Sunday, January 15, 2012

‹‹ሬሳ ማቃጠሉ ቢለመድ መሬትን ይቆጥባል›› ፕሮፌሰሩ ምን ነካቸው


(አንድ አድርገን ጥር ስላሴ ፤2004ዓ.ም)፡-ሰሞኑን መንግስ በመሬት ላይ ያወጣው ሀገር አቀፍ የሊዝ አዋጅ  ምክንያት በማድረግ ድሀውም ሀብታሙም ፤ ተከራዩም አከራዩም ፤ የገባውም ፤ ያልገባውም፤ የማያገባውም ፤ከተማ ውስጥ ያሉ ኤፍ ኤም ጣቢያዎቻችን ፤ አዋጁ ዱብ እዳ የሆነባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ፤ የመንግስት ህግ አስፈፃሚዎች፤  ብቸኛው ኢቲቪ  ጣቢያችን  ብቻ የሁሉም ሰው የመነጋገሪያ አርእስት ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ባልታሰበው አዋጅ አንጀታቸው ቅቤ የጠጣ ሰዎች እንዳሉ አንጀታቸው ያረረም ዜጎች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አሁን የኔ አላማ በቴሌቪዥን የሰለቸንን ወሬ ፤ ገና ሲመጣ Remote Control የምናነሳበትን ጉዳይ ለመድገም አይደለም፡፡  በዚህ ዙሪያ ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በፍትህ ጋዜጣ ቅፅ 5 ቁጥር 170 ፤ ጥር 4 2004 ዓ.ም   ላይ ያሰፈሩትን ፅሁፍ አንብቤ ‹‹ምነ ነካቸው›› ያስባለኝን ሀሳብ ለእናንተው ለማካፈል እንጂ ፡፡ ለማንኛውም እርስዎም እንዲያነቡት አንዱን አንቀፅ እንደወረደ አቅርበንዎለታል፡፡


‹‹ዛሬ የኢትዮጵያን መሬት እኩል ብንካፈል ለእያንዳንዳችን 14,123 ካሬ ሜትር ያህል ይደርሰናል ፤ …….››  በማለት ይጀምራሉ ፤ መሬት ማለት ለገበሬው ፤ ለከተማ ነዋሪው ፤ ለመንግስት ፤ ለወደፊት ትውልድ ምን ማለት እንደሆነ በጥሩ ሁኔታ ምሁራዊ ዳሰሳ አርድገዋል ፤ ቀጥለውም ‹‹… የመሬት ችግር መኖሩን የማያውቁ ባለስልጣኖችና የደላቸው ሀብታሞች ብቻ አይደሉም ፤ በመንገድ ላይ የሚተኛው ደሀና ዘመድ ሲሞትበት የሚቀበርበት እያጣ የሚንከራተተው ነው፡፡ ለአንድ መቃብር አስር ሺህ እና አስራ አምስት ሺህ ሲከፈልም መሬት አልተወደደም ማለት ይቻላልን? ስርአቱ ዘመናዊ መሰለ እንጂ ያው መሬት መብላቱን አልተወም ፤ ዘመናዊ ቀባሪዎች ተፈጥረዋል፤ ቀብርን የሚተካውና መሬት የማያስፈልገው የሬሳ ማስተናገጃ ማቃጠል ገና አልተጀመረም ፤ የባህሉ ጣጣ አስሮታል ፤ ማገዶውም እየተወደደ ነው ነገር ግን ሬሳ ማቃጠሉ ቢለመድ መሬትን ይቆጥባል ፤ ለደሀውም ለአካባቢውም የተሻለ ይሆን ነበር ፤ ሹሞቹ ግን ገና አላሰቡበትም…››ብለው ነበር የፃፉት

አንድ ጊዜ አንብቤ ስጨርስ ‹‹ፕሮፌሰሩ ምን ነካቸው?››  ብዬ ራሴን ጠየኩኝ ፤ ‹‹ሰው ሲያረጅ ወደ ህፃነነት ይመለሳል ›› ሲባል ሰምቻለሁ ፤ ሰው ግን ህፃንም ቢሆን እንዲህ ያስባል የሚል ግምት የለኝም ፤ ሰውየው የሀገሪቱን ባህል እምነት ውስጥ ያልኖሩ እና የማያውቁት ቢሆኑ ወይም የህንድ አያልያ ደግሞ የቻይና ፕሮፌሰር ቢሆኑ እኔም ባልገረመኝ ነበር ፤ ነገሩ ግን ኢትዮጵያ ላይ ተወልደው ፤ አፈር ፈጭተው አድገው ፤ እዚህው ተምረው ፤ ለረዥም ዓመት በሙያቸው ሀገራቸውን አገልግለው ጡረታ የወጡበት ሀገር ላይ ‹‹ሬሳ ማቃጠሉ ቢለመድ መሬትን ይቆጥባል›› የሚል ሀሳብ ለእኛ ይዞ መቅረብ ምን ይሉታል? ህንድ ፤ ቻይናና ፤ ሩቅ ምስራቅ አካባቢ የሚገኙ ሀገሮች ሬሳ እንደሚያቃጥሉ አውቃለሁ ፤ ለምን እንደሚያቃጥሉ ግን ከአሉባልታ የተሻለ እውቀት የለኝም ፡፡

እኛ ለዘመናት ሬሳን ቤተክርስትያን ወስደን የምንቀብረው  ስላልገባን ይሆን እንዴ ? ሬሳን ብናቃጥል የተሻለ አካባቢ መፍጠር እንችል ይሆን ? መሬትስ መቆጠብ እንችል ነበርን ? እንዴት አድርገው አስበው ይህን እንደፃፉት አላውቅም ፤ ነገር ግን ከ80 ዓመት የተማረም ይሁን ያልተማረ ትልቅ ከሚባል አዛውንት ይህን የመሰለ የወረደ ለትውልድ የማይጠቅም ፤ ማንነትን የሚያጎድፍ ፤ ስብእናን የሚነካ ፤ ሞራልን የሚያሳድፍ ሀሳብ ይቀርባል ብዬ አለማሰቤ እኔን አስገርሞኝ ሊሆን ይችላል፤ እርስዎስ ከእምነታችን ፤ ከባህላችን ፤ ከአኗኗር ዘይቤያችን ፤ ከታሪካችን አኳያ ይህን ሀሳብ እንዴት ያዩታል? መፅሀፍ ቅዱስ ሰው ከሞተ በኋላ እንዲቃጠል ያዘዘበት ቦታ ያለ አይመስለኝም ፤ ለዛውም የሞተው ሰው ተዝካር የማውጣት ፤ ሙት ዓመቱን ጠብቆ የማሰብ ልማድ በኦሪት መፅሀፍ ላይ ሰፍሮ እናኛለን ፤ መፅሀፈ መሳፍንት 11 ፤ 40

ማገዶ ምንም ያህል ቢወደድ እንዴት ሰውን የመሰለ በአምላክ አምሳል የተፈጠረን ፍጡር ለዚህ ነገር ያስቡታል ? ፕሮፌሰሩ በፈረቃ ማሰብ ጀመሩ እንዴ? አሁን አሁን የምንሰማቸው ነገሮች በጣም የሚገርሙ እየሆኑ መጥተዋል ፤ ለምን ይሆን ጆሯችን ጥሩ ነገር መስማት ቢናፍቅም መስማት ያልቻለው?

እውነት ነው በከተሞች አካባቢ የመቀበሪያ ቦታ እጥረት እንዳለ የማያውቅ የከተማ ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም ፤ 4 ኪሎ የሚገኝው ስላሴ ቤተክርስትያንም እናት አባትዎን ፤ እህት ወንድምዎን ፤ ሌላም ዘመድ አዝማድ ለመቀበር ቢሹ ከ10 ሺህ ብር በላይ እንደሚጠየቁ እናውቃለን ፤ በአሁኑ ሰዓት ሰው ቢሞትብን አዲስ አበባ ዳር ላይ ያሉ አብያተክርስትያናት ካልሆኑ በቀር መሀል ላይ የሚገኙት በቤተክርስትያኖች ላይ ቀድሞ የመቀበሪያ ቦታ በሰንበቴ ማህበርም ሆነ በሌላ መንገድ ካልያዙ በቀር እንዲህው በዋዛ እንደማገኝ ይታወቃል ፤ ሀገሪቱ ለመኖርም ሆነ ለመሞት የማትመች ብትሆንም ይህን የመሰለ የሬሳ ማቃጠል ስርዓት ታስተናግዳለች የሚል ሀሳብ የለንም ፤ ለመኖር ለከበደው ማህበረሰብ ስለ ነገ ማረፊያ መቃብር ቦታ አስብ ቢሉት ‹‹መጀመሪያ ልኑር›› ነው የሚልዎት  ፤  ነገ ለመኖር እንደምናስበው ከዚህች ዓለም ኮንትራታችን ለሚቋረጥባ ቀን ቁጭ ብለን ብናስብ መፍትሄ የምናጣ አይመስለንም ፤ መሬት ምንም ያህል ቢወደድ የፕሮፌሰሩ ሀሳብ መፍትሄ አይሆንም፡፡

በአዲስ አበባ ውስጥ ከ100 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፤  ኮልፌ አካባቢ የሚገኝ አንድ የሙስሊም መቃብር   ፤ ጀነራል ዊንጌት አካባቢ የሚገኝ አንድ የካቶሊክ የመቃብር ስፍራዎች ይገኛሉ ፡፡ሁሉም እንደ ቤተ እምነቱ በእነዚህ የቀብር ቦታዎች አገልግሎት ያገኛል ፤ ፕሮቴስታንቶች ደግሞ በቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ን እንደሚቀበሩ ይታወቃል፡፡

ከጊዜ ወዲህ ግን  በቦታ ጥበት ፤ የመቃብር ቦታ ከመሙላት ጋር፤ ቦታዎችን ለሌላ አገልግሎት ከማዋል ጋር ከማዋል ጋር በተያያዘ  እና በተለያዬ ጉዳዮች ምክንያት ከ100 በላይ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያኖች ውስጥ የቀብር አገልግሎት የሚሰጡት ጥቂቶቹ ናቸው ፤ ለንግድ የሚያመች ቦታ ያላቸው ቤተክርስትያኖች የመቃብር ቦታዎችን እያነሱ ለቤተክርስትያንያቱ ቋሚ የገቢ ምንጭ ይሆን ዘንድ ወደ ዘመናዊ ህንፃ መስሪያ ቦታ እየቀየሯቸው ይገኛሉ ፡፡ ይህ ጥሩ ሆኖ ሳለ ‹‹ሰው ዙሮ ዙሮ ከቤት ኖሮ ኖረ ከመሬት ›› ስለሆነ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ተተኪ የመቃብር ቦታ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ መቀበሪያው ለእኛ ለበታች የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን ለእነሱም ለባለስልጣኖቻችን መሆኑንም ማወቅ ይገባቸዋል፡፡

ለፕሮፌሰሩ ማለት የምንወደው ግን ፤ ይች ሀገር ኢትዮጵያ ነች እንጂ ህንድ ወይም ቻይና አይደለችም፤ ሬሳ ማቃጠልም ዘመናዊነት አያስብልም ፤ ሬሳ አቃጥለን የምናገኝው ነገር ቢኖር ሰላም ማጣት እንጂ ቦታ መቆጠብ አይደለም፤  ይህን ሀሳብ አይደለም ፊደል ከቆጠረ ይቅርና ካልተማረ ማህይም እንኳን አንጠብቅም ፤ ከእምነታችንም ሆነ ከባህላችን ጋር አብሮ የማይሄድን ነገር የምንቀበልበት አእምሮ ሆነ ህለና የሌለን መሆኑን ብቻ ነው፡፡   

42 comments:

 1. men nekahu yehe sewuye cherashe jaje ende ?
  lenegeru men hayemanot alewu yeteseran mekawomna tbaho (sigara) maches newu esu yemiyawukewu kehulum tetalto alhonlet sil demo bezih metabn ? men ale yemayakewun bayekebatr !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ሀሳብ አይደለም ፊደል ከቆጠረ ይቅርና ካልተማረ ማህይም እንኳን አንጠብቅም ፤ ከእምነታችንም ሆነ ከባህላችን ጋር አብሮ የማይሄድን ነገር የምንቀበልበት አእምሮ ሆነ ህለና የሌለን መሆኑን ብቻ ነው፡፡

   Delete
  2. ይህን ሀሳብ አይደለም ፊደል ከቆጠረ ይቅርና ካልተማረ ማህይም እንኳን አንጠብቅም ፤ ከእምነታችንም ሆነ ከባህላችን ጋር አብሮ የማይሄድን ነገር የምንቀበልበት አእምሮ ሆነ ህለና የሌለን መሆኑን ብቻ ነው፡፡

   Delete
  3. this is not comment you just reflect your hate and your woyanenet be positive!!!!

   Delete
 2. Egnh sew eko yaltadelu selehonu edmachew bynzazam alawekutim le nisseha endehone chirash kafeju behwla sira syatu gize endih yale neger mekeber jemeru malet new eski Mesihaf kidus yanbibuna yet endalu rasotin yemermiru ke mekedemwona kemekatelwo befit

  ReplyDelete
 3. ከጥጥ የቀለሉ የእንጨት ሽበት ናቸው! እግዚአበሔር ልቦናቸውን ይመልስላቸው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Shame on you!!! Erasehinee zikkee newu yaderekewu!!!

   Delete
 4. እርጅና ሲበዛ ልጅነት ይጀማምራል ይሉሃል እንግዲህ ይህ ነው፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዛሬ ተማሩ ከምንላቸው ‹‹ታላላቅ›› ሠዎቻችን ይልቅ ኬጂን ያጠናቀቀው ትንሹ ወንድማችን የተሻለ ሳያስብ አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 5. that so funny!!!! are you ETOC member? i don't think so! howeve please pray for the rest of your life.!

  ReplyDelete
 6. ፕሮፌሰሩ ምን ነካቸው!!!!!!

  ReplyDelete
 7. poletika alihone silachew

  ReplyDelete
 8. In my point of view, the professor could be right but it is too early. We have couple of other options on the table because we still have enough land. What we lack is in fact good governance and efficient land management system!

  ReplyDelete
 9. engidih esachew simotu maqatel newa!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Confused, simotu or semotu?

   Delete
  2. KKKKKKK BRAVO!! GOOD IDEA!

   Delete
 10. i don't think he is normal

  ReplyDelete
 11. mesilowote enjii mengiste yihinine yemakatel hasabe eyetewoyayebet newu

  ReplyDelete
 12. Yeseweyew hasab ke emnet aquaya ayaskedem gine enante ye profeserun hasab yetekawemachehu sewoch yekeber bota endihu eyetewedede bihed men amarach hasab alachehu?? Esachew bianse lerasachew awekewebetal...........enantes be arawit mebelat yeshalachuhal........amarach hasab makreb ende profeseru ke Ehadeg temaru....mekawem becha aydelem lemetekawemut guday amarach....amarach??

  ReplyDelete
 13. People, don't rush to judge. This is a universally accepted idea. http://en.wikipedia.org/wiki/Cremation

  ReplyDelete
 14. Menew Jale !!! yaletemare yegedelegn endamibal enantem besek gedelachugne !!! men cheger aleu tikatele aletekatel yahu new.
  I DONT THINK YOUR ARE RIGHT !!! He can say what he want to say.You have to oppose his idea not him :)

  ReplyDelete
 15. yemen apraroval new :(

  ReplyDelete
 16. Yeteshale hasab kale mamtat new enji sewuyewun mesdeb meftihe ayidelem. manim sew hasabun yemeglets mebt alew. enantem yihin mebtachihun tetekmachihu yerasachihun amarach akirbu. esti yeminagerin sew af afin malet enitew. zemenu eko yenetsanet new!!!!!!!

  ReplyDelete
 17. Minew sewu firewn tito geleba,gelebawn yayal?Min Ayinet Dedeboch nachihu Lemalet yefelegew ayigebachihum ende,I'll never read ur articles now onwards.Metsaf Silalebachihu Bicha Atitsafu......

  ReplyDelete
 18. Sewiyewin bemetechet lay yalachihu, min ale hasabun kesewiyew netilachihu bitikawemu. Ere ebakachinin Hasab endegif, hasab enkawem... roten sew anat lay aniwita

  ReplyDelete
 19. To Pro. think about human being otherwise u have to go back school or read this Bible of Ethiopian Orthodox Tewahido Church!!!

  ReplyDelete
 20. ante erasih denez neh, kuntsil yemitahil neger ansiteh hasabun satiredaw silekereh new

  ReplyDelete
 21. We also read the article of prof.but I do not understand like you....I think you are just splitting hair as woyane(EPLF)leader's are doing but i do not say you are woyane!!!

  ReplyDelete
 22. you stupid fool this is an opinion. He[the professor] is better than any one of you bunch of fool............ he can even teach you everything philosophy, religion history, politics but you nothing...
  It is not expected in religions blog... so just try to justify from bible or God's word otherwise you cant judge him.........
  "esti atasafirun hodamochi"

  ReplyDelete
  Replies
  1. manhe profeserun yedegefk men aynet tebab chenkelat naw yalehe...??? better then anyone telalhe yalehew Ye Islam weyem ye 1 tera protestant blog lay aydelehem...Yalehew ye Orthodox blog lay nehe...Ye seletane mench,Ye ewket mench ke orthodox kefelku sewoch gar naw yemtaweraw....Enkuan yehe tera profesor kerto kesu yemibeltu sent ye Ewket balebet lejoch Enat endehonech resethewal malet naw.....Ateresa ye hagerachen telalek yemibalu ye poletica,social,ye tibeb alem yehonu sewoch meneshachew ezi naw.....Egzihabeher lebonahen yimelseleh...dengel mariyam ewnetun endetawek terdahe..

   Delete
  2. manhe profeserun yedegefk men aynet tebab chenkelat naw yalehe...??? better then anyone telalhe yalehew Ye Islam weyem ye 1 tera protestant blog lay aydelehem...Yalehew ye Orthodox blog lay nehe...Ye seletane mench,Ye ewket mench ke orthodox kefelku sewoch gar naw yemtaweraw....Enkuan yehe tera profesor kerto kesu yemibeltu sent ye Ewket balebet lejoch Enat endehonech resethewal malet naw.....Ateresa ye hagerachen telalek yemibalu ye poletica,social,ye tibeb alem yehonu sewoch meneshachew ezi naw.....Egzihabeher lebonahen yimelseleh...dengel mariyam ewnetun endetawek terdahe..

   Delete
 23. እኛ የምንቃወመው ከእግዚአብሔር የተሰጠን አፈርነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ ነው የተባለነው ስለዚህም ምን አልባት ጊዜው ተበላሽቷልና የትም መቀበር አትችሉም ብንባል እንኳ አስከሬን ከምናቃጥል ወይም ከምንቃጠል ለእኛስ ከእምነታችንም ከባህላችንም አኳያ አውጥታችሁ ብትጥሉ ጥሩ አማራጭ ነው ብለን እናምናለን ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔርን እጅ ትቀምሱና ስህተታችሁ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አሁን በአፋችሁ ብትቀባጥሩ በእግዚአብሔር እጅ ብትያዙ አንድ ሰከንድ ትበቃችሁአለች ያኔ መሬት የማነው የእግዚአብሔር፣ ሰውን የሚገልም የሚያድንም የመቃብር ቦታ የሚያዘጋጅም ማን ነው? እግዚአብሔር ማን እና ምን እንደሆነ ታውቁት አላችሁ፡፡ ምን አልባት እግዚአብሔር እንደሰው አይቸኩልም እና ቶሎ ምላሹ ባይሰጣችሁም አስከሬኑን ከምታቃጥሉ አውጥታችሁ ጣሉትና አውሬውም ካልጠገበ በአውሬ መበላት ይሻላል፡፡ ለነገሩ አሁንስ የሰው አውሬ በቁማችን እየበላን አይደል!!! ምን ይደረግ !!!

  ReplyDelete
 24. በመጀመሪያ የአንተ አስከሬን ይቃጠልና የአስከሬን ቃጠሎ ጀማሪ ተብሎ ስምህ በታሪክ መጽሐፍ ይዘከርልሃል፡፡ ከዚህ የበለጠ ታሪክ መስራት ካማረህ ደግሞ አሁንም ሳትሞት የሞትክ ብትሆንም እንኳ ትንሽ ነፍስ ስላለህ በህይወት እያለ እራሱን አቃጥሎ አስከሬን ለማቃጠል ለምሳሌ የሆነ ማን ነው? ተብሎ ጥያቄ ሲቀርብ ኘሮፌሰሩ እየተባለ ስምህ በምድር ላይ ሲጠራና ታሪክህ ሲነገር እንዲኖር እራስህን በህይወት እያለህ ምሳሌ አድርገህ ብታቀርብልንስ!!! ምክንያቱም በአንተ ሃሳብ በምድር ላይ የሆነ ታሪክ ሰርተህ ብትሞትም እንኳ ስምህ በምድር ላይ ሲጠራ እንዲኖር የፈለግህ ትመስላለህ እንጅ ይህ አይነቱ ሐሳብ በአንተ የእድሜ ደረጃ ላይ ሆኖ ቀርቶ በማንም አይታሰብም ነበር፡፡
  ለማንኛውም በመጨረሻ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር አንተ አላወቅኸውም እንጂ እግዚአብሔር አምላክ ይህችን እድሜ የሰጠህ ለንስሐ ነውና ንሰሐ ለፈጣሪህ ገብተህ ታሪክህ በህይወት መጽሐፍ ሲነገርልህ እንዲኖር የዘወትር ፀሎቴ ነው!!! አንተም በተቻለህ መጠን ለንስሐ አብቃኝ እያልህ ፀልይ፡፡ እግዚአብሔር ምህረቱን ያምጣልህ "አሜን"

  ReplyDelete
 25. manhe profeserun yedegefk men aynet tebab chenkelat naw yalehe...??? better then anyone telalhe yalehew Ye Islam weyem ye 1 tera protestant blog lay aydelehem...Yalehew ye Orthodox blog lay nehe...Ye seletane mench,Ye ewket mench ke orthodox kefelku sewoch gar naw yemtaweraw....Enkuan yehe tera profesor kerto kesu yemibeltu sent ye Ewket balebet lejoch Enat endehonech resethewal malet naw.....Ateresa ye hagerachen telalek yemibalu ye poletica,social,ye tibeb alem yehonu sewoch meneshachew ezi naw.....Egzihabeher lebonahen yimelseleh...dengel mariyam ewnetun endetawek terdahe..

  ReplyDelete
 26. በመጀመሪያ የአንተ አስከሬን ይቃጠልና የአስከሬን ቃጠሎ ጀማሪ ተብሎ ስምህ በታሪክ መጽሐፍ ይዘከርልሃል፡፡
  sewyew gin Himanot alachew libona yistachew

  yodit

  ReplyDelete
 27. አሳቡን ከዚህ በአጭሩ እንደተረዳሁት ፕሮፌሰር ሬሳ ማቃጠል ቢለመድ አሉ እንጅ ማቃጠል መልመድ አለብን፣ ያስፈልገናል፤ የሚል አቋም አልሰነዘሩም ይህ ደግሞ ብዙ ዓለሞች በባህል መነሻነት የተለመደና እየተቀሙበት ያለ፣ ምንም ችግር የሌለዉና ከተወሰነ የማገዶ ወጪ በስተቀር ጠቃሚ አሰራር ነዉ፡፡ በአሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ምንም የግዳጅ እንድምታ የለዉም፡፡ ስለመሆኑም ስላለመሆኑም እግዚዓብሔር ጊዜ ሰጥቶ የሚያኖራቸዉ ሰዎች ያዩታል፡፡ ምንም ሆነ ምን ዋናዉ ዓላማዉ ሬሳን በክብር ወደሚፈለገዉ ቦታ ማኖር ነዉ ቁምነገሩ፡፡ ማቃጠልም ሆነ መቅበር በክር መሆኑን አንዘንጋና አሳባችንን በዚያ መልክ ብናንሸራሽር ጥሩ ይመስለኛል እንጂ ሰዎችን አግባብ ያልሆኑ ቃላቶችን በመሰንዘር መንቀፍ፣ መዘለፍ ራስን ምን ያህል በሞራል፣ በአስተሳሰብ ወዘተ. ወደዘብጥያ ማዉረድ ማዝቀጥ እንደሆነ እንወቅ፡፡ ምናልባት ከላይ አስተያየት የሰጣችሁት ብዙዎች በተለይም አንዳንዶች አገላለፃችሁ በጣም አሳዝኖኛል፡፡ ብታምኑም ባታምኑም ያገር አደንዛዥ ዕፆችን እያስተናገዱ በዚያ ኃይል የሚያስቡ፣ የሚሰበስቡና የሚሰሩ፣ ይህ ዕፅ ግን ሲጎድልባቸዉ ዐይናቸዉ የማያይ፣ አዕምሯቸዉ የማይሰራ…ወዘተ ዜጎች እየበዙብንና መካሪ ባለሙያዎችና ሳይንቲስቶችን እያጣን ነዉ ያለንዉ፡፡ ስለዚህ እኔ የምለዉ ፕሮፌሰሩን በዚህ በማይመች ሁኔታ ከማብጠልጠል ማለት የፈለጉትን በትህትና ቢጠየቁ ሊያብራሩ ይችላሉ፡፡ አላስፈላጊ ቃላቶችን ከመወርወር እንቆጠብ፡፡
  ማርጀቱ፣ መጃጀቱ እኮ ሁሉም የሚደርስበት የሚያልፈዉ ነዉ፣ ያዉም እንደእርሳቸዉ ስም ያለዉ ደረጃ ላይ ሳይደረስና በየሰፈሩ እየተኖረም ይህ እርጅና አይቀርም፣
  አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. To the above Anonymous :

   ማገዶውም እየተወደደ ነው ፤ ነገር ግን ሬሳ ማቃጠሉ ቢለመድ መሬትን ይቆጥባል . . . . . this is clear !! If he has been empowered to make a proclamation on this issue,what would be his fundamental remark(s)???

   To me, the prof. has made big mistake,,,,, he shall come back on the issue with new ..... and left the trash idea.

   Delete
 28. በመጀመሪያ የአንተ አስከሬን ይቃጠልና የአስከሬን ቃጠሎ ጀማሪ ተብሎ ስምህ በታሪክ መጽሐፍ ይዘከርልሃል፡፡

  ReplyDelete
 29. በመጀመሪያ የአንተ አስከሬን ይቃጠልና የአስከሬን ቃጠሎ ጀማሪ ተብሎ ስምህ በታሪክ መጽሐፍ ይዘከርልሃል፡፡
  AHUN ANTE PROFFESOR NEGN BILEH TAWERALEH.YEMATIREBA DEDEB NEGER NEH ESHI.STUPID ................

  ReplyDelete
 30. O' what does it mean algebagnim!

  ReplyDelete
 31. let us be positive, be ready to learn from others, tolerate others idea and let us allow people to talk what they feel. when i see the issue posted by the professor, i also agree that the idea is to early in Ethiopian context but the most surprising thing for me is when people confidently blame the idea of a well known professor.

  ReplyDelete