Friday, August 17, 2012

የፓትርያርክነት ምርጫና የመንግስት እጅ


============================================
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት እለት ነሐሴ 17/2004 ሀሙስ ከቀኑ 6.00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል መሆኑ ተገለፀ:: ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቋሚ ሲኖዶሱን በመሰብሰብ በሐላፊነት ይቆያሉ::
============================================

  •  “ፓትርያርክነቱን ትደርስበታለህ ሸክሙን ግን አትችለውም እንጂ” የዛሬ 40 ዓመት አቡነ ቴዎፍሎስ 2ተኛ ፓትርያርክ ለአቡነ ጳውሎስ የተናገሩት  

(አንድ አድርገን ነሐሴ 11 2004 ዓ.ም)፡- ስለ ሊቀ ጳጳሱና ጳጳሳቱ ሹመትና አስተዳደር በወትሮ ልማድ ሊቀ ጳጳሱ የኢትዮጵያ ጳጳሳት የበላይ ሆኖ ከእስክንድርያ ፓትርያርክ ተሹሞ ይመጣና ሥራውንም በንጉሰ ነገሥቱ ዋና ከተማ ተቀምጦ ያካሄድ ነበር ፤ ጳጳሶቹም ከዚያው ከግብጻውያን መካከል ተመርጠው እየተሸሙ መጥተው ንጉሥ የሚያሰኝ ታላላቅ የስብከት አገር የሚሰጣቸው ናቸው ፤ ሥራቸውም በየክፍል አገራቸው ሥልጣን መስጠትና በሕግ ፤ በተክሊል ፤ በሃይማኖት ፤ በጥምቀት በቁርባን ይህንንን በመሳሰለ በመንፈሳዊ ነገር ሁሉ መዳኘትና በንስሓ መቅጣት ነው፡፡ ከ1921 በፊት ከግብጽ አንድ መቶ አስራ አንድ ጳጳሳት ተሸመው ይችን ቤተክርስትያን አስተዳድረዋል፡፡


ከ1922 ዓ.ም በፊት የኢትዮጵያ መምህራን ምንም የተማሩ ቢሆኑ የጵጵስና ሥልጣን አይሰጣቸውም ነበር ፤ እንደ “ሞኖፖል” ሆኖ ተሹመው የሚመጡት እነዚያው ግብጻውያን ብቻ ነበሩ ፡፡ ይህም ከመንፈሳዊ ስራ ወጥቶ የንግድ መንገድ የያዘ ጉዳይ ህዝብን ሳይጠቅም ቤተክህነቱን የሚጨቁን በመሆኑ መንግስት ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ብዙ ተላልኮና ተከራክሮ የቀድሞውን ልማድ ፍቆ የኢትዮጵያ መምህራንም ከጵጵስናው ምርጫ ውስጥ እንዲገቡ አደረገ፡፡ ወዲያው 4 ሊቃውንት ተመርጠው ምድረ ግብጽ ሂደው የጵጵስና ሥልጣን ተቀብለው ተመለሱ፡፡

ደግሞ በ1922 ዓ.ም ከእነዚህ ከአራቱ ሌላ ዕጨጌ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አዲስ አበባ ላይ ዳግማዊ ሚኒልክ መታሰቢያ በበአታ ቤተክርስትያን ከብፁዕ አቡነ ዮሀንስ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የጵጵስና ሥልጣን ተቀበሉ፡፡ ለእነዚህ ለ5 ጳጳሳት ለእያንዳዳቸው ደንቡንና አስተዳደሩን አስቲያጤኑ ጥቂት ጊዜ በአዲስ አበባ ከቆዩ በኋላ የሚያስተምሩበት ሰፋፊ የስብከት አገር ተሰጣቸው፡፡

በ1933 ና በ1940 ዓ.ም መካከል በእስክንድርያና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አስቸጋሪ ውይይቶች ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን የውይይቶቹም ትኩረት የኢትጵያ ቤተክርስትያን ከተወላጆቿ መካከል ጳጳሳት መሾም በምትችልበት ሐሳብ ላይ ነበር ፡፡ የእስክንድሪያ ቤተክርስቲያን በጣሊያን ወረረራ ወቅት  ጠላት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ለማዳከም በሚጥርበት ጊዜ ይህን ጥረት ለመቋቋም በሚያስችል በማናቸውም መንገድ መደገፍ ባለመቻሏ የዚች ቤተክርስትያን የበታች ሆና  መኖር ብሔራዊ ስሜት እያደገ በመጣበት የሥልጣኔ ዘመን በተማሩ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዘንድ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ ሲደረግ የቆየው ጥረት በመጨረሻ ተሳክቶ በ1940 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንዲሾሙ ስምምነት ላይ ተደርሶ ተሾሙ ፤ እንዲሁም በ1941 ዓ.ም የቤተክርስትያኗ ነፃነት በሕግ በመረጋገጡ ብጹእ አቡነ ባስልዮስ የኢትዮጵያ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረግ ተቀዳጁ ፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከእስክንድርያ መንፈሳዊ አገዛዝ  ሙሉ በሙሉ መላቀቅ የቻለችው ለ8 ዓመታት በሊቀ ጳጳስነት  የቆዩት ብጹእ ቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በ1951 ዓ.ም ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሆነው ሲሾሙ ነበር፡፡   

 በመጀመሪያ ኢትዮጵያ የራሷን ተወላጅ ፓትርያርክ አድርጋ እንድትሾም ከእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ጋር ስምምነት ሲደረስ የመጀመሪያው ፓትርያርክ የንጉሰ ነገስቱ የንስሃ አባት እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ግብጽ ሀገር ሄደው ብጹእ አቡነ ባስልዮስ ተብለው ተሹመው መጡ ፤ እሳቸው በሞት ሲለዩ ምክትላቸው ሊቀ ስልጣናት መልዕክቱ ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ተብለው በሲኖዶስ ተሾሙ ፡፡ ባላቸው ከፍተኛ እውቀት ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ሰፊ አገልግሎት የሰጡት ብጹእ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ቀዳሚያቸው በሞት ሲለዩ ተጠባባቂ ፓትርያርክ በመሆን ለተወሰኑ ወራት አገልግለዋል ፤ አቡነ ቴዎፍሎስ የተማሩ እና ዘመናዊ ስለነበሩ ብዙዎች ካህናት እንዲሾሙ አለመፈለጋቸውና እንዲሁም ጎጃሜ መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ቅብአት ናቸው ተዋህዶ አይደሉም እያሉ አስቸገሯቸው ፤ እሳቸው ግን ይህን ሁኔታ ሲቃወሙ ራሳቸው ተዋህዶ መሆናቸውን በየጊዜው ሲናገሩ እና ሲያስረዱ ነበር ፤ በጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን “ኮፕት” መባል እንደሌለበት በይፋ አስታውቀው ነበር ፤ ተቃዋማዎቻቸው ካህናት ሹመታቸውን ባይፈልጉም የጃንሆይ ግፊት በዘመኑ ቀላል ስላልነበረ አቡነ ቴዎፍሎስ መጨረሻ ላይ መጋቢት 29 ቀን 1963 ዓ.ም 2ተኛ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ተብለው  የፓትርያርክነቱን ስልጣን ተቀበሉ ፡፡
ምንም እንኳን የሐይማኖት መሪዎች አመራረጥ ላይ መንግስት እጁን ማስገባት ባይኖርበትም የሀገሪቱ መሪዎች የአብዛኛውን ሕዝብ የሃይማኖት መሪዎችን አሿሿም ችላ ብለው አያውቁም ፤ ስለሆነም አቡነ ባስልዮስ በጊዜው ለንጉሰ ነገስቱ ታማኝ መሆናቸው የታወቀ ስለሆነ የሹመታቸው መሰረቱ ይህው መሆኑ በንግግራቸው ተንጸባርቋል  ፤ “ እኔ አባ ባስልዮስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ሊቀ ጵጵስና ተመርጬ ጃንሆይ ሹመቱን ፈቅደውልኝ  አሁን በግርማዊነትዎ ፊት ቀርቤ ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያንና ለግርማዊነትዎ አገልጋይ መሆኔን ስገልጥ በፊትዎ የታመንኩ አገልጋይ ነኝ ፤ ሃይማኖትና እውነት ይመሰክሩልኛል” በማለት ጉዳዩን አደባባይ አወጡት ፡፡

አቡነ ቴዎፍሎስም ሹመታቸው ሲጸድቅ ጃንሆይ ዘንድ ቀረብ ብለው “መርጠው ስለሾሙኝ በጣም አመሰግናለሁ” ሲሉ የሰሙት ካህናት ለካስ በምርጫ አይደለም ያሸነፉት በማለት ከዚያን እለት ጀምረው አቡነ ቴዎፍሎስን ጠምደው እንደያዟቸው በጊዜው የተጻፉ መጻህፍት ያስረዳሉ፡፡

የደርግ መንግስት ስልጣን ሲይዝ አቡነ ቴዎፍሎስ ደርግን ሳያማክሩ ስድስት ጳጳሳት በመሾማቸውና የማይወዷቸው የቤተክህነት ክህነት ካህናት አሳልፈው ስለሰጧቸው የካቲት 9 1968 ዓ.ም በግፍ ለመገደል እንደበቁ የሚታወቅ ነው ፤ አቡነ ቴዎፍሎስ ከ1933 እስከ 1968 ዓ.ም ባሉት 33 ዓመታት በተለያዩ የስልጣን ደረጃዎች በቆዩበት ወቅት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ታሪክ ውስጥ እንደ እንቁ ሲያበሩ የሚኖሩ ታላቅ ተግባራትን ፈጽመዋል ፤ አቡነ ቴዎፍሎስ ከሾሟቸው ስድስት ጳጳሶች መካከል አቡነ ጳውሎስ አንዱ ናቸው ፤ አቡነ ቴዎፍሎስ የአቡነ ጳውሎስን ሁኔታ በጊዜው ተመልክተው “ፓትርያርክነቱን ትደርስበታለህ ሸክሙን ግን አትችለውም እንጂ” ብለዋቸው ነበር ፡፡ ይህ አባባል እውነት ነው ፤ ባለፉት 20 ዓመታት አቡነ ጳውሎስ ህገቤተክርስትያንን መሰረት አድርገው ሲያስተዳድሩ አልተመለከትንም ፤ በአቡነ ቴዎፍሎስ ቃል አቡነ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ የፓትርያርክነቱ ሸክም ከብዷቸው ለመመልከት ችለናል፡፡

ሶስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ተክለይማኖት የተሾሙበት መንገድ አካሄዱ መልካም መሆኑ ይታወቃል ፤ ይህ ማለት የሌሎቹ ትንሽ ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ ስለታየበት መሆኑ ይታወቅልን ፤ አቡነ ተክለኃይማኖት በጊዜው አቡነ ቴዎፍሎስ እንደተገደሉ ምንም መረጃው የላቸውም ነበር ፤ በወላይታ አካባቢ ቤተክርስትያን ለማሰራት ብለው ሀገር አቋጠው ከፓትርያርኩ እርዳታ እንዲደረግላቸው ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ነበር በጊዜው ፓትርያርኩ በህይወት እንደሌሉ እና አብዮታዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ያወቁት ፤ በወቅቱ ደርግ የሾመው ስራ አስኪያጅ ለፓትርያርክነት አጭቶ እሳቸውን አቅርቧቸዋል ፤ ስራቸው በጊዜው በሰፊው ሲነገር በጋዜጣ ላይ ሲጻፍ ስለነበረ ህዝቡ የተቀበላቸው በደስታ ነበር ፤ ከወላይታ ወደ አዲስ አበባ ሲያመጧቸው ፓትርያርክነት እንደተመረጡ አያውቁም ነበር ፤ በሚሾሙበት ጊዜ የክብር ልብሱን እንዲያደርጉ ቢለመኑ ምንኩስና የተቀበሉበትን ልብስ አላወልቅም ፤ የመነኮስኩበት እና የምሞትበት ይህ ነው ብለው በጊዜው አስቸግረው ነበር ፤ ለቤተክርስትያን ክብር ሲባል ተብሎ የፓትርያርክነት የመዓረግ ልብስን በስንት መከራ በብዙ አባቶች ጣልቃ ገብነት ማድረግ ችለው ነበር ፡፡ ብጹእ አቡነ ተክለኃይማኖት ከ1968 እስከ 1980 ዓ.ም ይችን ቤተክርስትያን አስተዳድረዋል፡፡

የአቡነ ጳውሎስ አሿሿም በጣም ብዙ የተባለለት ነገር ነው ፤ የእሳቸውን አሿሿም አሁን መጻፍ የሰውን ጆሮ ማዶንቆር ነው የሚሆነው ፤ በጊዜው አዲስ አበባን የተቆጣጠው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት 4ተኛውን ፓትርያርክ በግልጽ ከሃገር እንዲወጡ ካደረገ በኋላ አቡነ ጳውሎስን ከምድረ አሜሪካ በማምጣት መንበሩ ላይ ያስቀመጠበት የተቀነባበረ ትያትር ነበር ፤ ጊዜውም 1984 ዓ.ም ፤ በጊዜው ውስጥ ውስጡን ሲነገር የነበረው ለዚች ቤተክርስትያን ዶክተር የሆኑ አባት በዘመኗ አይታ የማታውቀው የትምህርት ደረጃ ያላቸውን አባት እንደሚሾሙ ነበር ፤ ነገር ግን ለሃይማኖት መሪ ትምህርት ብቻ ሳይሆን እምነትም ያስፈልገዋል ፤ የአቡነ ጳውሎስ አሿሿም ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ስኳር በመላስ የተሳሳተው አቶ ታምራት ላይኔ እጅ እንዳለበት የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ጳጳስ በሐምሌ ወር 1991 ዓ.ም የወጣው ጦቢያ መጽሄት ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ “ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበረ ፕትርክናቸው ያወረድነው አቶ ታምራት ላይኔ ስላስፈራሩን ነው” በማለት ገልጸዋል (ሙሉ ቃለ መጠይቁ እጃችን ላይ አለ)፤ ምንም ቢድበሰበስ ነገሩ ከ4ተኛው ፓትርያርክ ወደ 5ተኛው ፓትርያርክ ቤተክርስትያኒቱ የሄደችበት መንገድ አግባብ አይደለም ፤ አሁንም ይህ ነገር እንዲደገም አንፈልግም ፤ ታምራ ላይኔ የሰራው ስራ ከእስር ከወጣ በኋላ ጸጽቶት ቀድሞ ያጠፋውን ጥፋት ሁለቱን የኢትዮጵያውንና የአሜሪካውን የሲኖዶስ አባቶች ሰንጥቆ ካበቃ በኋላ ለማስታረቅ እንደሚፈልግ በመጽሄት ላይ ባደረገው ቃለ መጠይቁ መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡ የዚህ ሰው ድፍረቱ ሃይማኖት የለሽ ሆኖ ለሁለት የሰነጠቃትን ቤተክርስቲያን አሁን መናፍቅ ሆኖ ለማስታረቅ መሞከሩ ነው ፤ ችግሮች በራሳችን ንዝህላልነት እና በመንግስት ጣልቃ ገብነት ተፈጥረው አሁን ሁለትም ሶስትም ሆነን ልንታይ እንችላለን ፤ ነገር ግን እርግጠኞች ሆነን መናገር የምንችለው በጥቂት ጊዜ ውስጥ አንድ እንሆናለን፡፡ አንድ የነበረችውን ቤተክርስትያን ሁለት አድርገን ለትውልድ አናስተላልፍም ፡፡

በታሪክ የፓትርያርክነት ምርጫ እና ሹመት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት የጸዳበት ጊዜ አላየንም ፤ አሁንም የሚቀጥለው 6ተኛው የፓትርያርክ ምርጫ መንግስት እጁን አያስገባም የሚል ተስፋ የለንም ፤ ለምዕመኑ “መንግስት በእምነት ተቋማት ላይ የእምነት ተቋማትም በመንግስት ላይ ጣልቃ አይገቡም” በማለት ዘወትር ፕሮፖጋንዳውን ያቀርባል ፤ እውነታው ግን ከዚህ የራቀ ነው ፤ የአቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር ከተፈጸመ በኋላ ሁሉን ነገር በጊዜው የምናየው ይሆናል ፤ ነገር ግን ይች ቤተክርስትያን ሰላም እንድትሆን የሚፈለግ ከሆነ ነገሮች ሁሉ በህገ ቤተክርስትያን ብቻ መከናወን አለባቸው ፤ ያለፍናቸው 20 ዓመታት ችግሮቹ የተፈጠሩት ሲጀመር መሆኑን አንዘንጋ ፤ አባቶችም ስለ ቤተክርስትያንና ስለ ህዝበ ክርስቲያን ብለው ችግር ፈቺ አባት ከመካከላቸው መርጠው ያስቀምጡ ዘንድ የእኛ የልጆቻቸው ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የተጀመረው እርቀ ሰላም መፍትሄ እስኪመጣ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው ፡፡

“አንድ አድርገን”
ምንጭ ፡-
  1.    የብጹእ ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ አጭር የህይወት ታሪክ (የመጽሀፉ ጸሀፊ ብጹእ ቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ  1987 ዓ.ም)
  2.  ዝክረ ነገር ፡ ከብላቴ ጌታ ማህተመ ስላሴ 1962 ዓ.ም
  3. የ20ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ (ከጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ 1996 ዓ.ም) 

12 comments:

  1. Please leave him for today. "Mut wokash". I think MK will fight to put its own papas like Aba Filipos ,Aba Abraham or other close friends as patriarch. That will worsen the church problem. Let the bishops take time and discuss about it. Don't hurry for this......

    ReplyDelete
  2. *** ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ ምን ይላል??? ***
    ===========================================
    http://www.ahatitewahedo.com/2012/08/blog-post_2504.html#more

    ReplyDelete
  3. Uuuuu ebakachehu hulachehu beyalachehubte ande abune zebsemayate enbel! Be medhanialem fekade endihone

    ReplyDelete
  4. this is really sin in front of God. MK why you take the power of God and judge H.H. Abune Paulos. please pray for his soul.
    we see your clear satanic ambition up on the Holy and Apostolic church.
    please get away from the leading of the Holy Synod. let them to pray and contact with him.

    ReplyDelete
  5. Anonym Aug 17 @ 12:14am and 4:51am
    What are you talking about. Why do u have to include MK in everything. You only find MK's voice on its own official web sites. You say don't judge others but you just did without knowing if this is MK's idea or not. Don't spread hate. "clear satanic ambition" is this, judging others without knowing about them. God bless you both anonym in this holy fasing time. RIP for Abatachin.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Thank you. This is what I always don't understand. Why people blaming Mahiber Kidusan for everything. As far as I know, MK did a good job for our church, and its members are dedecated to serve the church. I still don't understand why blaming MK for everything??????

      Delete
  6. ''አቡነ ቴዎፍሎስ የተማሩ እና ዘመናዊ ስለነበሩ ብዙዎች ካህናት እንዲሾሙ አለመፈለጋቸውና እንዲሁም ጎጃሜ መሆናቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ቅብአት ናቸው ተዋህዶ አይደሉም እያሉ አስቸገሯቸው ''

    It's not true the main opposition of Abune Tewoflos was racist; royal family of Shewa didn’t like to go up anyone from other region of countries to this level (patriarch) unless he was in Shewa race. That was the main cause of it. Please don’t distort the truth history that everyone knew. We contrive for future with forgiveness the past bad history neither laying nor repeating the same mistake.

    ReplyDelete
  7. It's not true the main opposition of Abune Tewoflos was racist; royal family of Shewa didn’t like to go up anyone from other region of countries to this level (patriarch) unless he was in Shewa race. That was the main cause of it. Please don’t distort the truth history that everyone knew. We contrive for future with forgiveness the past bad history neither laying nor repeating the same mistake.

    ReplyDelete
  8. The above anonym

    Pls leave Mahebere Kidusan , I think U must be one of the tehadeso or Menafik.
    May GOD bless ur soul.

    What are you talking about. Why do u have to include MK in everything. You only find MK's voice on its own official web sites. You say don't judge others but you just did without knowing if this is MK's idea or not. Don't spread hate. "clear satanic ambition" is this, judging others without knowing about them. God bless you both anonym in this holy fasing time. RIP for Abatachin.

    ReplyDelete
  9. ዘሐመረ ኖህAugust 17, 2012 at 3:56 PM

    ነገር ግን እርግጠኞች ሆነን መናገር የምንችለው በጥቂት ጊዜ ውስጥ አንድ እንሆናለን፡፡ አንድ የነበረችውን ቤተክርስትያን ሁለት አድርገን ለትውልድ አናስተላልፍም ፡፡
    ለዚህ እግዚአብሔር እንዲረዳን በመፆም በመጸለይ ሰማእት ለመሆን ቆርጠን መነሳት ይጠበቅብናል

    ReplyDelete
  10. Me Too. This is what I always don't understand. Why people blaming Mahiber Kidusan for everything. As far as I know, MK did a good job for our church, and its members are dedecated to serve the church. I still don't understand why blaming MK for everything??????

    ReplyDelete