Thursday, August 16, 2012

ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ



  • ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ስርዓተ ቅዳሴ ላይ በአቡነ ኤጲፋንዮስ የምዕራብ ሸዋ (አምቦ) ሊቀ ጳጳስ የብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ነፍስ  ይማር ብለዋል፡፡

የመግቢያው በር በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው(ታርጋ ፓሊስ -1881)


(አንድ አድርገን ነሐሴ 10 2004 ዓ.ም)፡- የተለያዩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የአቡነ ጳውሎስን እረፍት እየዘገቡ ይገኛሉ ፤ ነገሩ ከተሰማ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ 20 የሚጠጉ ጸጥታ አስከባሪ ፖሊስ በመላክ ቤተክህነት አካባቢ ልኳል ፤ ከ15 የማያንሱ ፌደራል ፖሊሶች በቦታው ላይ ችግር እንዳይፈጠር አለፍ አለፍ ብለው ቆመዋል ፤ የቤተክህነቱ ግቢ በሰዎች ግርግር ታፍኗል ፤ የአቡነ ጳውሎስ አስከሬን ባልቻ ሆስፒታል ስለሚገኝ ብዙዎች ወደ ቦታው አምርተዋል ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን የቅዳሴ መርሃ ግብሩ እንደ ከዚህ በፊቱ በጣም በርካታ ምዕመናን በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል ፤ በአካባቢው ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል ፖሊሶች እና ትንሽ ግርግር በቀር ይህ ነው የሚባል ነገር አይታይም ፤ የአቡነ ጳውሎስ የህይወት ታሪክ በተለያዩ ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች ላይ እየተነገረ ይገኛል ፤ በጣም ትልቅ አባት ሀገሪቱ እንዳጣች በተጨማሪ እየተዘገበ ይገኛል ፤ የቀብራቸው ሁኔታ ከቤተክህነቱ ዛሬ ወይም ነገ የሚገለጽ ይሆናል ተብሏል፡፡

የቅዱስነታቸውን ዕረፍት አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ለተገኙት ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለምእመናንና ምእመናት ባስተላለፉት መልእክት የቅዱስ ፖትርያርኩ ዕረፍት የመላው ዓለምና የቤተ ክርስቲያኒቱ ኀዘን መሆኑን ገልጸው የሥርዐተ ቀብራቸውን አፈጻጸም አስመልክቶ በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ በሚወሰነው መሠረት ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርገዋል፡

ይህን ክፍተት ለመጠቀም የሚሯሯጡ ሰዎች አይጠፉምና መጠንቀቅ ያስፈልጋል ፤ ከዚህ በፊት ሲያውኩ የነበሩ ሰዎች አሁን ስለማይተኙ ነቅተን ልንጠብቅ ይገባናል ፤ የአንዱ ግርግር ለሌላው በር መክፈት መቻል የለበትም ፤ ቤተክህነቱም ሆነ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአሁን በኋላ የሚደረገውን ነገር በጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ፤ ቤተክርስትያኒቱ የምትጠቀምባቸው የሂሳብ አካውንቶች ፤ ቼኮች እና መሰል ሰነዶች በአግባቡ በጥንቃቄ መያዝ መቻል አለባቸው ፤ የሚቀጥለው ፓትርያርክ በህገ እግዚአብሔር እና በቤተክርስትያን ህግ መሰረት ብቻ መመረጥ  መቻል አለበት ፤ የ1984 ዓ.ም በታምራት ላይኔ እና በቤተክህነቱ አማካኝነት የተደረጉትን  ነገሮች ደግመው እንዳይደረጉ ሁሉም አባቶች ስለ ቤተክርስትያን እና ስለ ህዝበ ክርስትያን ብለው ቀጣዩን ፓትርያርክ በጣም በጥንቃቄ መምረጥ መቻል አለባቸው ፤ ወይዘሮ እጅጋየሁንና መሰል ሰዎች የቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ተጽህኗቸውን እንዳያሳድሩ ብርቱ ጥንቃቄ ያሻል፡፡ ምዕመኑም በእነዚህ አይነት ጊዜ በሰከነ መንፈስ ነገሮችን መከታተል መቻል አለበት ፤ያሳለፍናቸው እነዚያ ጊዜያት ዳግም እንዳይመጡ አሁን ላይ ቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ልንጠነቀቅ ይገባል ፤ ምዕመኑ በቀጥታ የመምረጥ መብት ባይኖረው እንኳን አባቶች ስለ ህዝበ ክርስትያኑ እና ስለ አንዲት ቤተክርስትያን ብለው የመምረጥ ሃላፊነታቸውን በጥንቃቄ ሊያከናውኑት ይገባቸዋል ፤ ሲኖዶሱ ቤተክርስትያኑቱ የሰጠችውን ኃላፊነት በአግባቡ ከመንግስትም ሆነ በሰርጎ ገቦች ተጽህኖ ራሱን ነጻ አድርጎ ማከናወን መቻል አለበት ፤

መጠንቀቅአሁን ነው  ምክንያቱም ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባልና ፤ ለሚቀጥለው ምርጫ እንደ ግብጾች ቢቻል ሁሉንም የቤተክርስቲያን ልጆችን የሚያሳትይፍ ቢሆን ፤ ያም ባይሆን እንኳን የተመረጡ ምእመናንንና ማህበራትን የሚያሳትፍ ቢሆን መልካም ይመስለናል ፤ አሁን መታሰብ ያለበት ጉዳይ ሌላ 20 አመታትትን የመከራ ቀንበር ቤተክርስትያናችን የምታስተናግድበት አቅሙ ያላት አይመስለንም ፤ 

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን ከቅዱሳኑ ጋር ይጨምርልን። 
እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን! ሰላም እና ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን። 

5 comments:

  1. what election you are talking? ቀጣዩን ፓትርያርክ በጣም በጥንቃቄ መምረጥ መቻል አለባቸው:: there is one pope in abroad. This is our right time the church unify and become one. I think election is not the right chose for us now. Whatever the problems we have it is better to give the place to pope Merkorious.
    I wish God make our church one!

    ReplyDelete
    Replies
    1. After Aba Paulo you suggest Aba merkorios, the one who flee for his fear and comfort of his flash? We deserve better. The one we all cry when he died. Not the one we felt relief when we lost him.

      Delete
  2. መጀመሪያ የአባታችንን አቡነ ጳውሎስን ነፍስ ይማርልን
    እኛ ብንተኛም እግዚአብሔር አላረፈም ፤ ሥራውን ይሠራል ፡፡ ጥቂትም ቢሆኑ ፣ ሥጋቸውን በድለው ፣ በጾም በጸሎት የሚተጉ አባቶችና እናቶች ያሉባት አገር ስለሆነች ለማንም አይተዋትም ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለተነሳ ፣ ቢዘገይ እንጅ ሁሉም መቀጨቱ አይቀርም ፡፡ እዚሀ ካደረሰን ደግሞ አፈጻጸሙን እራሱ ያሳምረዋል ፡፡ ይኸ እኛን ሊያስተምረን የጀመረውን ጉዞ ፣ በራሱ መንገድ ሳይቋጭ አይተወውም ፡፡

    ይህች እጅጋየሁ የምትሏት ነገር ፣ በቤተ ክህነት ስልጣኗ ምን ቢሆን ነው እንዲህ የምታሰጋው ፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና አመራርስ ላይ መጽሐፋችን ስለ ሴቶች ስልጣንና ሥራ ምን ቢል ነው እንዲህ በየጊዜው ስሟ የሚነሳው ፡፡ መነኩሲት አይደለች እዛ አካባቢ ምን ሥራ ቢኖራት እንዲህ አዲስ ህመም እንደምትሆን ይነገርላታል ፡፡ ታሪኳን ካወቃችሁ አስነብቡን ፡፡
    እንደ እኔ ግን ሰይፉ ተመዟልና ፤ ዞር በይ በሏት ፤ ሳያጠራ ወደ አፎቱ ላይመለስ ነው የወጣው ፡፡
    ከሳምንት በፊት የሙሽርነት ዘመንን ሲደግሱ ዛሬ ላይ ለእረፍት መብቃትን እያየን ካልተማርንና ራሳችንን ካላረምን ፤ ከወር በፊት ሹመት ሲጨመር ፣ በወግ ሳይጠሩበት ትቶ መሄድን እያየን ቀሪዎችም ራሳችንን አስተካክለን ይህችን ቤተ ክርስቲያን ካልጠበቅን ጽዋችን ይጠብቀናል ፡፡

    ReplyDelete
  3. ብላቴናዋ ከጀርመንAugust 16, 2012 at 10:54 AM

    አንድአድርገኖች እንደምን ከረማችሁ ስለዘገባችሁ እናመሰግናለን ነገርግን በደጀ ሰላምላይ የወጣን አስተያየት እንዳለ ወስዳችሁ በራሳችሁ ጽሁፍ ላይ አስገብታችሁ ማውጣታችሁን ሳይ ገርሞኛለ ምነው ጃል የሚባል ነገር ሳይጠፋ አይበጅም!

    ReplyDelete
  4. “የጫንክብኝን አውርድልኝ
    ያመጣሀውን ውሰድልኝ”
    ብየ እንጂ የተማጸንኩት
    ግደል አትግደል መች አልኩት
    ‘እሱ’ ም ሚስጥሩን አልገለጠ
    የሚሻለውን መረጠ
    አሁንም….ተዘጋጅ ባለተራ
    ስምህ እስከሚጠራ

    ReplyDelete