Thursday, August 16, 2012

አራት ኪሎ ቤተመንግስት ይህ ሆኗል……



(አንድ አድርገን  ነሐሴ 10 2004 ዓ.ም)፡- ከወራት በፊት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሞቱ ተብሎ በርካታ ወሬዎች ሲናፈሱ ነበር ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞቱ ተብሎ ሲወራ ነበር ፤ የአቶ መለስ ነገርን ማንም ባያውቅም መንግስትም ዝም ቢል አቡነ ጳውሎስ ግን ሆስፒታል በገቡ በ48 ሰዓት ውስጥ አርፈዋል ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲሆኑ ከ3 ቀናት በፊት በቤተመንግስት የተከሰተው ነገር በጣሙን አስገርሞናል ፤ ለስራ ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ካሳንቺስ እያመራን ሳለ በጣም ትልቅ ዛፍ ቀደምት በኃይለስላሴ ጊዜ የተተከለ ዛፍ ቤተመንግስት ግቢ ውስጥ በንፋስ ሲወድቅ ተመለከትን ፤ በጣም የሚገርመው ነገር ይህ ዛፍ መውደቅ ያለበት ከቤተመንግስቱ አቀማመጥ ሁኔታ ወደ ውጭ በኩል መሆን ሲገባው የወደቀው ግን ወደ ውስጥ መሆኑ ነው ፤ በጊዜው ከፊት ለፊቱ ያለውን ቤት ሁለት ቦታ ከፍሎታል ፤ ቤተመንግስት አካባቢ አጥሩ ስር ያሉ ዛፎች ከላይ ሲሆኑ አስፋልቱ ደግሞ ከበታች ሆኖ ሳለ አወዳደቁ ወደ ውጭ መሆን ሲገባው ወደ ውስጥ መውደቁ አስገርሞናል ፤ በቤቱ ውስጥ ሰው ይኑር አይኑር አላወቅንም ፤ በቦታው ብዙ መቆምም ሆነ ፎቶ ማንሳት ስለማይቻል እንደ አመጣጣችን ለደቂቃዎች ብቻ ቆይተን መንገዳችንን ቀጥለናል ፤ በአሁኑ ሰዓት የወደቀው ዛፍ ይነሳ አይነሳ አላወቅንም ፤ በፊት ቢሆን ኖሮ በቤተመንግስት አካባቢው በርካታ ነዋሪዎች ስለሚኖሩ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻል ነበር ፤ አሁን ግን ከቤተመንግስ ፊት ለፊት ያለው በቆርቆሮ ስለታጠረ በቀላሉ ማረጋገጥ አይቻልም ፤ ይህን ነገር ለሰዎች የሆነውን እና የተደረገውን ነገር በጊዜው በማከፈል ነገሩን የሰሙ ሁሉ የራሳቸውን ፍቺ አስቀምጠዋል፡፡ አንዳንዱ በእድሜ ያረጀ ዛፍ ስለሆነ ነው የወደቀው በማለት ምክንያቱን ሲያስቀምጥ ፤ ሌሎች ደግሞ በሌላ እይታ ነገሩን ተመልክተውታል ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ ?

እግዚአብሔር በአንድም ይሁን በሌላ ይናገራል ፤ አሁን በርትተን መጸለይ ሚገባን ወቅት ላይ እንገኛለን ፤ ሀገሪቱ ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ አይደለች ፤ ዛሬ ደግሞ የአቡነ ጳውሎስ ሞት ከወደ ቤተክህነቱ ተሰምቷል ፤ ነገ ቀጣይ ማን እንደሚሆን አንድ አምላክ ብቻ ያውቃል ፤ ሀገር ሰላም ስትሆን ቤተክርስትያንም ሆነች ምዕመኑ ሰላም ይሆናል ሀገር ሰላም ካልሆነች ግን ለሁሉም መልካም አይደለም ፡፡

ቸር ሰንብቱ

8 comments:

  1. ያለነው በ21ኛው ክ/ዘመን እንደ መሆኑ ተረት ተረት አቁሙ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. የሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን ትውልድ እግዜር የለውም ማለትህ ነው ወይስ ኤቲየስት የሚሏቸውን ነህ ፡፡ በሳይንስ ነው ዓለም የምትተዳደረው ብለህ አስበህ ይሆን ፡፡ ቢገባህ በአንደኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ፈጣሪ ዛሬም አለ ፡፡ መኖሩን ካመንክ ደግሞ መገለጫውን በተለያየ መንገድና መልክ ያሳያል ፡፡ እኛ እውሮች ሆነን አናይም ፤ ደንቆሮችም ሆነን አንሰማውም እንጅ ፡፡ በል ወዳጄ አንተም ቀልድህን አቁመው ፡፡

      Delete
    2. ayegebahem teretena emenet mene agenagnewe denegaye!!!

      Delete
  2. የህ መቸስ የሃያሉ እግዜአብሄር ተአምር ብሎም የቋርፍ ውጤት ነው:: መቸስ በአገሪ ወግና ደንብ መሰረት እንኳንስ የክብርት ኦርቶዶክስ በተክርስትያን ሀይማኖት አባት ህልፈተ ሞት ዜና ሴሰማ ይቅርና አንድ ቀን ያዩት ሰው ሲያልፍም ለወዳጅ ዘመድ ቀረብ ብለው እግዜአብሔር ያጽናህ ይባለል:: እኔም እንዴሁ ለወይዘሮ እጅጋየሁ እና ለዲያቆን በጋሻው እንዲሁም ሰሞኑ ሲያሸበሽቡ ለነበሩ ፀረ ዋልድባ ገዳም በሙሉ እግዜአብሄር ያጽናችሁ ሰል ሁሉን ማድረግ ለሜችለው ለታላቁ ክንዳችን ለድንግል ማርያም ልጅም ቅዱስ :ቅዱስ : የሰማይና የመሪት ፈጣሪ በማለት ምስጋናየን አቀርባለሁ:: ተጨማሪም ለታላቁ ንጉስ ለፈጣሪየ የምለምነው አለኝ የዋልድባ ገዳምን ሆነ ሌሎች ገዳሞቻችን: ኦርተዶክስ በተክርስቴያናችንን : ካለጠንካራ እረኛ የሜኖረውን የውስጡን የውጩን ምእመን አንድ አድርጐ የሜመራ ጨረቃና ፀሐይ ሰጠን : ፈተናችንን በቃችሁ በለን ነው:: እባካችሁ የዚህ አምድ ተከታታዩች የሆነው ሆነና የድንግል ልጅ ከኛ ጋር መሆኑን አምነን አሁንም ጾለታችንን አናቋርጥ:: አሜን!
    አንድ ያድርገን ማለት ይህ ነው:: በጾለት እንበርታ::

    ReplyDelete
  3. It looks very traditional....... The fall of a Tree== death of Aba Paulos and Meles. Funny!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ውሃ ወደ ተራራ ቢፈስ የተፈጥሮ ህግ ነው አይባልም ፡፡ ንፋስ የገፋው ዛፍ ፣ ሚዛኑንም ጨምሮ መውደቅ ከሚገባው አቅጣጫ በተጻራሪ ከተጋደመ ነገሩን ምን ይሆን ብለው ይጠርጥሩ ፡፡ በእርግጠኛነት መናገር ባይሞከርም እንኳን ስለምን እንዲህ ሊሆን ቻለ ብለው ትንሽ ጭንቅላትዎን ያዙሩት ፡፡ የሰዎች ሃሳብ ሁሉ ለእኛም ሊያስቀን ወይም ሊያስገርመን ይችላል ፡፡ በአገራችን ግን በትክክል ተፈጥሮአዊውን ገጠመኝ አይተው ፣ ትንቢት ተናግረው የሚፈጸምላቸው ብዙ ሰዎች እንደነበሩ አልዘነጋም ፡፡ አሁን ጊዜው በመበላሸቱ ፣ ያ ጥበብ በምን ደረጃ እንዳለ አላውቅም ፡፡ ከጥንቆላ ጋር የሚያያዝ አይደለም ፡፡ የውሻን የማላዘን ጩኸት ሰምተው ፣ ያለወቅቱ የመጣ ዝናምና ነፋስን አይተው ሲናገሩና ፣ የተናገሩት እውን ሲሆን ስላየሁት ነው ፡፡

      Delete
  4. erigitegna hogne endeminegrachihu edime tegeb zafoch wodeku malet betam yetekebere azawunt yimotal malet new. I have seen it through our my live different times. A big tree fall down my grad father died. a big tree fall down a very respected man in my neighbor died. I cannot be sure but I can say it has some consequence, believe it or not.

    ReplyDelete
  5. *** ዳኛው መጣ ***
    =================
    ጮራ አይሉት መብረቅ በነሃሴ ነጸብራቅ
    ዎፍ አይሉት አሞራ በሰማይ የሚፈልቅ፤
    በጣም ግዙፍ ነው አንጋጥጦ ላየው
    መላእክት ያጀቡት ለካስ ፈጣሪ ነው
    ሊፈርድ መጣ በቶሎ ስላስጨንቅነው፤
    እሳት ይነዳል ከስሩ ቁጭ ካለበት ከመንበሩ
    ጌታ መጣ ሊዘጋው ተከፍቶበት የገዳም ብሩ፤
    ዝቅ በሉ እንስገድ ለእግዚአብሔር ለክብሩ
    ገስግሱ ኑ እንግባ ከገዳሙ ሳይዘጋብን በሩ ፤
    አትፍረዱ እግዚኦ በሉ ይገባል ለሰው ልጅ
    በፍጥረቱ ጌታ ነው ሰው አይደለም ፈራጅ፤
    ዋይ ዋይ እንበል ለወሰዱት ሃላፊነት
    ለሕዝብ መሪዎች ትእዛዙን ለረሱት
    እናቱን እምየ ማርያምን ለአቃለሉት
    ያሳደግችውን በስደት ቀንና ሌሊት፤
    ፍርዱ ለአምላክ ነው ዝም በሉ
    በጋዜጣው በስልኩ ነገር አትብሉ።

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።

    ReplyDelete