Monday, January 16, 2012

እንዲህም አስበው ነበር


(አንድ አድርገን ፤ ጥር 7 ፤ 2004)፡- በአሁኑ ሰዓት በታላቅ ድምቀት ጥምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች  ጎንደር አንዷ ናት ፤ በጥምቀት እለት የሚወጡ ታቦታት በዛ ስለሚሉ አከባበሩም ከሌላው ቦታ ይልቅ ልዩ ስለሚሆን የውጭ ዜጎች ጥምቀትን ለማየት ወደ ጎንደር ማቅናት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ የካርኒቫል ዝግጅት የተጀመረው ባለፈው ዓመት ነበር ፡፡ መጀመሩ ባልከፋ ነገር ግን የካርኒቫሉ አዘጋጆች እና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ከስርአተ ቤተክርስትያን ውጪ በሆነ መልኩ ለአብያተክርስትያኖቹ ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር ፤ ትዕዛዙም ‹‹ለካርኒቫሉ ድምቀት ሲባል ከ04/05/2004 ጀምሮ እስከ 10/05/2004 ዓ.ም ድረስ ታቦታቱ ወደ ጥምቀተ ባህር ቀስ በቀስ እያሉ ቢወጡ››  ብለው መመሪያ አስተላልፈው ነበር ፤ ነገር ግን በምዕመናን እና በካህናት በደረሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ሀሳባቸውን ሊያጥፉ እና አላልንም ፤አልወጣንም ብለዋል፤
 ሀገሪቱ ያላትን የእምነት ስርዓት እና ትውፊቶቻችንን ለውጭ ዜጎች ማስተዋወቅ ተገቢ ነው ፤ ሀገሪቱ ከቱሪዝም የምታገኝውን ገቢ እና የጎብኝን ፍሰት ከመጨመር አኳያ ጉልህ ሚና ያለው ስራ ነው ፤ ነገር ግን የእኛን ስርዓት ለእኛ ትታችሁልን እናንተ የሚመለከታችሁን ብቻ ብትሰሩ መልካም ነው፡፡ነገሩም ብዙ ቢያነጋግርም በአንድ አቋም ስርዓተ ቤተክርስትያን መፋለስ የለበትም በሚሉ ምእመናን ምክንያት ነገሩን ረገብ ሊያደርጉት ችለዋል፤ መንግስት ካርኒቫሉን ለማድመቅ እና ከፍተኛ ገቢ ለማግኝት ማሰቡን አንቃወምም ፤  ነገር ግን ሁሉ ነገር በስርዓት ቢሆን ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለን ፤ እስካሁን በዘመናችን ከጥር 10 በፊት ለጥምቀት ታቦት ሲወጣ አላየንም ወደፊትም ማየት አንፈልግም ፤ አባቶቻችን አደራ ብለው ያስረከቡንን ቀኖና እና ዶግማ ሳናሳንስ ሳንጨምር ለልጅ ልጆቻችን የማውረስ ታሪካዊ ሀላፊነት አለብን ፤ህገ መንግስቱ በሀይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ እንደማይገባ ይናገራል ፤ ይ ቢሆንም ቅሉ በተለያየ መንገድ ቤተክርስትያን ከመንግስት ጫና ተላቃ አታውቅም ፤ በግልፅ ባይሆን እንኳን ስውር የማይታዩ እጆች ከመንግስት በኩል የተሰበሰቡበት ጊዜ የለም፡፡  በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ታላቁን በዓል ለማክበር የሰርጓ ቀን የደረሰ ሴት ይመስል እየተዋበች ትገኛለች  ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወጣቱ ፤ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በአንድ ላይ በመሆን በዓሉ የደመቀ ሆኖ እንዲያልፍ የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ 


‹‹የመረጃ ምንጭዎ ሆነን እንሰራለን ››

2 comments:

  1. ሱስንዮስ ዳግመኛ በጎንደር ነገሠ!!!!!!
    ካርኒቫል የሚባለውን ቃል ጎንደር ሰምታም፣ አይታም አታውቅ። ሱስንዮስ ግን ካቶሊክን ያውቃል። ዛሬ ደግሞ የጥንቷ የሱስንዮስ ካቶሊክ መንግስታዊ ካርኒቫል ሆና ዳግም መጣች። ያ ማለት ደግሞ ሱስንዮስ ዳግመኛ በጎንደር ነገሠ ማለት ነው። እነወሬ ብቻ ደጀሰላምም ሆኑ አንድ አድርገን ራሱ ትልቁ ማኅበር በዚህ ዙሪያ ምንም ትንፍሽ አለማለታችሁ «ይህቺን ቤተክርስቲያን ሲፈጅ በማንኪያ፣ ሲቀዘቅዝ በእጅ » ከምትቀርቧት በስተቀር ዓይን ያፈጠጠ ችግሯን ለመጋራት አትፈልጉም። ለመሆኑ «ካርኒቫል» ምንድነው? « ሥጋን መብላት ለማቆም ማለት ነው»
    ካርኒቫል የካቶሊክ እምነት ባህልና ወግ የሚታይበት የጭፈራና የዳንስ ትርዒት በዓል ሲሆን ይህም ሁልጊዜ ከኩዳዴ ጾም በፊት ባሉት ሳምንታት የሚከናወን ሥርዓት ነው። «Where did the word “carnival” come from?
    Hundred and hundreds of years ago, the followers of the Catholic religion in Italy started the tradition of holding a wild costume festival right before the first day of Lent. Because Catholics are not supposed to eat meat during Lent, they called their festival, carnevale — which means “to put away the meat.” As time passed, carnivals in Italy became quite famous; and in fact the practice spread to France, Spain, and all the Catholic countries in Europe. Then as the French, Spanish, and Portuguese began to take control of the Americas and other parts of the world, they brought with them their tradition of celebrating carnival. »
    ታዲያ የጎንደሩ ካርኒቫል በኦርቶዶክሱ ጥምቀት ላይ ምን ይሰራል? የማንን ካርኒቫል ነው ጎንደር የምታከብረው? «መጽአ ሱስንዮስ ንጉሥኪ፣ ከመ ያማስን ክብርኪ ኤጲፋንያ፣ እንዘ ይብል ካርኒቫልሃ ሃሌ ሃሌ ሉያ»
    ባይ ባይ ሚያ ማማ ጎንደር!!!! ciao mia mamma Gonder!!!!!!!

    ReplyDelete
  2. ahunis min yishalenal minim albeqa alachech yezihch betekrstian neger bewistim bewichim metenfesha asatuat eko gobez. Tenseu!!!
    Meyisaw Kassa

    ReplyDelete