓተ መሬት እስኪፈጸምበት
ጊዜ ድረስ በሚሊየን የሚቆጠሩ ምዕመናን በረከታቸውን ለመካፈል ወደ ካቴድራሉ ሲጎርፉ ተመልክተናል ፤ ሚሊዮኖች የእምነት ልዩነት
ሳይገድባቸው እምባቸውን አውጥተው ስለ አቡነ ሺኖዳ አልቅሰዋል ፤ ቀብራቸው በሚፈጸምበት ጊዜ በሰዎች ብዛት የተነሳ በመገፋፋት ምክንያት
4 ሰዎች ሞተዋል በርካቶች ተዝለፍልፈው ወድቀዋል ፤ ግብጽ በታሪኳ እንደ አቡነ ሺኖዳ አይነት አባት ብዙዎች በተገኙበት የቀብር
ስነ-ስርዓት አከናውና አታውቅም ፤ ምንኛ መታደል ነው? የሃይማኖት አባት ሆኖ ሚሊየኖች ልብ ውስጥ መግባት መቻል ፡፡
የአቡነ ጳውሎስን ሞት የሰማን ጊዜ
መረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ወደ ቤተክህነት አዳራሽ አመራን ጥቂት ሰዎች ሲያለቅሱ ተመለከትን ፤ አኛም አዘንን ፤ ሰዓቶች
ካለፉ በኋላ ዜናው ብዙ ምዕመናን ጋር ሲደርስ በርካታ ሰዎች በቤተክህነት ይሰበሰባሉ ሀዘናቸውንም ይገልጻሉ የሚል ሃሳብ ነበረን
፤ ዜናው በኤፍ ኤም ሬዲዮኖች እና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከተነገረ በኋላ ቤተክህነት ገብቶ የሚወጣው ጋዜጠኛ እና የጋዜጠኛ መኪና
ብቻ መሆናቸው እጅጉን አስገረመን ፤ አቡነ ሺኖዳ ሞታቸው ሲሰማ ወደ መንበረ ማርቆስ የመጣው ምዕመን እጅግ ብዙ ነበር ፤ አሁን
ግን አቡነ ጳውሎስ ህልፈተ ህይወታቸው ከተሰማ ጀምሮ ወደ መንበረ ፓትርያርክ የሚመጣ ብዙ ሰው መመልከት አልቻልንም ፤ ግማሽ አዳራሽ
የሚሞላ ሰው ለመመልከት ችለናል
፤ በኢቲቪ ላይ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በጣም በእረፍታቸው እንዳዘኑ የሚገልጽ ደብዳቤ እያስነበቡ ይገኛሉ
፤ ምዕመኑስ ምነ ያህል ሀዘን ተሰምቷቸዋል? እኛ አናውቅም ፤ ግብጽ መንገዶች ሁላ በሰዎች ብዛት ለቀናት ተዘግተው ነበር ፤ እኛ ጋር ግን የቤተክህነት
አዳራሽ በአግባቡ ሲሞላ እንኳን አልተመለከትንም ፤ ይህ ምዕመኑ በውስጡ አቡነ ጳውሎስ ላይ ያለውን ቅሬታን ያመለክታል ፤ ጥቂት
የስጋ ዘመዶችና ለጥቅም የቀረቧቸው ሰዎች “አባታችን” እያሉ ሲያለቅሱ በርካቶች ደግሞ ተመልካች ሆነው ቆመዋል ፤ ስራቸውን መቃወም
እንችላለን እንጂ አባትነታቸውን ግን መካድ አንችልም ፤ ፓትርያርክነት እኛ እስኪገባን ድረስ ትልቁና የመጀመሪያው የቤተክርስትያኒቱ
ሹመት ነው ፤ ታዲያ ለምን ለአቡነ ጳውሎስ እንደ አቡነ ሺኖዳ እውነተኛ ሃዘን ማዘን ምዕመኑ አቃተው ? አቡነ ሺኖዳ የግብጽ ኮፕቲክ
ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ሆነው ከቀብራቸው በፊት አስከሬናቸውን ለመመልከትና በረከት ለመቀበል ለሶስት ቀን በግልጽ ለምእመናን አስከሬናቸውን
በወንበራቸው ላይ አስቀምጠዋቸው ህዝብ ሲጎርፍ ተመልክተናል ፤ አሁን ግን በቤተክህነቱ ተገላቢጦሽ ሆኖብናል ፤ 5 ኪሎ አካባቢ ቢንቀሳቀሱ
ከወትሮ የተለየ ነገር አይመለከቱም ፤ የስብከተ ወንጌል አዳራሹ ለአቡነ ጳውሎስ ሀዘኑን የሚገልጽ ምዕመን በቂ ነው የሚባል የሰው
ብዛት አይታይበትም ፤ ነገር ግን ከ4 ኪሎ እስከ 5 ኪሎ ያሉት ካፍቴሪያዎች በሰዎች ሙሉ ሆነው ይመለከታሉ ፤ አቡነ ጳውሎስ በፓትርያርክነት
ዘመናቸው በርካታ ችግሮች እንዲፈጠሩ በር ከፍተው ሊሆን ይችላል ፤ ከስርአተ ቤተክርስትያን ውጪ በርካታ ነገር አድርገውም ሊሆን
ይችላል ፤ ስርአተ ቤተክርስትያንን ሳያከብሩ በርካቶችን ሹመው በርካቶችን ደግሞ አውርደው ሊሆን ይችላል ፤ ከሲኖዶስ በላይ ሆነው
ለቅዱስ ሲኖዶስ አልገዛም ብለውም ይናል ፤ በዘመናቸው የቤተክርስቲያኒቱን ገንዘብ ያለአግባብ በትነው ሊሆን ይችላል ፤ ይህን እና
መሰል በርካታ ነገሮችን አከናውነው ሊሆን ይችላል ፤ እኛ ግን እንደ አንድ ክርስትያን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከአብርሐም ከይስሀቅ
ከያቆብ ጎን እንዲያሳርፍ ልንጸልይላቸው ይገባል ፤ የእርሳቸውን በደል ስንመለከት የእኛ ቢታወሰን ኖሮ እጅ መጠቋቆሚያ ባላደረግናቸው
ነበር ፤ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በወንድምህም
ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?” ማቴዎስ ወንጌል 7፤1
አንድ አባት በአንድ ወቅት አውደ
ምህረት ላይ “እንደ እኛ ሃጥያትና ክፉ አባት ቢሰጠን ለምን እናማርራለን ? መጀመሪያ ጥሩ መሪ እንዲሰጠን ጥሩ አባት እንዲሾምልን
የምንፈልግ ከሆነ እኛ ጥሩ ሆነን መገኝት ይኖርብናል” በማለት ሲያስተምሩ ነበር ፤ ያለፉትን 20 ዓመታት ቤተክርስትያን ያሳለፈችውን
መከራ ሳንረሳ በዚህ በሱባኤ ወቅት ልናስባቸውና አስከሬናቸው ግብአተ መሬት የሚፈጸምበት ቀን የሚገባውን ክብር ለመስጠት በቅድስት
ሥላሴ ቤተክርስትያን በመገኝት ከአባቶች ጋርም ጸሎት ልናደርግላቸው ይገባናል ፤
መወድስ ተቀኙ ካህናቶች በያምባው
ፓትርያርክ ነው ብለው ሥላሴ የገባው
የሚያሳዱንን ካሳደድናቸው ፤ የሚሰድቡንን
ከሰደብናቸው ፤ በደል ላደረሱብን ሰዎች ቂም ከያዝን የእኛ ክርስትና የቱ ጋር ነው ? “ቂም አትያዝ” ኦሪት ዘሌዋውያን 19፤18
አሁን የያዝንባቸውን ነገሮች በመርሳት የምድር የመጨረሻ ስንብታቸው ላይ እንደ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትያን በቀብር ቦታው ላይ መገኝት
አስከሬኑንም ማጀብ ይገባናል ፤ የሳቸው ዘመን እንባ አስለቅሶን ሊሆን ይችላል ፤ ወደፊት ደም እንዳናለቅስ በርትተን እንጸልይ ፤
“ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው።” የሉቃስ ወንጌል 22፤46 ስለዚህ እግዚአብሔር በአባቶች
ጉባኤ ተገኝቶ መልካሙን ያመላክታቸው ዘንድ ልንጸልይ ይገባል ፤ የእሳቸው እረፍት ለቤተክርስቲያን የተሻለ ዘመን እንደሚመጣላት የሚናገሩ
ሰዎች አሉ ፤ የባሰው እንዳይሆን መጸለይ ይገባል ፤ ሚዛኑን ለአምላክ
ትተን ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ምንም ይሁን ምን ለ20 ዓመታት ቤተክርስቲያንን በፓትርያርክነት መርተዋል ፤ ይህ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የ5ተኛው ፓትርያርክ ሞት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ
“አምላክ በጨለማ እንዳይሄድ ዐውቃለሁ
ቀን ያልፋል ብለውኝ እጠባበቃለሁ
.” እንዳለ ያገሬ ሰው እኛም ይህ ጊዜ ሃላፊ መሆኑን ተረድተን በትእግስት መጪውን መልካሙን ጊዜ ብንጠባበቅ መልካም ነው፡፡
ቸር ሰንብቱ
|
let me tell you you crazy mk . Before the pope passed away you made mistake , you criticize him a lot , so most of people confused and crused their father and then , after he passedaway the people didnot come to sebeketwongel addaresh . The cause oh his death is mk.
ReplyDeleteየምታወራውን የማታውቅ ምስኪን።
Deleteታዲያ ለምን ለአቡነ ጳውሎስ እንደ አቡነ ሺኖዳ እውነተኛ ሃዘን ማዘን ምዕመኑ አቃተው ? It is because of some mistakes of Abune Paulos plus your false propoganda to make him be hate by laity. Now you look like to be different. Kikik
ReplyDeleteይገርማል! አሁን እናንተ በዚህ ጽሑፍ ማክበራችሁ ነው ወይስ ማዋረዳችሁ?
Deleteእስከ ዛሬ ድረስስ በየዋሁ ምእመን ውስጥ ስትረጩት የነበረው የጥላቻ መንፈስ እንዴት በቀላሉ ይሰበራል?
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን።
ሲጀመርም አባ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለኢሕአዴግ እጅግ አስፈላጊ አባት ነበሩ የቤተክርስቲያን አባት ሆነው አያውቁም። ለ20 ዓመት የኢሕአዴግ አባት ነበሩ። 20 ዓመት ሙሉ የኢሕአዴግን ፖሊስ ሲፈጽሙና ሲያስፈፅሙ ነበሩ። ለዚህም ነው አባ ጳውሎስ ትምክህታቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን በኢሕአዴግ በተለይም በጠ/ ሚ/ መለሰ ዜናዊ ላይ እንደነበረ ከራሳቸው ከአባ ጳውሎስ አንደበት ስንሰማው የኖረ ነው። የኢሕአዴግ መንግስት ደግሞ ከጫካ ጀምሮ 17 ዓመት በበረሃ፣ 21 ዓመት በስልጣን ወይም በመንግሥትነት በሃገራችንና በቤተክርስቲያናችን ላይ ግፉን የሰራብንና እየሰራብን ያለው ። እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ገለጻ ከአብዮቱ በኋላ የትግራይ ሕዝቦች ነጻ አውጪ ግንባር ሕወሐት ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ መካከል ያላትን ሚና እና አብዮቱን ከሚቃወሙ ኃይሎች ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት ተረዳ። ግንባሩ በሚያደርገው ትግል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከመንገዱ ላይ እንደተደነቀረች እና በጥንቃቄ ሊይዛት እንደሚገባ አወቀ። ቤተ ክርስቲያኒቱን የትግሉ አካል እና ደጋፊ ማድረግ እንደሚገባው ተገነዘበ። ስለዚህም ሊያዳክሟትና እና ለዓላማው መሳካት እንድትቆም ሊያደርጉ የሚችሉ ተከታታይ ሥራዎችን ሠራ። በማን ሰራ በአቡነ ጳውሎስ ለበለጠ መረጃ Agust 18,2012 ደጀ ሰላም ላይ የተጻፈውን ያንብቡ።
ReplyDeleteሃዘን የሚመነጨው ከፍቅር ነው የመከራን ገፈት ላስጋቱን ሰው በየትኛው አንጀታችን እንዘንላቸው የደም እንባ ሲያስነቡን ለነበሩ ሰው እንዴት ብለን እንዘን ሀዘንና ለቅሶ ከኪስ ተወጥቶ የሚሰጥ ነገር አይደለም ታዲያ እናንተስ ለምን ትፈርዱብናላችሁ አኛ አልገደልናቸው ያልሰሩትን ሰሩ አላልን ሲዖል ይውረዱም አላልን ምኑ ላይ ነው የፈረድንባቸው ተው እናንተ እራሳችሁ እግዚአብሔር ፍሩ በማያገባችሁ ገብታችሁ ቀብር ሂዱ እያላችሁ ጥሩንባ አትንፉ 20 ዓመት የተቃጠለና የቆሰለ አንጀታችን ላይ ጨው አትነስንሱብን
እግዚአብሔር የሕዝበ ክርስቲያኑን፣ የአባቶችን በተለይም የዋልድባ አባቶች እንባና ጸሎት እየሰማ ነው ገና ብዙ ተዓምር ያሳየናል።
እኛ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የምንጸልይበት፣ ጊዜአዊና ዘመነ አመጣሽ ልዪነቶች አስወግደን ለአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን በአንድነት የምንቆምበትና የመንሰዋበት ጊዜ አሁን ነው። ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግስት ስበክ የሉቃስ ወንጌል 9፥60
ቸር ይግጠመን
betam tasaznalachi tsihufachu astemari aydelem
ReplyDeletemaferya asafari derejawn yaltebeke tshuf lemehonu enante sle krstnaw sle kenonaw sle dogmaw tawkalachihu?lemehonu egnih sewye ye haymanot abat neberu?orthodoxawis nachewn endiawm mutann tewuachew mutan ykberuachew newna esachewn lemekber yemimeta botaw kemutan gar new
ReplyDeletemaferyawoch lemhonu esachew haymonotawi abat neberu?
ReplyDelete"ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን የሚገባውን ክብር አንስጥ"
ReplyDeleteየሚለው
ለ. . . . . . . . . . . . . . . . . . "እንስጥ"
በሚለው ቢስተካከል መልካም ነው:: አጻጻፋችሁን ተረድቼው ከሆነ "እንስጥ" ለማለት ብላችሁ የፊደል ግድፈት የተፈጠረ ይመስለኛል:: ሙሉ ሀተታውም ያንን ያዘለ ይመስለኛል:: ርዕሱን ያየ ሰው ግን ቶሎ ሲለሚደነግጥ በአስቸኳይ ብታስተካክሉ እላለሁ::
ደስታ
+++
ReplyDeleteSelam ande yadergen,
would you please stop positing such nasty comments,if you can try to check before posting all comment, I am not member of mk but it is not fair blaming someone. And we just need positive information and mekir from you mk latefawu tifat mk rasu yiteyek.who are we??? to blame someone.
Yeberket Tsom yadergelin.
from Uk LB
Yihe Ye Egzeabher dinke teamratu bemehonu, Ye Egziabhern dink sira mawrat Ende Hatiat alayewm. Yihen yaderege Amlak lebetu sew yatal biyem alamnin. Kezih behuala degmo bebetekirstian layi ejun yemiyanesa sewu kale Egziabher beyetera endemiyantebatbewu amnalehu.
ReplyDelete"Enant Metetamoch yalachihu" Betekrstian sile metet bota yelatm kemtikawemachewm ekuyi tegbarat andu esun newu. Enant metetamoch yalachihu kemetet yilk Egziabhern bitamne Noro beabatochachin menekosat layi bedelin balfetsmachihu neber. Enesu tor altemazezu, gedamachin yikeber balu endezih yale bedel yemtfetsmubachew? melsun lib lemil sewu.
Egziabher betun endejemere yatralin Amen!!!
sew mingzem kesitet tsedito ayawkim::behonum sewoch tesasatu bilen metilat,mewded egna aga aytebekim:: mikiniatum rasu amlaki be este meskel lay beneberbet wokit"abat hoy yemiadergutin ayawkum ena yikir belacehew" neber yalew:: yihin yalew enatem endihu adrgu maletu enji, tiluwachew, kim yazu malet aydelem... be mastewal eniyew wondimoche::
ReplyDeletefetari bete kiristianachinin yitebikilin
I am afraid that you are suggesting that we should cry for him by force like the North Korean president. or are you advising us to pretend " ye shingela lekso" or Are you advising us to pretend we pray for him ! God does not accept such prayer. No this can not happen. What the christains are doing is right !!!
ReplyDeleteMy brothers and sisters, this shall be a big lesson to the forth coming Patriarchs ! If they are affiliated to cursed politicians and forget their responsibility; if they disrespect them selves act as a tourist guide for people like Beyonce; if they establish shame full relation ship with graceless corrupt woman like Ejigayehu and embazzel the resource of the church; if they fight for their personal interest than the interest of the church; if they disrespect the holy fathers and intemediate them and violently attack them through the hidden gangs, if they celeberate with politician and celebrities than the orphaned and the poor the same thing will happen to them. He has been called the worlds churchs president....that does not help !
So please do not try to influence the christains, let them do what they want to do.
For the comment given above: MK is the defender of truth nothing more nothing less.
ere ebakachihu ke MK jerba weredu. ahun min agenagnew ye Abunu memot ke MK gar....
ReplyDeleteThe one who comment about Mahibere Kidusan , you must be menafik or tehadeso pls grow up, learn , read, research just don't be guided like blind. Pls leave MK and live ur live.
ReplyDeleteሰላም አንድአድርገኖች ሲጀመር እንዲህ አድርገው ይሆናል እንዲህምሰርተው ይሆናል እያላችሁ የጻፋችሁት ምንለማለት ነው ላደረጉት ጥፋት ሁሉ ማረጋገጫ ከናንተ በላይ ማንሊሰጥይችላልናነው የምትወላውሉት ፓትርያሪኩ ዛሬ በዚህወጡ እንዲህአደረጉ ይሄንሰሩ ይሄንያህለ ዘረፉ ስትሉን ከረማችሁና ምስኪኑን ህዝብ ምንአድርግ ትሉታላችሁ ነው ወይስ ተናግሮ ያልወጣለት ሁሉ የልቡን እንዲናገር በነገር መጎትጎታችሁ ነው ለማንኛውም የወንድሜን ጥቅስ ልዋስና ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንንተዋቸው እንዳለው መጽሀፉ ሰውአነሰና አልቀበርም አይሉ ምንአስፈራችሁ ለማንኛውም በቤተክርስቲያናችንን ከሚቀጥለው ጥቃት ለመጠበቅ ብንሰራ ይሻላል በሞቱሰውየ ላይ አፋችንን ስናላቅቅ ከምንውል
ReplyDeleteAtfered yeferdehbal ye abtachnen be gent yanurelen. Amen!!!
ReplyDeleteEresachehu yegeremale aneset new weyese enset??? aneset belo jemero eneset men ayenet neger new .... eneset kehone melieketachehu eriesachehum enset belo mejemer nebereber......chek when you post before
ReplyDeleteእባካችሁ በአግባቡ ለመረዳት እንሞክር:: 1ኛ ፕሮበጋንዳ የሜባል ነገር የለም በዘመናቸው እኔህ አባት ለምእመንና ለበተክርስቴያናችን የማያመች ወይም በበተክርስቴያናችን ያልተለመደ ሥራ ሰርተዋል ይህ ማንም ሊክደው የሜገባ ባይሆንም : እንደበተክርስትያን አባትነታቸው ግን ቅንነትና ሀዘኔታ በተሞላበት ፍጹም ክርስቴያናዌ በሆነ መርሆ ለአንዴና ለመጨረሻ ልንሸኛቸው ይገባል:: ነፍስ ይማር!!
ReplyDelete