Sunday, January 15, 2012

ይህን ማየት የማይናፍቅ ማን አለ?

ምዕመናን ለታቦቱ ክብር የለበሱትን ነጠላ ሲያነጥፉ

የዘንድሮ ወጣቶቹ

(አንድ አድርገን ፤ ጥር ስላሴ 2004ዓ.ም)፡- ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ለጥምቀት ወደ ጥምቀተ ባህር ለሚሄዱ ታቦታት መረማመጃ ይሆን ዘንድ ምንጣፍ ማንጠፍ በአንዳንድ አብያተክርስትያናት አካባቢ የሚገኙ ጥቂት ወጣቶች አማካኝነት ቢጀመርም በአሁኑ ሰዓት በመላው አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ላይ እየተለመደ ይገኛል፡፡እግዚአብሔር ይመስገን ባለፉት 2 ዓመታት ለጥምቀት አስፋልት ላይ የሚነጠፍ ምንጣፍ በቅዱስ ራጉኤል ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፤በቅዱስ ኡራኤል ፤ በየካ ሚካኤል እና ሌሎች  የቤተክርስትያን ወጣቶች አማካኝነት ተነጥፈው ለአይን በሚማርክ ሁኔታ ማየት ችለናል፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ታቦታቱ የሚሄዱበት መንገድ በጣም ረዥም ስለሆነ ያን የሚያህል ረዥም ምንጣፍ ገዝተው ማንጠፍ ሳይችሉ ቢቀሩም የቻሉትን ያህል አንጥፈው የተቀረውን ደግሞ በሸክም ወደፊት ታቦታቱን በመቅደም አስፋልት ጠርገው ፤ ሳር ጎዝጉዘው ፤ ምንጣፍ  ሲያነጥፉ ፤  አበባ ሲበትኑ ፤ ሽቶ ሲረጩ ሲመለከቱ አንዳች መንፈሳዊ ቅናት ውስጥዎት ያርደዋል፡፡  

ዛሬ በ07/05/2004 4ኪሎ ስላሴ ቤተክርስትያን የተነሳ ፎቶ
ይህ የምታዩት ፎቶ ዛሬ ጥር ስላሴ ስላሴ ቤተክርስትያን አካባቢ ለምንጣፍ መግዣ ብለው ከምዕመናን እየሰበሰቡ በሚገኙበት ወቅት በጠዋት ያነሳናቸው ፎቶ ግራፍ ነው ፤ እነዚህን ወጣቶች በብርም በጉልበትም ለመርዳት ከፈለጉ 0913-955029 ወጣት አለሙ ብለው በማነጋገር የአቅሞትን ያህል መርዳት ይችላሉ፡፡


ይህን ስራ የሚሰሩት ወጣቶችን ምንጣፍ መግዣ ይሆናቸው ዘንድ በታህሳስ 3 ባዕታና ፤ በታህሳስ 19 በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ምንጣፍ አንጥፈው ‹‹ ለጥምቀት ለታቦታቱ መረማመጃ የሚሆን ምንጣፍ ለመግዛት ነው›› የቻላችሁትን እርዱን ‹‹ለታቦታቱ መረማመጃ የሚሆን መንጣፍ ለመግዛት ነው ምዕመናን የቻላችሁትን እርዱን›› ሲሉ ነበር ፤  በዓሉን ለማክበር ከመጣው ምዕመን ላይ በእንደዚህ ሁኔታ ጥቂት ገንዘብ መሰብሰብ ችለው ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከጃልሜዳ አንስተው የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እና የእመቤታችን የበዓታ ለማርያም ታቦታ ቤታቸው እስኪገቡ ድረስ ምንጣፍ የማንጠፍ እና የመዘርጋት ስራን ለመስራት ቢያንስ ከ3 ኪሎ ሜትር ያላነሰ  ምንጣፍ መግዛት ግድ ይላችዋል ፤ ለዚህ ምንጣፍ መግዣ ደግሞ ከጠዋት አንስተው እስከ ማታ ድረስ ምዕመናን እንዲረዷቸው ሲጠይቁ አርፍደው አምሽተዋል፤  ማየት ለምንጓጓለትን የጥምቀት በዓልን ሊያደምቁ ፤ ጊዜያቸውን ፤ ገንዘባቸውን ፤ ጉለበታቸውን በማጣመር ተነስተዋል ፤ እኛም በአቅማች ልንረዳቸው ግድ ይለናል፡፡እኛም ይህን በጎ ሀሳብ በብሎጋችን አማካኝነት ከሀገር ውጭም ሆነ ሀገር ውስጥ ላሉ ምዕመናን ዘንድ ብናደርስ የተሻለ ገንዘብ መሰብሰብ ይችላሉ ብለን አስበን ፎቶ በማንሳት ፤ አድራሻቸውን በመቀበል እናንተው ዘንድ ለማድረስ ከሳምንታት በፊት አስበን ሳለ በብሎጋችን ላይ ባጋጠመን የመዘጋት አደጋ አማካኝት ማድረስ አልቻልንም ነበር ፤ሰዓቱ ቢረፍድም  አሁን ላይ ከ4 ቀን በፊትእናንተው ዘንድ ማድረስ ችለናል ፤  እናንተም በረከት ታገኙበት ዘንድ የቻላችሁ  ባስቀመጥነው ስልክ ተጠቅማችሁ ምንጣፍ ገዝቶ በመስጠት ፤ ምንጣፍ መግዛት ያልቻላችሁ  የቻላችሁትን ያህል ገንዘብ በማዋጣት ፤ ገንዘብ ለማዋጣት አቅማችሁ ያልፈቀደ ምዕመኖች ደግሞ ከእነዚህ ወጣቶች ጋር በመሆን አስፋልት በመጥረግ ፤ ምንጣፍ በመዘርጋት ፤ ምንጣፍ በመሸከም ፤ ሳር በመጎዝጎዝ የቻላችሁትን ያህል አገልግሎት ታደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ፡፡

መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልን

ግቢ ገብርኤል አካባቢ ለሚገኙ ወጣቶች
ዜና ብለው 0913-090930 ደውለው የአቅሞትን በምን አይነት ሁኔታ መርዳት እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ

18 comments:

 1. I hope this year Epiphany will be celebrated in a good ways than the past years.our church youths will show us more decoration than the earlier years.For this I wish God blesses their good efforts.'gimariew tanash bihonm fitsamiew talak new'

  ReplyDelete
 2. እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ አሁን አሁን በጥምቀት በዓል እየተለመደ የመጡት ነገሮች በጣም የሚያስደሱቱ ነገሮች ናቸው፡፡ የጥምቀት በዓል በሂደቱ ብዙ ለውጦች የምናይበት ሲሆን ለምሳሌ በፊት ዘፈንና አልባሌ ነገሮች የሚደረጉበት አለማዊነት በጣም በሰፊው የሚገለጽበት ሲሆን አሁን ግን ያሁሉ ቀርቶ በመዝሙር በመተካቱ ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ የወጣቱ ተነሳሽነትና መንፈሳዊነት ገኖ መታየትም በጣም የሚያስደስት በመሆኑ በዚህ የበረከት ስራ ውስጥ የተሰማራችሁ በርቱ ግፍበት የሚያሰኝ ነው ነገር ግን ይህ ሁኔታ ወረት እንዳይሆን ስጋቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

  ReplyDelete
 3. እንኳን አደረሰን ሁላችንንም እንኳንም የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን አበቃን
  በጣም ደስ እያለኝ የበኩሌን አደርጋለሁ.
  @@ አለሙ ነገ እጠብቅሃለሁ
  Sara

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ
  Sara

  ReplyDelete
 5. Endet dese yemile kibir newe? wotatu teweled endigefubet masaseb ena ye tabotun mister endiawk madreg melkam yemeselegnal.

  ReplyDelete
 6. Enante feriwoch lemenden newe yemitsafelachehun asteyayet bedefret yematawetut. yehenen yemechereshawen 4:46 AM yetesafewen wushet yesafkut ene negne gene keza befit astemari yehone ewnet sefe neber..........Sara lay tenish tesaleku ende? Yemigermachehu neger Sara yenanten bezu baheri tewekelalech.........eza kuche beleh yehenen sansur yemetaderge hodamenem yechemeral...........hodeh sitegeb enkelf tataleh.

  ReplyDelete
 7. Berta, sewe lehodu becha aynorem............tadia kebefitu gare ayayzeh awtalign...degmo ketayunem chemerebet. Ayzoh........wodaje..........lewunet belew abatoch ye semaet mot motu....... bemegaz tesentekew..... be fella wuha tekekelew...........tardew.....tezekzekew tesekelew.

  ReplyDelete
 8. enbaye newu yemetawu kedestaye bizat bertu tebareku!!!

  ReplyDelete
 9. kedestay izat enbaye newu yemetawu tebareku!!!

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሄህ ሃገራችንን ይባሪክ ድንቅ ስራ ነው

  ReplyDelete
 11. betam dink yehone ye Egziabher Fikir Be Ethiopia wetatoch Eyetaye new.
  Engidih lib yalew li yibel,joro yalew yisma...:yewetatu meliekit min endehone meredat yasfeligal..Ethiopia min getsita endalat ena linorat endemigeba yasayenal..

  ReplyDelete
 12. temesegen............egziyabher andenetachen be alem yisefa eziben aden amelak hoye ,,,,betam desese yilale bereketu lehulum yideese,,,,yeagelegelote zemenachewen ybarekelache amelak ohye GOD BLESS ALL,,,

  ReplyDelete
 13. betam des yamel hasab new e/r yebarekachehu!!!

  ReplyDelete
 14. God bless Ethiopia.......i love u all who tried ur best to make this happen

  ReplyDelete
 15. አቤቱ ክርስቶስ እየሱስ ሆይ ልባችንንም እንድናነጥፍልህ አንተ ማስተዋልንና ጥበብን ስጠን፡፡

  ReplyDelete