Sunday, January 22, 2012

ለጥምቀት በአል ታቦተ ህጉ ከመንበሩ አልንቀሳቀስ አለ


(አንድ አድርገን ጥር 14 2004ዓ.ም)፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ከከተራ ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በመላው ሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ በሰላም ሊያልፍ ችሏል፡፡ ብዙ አዳዲስ ክስተቶችን ከባለፈው ዓመት ጨምሮ ይዞ መጥቶ ነበር ፤ ብዙ ያልተሰሙና ከዚህ በፊትም ያልታዩ ነገሮች ተከስተዋል፤ በአዲስ አበባ በመገናኛ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስትያን የተፈጠረው ነገር የሚገርምም የሚደንቅም ነበር ፤ በቤተክርስትያኑ ውስጥ በዋናነት የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፅላት ሲኖር በድርብነት ደግሞ የእመቤታችን የቅድስት  ድንግል ማርያም  ፤የመልአኩ  የቅዱስ ገብርኤል ፤ የፃድቁ አባታችን  የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስና ፤ የመድሀኒዓለም ታቦታት አንድ ላይ ይገኛሉ ፤ ከዚህ በፊት  የቅዱስ ገብርኤል እና የእመቤታችንን ታቦተ ህጎችን ጥር  10 ወጥተው ጥር 11 ወደ ማደርያቸው ሲመለሱ የእግዚአብሔር አብ ታቦት ግን ጥር 12 ወጥቶ ጥር 13 ወደ መንበሩ ይመለስ ነበር ፡፡ በዚህኛው የጥምቀት በአል አከባባር ላይ ግን የቤተክርስያኑ ካህናት አባቶች ከበአሉ ከቀናት በፊት ተሰባስበው እስከ ዛሬ ድረስ የእመቤታችን እና የቅዱስ ገብርኤልን ታቦተ ህጎች ነበር የምናወጣው አሁን ለምን ቀይረን የመድሀኒአለምን እና የፃድቁን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦተ ህጎች በመቀየር እናውጣ ተባብለው ሁሉም በሀሳቡ ተስማምተው ይለያያሉ ፡፡ ጥር 10 ቀን ደረሰ ፤ መዘምራን ፤ ህፃናት ፤ የአካባቢ ወጣቶች ፤ አዛውንት እናት አባቶች ፤ ብቻ ሁሉ ሰው የታቦታቱን መውጣት እየተጠባበቀ ቤተክርስትያኑን በመክበብ በሰንበት ተማሪዎች ዝማሬ  ፤ በእናቶቻቸን እልልታ በጣም በደመቀ ሁኔታ የታቦቱን መውጣት ሲጠባበቁ ሳሉ ታቦተ ህጉን ለማውጣት ወደ ውስጥ የገቡ ካህናት አባቶች ግን ያጋጠማቸው ሌላ ነገር ነበር፡፡


ከቀናት በፊት ካህናት አባቶች እንደተነጋገሩት የመድሀኒአለምንና የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦታት ለማውጣት ቅድስት ውስጥ ገብተዋ   ታቦት አክባሪው ካህን  የተመረጡት አባቶች ታቦቶቹን ከመንበሩ ላይ ማንሳት ቢሞክሩ ማንሳት ያቅታቸዋል ፤ አንዴ ሞከሩ፤ ሁለቴ  ቢሞክሩም ሁለቱንም ታቦታት  ማንሳት ተሳናቸው ፤ በሁኔታው ግራ የተጋቡት ካህናት ‹‹ለምን ታቦት አክባሪው ካህን   አንቀይርም›› በማለት  ታቦት አክባሪው ካህን  አባቶች ቀይረው ፤የእግዚአብሔር ፍቃዱ እንዲሆን ረዘም ያለ ጸሎት አድርገው የተቀየሩት አባቶች ታቦቱን ከመንበረ ክብሩ ለማንሳት ሲሞክሩ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ታቦት ሲነሳላቸው የመድሀኒአለም ግን በተቀየሩት ካህንም አልነሳም አላቸው ፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስን ታቦት  አክባሪው ካህን ጥቂት እርምጃ ተራምደው ከቤተክርስትያኑ ሳይወጡ እንዳልቻሉ ፤ እንዳቃታቸው እና እንዲያወርዱላቸው አጠገባቸው ያሉትን ካህናት አባቶች በመጠየቅ ሊያወርዱላቸው እና ወደ መንበረ ክብሩ  ሊመልሱላቸው ችለዋል ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከውጭ የሚሰማው ዝማሬ እልልታ እንደቀጠለ ነው ፤ ወጣቶቹም ለታቦተ ህጉ መረማመጃ ይሆን ዘንድ ምንጣፍ ማንጠፉን ተያይዘውታል ፤ በመጨረሻም  የእግዚአብሄር መልካም ፍቃድ ስላልሆነ ለሶስተኛ ጊዜ ለማንሳት ሳይሞክሩ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የእመቤታችንን ፤ የቅዱስ ገብርኤልን እና የእግዚአብሔር አብን ታቦታት በማውጣት በአሉን ሊያከብሩ  ችለዋል፡፡

የዛሬ ሶስት ዓመት ቃሊቲ የሚገኝው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስያን ውስጥ ለበአለ ጥምቀት የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባህር ቢወስዷቸውም የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት መመለስ ሲችል የእመቤታችንን ታቦት የተሸከሙት ካህን መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እና ቦታው ላይ ቆመው መንቀሳቀስ እንዳቃታቸው ፤ በብዙ  ፀሎትና ፤ በብዙ እግዚኦታ ከቆመበት ቦታ መንቀሳቀስ ስላልቻለ እዚያው ድንኳን ተጥሎ ፤  በሱባኤ የቆመችበት ቦታ ላይ በአሁኑ ሰዓት የጉስቋም ቤተክርስያን ተሰርቶ ከዚህ በፊት ቦታው ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ብዙ ህመምተኞች ቦታውን በመርገጥ ፤ ጸበል በመጠመቅ ፤እምነቱን በመቀባት እየተፈወሱ ይገኛሉ ፤

12 comments:

  1. አንድ አድርገኖች ያላወቃችሁት ነገር የስብከተ ወንጌል ኃላፊው የለየለት መናፍቅ መሆኑን እና ከሳምንት(ወይም ከአስራ አምስት) ቀን በፊት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ያሳሰረ መሆኑን ነው:: እስቲ አጣሩት እና ታዘቡኝ::

    ReplyDelete
  2. ርብቃ ከጀርመንJanuary 23, 2012 at 12:55 AM

    ተናገሩ ድንቅስራውን መስክሩ ታምሩን ለዓም ንገሩ ማለት ይሄ ነው ምንምብናሳዝነውም ቅሉ ያባቶቻችን አምላክ አሁንም ምህረቱን ጨርሶ አልወሰደብንም በቸርአይኑ አሁንም ሀገራችንን እንደሚጎበኛት ነው የሚያሳየው:: ጨርሰን እንዳናስቀይመው የምህረት አይኑን በቁጣ እንዳናደፈርሰው ማስተዋልን በቸርነቱ ከህጻን እስካዋቂ, ከካህናት እስከምእመናን, ከመሪ እሰከተመሪ ይሰጠን ዘንድ ባንቃእዶ ልቡና ወደርሱ ፊታችንን ልናዞር ይገባናል:: አለበለዚያ ካለፈው መጭው ይብሳል እንዳይሆንብን የድንግል ማርያምልጅ በፍቅሩ በርህራሄው ይጎብኘን አሜን::

    ReplyDelete
  3. beliwo le egzi abher girum gebrike!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ክብር ለአምላካችን ይሁን።

      Delete
    2. yemegerem new bewenu le egezeabeher yemesanew neger alen? gen abatoch ande embe kale lemen tolo ayeredum melekoten aydel ende yemeyagelegelut
      EGEZEABEHER AMLAKEHEN ATEFETATENEW TEBELO TESEFUWAL AYDEL

      Delete
  4. egziabher siraw grum chernetum deniq new!!! bemegerem kemanbat beqer min enilalen? mihretun yalaraqe amlak kiber hulu le ersu yihun! amen!!

    ReplyDelete
  5. Temesgen Amlakachin. Egziabher kegna gar menorun beteleyaye melku yigeltsal. yihem andu new. Temesgen.

    ReplyDelete
  6. ከመቼውም ጊዜ በላይ በፈጣሪ ላይ ከፍተን ተነስተናልና አሁንም የቀደመውን ያባቶቻችንን ዘመን ይመልስልን፡፡መከፋፈላችን መባላታችን
    መናከሳችን ይልቁንም ስዩማነ እግዚዓብሄር በሆኑ ጳጳሳት አባቶች መካከል የሚታየው የጎላ መናከስ እና መባላት ቅስፈቱ ለሁላችን የሚተርፍ ነውና እባካችሁ ታቦቱም ከመንበረ ክብሩ አልወጣ ማለቱ የኛው የጉዳችን ውጤት ነውና እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ በፀሎት በለቅሶ እንበርታ፡፡እግዚዓብሄር የቀደመውን ያባቶቻችንን ዘመን ይመልስልን፡፡

    ReplyDelete
  7. እመ ብርሃን የብርሃን እናቱ እናታችን ድንግል ማርያም ክብሯ ይስፋ ፀጋዋ አይጓደል
    እሷን የሰጠን ይክበር ይመስገን!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  8. የአምላካችን ሥራው ግሩም፣ትዕግስቱም ብዙ ነው፣ የእኛ የበደላችን ብዛት እየተነገረን ይገኛል፡፡

    ReplyDelete
  9. ቃለ ሕይወትን ያሰማቹ። ለታቦት ተሸከመ አይባልም። ታቦት አክባሪው ካህን በሚለው ይስተካከል። ስራችሁ ጥሩ ነው አባቶቻችን ለፊደላት ለቃላት እንደሚጠነቀቁ እኛም ፈለጋቸው እንከተል።

    ReplyDelete
  10. ye'amlakachn egziabher sim besemayim bemidirm ke atsnaf eske atsnaf yetemesegene yihihun.

    ReplyDelete