Wednesday, January 18, 2012

አሁንም እሳቱ እየወረደ ይገኛል


(አንድ አድርገን ጥር 10 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በከምባታ ሐዲያ ጉራጌ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት በሐዲያ ዞን ሊሙ ወረዳ ናራ መድኃኔ ዓለም አጥቢያ ከቀናት በፊት እሳት በአካባቢው ላይ እንደሚወርድ ሰምተናል ፤ እስከ 09/05/2004 ዓ.ም ድረስ እሳቱ መውረዱን አለማቋረጡንም ለማወቅ ችለናል ፤ የእሳቱ ፀባይ ከጣሪያ ጀምሮ ማቃጠል ይጀምራል ወደ ታች በመውረድ እስከ መሰረቱ ይበላዋል ፤ አመድም ያደርገዋል ፤ እንዲህ አይነት እሳት ከዓመት በፊት በሀረርጌ ክልል የተከሰተ አይነት እሳት ነው ፤ በአካባቢው መናፍቃን በብዛት ያሉበት ቦታ ነው ከአካባው ሰዎች ጠይቀን ለማወቅ እንደቻልነው ፤ እሳቱ እስካሁን የወረደው እየወረደም ያለው መናፍቃኑ እና ኢ-አማንያኑ ቤቶች ላይ ነው ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ይህን ድርጊት የፈጸሙት ክርስያኖቹ ናቸው ብለው የአካባቢው ፖሊሶች ጥቂት ሰዎችን ወደ እስር ቤት እንደወሰዷቸው ለማወቅ ችለናል ፤ ነገር ግን እነዚህ ሰዎችም ታስረውም እሳቱ ቤቶቹን መብላት አላቆመም ነበር ፤ ይህን ዜና የሰሙት የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአስቸኳይ ቤታቸው ለተቃጠለባቸው ሰዎች ድንኳን እንዲጣል እና ማረፊያ እንዲሆናቸው ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር ፡፡ የክልል ፕሬዝዳንት በሁኔታው ግራ ከተጋቡት የመንግስት ተወካዮቻቸው ጋር ችግሩ የደረሰባቸውን በድንኳን ማረፊያቸው ሊጎበኙ የመጡ ሲሆን ቤታቸው የተቃጠለባቸውን ሰዎች እየጎበኙ ሳሉ እነርሱ ያሉበት አካባቢ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ እሳቱ ከሰማይ ሲወርድና ቤቶቹን ሲበላ ሊመለከቱ ችለዋል፡፡ የታሰሩትንም ሰዎች እነርሱ እዳላቃጠሉ ከሰማይ የሚወርድ እሳት ስለሆነ በነፃ ሊለቋቸው ችለዋል፡፡ አሁንም እሳቱ እየወረደ ይገኛል፡፡ ቁጣህን አብርደው ምህረትህን አውርደው ማለት አሁን ነው፡፡

13 comments:

  1. awon ahun adin malet new

    ReplyDelete
  2. አቤቱ ምህረትህን አብዛልን!

    ReplyDelete
  3. ምነው ከእናንተ በስተቀር አንድም የዜና ማሰራጫ ይህንን ዓይነት ክስተት በመረጃ አስደግፎ አላቀረበም። ምነው ተረት መሰለ? ጂኦሎጂስት ወይም አስትሮ ፊዚሲስት ወይም ተመሳሳይ ባለሙያ አስተያየት ያልሰጠ? የግል ሚዲያ ወይም የመንግስት ምነው ያልዘገበ? ወይም እናንተ ይህ ምስጢር የተገለጠላችሁ መረጃው ለሁሉም እንዲዳደረስ በሚዲያው ይታወቅ ዘንድ ያላደረጋችሁ? መጽሐፍ «ምስክር በሁለት ወይም በሦስት አፍ ይጸናል» እንዳለው ከእናንተ ውጪ «አንድ አድርገን/ደጀሰላም» ውጪ በተመሰከረለት ማስረጃ ካልሆነ ከወሬነቱ በዘለለ እንዴት «ይገርማል፣ ይደንቃል ልንል እንችላለን። የሚሰማ ሁሉ እውነት ነው ይባል ዘንድ አግባብ አይደለምና አስቡበት!!!!!

    ReplyDelete
  4. ለምን የተቃጠሉት በቶች አታሳዪንም

    ReplyDelete
  5. Regardless of whose house was under fire one thing is for sure. Our God is a loving and forgiving God!! Compared to our sin this is very monor. What is amazing to me is that we still are moving the same direction. I mean we don't live the way christians are supposed to live. No positive change at all!!

    ReplyDelete
  6. አሜን! አምላክ ምህረቱን ያውርድ

    ReplyDelete
  7. ere men ale yehen meatun kindune le resut le ahezab memarjia behonachew?

    ReplyDelete
  8. እሳቱ እስካሁን የወረደው እየወረደም ያለው መናፍቃኑ እና ኢ-አማንያኑ ቤቶች ላይ ነው ? ምን ማለት ነው?ኢ-አማንያን እና የሌላ እምነት ተከታዮች በዓለም ላይ በየሃገራቱ ይገኛሉ : ፈጣሪ እነሱን መቅጣት ከፈለገ ኢትዮጵያ ውስጥ : ለዛውም ምንም ዓይነት ዘመናዊነት የሌለበት የገጥር ከተማ መቸም አይመርጥም :: ከሆነም ደግሞ ቴክኖሎጂ በሞላበት ዘመን በቭዲዮ እና በ ፎቶ የተደገፈ መረጃን ዘገባ ማቅረብ ግድ ይላል::

    ReplyDelete
  9. Betam yasekal!! Sew enkuan lesew leji asebo yekelelu menegeset enekuan denekuan tklelachew alachihu gen fetari esun bemayakut laye chekeno esate aworedebachew degemo kehonem lemen denekuanu meleso aletekatelem? Ways fetari sewene sayhon botawen new yemifelegew? Anede negere masebe yalebene yemeselegnal lesew leji sile eneji lebota sile aydelem Jesus demun yafesesew ?. Ere gene lemehonu esatun kayachehut eskahun eyezenebe kehone lemene bemasereja lemesekerenet atakerebutem be adobe yetesera photo post kemetaderegu degmo esatun leke yefetari kuta enedehone maregagchachehu meneden new wyes subae gebetachehu new?

    "Love is patient. Love is kind. It does not envy. It does not boast. It is not proud. It is not rude. It is not self-seeking. It is not easily angered. It keeps no record of wrong doing. It does not delight in evil, but rejoices in the truth. It always protects, trusts, hopes, perseveres."
    ~ 1 Corinthians 13

    ReplyDelete
  10. Engidih min enlalen?wede amlakachin metseley new enji.Mihiretihin awred.
    Mecheme yihin yemayamnu sewoch yerasachewin asteyayet sisetu yitayal.lemamen bebotaw hedo mayet sigeba...meterater min ametaw?

    Enante emnetachihu yegodele...Ebakachihu le Egziabher yemisanew neger endelele teredut...libachihu yimeles...

    May God Bless Ethiopia.

    ReplyDelete
  11. please you guys,don't write such rubbish and unbelievable things.As it is said you have to support it with evidence if your news is true.I am Orthodox but I can't believe it.

    ReplyDelete