ከሎሚ መጽሄት የነሐሴ እትም ጋር ያደረገችው ቃለ መጠይቅ እንደወረደ አቅርበነዋል
ከሁለት ሳንት በፊት በሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ አንድ ቪሲዲ ተመርቆ ነበር
ይህ ቪሲዲ የተሰራው በአርቲስቶች ሲሆን አርቲስቹ ደግሞ የአቡነ መልከ ጼዲቅ ገዳም እድሳት እንዲደረግለት በማለት ነው የጋራ ቪሲዲ
ያቀረቡት፡፡ በዚሁ ቪሲዲ ላይ ከተሳተፉት መካከል አርቲስት መሰረት
መብራቴ አንዷ ናት መሲ ጥሩ ኃይማኖታዊ እውቀት ያላት አርቲስት ናት ፡፡
ጥያቄ፡- መሲ በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ከልጅነትሽ ጀምሮ ትንቀሳቀሺ ነበር
አርቲስት መሰረት ፡-በተደጋጋሚ ተናግሬዋለሁ ደግሞ መግለጽ ካስፈለገ
ከልጅነቴ ጀምሮ እድገቴ ቤተክርስትያን ነው እና አገልግሎት ያው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው አዲስ አይደለም፡፡
ጥያቄ፡- ባለፈው ሳምንት አንድ አዲስ ቪሲዲ አውጥታችኋል ቪሲዲው መንፈሳዊ መዝሙር ሲሆን
ገቢው ደግሞ ለቤተክርስትያኒቱ ማሰሪያ ነው እንዴት ነው ስለ ቪሲዲው
ምን ትያለሽ ?
አርቲስት መሰረት ፡- ቪሲዲው የሚገርም ነው በሚዳ ወረዳ መራኛ ለሚገኝው ለአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም
ለመስራ ታስቦ የተሰራ ነው ፤ መጀመሪያ አስበነው አልነበረም ወንድማችን ሌይኩን አማካኝነት ገዳሙን እንድንጎበኝ ተደረገና እዛ ቦታ
ላይ ሆነን ሁላችንም የተሰማን አንድ ስሜት ነበር፡፡ እዛ የሚኖሩ መነኮሳት
የሚኖሩበት ሁኔታ አየን ፤ አኗኗራቸውን ተመለከትን ገዳሙ ካለው ጥንታዊነትና ታሪካዊነት አኳያ ጠባቂ ከሌለው ወደፊት
ባዶ ነው የሚሆነው ፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን መነኮሳት አባቶች መንከባከብ አለብን ብለን ለራሳችን ቃል ገብተን መጥተን ነበር፡፡ ቦታው ላይ የምንችል ሰዎች ድጋፍ እናደርጋለን ብለን መጥተን እዚህ ተሰባሰብን ዝማሬዎችን አቅርበን አንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማድረግ ነበር የታሰበው፡፡ ከዛ ሲታሰብ ግን ለምን የገባው ገቢ ብዙ የሚያመረቃ ስልሆነ በጊዜው በቪሲዲ መልክ ቢሸጥ
ሁሉም ጋር ይደርሳል ፤ አገልግሎቱ በዛ ላይ ደግሞ የተሻለ ገቢ ማግኝት ይቻላል በሚል እሳቤ የተሰራ ነው እና እግዚአብሔር ይመስገን
ጥያቄ፡- እንዴት ነበር ስራው አድካሚ ነበር ?
አርቲስት መሰረት ፡- እንደ ድካም አናስበውም እኛ እድለኞች ነን ብለን ነው የምናስበው ፤ ተጠርተን
ነው ፤ ማንም ሳይፈቀድለት ሳይጠራ እግዚአብሔር ቤት ለአገልግሎት አይቆምም ፤ የእግዚአብሔርን ቤት መስራት ሲፈቀድልህ ነው ፤ ንጉስ
ዳዊት በንግስና ዘመኑ የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሰራ አልተፈቀደለትም ፤ በእጁ ደም አለና ፤ ልጁ ሰለሞን እንዲያንጽ ነው የተደረገው
፤ እና እኛ እድለኛ እንደሆንን ነው የምናስበው ፤ ስንሰበሰብ መሰባሰባችን
ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ነበረበት ፤ አላማ ነበረው እኛን ያሰባሰበበት ብለን ነው የምናስበው ፤ በእርግጥ ካለን የግል ስራዎቻችን
አኳያ እግዚአብሔር አመቻችቶ አንደኛው ሲመቸው ሌላኛው አይመቸውም ፤ እንደዚህ አይነት መንጠባጠቦች በተወሰነ መልኩ ነበሩ ፤ ግን
እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ሞገስ ሆነን በመድረኩ ደስ የሚል ፕሮግራም ነበር ፤ ህዝቡም የተለወጠበት ፤ የታነጸበት እኛም
የተሰራንበት ነበር ፤ በነገራችን ላይ በጣም ደስ የሚል ነበር ፡፡ ከድካም አኳያ እግዚአብሔር ለኛ በህይወታችን ካደረገው ነገር
አኳያ በጣም ኢምንት ነገር ነው ያበረከትነው፡፡
ጥያቄ፡- ወደ ቦታው ሄደሽ ነበር?
አርቲስት መሰረት ፡- “አዎን ወደ ቦታ ሄጄ ነበር፡፡
ጥያቄ፡- እንዴት አየሽው ?
አርቲስት መሰረት ፡- በጣም በጣም የሚገር ታሪካዊ ቦታ ነው ፤ አንዳንዴ
ታሪክ በጆሮ ስትሰማና በአይንህ በቦታው ላይ ረግጠህ ስታየው የሚሰማህ
ስሜት ይለያያል ፤ እና እኔም ከዛ በፊት እሰማ ነበር ፤ ስለቦታው ታሪክ ግን በአይናችን ሄደን በትክክል ተደረገውን ነገር ማየት
በጣም ይገርማል፡፡ የአባታችን አቡነ መልከ ጼዴቅ ከተሰጣቸው ቃል
ኪዳን አንዱ ቦታቸው ላይ የተቀበረ ሬሳ ሳይበሰብስ እንደተገኝ ቅርጹን ጠብቆ ለዘመናት ኖሯል፡፡ እርሱን ነገር ሄደን በተጨባጭ
አይተናል እና በጣም ደስ ይላል ፤ ብዙ ሀብት አለን ከሰራንበት ከተጠቀምንበት ካወቅንበት ቤተክርስትያን ብዙ ሃብቶች አሏት እና በጣም የሚገርም ስሜት ነው የተሰማን ፤ ማየት ማመን እንደመሆኑ
መጠን መርገጣችንም መባረክ ነው ፤ ትልቅ ነገር ነው ብዬ የማስበው ከቦታው የሚገኝ በረከት እንዳለ ሆኖ አይተን በመጣነው ነገር ሁላችንም ተባርከን ልባችንም እረክቶ ነው የመጣነው፡፡
ጥያቄ፡- የምታስተላልፊው መልዕክት ፤ እናንተ በሙያቹ ያደረጋችሁትን ነገር አለ ፤ ሌላው ምዕመን ምን ማድረግ አለበት ፤ በአቅሙ ለዚች ቦታ ምን አይነት አስተያየት
አለሽ ?
አርቲስት መሰረት ፡- እንግዲህ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ነው ፤ ክርስትና የእድሜ ዘመን ጉዞ
ነው ፤ አንድ ቦታ ጀምረህ አንድ ቦታ የምታቋርጠው አይደለም ፤ እኛ ሁላችንም ሃላፊነት አለብን ፤ ለመንከባከብና አደራ ለመቀበል ፤ አባቶቻችን ተገርፈውና ተሰደውም በበርሃም ተሯሩጠው
ብዙ መከራና ፈተና አይተው ሃይማኖትን ጠብቀው ለዛሬ ትውልድ አድርሰዋል፡፡ ይህ ትውልድ ደግሞ በጣም ብዙ ሃላፊነት አለበት
፤ አባቶቹ ያቆዩለትን አደራ ጠብቆ ለማቆየት ለቀጣይ ትውልድ ከማስተላለፍ አኳያ አደራ አለበት ፤ እያንዳንዱ ክርስትያን የሚችለውን ያድርግ ፡፡ አገልግሎት እኛ የኪነ ጥበብ
ባለሙያዎች ለህዝብ ቅርብ ስለሆንን ምናልባት ለዝማሬ አገልግሎት
ይህንን አበርክተን ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ምዕመን ቪሲዲውን መግዛት አለበት፡፡ ሲገዛ ሁለት ነገር እንዳበረከተ አድርጎ ማሰብ አለበት ፤ ገዳሙንም እንደረዳ
ማሰብ አለበት ፤ ለክርስትናው አንድ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሆነ እንዲያስበው የሚል መልዕክት ነው እና እንበርታ፡፡
ጸሎት ደግሞ ከምንም በላይ ሃይል አለው ከሩጫም ከምንም
በላይ ፤ ጉልበት አቅም ያለው በሙሉ ባለው አቅም ያድርግ ፤ እያንዳንዱ ምዕመን ደግሞ በጸሎት ያስብ ፡፡ ጸሎት ለምንድነው የሚቆመው?
ስለቤተክርስትያን ስለሃገራችን ስለእያንዳንዱ ሰው እንጸልይ የሚል መልዕክት ነው ያለኝ፡፡
Well articulated orthodoxy answers from Mesi. My advice for mesi: As you are a public artist, you have more spiritual challenges (both from Satan and people) for sure. Therefore, don't forget to work hard spiritually so that your spirituality beats the worldly challenges, which in turn makes you the best both in front of God and Ethiopian/African/Earth people. God always be with you!
ReplyDeleteBerchi Mesi
ReplyDeletemesi read bible ok ?
ReplyDeleteIt is a very nice article. Keep it up AndAdirgen. I also am very happy having related sites, except you made a mistake on www.debelo.org . The link does not work, because you used http://www.%20debelo.org/ instead of http://www.debelo.org/.
ReplyDeleteI feel it is one of the sites every body should be benefited. I got a lot from it. It has really true fruits of our church.
Please correct for others to use.
It is good that you,the artist, claim spirituality. But how can we believe?:you show the Ethiopian people,through that terrible ETV,how "beautiful and important" Lipstick, Sticky Pants,...are. I see you always "carrying" these evil things. Can't you wear the beautiful Kemis? or can't you let your natural beauty make you proud? Take care! Those that say we are "artists" are responsible for distorting the lives of the naive sheep of God,people. you have an influence on this generation's behavior,if not on its religion. .....
ReplyDeleteYes, may god help you in your spiritual journey. But ... it's very clear.
ተሃድሶዎች ይላሉ ግን ምግባር አያደርጉም፡፡ እንደነሱ እንዳንሆን እንጠንቀቅ!
"የኛ ዘመን ሴቶች ከንፈራቸዉን በመለቅለቅ… እመቤታችንን ለመምሰል ይሞከራሉ. ይህስ ይቅር … ምነ ወንድ ለመምሰል መፏጨሩን በተዉት…. ደሞ መንፈሳዊ ነኝ? ይባላል…" one person said.
ልብ ይስጠን፡፡