(አንድ
አድርገን ሚያዚያ 10 2004ዓ.ም)፡- በትላንትናው ቀን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
በምክር ቤቱ አባላት በተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ነበር ፤ ስለ ሀይማኖት አክራሪነት ላይ በተነሳው ጥያቄ ላይ በተነሳ
ጥያቄ ላይ ውሀቢዝምን ካስረዱ በኋላ አንዳንድ የዚህ አይዲዎሎጂ ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ‹‹የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ›› በማለት መስለዋቸዋል ፤ ይህ ምን ማለት ነው? ክቡር ጠቅላይ
ሚኒስትር የተረዱት ማህበረ ቅዱሳን የሀይማኖት አክራሪነት የሚያራምድ ማህበር አድርገው ነው የሚያስቡት ፤ ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ
እንዴት አክራሪ ይባላል? ፤ ከአባቶች የተረከቡትን እምነታቸውን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ስራ ቢሰሩ እንዴት የሀይማኖት
አክራሪዎች ሊባሉ ይችላሉ ? ፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የእውቀት ማነስ ከሌለብዎ በስተቀር ይህን ማለት ባልቻሉ ነበር ፤ እኔ
በበኩሌ ወሀቢዝም የሚለውን አይዲዎሎጂ በመሰረቱ የገባዎት ራሱ አይመስለኝም ፤ አለማወቅ ሀጥያት አይደለም ነገር ግን አለማወቅን
እንደ እውቀት ቆጥሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ በምክር ቤቱ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም ፤
ማህበሩን ለማያውቀው
ሰው እንዲህ ነው ብሎ ለንግግር ማጣፈጫዎ መጠቀምዎ ተገቢ አይደለም ፤ ከበታችዎ ያሉት ሰዎች እውነቱን ሳይሆን መስማት
የሚፈልጉትን ነገር ነው የሚግርዎት ፤ ከወራት በፊት ሳያስቡ የሚናገሩት አቦይ ስብሀት ‹‹ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው
›› በማለት ከአንድ የሀገር ሽማግሌ ሊጠበቅ የማይችል ንግግር በአደባባይ ተናገሩ ፤ እኔ በበኩሌ እርጅና ሊሆን ይችላል በማለት
አልፌዋለሁ ፤ ሰው ሲያረጅ ወደ ህጻንነት ይመለሳል ይባላል ፤ ይህ ነገር እውነት መሆኑን የዛኔ ነው ያየሁት ? በዚህ አጋጣሚ
ጭንቅላት ያለው ሁሉ አያስብም የሚል ጥቅስ በልጅነቴ አንብቤ ነበር
፤ ለካንስ እውነት መሆኑ የገባኝ ዘንድሮ ነው ፤ ያኛው የትግል አጋርዎ በቅርቡ በውጭ ሚዲያ ሀገራችንን የማይመጥን
አሳፋሪ ቃለ መጠይቅ ያደረገው አቶ ታምራት ላይኔ ፓትርያርክ ሸኝቶ ፓትርያርክ ሲያመጣልን ፤ አቦይ ስብሀት ደግሞ መደራጀቱ
ያላማራቸው ማህበረ ቅዱሳን ላይ የቃላት ጦርነት ይከፍቱ ጀመር ፤ ቤተክርስትኒቷ ጌታ በወንጌል ‹‹ አይችሉሽም›› ተብላለች ፡፡
የኢህአዴግ
ትልቁ ችግሩ ከ1997 በኋላ ሰዎች ማህበር ሲፈጥሩ አይኑ ደም ይለብሳል ፤ ጥሩ እቅልፍ ላይ ካለም ይባንናል ፤ ፍርሀት ጥሩ
ነው ፍርሀቱ ደግሞ ጠርዙን ያለፈ ይመስለናል ፤ ሰው በሀይማኖት ስም ስለ ቤተክርስትያ ብሎ ማህበር ሲመሰርት በሌላ አይን
መመልከት ጤነኝነት አይመስለንም ፤ እናንተ ፖለቲካችሁ ላይ ብትበረቱ እኛ ደግሞ እምነታችን ላይ እንበረታለን ፤ ከአባቶቻችን
የተቀበልነውን እምነት እና ስርዓት ለልጆቻችንና ለልጆቻችሁ ለማውረስ እንሰራለን ፤ ወሀቢዝም ምን ማለት እንደሆነ ካላወቃችሁት
እኛ ልናስረዳችሁ ፍቃደኞች ነን ፤ እናንተ ጋር ካለው አመለካከት እኛ ጋር ያለው መረጃ የሚሻል ሊሆንም ይችላል ፤ ይህን
አመለካት ከጥቂት ሰዎች በስተቀር እስከ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ድረስ ገብቷቸዋል ብዬ አላስብም ፤ እነዚህ ሀይሎች ሀገሪቱ
በእስላማዊ መንግስት እንድትተዳደር የሚፈልጉ ፤ ሙስሊም ማህበረሰቡ ግብር መክፈል ያለበት ለእስላማዊ መንግስ እንጅ ለሌላ
አለመሆኑን አጥብቀው የሚሰብኩ በ2020 ዓ.ም በመላው አፍሪካ ላይ አይዲዎሎጂውን በማሰራፋት የእምነቱን ተከታዮችን እንደ
ነብያቸው መሀመድ ከተቻለ በስብከት ካተቻለ በሀይል ለማበርከክ ቆርጠው የተነሱ ፤ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ከአረብ መንግስታት
የተመደበላቸው ለአላማቸው መሳካትም ውስጥ ውስጡን ቀን ከሌት የሚሰሩ ሰዎች ናቸው ፡፡ የቀድሞ የአሜሪካን ኢምባሲ አምባሳደር
በአገሪቱ ላይ ምን እንደሚሰሩ መረጃ ደርሷቸው ለስቴት ዲፓርትመትን የጻፉት ምልእክት በዊኪሊክስ አማካኝነት ይፋ መውጣቱን
አታውቁትም ብለን አንገምትም ፤ ታዲያ እነዚህን በምን ምግባራቸው እና ስራቸው ነው ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ያመሳሰሏቸው? ማህበረ
ቅዱሳን ክርስትያናዊ መንግስት ለማቋቋም የሚሰራ ተቋም አይደለም ፤ ባይሆን የእምነቱ ተከታዮች በክርስትና እንዲኖሩ የሚጥር ተቋም
እንጂ፡፡
ጠቅላይ
ሚኒስትራችን የተናገሩት ለእኔ እንደገባኝ ‹‹እነዚህ ሰዎች
የእስልምና አክራሪዎች ናቸው ፤ ማህበረ ቅዱሳንም የኦርቶዶክስ አክራሪ ማህበር ነው›› ለማለት ፈልገው መሰለኝ ፤
ቤተክርስትያንን ስርአቷ መጠበቅ እና ማስጠበቅ ፤ ለቀጣይ ለልጆቻችን እና ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ መቻል እንዴት አክራሪ ያስብላል
፤ ስጋችሁ ከነፍሳችሁ ስትለይ ቀብራችሁ እንኳን እንዲደምቅላችሁ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን የምትመጡ ሰዎች እኮ ናችሁ ፤
መቼስ ቀብሩ ስለደመቀ መንግስተ ሰማያት የሚገባ ፤ ቀብሩ ስላልደመቀ ሲኦል የሚገባ ነፍስ የለም ፤
ጠቅላይ
ሚኒስትራችን ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5 ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ብለው ጥምቀት በዓል ላይ የሚለብሱ
ወጣቶች የሚለብሱት ቲሸርት ላይ የተጻፈው ጥቅስ ሊዋጥላቸው ባለመቻሉ ቅሬታ ያለባቸው መሆኑን በንግግራቸው ማወቅ ይቻላል ፤
ይህን ጥቅስ ማህበረ ቅዱሳን የጻፈው ጥቅስ አይደለም ፤ ማህበሩ ገና 20 ዓመት አልሞላውም ፤ ጥቅሱ ግን 2000ዓመት አለፈው ፤ ይህ እስከ ህይወታችን መጨረሻ
የምንታመንበትና የምናምንበት የወንጌሉ ቃል ነው ፤ በሀገሪቷ ህገ መንግስት አንቀጽ 27 ‹‹የሀይማኖት የእምነትና የአመለካከት
ነጻነት›› በማለት ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ ‹‹ ማንኛውም ሰው የማሰብ የህሊናና የሀይማኖት ነጻነት አለው ፤ ይህ መብት ማኛውም
ሰው የመረጠውን ሀይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል መብት›› እንዳለው ይደነግጋል ፤ ይህ ወደ ኤፌሶን ሰዎች የተጻፈው
መልእክት ደግሞ ህገ መንግስቱን ይጋፋል ፤ ስለዚህ ይህን ነገር አቶ መለስ ቢቃወሙ እኔ በበኩሌ አልፈርድም ፤ ወንጌሉ ሲጻፍ
ሙስሊሞች ፤ ፕሮቴስታንቶች ፤ ካቶሊኮች ፤ አድቬንቲስቶች የሉም የነበርነው እኛ ብቻ ነን ፤ ለዚህ ደግሞ እኛ ዝም ብንል የእነዚህ
እምነት መሰረቶቻቸው ምስክሮች ናቸው ፡፡ እኔ ያልገባኝ ነገር ‹‹አንድ
ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ብሎ ማመን እንዴት አክራሪ ክርስትያን ያስብላል ? ‹‹አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና
ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።››ዮሐንስ ራእይ 22፤13
ይላል አንድ ጌታ ብለን እናምናለን ፤ አንዲት እውነተኛ እምነት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብለን እናምናለን ፤ አንዲት
ጥምቀት ብለንም እናምናለን ታዲያ የኦርቶዶክስ አክራሪዎች እንባላለን ? እኛ እኮ እናንተ በአፋችሁ የምትክዱትን በውስጣችሁ
የምታምኑትን እምነት ነው የምንከተለው ፤ በርካታ አባላቶቻችሁ የዚች እምነት ተከታይ ናቸው እናውቃለን ፤ወንጌሉ የሚያዘን ‹‹ ንቁ፥
በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።›› 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 16 ፤13 ታዲያ ሰው በሃይማኖቱ ስለቆመ ፤ በእምነቱ
ስለጎለመሰ እንዴት አክራሪ ሊባል ይችላል ?
ባለፈው
ጥምቀት ምን ሆነ መሰላችሁ ፤ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች የጥምቀትን በዓል ለማክበር ሲንቀሳቀሱ ለመንገዶች ማስዋቢያ የገዙት ባንዲራ መሀሉ ላይ ኮከብ የሌለበት ነበር ፤
ይህ ባንዲራ በተሰቀለ በሰዓታት እድሜ ውስጥ የፌደራል ፖሊስ አባላት መጥተው አማርኛ መናገር የማይችሉ አባላት ፤ ‹‹ባንዲራው
ላይ አንባሻ አድርጉበት ወይም አውርዱት አሏቸው››(ይህ አነጋገር ከአንደበታቸው የተሰማው እንጂ የኔ አይደለም) ፤ ወጣቶቹም ‹‹መሀሉ
ላይ አንባሻ እድርገን ባንዲራውን አንሰቅልም ›› ፤ ብለው በማውረድ አረንጓዴውን ለብቻ ፤ ቢጫውን ለብቻ ፤ ቀዩን ለብቻ ፤ መሀል
ላይ ነጭ ቀላቅለውበት በየስልክንጨቱ በመስቀል በዓሉን ሊያከብሩ ችለዋል ፤ ከ10 ዓመት በፊት የማከብራቸው ጠቅላይ ሚኒስትራችን
ባንዲራ ጨርቅ ነው ብለው ሲናገሩ አጨብጭበው ሲያበቁ ፤ አሁን ደግሞ ስለ ባንዲራ ክብር ለኛ ሊነግሩን መጡ ፤ እናት ለልጇ
አይነት ነገር ……. እነዚህ ወጣቶች ውስጣቸው የሌለውን ማድረግ
አልፈለጉም ፤ እኛም በሀገራችን ላይ 1000 ዓይነት ሀይማኖት መንግስት ህገ መንግስቱን መከታ አድርጎ ቢፈቅድ ‹‹ሃይማኖት ብዙ
ነው ፤ ጥምቀት አንዲት ናት›› አንልም ፤ ብለንም አናምንም አናስተምርም ፤ ህገ መንግስቱ በሰዎች አማካኝነት የተጻፈ ነው ፤ እኛ
ምናምንበት ወንጌል ግን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ነው ፤ ስለዚህ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ ነገሮች ቢኖሩ እንኳን እርሱን
ከመስበክም ሆነ ከማመን ወደ ኋላ አንልም ፤ ደግሜ ለማስረገጥ ‹‹አንድ
ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› የማይዋጥ እውነት ፡፡
ከ20
ዓመት በፊት በራሳችሁ አባል ይችን ቤተክርስትያን ላይ የዶለታችሁላት ነገርን እናውቃለን ፤ ይህች ስለ ሀገር አንድነት
ስለቤተክርስያንና እለ ህዝብ ሰላም ዘወትር የምትጸልይ ቤተክርስትያን ላይ ያሰባችሁላት ሴራ ከኛ ጠፍቶ ሳናውቀው ቀርተንም
አይደለም ፤ በዓመት 365 ቀን የሚጸለየው ጸሎት እናንተንም እንደሚያካት ብታውቁ ኖሮ እንዲህ ባላላችኋት ነበር ፡፡ እኛ
ክርስትያኖች ምናችን ነው ከአክራሪ ሙስሊሞች ጋር ተዛምዶ የነሱ ተቃራኒ ምሳሌ የምንሆነው ? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን
አንደበት የሚናገረው ጭንቅላት ውስጥ ያለውን ነው ፤ እኛን በየትኛው ጎራ እንደመደባችሁን ስለነገሩን ሳናመሰግን አናልፍም ፤ ማንም
ተናገረው ማን ነገሩን የሰማው ጆሮዬ ነገሩ ከአመለካከቴ ጋር ከተጋጨ እቃወማለሁ ፤ ባልቃወም ነገ ጭንቅላቴ እኔን ይቃወመኛል፡፡
ይህ
የአንድ ሰው አስተያየት እንጂ የማንን አለመሆኑን ተረዱልኝ
መቃወም ያለብኝን ያለ መስፈርት እቃወማለሁ
መደገፍ ያለብኝንም እደግፋለሁ ፤
ዛሬ ከማህበሩ ጎን በመሆን እቆማለሁ ፤
ነገ ጥሩ ያልሆነ ነገር ካየሁም ከማህበሩ በተቃራኒ እቆማለሁ ፤
ለእኔ መሰረቴ እውነት ብቻ ናት
Click the following link to see the image of Wahabism in Ethiopia found by Wiki Leaks
Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM"
Click the following link to see the image of Wahabism in Ethiopia found by Wiki Leaks
Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM"
Wawu. Good job AndiAdirigen.
ReplyDeleteI agreee with most of your comments, but I would like to comment on the difference between fundamentalism (akrari) and extremism or terrorism (ashebari). In every religion, there are fundamantalists, those who intereprete their religious text-bible, kuran, and Torah to name a few, very strictly or literally. When fundamentalism involves violence or force then it is a form of extremism or terrorism. I think Mahibere Kidusan would fall under a fundamentalist organization, but it is not an extremist organization. Wuhabism as I understand it is probably both.
DeleteI appreciate the work Mahibere Kidusan has done over the last 20 years in terms of educating the Ethiopian public about their religion, but there is a need for a dialogue in the association to right the wrongs that the association made in recent years and to make sure that it does not convert to an extremist organization.
Let's have an honest dialogue and do some soul searching.
እንዴ እንደ አርጤክስስ በሐማ ላ የታወጀ አዋጅ ሊመጣ ነው እንዴ ይህ ጻድቅ ጌታ ድንቅ ነው የሚሰራው፡፡ ነገር ግን እንደ ሐማ በግንድ ተሰቅሎ ሲኦል የሚገባ እንዲኖር ምኞቴ ባይሆንም ቅን የሆነችው ፍርድ ስትፈጸም ማየት ግን ናፍቆቴ ነው፡፡ የፖለቲካ ዓላማ የሌለው ማኅበር እኮ ሕዝብ በተሳሳተ መረጃ ማነሳሳት የለበትም ሃይማኖተኛ ከሆነ ምክንያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አደረገ; እ2ውነተና ክርስቲን የሰላሙን ጎዳና ይመርጣል፡፡ የክርስትና ጉዞ በጾም በጸሎት እንጂ በውሸትና ሁከት በማስነሳት አደለም፡፡ ማስተዋልን ይስጠን
DeleteE/r abzito yibarkihi
ReplyDeleteበጣም ጠንከር ያለ አስተያየት ነው፡፡ ጉዳዩ (የአቶ መለስ ንግግር) ግን ብዙ ያስብላል፤፤ ...ማህበረ ቅዱሳንና እስልምና አክራሪነት- ዱባና ቅል..ናቸውና ወደህሊናችው ይመለሱ..መለስ ዜናዊ!
ReplyDeleteDinke Dinke Dinke!!!! God bless U!!!
ReplyDeleteGood views
ReplyDeleteማህበረ ቅዱሳንና እስልምና አክራሪነት- ዱባና ቅል..ናቸውና ወደህሊናችው ይመለሱ..መለስ ዜናዊ!
ReplyDeleteመቼስ ቀብሩ ስለደመቀ መንግስተ ሰማያት የሚገባ ፤ ቀብሩ ስላልደመቀ ሲኦል የሚገባ ነፍስ የለም ፤
ReplyDeleteThis comment has been removed by a blog administrator.
ReplyDeleteYou guys are funny, what is wrong with my message. I am just asking, can you please write Meles's speech word by word. That is all. From that we can conclude if it is really what he is saying.
DeleteThis is their mission to demolish the church and make the people unfaithfully.
ReplyDeleteThey have not good deeds except talking, they are done a lot of evil deed in their government.
But, it is time for all orthodox Tewahedo to stand together, our savior the Lord Jesus Christ who sacrificed his life for all of us. we have to keep our faith till the end. We have to pray and struggle what is going on against the church, surely God helps us. He is the winner.
Glory to be God
Glory to be Virgin Marry
Glory to be the Cross
እንዴ "የትግራይ" ክርስቲያኖች የሚለው ትክክል አይደለም ቢያንስ ቢያንስ የመድሀሊአለም ተሳላሚዎች የሰጡትን ምስክርነት አንብበናል፣ ምን ነካህ ዋልድባ ታረሰ ብላ ስላዜመች በፖሊስ ነን ባዮች አይደል እያመናጨቁ የወሰዶት፡፡ ተቃውሞው እና ድጋፉ ብሄርን መሰረት ያደረገ አይደለም ወገኖቸ በማወቅም ባለማወቅም በሌሎች ምክንያቶች ነው ፡፡ ስለዚህ ርህስህን አስተካክል ከ ተስማማህበትም "የአካባቢው ሀ/ስብከት እና አንዳንድ ምዕምናን ለምን የዋልድባን ገዳም ልማት አልተቃወሙም" ማለት ይቻላል፡፡;
ReplyDeleteይህ የግልህ ግንዛቤ ቢሆንም እኔ እንደገባኝ ግን የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ ማለት መጥፎ የሚሰራና የሚያስብ ማለት ነው:: የጥሩ ተቃራኒ መጥፎ; የክፉ ተቃራኒ ደግ; የብልጥ ተቃራኒ ቂል; የቅዱስ ተቃራኒ ርኩስ እንጅ የክፉ ተቃራኒ ሌላ ክፉ; የመጥፎ ተቃራኒ ሌላ መጥፎ; የቅዱስ ተቃራኒ ሌላ ቅዱስ; የሰይጣን ተቃራኒ ሌላ ሰይጣን ሆኖ አያውቅም:: ለሁሉም ልቦና ይስጥ አምላከ አበው::
ReplyDeleteበርግጥም ከዚህ ጽሁፍ የጸሃፊውን ችኩልነትና የጽሁፉን ስሜታዊነት ነው የተረዳሁት፡፡ በዚያ ላይ የሚወላውል አቋም ይታይበታል፡፡ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ከመጻፍ ደጋግሞ ማሰብ የሚሻል ይመስለኛል፤ ልቦና ይስጠን፡፡
Deleteenem endezi new yegebagn.
Deleteአይመስለኝም እናንት እንዲህ ብትሉም የአነጋገር ዘይብያቸው አንደዛ አልነበረም:: ካላዳመጣችሁት እንደገና አዳምጡት:: ሰውዬው ያለው ልክ ማቅ እንደ ተዋሕዶ አክራሪ አድርጎ ነው:: ሲጀመር ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ዝም ያል ሰውዬ አሁን በስልጣኑ ስመጡበት አገር ይያዝ ይላል :: አሳፋሪ ነው!
Deletemeles yalew "yemahibere Kidusan Gilbach" new "tekarani" bedenb enastewl! melesmmahiberun yemitelabet beki mikniyat yinorewal.
Deleteቤ/ክን ለመጠበቅ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ መጠንክር አለብን፡፡ በዚህም እግዚአብሄር ይደሰታል ሰይጠንና መሰሎቹ ይደነግጣሉ!!
Deleteአንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት THIS IS COMMON FOR ALL DONT ADD OTHER
ReplyDeleteWhat do you mean by this ????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????
DeleteHe mean that where in the bible is ONE COUNTRY AND ONE BELIFE? it is written in the bible as .... "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ4:5 .... that is all! any one who believes in this sh/e will got what God promised while the other.......! So, we have to preach the bible not our interests, we have to win with all the evidences we have not with some stretched quotes!
Deleteብዙዎች ይህንን ጥቅስ የራሳቸው ሃይማኖት ብቸኛውና ትክክለኛው የመዳኛ መንገድ እንደሆነ ለማሳመን የሚጠቀሙበት ጥቅስ ነው። ችግሩ ግን ከአማርኛው ትርጉም በስተቀር በመጀመሪያ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት በግሪኩም ይሁን በእንግሊዝኛው ትርጉም በዚህ ጥቅስ ላይ "ሃይማኖት" የሚል ቃል የለም። በአዲስ ኪዳን በአማርኛው "ሃይማኖት" ተብለው የተተረጎሙት ቃላት በአብዛኛው በግሪኩ "እምነት" የሚለው ቃል ነው። በዚህ ክፍልም "ሃይማኖት" ተብሎ በአማርኛው የተተረጎመው ቃል በግሪኩ pistis የሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም እምነት ወይም faith, believe, assurance ማለት እንጂ ሃይማኖት ማለት አይደለም። ስለዚህ ይህ ክፍል የሚያወራው ኦርቶዶክስ ወይም ፕሮቴስታንት ወይም ካቶሊክ ወዘተ ስለሚባሉ ሃይማኖቶች ሳይሆን፤ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ በልባቸው ስለሚያምኑት አንዲት እምነት ነው። ይህም ለሃጢአታችን ደሙን ባፈሰሰው በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ማመን ነው።
Deleteበጄ! "በ'እምነት" እና በ"ሃይማኖት" መካከል ያለዉ ልዩነት ምን ይሆን?
Deleteለእኔ መሰረቴ እውነት ብቻ ናት አልክ ስለ ሌላ ሃይማኖት ምን ያህል ታውካለህ?
ReplyDeleteየማወቅ ግዴታ አለበት ማለት ነዉ እንዴ!? ስለሁሉም ማወቅ ከተቻለ ክፋት የለዉም። እዚህ የቀረበዉ ጥያቄ ዓላማ ግን ግልጽ አ'ይደለም።
DeleteSemugnema, enante sele ewnet yemetezebezebu hulu..........meche newe "protestant" saynore Ye Orthodox Tewahedo yeneberew?? ke Abreham jemero yeneberu "Amagnoche" bemulu "Protestantoch" neberu!! "Hulum emenetachewe Tsedeke hono tekoterelachew" enji beye zafu bementeltel ena beye gudguadu bemeshenkore, teret teret bemawrat tsedeke yelem yalu hulu "protestantoch nachew".
Deleteየቀጣዩን ፅሁፍ ርዕስ በማስተካከልህ ጥሩ ነው፡፡ ወንድሞች በአሁኑ ሰአት የብሄር እና የሀይማኖት ጉዳዮች ላይ በጣም ማስተዋል አለብን፣ ምናልባትም እኛ ለጥሩ ያልነው ለመጥፎ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ እግዚአብሄር ለሁላችንንም ማስተዋሉነ ያድለን፡፡ በተረፈ በአሁኑ ሰአት ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ስለሀገሩ ስለሀይማኖቱ በአንድነት መቆም አለበት፤ በሀይማኖት ብንለያይም አንድም ኢትዮጵያዊ በመሆናችን በዋናነትም ሰው በመሆናችን የአንዱ ሀይማኖት ቁስል እኛንም ይገደናል ልንል ይገባል፡፡ በመጨረሻ አሁንም ብሄር መጥቀሱን ብትተወው ምናለባትም የፅሁፉን ይዘት ባትቀይረውም ርዕሱን ግን ብታሻሽለው ጥሩ ይመስለኛል፣ "ለትግራይ ተወላጆች የቀረበ ጥሪ" የሚለውን ብትተወው እና "ታሪክን የኋሊት" ብቻ ቢባል፡፡ ርዕሱን ብቻ በማየት በብሄር መከፋፈል ጀመሩ የሚል ፕሮፓጋነዳ እንዳይጀመር እባክህ ወገኔ፣ ዋናው ቁም ነገር መለዕክቱ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስራችሁን ይባርከው.
ReplyDeleteWow, nice one! I really appreciate your argument.
ReplyDeleteIt is a very bold fact that government is against the church by any virtue.I have no doubt about it. but here, I have a different view and please be informed that I am not trying to patronize you.
It is really difficult to give a comment based on your report.It would have been nice if you had presented what he said in full not the verse, even as a journalist try to put the full video so that we can make a sound judgement.Hence, I fully agree with the comment above @ Gebre the cape
Anyways, For me what PM Melese said may be something positive and can also be seen in such a way,
1)Wahhabism is a fundamentalist
2)the followers of this ideology are few in the country
3)the followers are also fundamentalists
4)Peoples in this country can follow any ideology to mention like Mahibere Kidusan
5)Mahibere kidusan is an organization devoted to its religion merely for the sake of eternal life.
6)the followers of Mahibere Kidusan are also devoted merely for the sake of their eternal life.
7)MK and its followers are not a problem to this country though they are devoted in Christianity.
8)wahhabism is not devoted for its religion as it has been said rather it is a bad political ideology dangerous to our country and by large to the world.
እኔ እንደገባኝ ግን የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ ማለት የጥሩ ተቃራኒ መጥፎ; የደግ ተቃራኒ ክፉ ; የብልጥ ተቃራኒ ቂል; የቅዱስ ተቃራኒ ርኩስ እንደማለት ነው.... ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተረዱት ግን ማህበረ ቅዱሳን የሀይማኖት አክራሪነት የሚያራምድ ማህበር አድርገው ነው የሚያስቡት..... <> In my opinion ato Meles do not understand the meaning Akrari pls let us tell him
ReplyDeleteምን አይነት ስራ ነው የምትሰሩት? እኔኮ ክርስቲያኖች ትመስሉኝ ነበር:: ለካ ነገሩ ወዲህ ነው:: እኔ የሰጠሁትን አስተያየት ካልፈለጋችሁት መተው እንጂ ለምን እኔ ያላልኩትን ትጨምራላችሁ? ይሄ ነውር ነው:: "ክቡር ጠቅላይ...ከሚለው ጀምሮ ያለው የኔ አይደለም:: እረ ተው እኛ እኮ እውነትን የሚሰራና የሚስብክ ነው ያጣነው ኢዲት ለማድረግማ ETV አለልንኮ:: ተማምረን ልንተባበር እንጂ ያንድ ሰው ሃሳብ እያነበብን ልንጠላላ አይገባም:: ሰውየው ማለት የፈለገውን ሳንረዳ ግምት ከጻፋችሁ የሌሎችንም ግምት ማክበር ይገባል::
DeleteYewahabism opposit MK. I think this makes MK good not evil. Be careful what you post.
ReplyDeleteእኔ በቅንነት ሳስበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት “ዋሃቢያ የእስልምና አክራሪ ይህም ሃይማኖቱን በበጎ አገልግሎት ለማገልገል የሚተጋው የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ የሆነው ክፍል” ለማለት እንጂ “ዋሃቢያ የእስልምና አክራሪ ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ የክርስትና አክራሪ” ለማለት አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ምን ለማለት እንደፈለጉ ነገ ከተግባራቸው የምናየው ይሆናልና እኛ እንደክርስቲያንነታችን በተማርንበትና በተረዳንበት ጸንተን ልንቆም ይገባናል ዋጋችን ከላይ ነውና፡፡
ReplyDeleteነገር ግን በበጎም ይሁን በክፉ መልኩ ማህበሩን ከወሀቢያ ጋር ማመሳሰላቸውን አልደግፍም:: ለምን ? ቢባል እንደእኔ አመለካከት በበጎ ቢሆን መንግስት ከኦርቶዶክስ ጋር ዛሬም አብሮ እንደሚሰራ በማስመሰል ቤተክርስቲናችንን ስለሚያሳጣ በክፉ ጎኑ ማለትም በአክራሪነት ፈርጀውት ከሆነ ደግሞ ከእውነት የራቀ አመለካከት በመሆኑና ማህበሩ ለቤተክርስቲያናችን እስካሁን እያበረከተ ካለው እና ወደፊትም ሊያበረክት በሚችለው አገልግሎት በመጠኑም ቢሆን እንቅፋት ሊፈጥር ስለሚችል ነው፡፡
ለማንኛውም “እህል ከሆነ ይጠፋል ሽል ከሆነ ይገፋል” እንደተባለው ሁሉንም ወደፊት እናየዋለን:: ግን ፈጣሪ መልካሙን ዘመን መልካሙን አመለካከት እንደ ሰሎሞንም “ይህንን ሕዝብ የማስተዳድርበትን ማስተዋልና ጥበብ ስጠኝ” የሚል ጥበበኛ መሪ አያሳጣን፡፡ ቤተክርስቲናቸችንንም ከጥፋት ይጠብቅልን አሜን፡፡
Please think two/three times before you write in this blog, lewere yechekolech afisa lekemech ale yagere sew
Deleteሃቢያ የእስልምና አክራሪ ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ የክርስትና አክራሪ” ለማለት አይመስለኝም . I agree with this idea, don't be hasty to insult people especially the top of the country like this. it is unexpected all in all from the religious person (member of Mahiber kidusan).
Delete"አይመስለኝም..." ባዮች ተሰባስባችሁ ለምን ተናጋሪዉን አትጠይቁም? በመረጃ እንጂ "አይመስለኝም" ብሎ ነገር የለም።
Deleteእባካችሁ ሃይማኖት ከ ፖለቲካ ጋር ኣትቀላቅሉ:: ሃይማኖተኛ ሆናችሁ ሃይማኖታችሁን በ ኣግባቡ ኣትመሰክሩም ፖለቲኬኛ ሆናችሁም ኣቋሟችሁንና ጥንካሬኣችሁን ኣታሳዩም:: ታዲያ እናንተ ምን እንደሆናችሁ ማወቅ እኮ ኣልተቻለም
ReplyDeleteታዲያ አንተ ምንድነህ
Deleteberget maheber kedusan ena eselemena akrarenet endmayegenangu yemitawek new gen behonem aseteyayetu betam tenekere ezeh yemiyaders ayemeselegnem ena wedfet yeleslese hasabe betsaf enji endezeh matenkeru teru ayedelem
ReplyDeleteHello dear sisters and brothers who are working for this blog. I would like to comment on your post regarding what ato meles said in the HR. I have the copy of his voice. Totally we can not conclude that he talked against M.K.
ReplyDeleteI know you have been striving to give us information timely. I appreciate this effort. but some times we have to be systematic and speak only the truth. What you have written about his speech about M.K is I think wrong.
Now what I would like to comment is the following;
1. do not generalize with out tangible evidence
2. when defending for M.K and generally the church be systematic( some times
even the truth will not be breathed out if it is not time)
3.We are not expected totally to ignore about development in Ethiopia (for example the sugar factory and the case of WALDIBA GEDAM). I have not heard some body who want to deal about "limate". we should not be against the limat, but we have to strive for the security of our church. here discussion is vital. do not consider that religious issues will not be changed with discussions but some canonical issues could be solved with discussion. even from the government side there should be willingness to hear the voice of tthe believers. the chirch is the first here in ethiopia. EPRDF members were even in the church during times of difficulties during the durge regime.
4. Even mahibere kidusan is not expected to saysomething now. . Eventhough there exists some truth, it should wait until time allows to say that.
generally please try not to generalize. try to listen what melese said in the HR.
thanks.
may the almighty GOD help the church to solve all such problems!
"በ'እጄ አለ።" የተባለዉን መረጃ ማቅረብ ወይንስ ዘለፋ ይቀድማል?_"generally please try not to generalize." የተባለዉን ይመለከቷል።
Delete"ለእኔ መሰረቴ እውነት ብቻ ናት" ውሸታም!!! ሲሉ ሰምተሃል:: ምናልባት ብሎጉ ያንተ ካልሆነ ከዚህ በሁዋላ እንደማያጽፉህ የታወቀ ነው:: አንባቢ ግን ማነንትህን የሚረዳ ይመስለኛል:: የፉኝት ልጆች:: ጳጳስ ነኝ ብሎ ዲያቢሎስን ከሚያገለግለው አቶ ጳውሎስ በምንም አትለዩም:: ሌቦች:: ማህበሩን ለማጋጨት ነው ይሄ ሁሉ ዝባዝንኬ? አዛኝ ቅቤ አንጉዋች ሁሉ:: ጻድቁ ተክልዬ ይገስጹህ!!!
ReplyDeleteI don't think Mr. Meles acknowledged or like MK, but his saying may have different meaning that you thought. It is true Wahhabism is opposite to Mk and an extreme end of MK. Without going in detail it is a fact that everyone can agree why MK and Wahhabism two extremes. Few examples that clears these arguments, Wahhabism is a fundamentalist but not Mk, Wahhabism believes in force but not mk, Wahhabism never tolerate other religions but mk does. They are two extreme (SEMAYINA MIDER). I think that is why he uses this words and I don't see a problem with this.
ReplyDeletebut why?
ReplyDeleteድሮስ ምን ይጠበቃልና ነው ከሰውየው
ReplyDeletemelese some mk memberes metfo new yalut.mk yechrist goverement yasibal,whabeya yemusilim mengist. degimos some memiber malet min malet new?????
ReplyDeleteፖለቲካ አውነቱን ሐሰት ሐሰቱን እውነት በሎ ይሚታመንበት እንደሆነ ዛሬ በደንብ ገባኝ ከሰውየው ንግግር
ReplyDeletewhy MK guys shoking??.Pm meles says MK is good.but whabiyism is wrog?He isnot saied like that.anifra eiwnetin bemenager yememetabinin betsega mekebel yishalal!!!!
ReplyDeleteI agreee with most of your comments, but I would like to comment on the difference between fundamentalism (akrari) and extremism or terrorism (ashebari). In every religion, there are fundamantalists, those who intereprete their religious text-bible, kuran, and Torah to name a few, very strictly or literally. When fundamentalism involves violence or force then it is a form of extremism or terrorism. I think Mahibere Kidusan would fall under a fundamentalist organization, but it is not an extremist organization. Wuhabism as I understand it is probably both.
ReplyDeleteI appreciate the work Mahibere Kidusan has done over the last 20 years in terms of educating the Ethiopian public about their religion, but there is a need for a dialogue in the association to right the wrongs that the association made in recent years and to make sure that it does not convert to an extremist organization.
Let's have an honest dialogue and do some soul searching.
I like your explanation on fundamentalism and extremist.Thank you but, can you mention some of the wrong that MK made(may convert to extremist organization).others wise your suspect couldn't have a ground.
DeleteBe honest and tell us to right the association. do you want to say us MK can say "one country one religion" as prime minister said us? btw I didn't not read such kind of verse from any.It was "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት" verse taken from bible written and seen on tshirts of EOTC youths for TIMKET holiday.
As I have explained it earlier, Extemists use some form of violence to back up their fundamental beleifs. Most of what MK has done would not fall under any form of extremism, but there have been several preachers who alleged that they have been beaten and wrongly arrested by violence instigated by MK members. There is also a lot of name calling, especially on moderate Christians and song writers that may not prescribe to the very fundamantal teachings of MK. Hope some of this would give you an idea why we need dialogue in MK.
DeleteI also understood the phrase as one of our brother put it " Whahibism is proxy tool of international islamic fundamentalism where as mahiber kidusan is local and self organized; Wahibism targets political power to establish islamic Ethiopia where as Mahibere kidusan is purely religious association established to help the church "..... and I do not think that the prime minster wanted to say what you put. No unless he is crazy
ReplyDeletehulunim asteyayet sechiwochin hasab anebebku gin kandu andu enkuan yemishal tefa abetu hulun temelket
ReplyDeleteበቅድሚያ ምስጋና: በመቀጠል የራሴን ስሜት: ጠቅለል ባለ አነጋገር ይህ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ ጸረ-ኢትዮጵያዊ ነው:: ከነ ዮዲት ጉዲት እና መሀመድ ግራኝ በበለጠ የኢትዮጵያዊ ባህል እና እምነት እያጠፋ ያለ ሰው ነው:: ይህ ሰው የድሮ ጀግኖች አባቶቻችን በጥምረት የሰሩት ስራ የሚያመው: የሚያገሸግሸው: እንቅልፍ የማያስተኛው ሰው ነው:: እርግጠኛነኝ ነገ 'ኢትዮጵያ' የሚለው ስም ይቀየር ይላል::እግዚሐብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!!
ReplyDeleteWhat i would like to say is stop arguing about what P.M Meles said, let us united beside our church. We all know this government always come up with something that make us diveded in any issues. Let us forget everything and save our church leting them know we no longer going to divided by his provocative words or warning. This isn't politicals this is religion. We always stood for peace and will do again stand for peace forever. But not forget that we will give our life on behalf of our belief. If accusition of MK comes true then he is making big mistakes. We will let him know that he is not going war with a some interest groups, they are devoted their life, their work, their knowledge, for this religion, it could be harmful in both side before it get better. I will suggest P.M Meles not to rush to use childish word.
ReplyDeleteyou said "ወንጌሉ ሲጻፍ ሙስሊሞች ፤ ፕሮቴስታንቶች ፤ ካቶሊኮች ፤ አድቬንቲስቶች የሉም የነበርነው እኛ ብቻ ነን"
ReplyDeletewho are you?
I think you know that there was on orthodx as well ወንጌሉ ሲጻፍ.
so you should write ወንጌሉ ሲጻፍ ሙስሊሞች ፤ ፕሮቴስታንቶች ፤ ካቶሊኮች ፤ አድቬንቲስቶች ኦርቶዶክስች የሉም. There were TURE CHRISTIANS. They never impose their religion on others. They preached by love and sacrifice. The never have moto like "ONE COUNTRY ONE RELIGION". By the way ONE COUNTRY ONE RELIGION is totally different from አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት. I believe you have an understanding problem. I did not hear the PM saying አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት. If you do not know the history of the church LEARN. ወንጌል will be preached by love, prayer and by being an example not by insulting others. Read the ACTS.
you said "እኛ ምናምንበት ወንጌል ግን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ነው ፤ ስለዚህ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ ነገሮች ቢኖሩ እንኳን እርሱን ከመስበክም ሆነ ከማመን ወደ ኋላ አንልም". True christian will obey ወንጌል LAW and earthly government LAWS as long as the government is not telling him to stop worshiping his God. Read Rome 13
''ይህ የአንድ ሰው አስተያየት እንጂ የማንን አለመሆኑን ተረዱልኝ''
ReplyDelete''እናንተ ፖለቲካችሁ ላይ ብትበረቱ እኛ ደግሞ እምነታችን ላይ እንበረታለን ፤ ከአባቶቻችን የተቀበልነውን እምነት እና ስርዓት ለልጆቻችንና ለልጆቻችሁ ለማውረስ እንሰራለን ፤ ወሀቢዝም ምን ማለት እንደሆነ ካላወቃችሁት እኛ ልናስረዳችሁ ፍቃደኞች ነን ፤ እናንተ ጋር ካለው አመለካከት እኛ ጋር ያለው መረጃ የሚሻል ሊሆንም ይችላል''
1 gize ena lela gize egna tlale ante handm sostm neh?..........lol
enante mahbere kidusaninm eyadignm tswachu simola medanyalem yanesachual batekrstyan gin lezelalem tnoralech.
አቶ መለስ እስከ ዛሬ እግዚአብሔር ታግሶህ ነበር አሁን ግን ልጓም የሌለህ አፍህንና የውስጥ ሸረኝነትህ እግዚአብሔር በቅርብ ቀን ያጋልጥህና እራቁትህን ትቆማለህ ከነ ሳዳም ሁሴን ከነ ሆስኒ ሙባረክና መሐመድ ጋዳፊ ተማር የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሰዎች ወይም ለገንዘብ ያደሩ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ለመናገር የሚፈሩ ጳጳሳት አይደሉም የሚመሯት ልዑል እግዚአብሔር ነው ተጠንቀቅ በጣም እየተጋፋሃት ነውና እሱ ከተቀመጥክበት ወንበር ያይ ይገለብጥሐል በአጭር ጊዜ ውስጥ አንተና ግብረ አበሮችህ ትጠፋላችሁ ይልቁንም ንስሀ ግባና ዳን
ReplyDeleteበርግጥም ከዚህ ጽሁፍ የጸሃፊውን ችኩልነትና የጽሁፉን ስሜታዊነት ነው የተረዳሁት፡፡ በዚያ ላይ የሚወላውል አቋም ይታይበታል፡፡ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ከመጻፍ ደጋግሞ ማሰብ የሚሻል ይመስለኛል፤ ልቦና ይስጠን፡፡
ReplyDeleteI am very happy with the d/t comments I read but still I have doubt that the prime minister has positive attitude to MK. My reason is one he don't want to leave his position and for this his mechanism is by dividing the people but Mk strongly works for equality, unity, familiness of all ethnic groups by God, which is really reflected by all mk members from different ethnic groups. Second those who feeds information may gave him wrong information for their own religious consumption (I know some one at lower position who were misleading leaders b/c he is against mk due to his act on our church)and third as we all know he ignores orthodox Christians issue b/c I think he feel like we are powerless since we don't have support outside like the Muslims (we know how they respond even for wrong actions of the Muslims). So I think Mr Melese couldn't speak positively to MK. So the writer's idea is correct though somewhat strong. Anyways lets discuss and try our best to protect our church but I believe the prime minister and his govt is purposely attaching the church by putting his pupate Paulos.
ReplyDeleteGod bless you.
I agree.
Deleteግን አቡነ ጳውሎስ ምን ብለው ይሆን ?
ReplyDeleteጠቅላይ ሚኒስተር ሆይ፣ ምንም ቁም ነገር አጣሁብዎት፡፡ ደግሞ የመንደር ወሬ ይዘው ፓርላማ ገቡ?
ReplyDeleteድሮስ ምን ይጠበቃልና ነው ከሰውየው
ReplyDeleteyou said "ወንጌሉ ሲጻፍ ሙስሊሞች ፤ ፕሮቴስታንቶች ፤ ካቶሊኮች ፤ አድቬንቲስቶች የሉም የነበርነው እኛ ብቻ ነን የሚባል ነገር ስህተት ነው፡፡
ReplyDeleteሙስሊም ማለት ለፈጣሪ እጅ መስጠት ማለት ነው፡፡ሁሉም ነብያት ሙስሊም ነበሩ፡፡ስለ እስላም መረጃ ስንፈልግ ቀርአን ምን ይላል ማለት አለብን፡፡ማህበረ ቅዱሳን መረጃ ልሆነን ኣይገባም፡፡እኔ ሙስሊም friend አለኝ ፡፡የማህበረ ቅዱሳን news ስህተት ነው፡፡we must hear about islam,wahabism and so on from the original source(from muslim and ቀርአን ).muslim and christian are brothers,በማህበረ ቅዱሳን news each other እየፈራን መኖር የለብንም፡፡islam is peace.
አይ መሰረት ክቡር መለስ ዜናዊ ንግግር ሲያደርጉ እሳቸውና የሙስሊሙ መሪ ለሽ ያለ እንቅልፍ ላይ ነበሩ፡፡
ReplyDeleteእኔ በቅንነት ሳስበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት “ዋሃቢያ የእስልምና አክራሪ ይህም ሃይማኖቱን በበጎ አገልግሎት ለማገልገል የሚተጋው የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ የሆነው ክፍል” ለማለት እንጂ “ዋሃቢያ የእስልምና አክራሪ ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ የክርስትና አክራሪ” ለማለት አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ምን ለማለት እንደፈለጉ ነገ ከተግባራቸው የምናየው ይሆናልና እኛ እንደክርስቲያንነታችን በተማርንበትና በተረዳንበት ጸንተን ልንቆም ይገባናል ዋጋችን ከላይ ነውና፡፡
ReplyDeleteየጠ/ሚ አባባል ትርጉሙ አንድና አንድ ነው። እሱም እርሳቸው ብቻ ነው የሚያውቁት ሌላው ሰው ግን በመሰለው አቅጣጫ ይተረጉመዋል። ይህ ደግሞ የታወቀ ነው ፤ SUBJECTIVE አተረጓጎም ነውና። ሁሉም ማወቅ ያለበት ሀቅ ግን ዋሀብያ አሁንም ለቀጣይም የሀይማኖትና የሀገር አጥፊና አስጊ ነው ማኅበረ ቅዱሳን ግን የዚህ ተቃራኒ(አለኝታና ተስፋ የሚጣልበት)
አንድ ሀይማኖት አንድ ሀገር
ReplyDeleteእንዲህ ማለቴ የሌላ እምነት ተከታይ የሆነ በአምሳለ ስላሴ የተፈጠረ ወንድም /እህት/ የለም ማለቴ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ ነገር ግ እኔ የማምነው ግን በአንድ ሀይማኖት ብቻ መሆኑን ያመላክታል
የኢሕአዲግ ጠቅላይ ሚኒስትር/የኢትዮጵያ አላልኩም ለእኔ አይደሉምና /ለእርሳቸውና ለደጋፊዎቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ምክንያቱም ለእርሳቸው ኢትዮጵያዊነት ኢሕአድግ የሆነ ወይም ኢሕአድግን የደገፈ ብቻ ነውና።
በዚህ አጋጣሚ ትክክለኛ ልማትን አልቃወምም ሀገሬ አሁን ባላት የለውጥ ጉዞ ከሚኮሩት አንዱነኝ ለውጥን/ልማትን/ የሚሰራ ህዝብ ነው ብዬ አምናለሁ ዛሬም ታድያ ኢሕአዲግ በዋልድባ የሚሰራውን ልማት መሰል ጥፋት ያልደገፈ ወይም ለመቃወም የሞከረ ሁሌም የሚለጠፍ ነገር አያጣምና በልማት ስም ግን ሀይማኖትን ከፖለቲካ ጋር ማነካካት ተገቢ አይደለም ።በሀይማኖት ግን አልደራደርም አቶ መለስ ወራጅ አለ መልማት የሚጋባው ቦታ ልማቱ ይቀጥል ሀይማኖተኛን በሚያስከፋ ቦታ ላይ ልማቱ ይቁም።
ውድ አንባቢያን ሆይ ( አብዛኞቻችሁ)
ReplyDeleteጠቅላይ ሚኒስቲሩ እኮ ያሉት ግልጽ ነው። ዋሃቢይ የእስልምና ቁጥር ብዙ ነው ይላላ፡ ማቅ የክርስቲያኖች ቁጥር ብዙ ነው ይላል። ሰውየው በቅርብ ያብዳል፤ ልጆቹም ይንከራተታሉ፤ ስማቸውን ይቅይራሉ። ሀጋራቺንም ለሁሉም እኩል ሆና በሰላም ትኖራለች። ሁላችንም እንጸልይ፤ ይህን መንግስት በሚያሸንፍ መልኩ እንጠናከር...
ይህማ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ነው!!!
ReplyDeleteONE COUNTRY AND ONE BELIFE???? it is written in the bible as .... "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ4:5 .... that is all! any one who believes in this sh/e will got what God promised while the other.......! So, we have to preach the bible not our interests, we have to win with all the evidences we have not with some stretched quotes! It is not bad to have different interests and ideologies, but we shouldn't be too biased and exaggerate thing to our narrow interests, we are after all judged by the lord.
ReplyDeleteYou are quite right about the verse, however it doesn´t say one country. it is told to the whole world. Hence, we respect others ideology and philosophy in parallel to telling the absolute truths all written in the Holy Bible.I think that is Christianity, we tell the truth to the whole world but we don´t impose or pose any trouble to anyone.
DeleteIs that my ear or I heard PM saying "some (Andand) members of MK" ? I think he didn't said "MK, Most MK members or the majority" So dear writer would you argue defending all members? Do you have intelligence service like him or do you have examined all the minds of the members that they have no such idea?
ReplyDeleteI think in all religions there are people who would like to take advantage of the innocent followers who honestly seek the Kingdom of God. Religious groups or churches and mosques need to be shelters for all who would like spiritual freedom. On the contrary, members of any religion could form or join parties and promote philosophies they think will help the people to lead a better life in this world.
Please brothers and sisters let's not mix religion with politics.
ውድ ወንድሞቼ
ReplyDeleteእኔ እንደተረዳሁት ውዩቢዝሞች ሀይማኖታቸውን በሀይል ለማስፋፋት ሲሞክሩ በተቃራኒው ግን ማህበራችን(አባል ስለሆንኩ ነው)ማህበረ ቅዱሳን በሰላማዊ መንገድ ሀይማኖቱን ያስተምራል ለማለት ይመስለመኛል.እግዚአብሄር ህማኖታችንን ይጠብቅ ሀገራችንን ይባርክ. እግዚአብሄር ይስጥልኝ.
ውድ ወንድሞቼ
ReplyDeleteእኔ እንደተረዳሁት ውዩቢዝሞች ሀይማኖታቸውን በሀይል ለማስፋፋት ሲሞክሩ በተቃራኒው ግን ማህበራችን(አባል ስለሆንኩ ነው)ማህበረ ቅዱሳን በሰላማዊ መንገድ ሀይማኖቱን ያስተምራል ለማለት ይመስለመኛል.እግዚአብሄር ህማኖታችንን ይጠብቅ ሀገራችንን ይባርክ. እግዚአብሄር ይስጥልኝ.
Zim bel Asemesay neh/sh
DeleteME] OO ˜E O EkÉ]} px œZ]zÁ MGO QZ~ ˜ÁªkO šO MÖpk ¾ErO because he is politician. Pleas stand together against our religious leader “aba “ Paulos. That is the solution.
ReplyDeleteMGO ˜q} p#U ¾NO Mݦ„ qGD pZ
የጹሁፉ አባባል አልገባኝም ጠቅላይ ሚኒብቴሩ ያሉትን ባልሰማም ከጽሁፉ እንደተረዳሁት የአክራሪ ሙስሊሞች ተቃራኒ ማህበረ ቅዱሳን እንዳሉ አድርገህ ነው ያቀረብከው፡፡ እናም እንደዛ ያሉ ከሆነ እኮ ተመሳሳይ ቢሉ ኖሮ ነው እንጅ እንደ አክራሪ መስሊም ተቆጠርን የሚባለው ተቃራኒ ካሉ ማህበሩን እንደአክራሪ የቆጠሩት አልመሰለኝም፡፡ ስለዚህ የኔ የመረዳት ችግር ከሆነ ግን ፀሐፊው ብታብራራልኝ፡፡
ReplyDeleteእኔም!ዛሬ ከማህበሩ ጎን በመሆን እቆማለሁ!
ReplyDeletewhat is going on
ReplyDeleteBUT this blog is twisted and i think it is too much stretched to include some personal interest or believe. I mean WHAT WOULD YOU ANSWER, ASSUMING YOU FACE THIS QUESTION, can you just listen and judge, even to me the guy talks in favor of Orthodox??? God bless our Orthodox and the Lord only judge!
ReplyDeletehttp://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=FCwRyVCanFE#!
they do like Fashist Italia have done in Ethiopia, YEwunet Amlak yitebiken
ReplyDeletethank you the bloger
'አወቀች ቢሏት መጽሀፍ አጠበች'ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ መለስ ንግግር ይችላል ቢሉት መጽሐፍ ቅዱስ እኔ ልተርጉመው አለ። ሀ..ሀ..ሀ
ReplyDeleteይህስ ለፈላስፎች፤ለሳይንቲስቶች፤እናም ለሌሎችም አልበጀም!!! ያኔ የለም ያሉት ዛሬ እራሳቸው የሉም!!እናም አቶ መለስ ሲያረጁ ወደ ህጻንነት እንዳይመለሱ እፈራለሁ፡ ሕጻን ሁሉንም አውቃለሁ ይላልና፡፡ ይልቅስ "አለማወቄን እርዳው" ብለው እንዲጸልዩ እመክሮታለሁ.በድጋሚ
‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤››
teklay ministr bemayashama huneta yemuslim akrarinetin tenageruna selefiwoch yemahbere kidusan gilibach it is clear.bemuslimu selefi yemibal akrari endale hulu becrstiyanum mahbere k8idusan yemibal akrari ale malet new!
ReplyDeleteenam kehuletum group andandoch akahedacew tikikil aydelem lemalet new!
ende ene eyita gin mahbere kidusanim yebetecrstiyann kenona letwuld mastelalef yifelgal enj 1 haymanot 1 hizb yilal biye alaminm
muslimochim emnetacewn benesa metegber yifelgalu enj 40 miliyon shrstiyan balebet hager sheria yikum mengist yemil ye ebid tiyaqe ayaqerbum.
mengist siltanun lemarazem sil ega mefajet alebin?aymeslegim!! enikebaber muslimum chrstiyanum beselam hageru ena emntun yaskebir mengistin begara enkawem.
ye enante yehizbe chrstiyan meri man endehonu ena yepoletika alamacew min endehone tenkiken enawkalen ye ega mejlis alamaw min endehone enawqalen.hulum amagun hizb afinew yemelesin siltan lemetebek ashangulit meriwoc nacew silezih lib enibel
amesegnalehu
AndiAdirigen, thanks at least for opening this dialog.
ReplyDeleteI could see the article as a non-political, full-of-emotion, 'erroro'-type commentary.
I agree, that most of the MK members should educate themselves the theo-political dynamics of Ethiopia. There is no good culture of dialog in MK - I agree. Nobody with a different opinion is allowed to discuss in MK. I know most MK members(engaged ones), are at least kind and positive. But there are a group of militant non-conversant Christians who are not fully involved, but simply want to be called as "members of the prestigious MK". As far as MK is not refining its members, the image of MK will always be blackened by them.
Second, none of MK members are aware that the EPRDF manifesto is copied from Soviet Russia Communism, which has a long-term plan of destabilizing the Church. It is similar to the Derg era, although now its implementation is covertly managed by the ruling elites. Simply put, EPRDF wants to make deactivate The Orthodox Church from public engagement. First, EOTC is the only unifying entity in Ethiopia with diverse social, theological and historical lures, against the divide and rule policy of EPRDF. Secondly, none of the dictators are okay with Christianity at all. Even Islam is preferable for them[this is literally spoken by the Fascist dictator Mossoloni]. You can see the distribution of democratic nations - there is no democracy that could come out of the Middle East, which is predominantly Islam. Even semi-democratic nations like Libanon, Egypt, Turkey become so because of the high degree of influence by the Christian culture prevalent in the Western Nations.
China, which is a best model of Meles's totalitarian system, is fighting to reject Christianity. Because with Christianity, then follows human rights movements, which is against the Chinese government's political dogma.
Please leave out of emotion, rethink and devise tactics to handle the current political drama waged against our Church.
ጽሁፉን ከአንበብኩ በኋላ ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሰምቼ ሁለት የግምት ነጥቦቼን ለማስቀመጥ ወሰንኩ ፡፡ ይኸችን ወቅት ለማለፍ ማኀበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ተግቶ መሥራት እንደሚገባው ለማሳሰብ እፈልጋለሁ ፡፡
ReplyDelete1. ጥንቃቄ ማድረግ የምለው ፡- በዚህ ወቀሳ ምክንያት ማንኛውንም እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የሁሉም ትኩረት ወደዚሁ ማኀበር ላይ ስለሚያነጣጥር ነው ፡፡ በአጋጣሚ አንድ ስህተት እንኳን ቢፈጠም የማኀበሩ ህልውና ስለሚያበቃ ፣ በየሥርቻው ያደፈጡት ሠርጎ ገቦች ወደ ዓውደ ምህረት ያለተከላካይ በመውጣት የሚፈልጉትን መፈጸም ይችላሉ ፡፡
2. ተግቶ መሥራት አለበት የምለውም፡- ማኀበሩ እንዲወቀስ በማኀበሩ አባል ስም ወንጀል እንዳይሠሩና ከላይ የተጠቀሰው ፍርሃትና ችግር እንዳይከሰት መከላከል ስለሚያስፈልግ ነው ፡፡ ምናልባት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር መነሻ የሆነውን “አንድ ሃይማኖት አንድ አገር” የሚለውን መፈክር ፣ ከመንግሥት ለማጋጨት ሲሉ በማኀበሩ ስም ይዘውም ታይተው ይሆናልና ፣ ለወደፊቱ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ክትትል ይደረግ ፡፡ በቤተ ክርስቲያን አልሆን ሲላቸው በመንግሥት ጀርባ ታዝለው ለመግባት መሞከራቸው ስለሚሆን ሰፋ ያለ ትኩረት ይደረግ ፡፡
ክርስትናችን አንድ አገር አንድ ሃይማኖት ብላ አላስተማረችም ፣ አታስተምርምም ፡፡ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት የሚለው የወንጌል ቃል ስለሆነ እስከ ዓለም ፍጻሜ ከመባል የሚገታው ኃይል አይኖርም ፡፡
yih eko mastenkekiya new algebachihum ende enante erfu waldiba zikuala minamin atibelu egna yefeleginewun neger enadirig new yaleziya mk key mesimer alfual malet eko new-yih gize alfo enayew yihone
ReplyDeleteየቀጣዩን ፅሁፍ ርዕስ በማስተካከልህ ጥሩ ነው፡፡ ወንድሞች በአሁኑ ሰአት የብሄር እና የሀይማኖት ጉዳዮች ላይ በጣም ማስተዋል አለብን፣ ምናልባትም እኛ ለጥሩ ያልነው ለመጥፎ ሊጠቀሙበት ስለሚችሉ እግዚአብሄር ለሁላችንንም ማስተዋሉነ ያድለን፡፡ በተረፈ በአሁኑ ሰአት ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ስለሀገሩ ስለሀይማኖቱ በአንድነት መቆም አለበት፤ በሀይማኖት ብንለያይም አንድም ኢትዮጵያዊ በመሆናችን በዋናነትም ሰው በመሆናችን የአንዱ ሀይማኖት ቁስል እኛንም ይገደናል ልንል ይገባል፡፡ለተሃድሶ ሆነ ለሙስሊሞች ባንሳደብ መልካም ነው፡፡ዋሃቢያኣክራሪ እያለ መንግስት እርስ ራሳችን እንድንባላ እያደረገ ያለው
ReplyDeleteበ ቀላሉ እየተሸወደ ያለው ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡
Please please yehye sehufe btame mnefsawi kmehone yeleke semytawina bechekola yanedesewe amelekaketene yeyaze newe .Ebakachu lemetesefubetena sewoch lemiyanebute negere tetenkeku .Mkeneyatume bytekeresetiyanachen mene gizyeme bihone yemetesebkewe selamen newena .Dont be Emotional !1!!1111!!!
ReplyDeleteGreat work! This is the kind of info that should be shared across the
ReplyDeletenet. Disgrace on the search engines for no longer positioning this
publish upper! Come on over and visit my website . Thanks =)
Here is my web-site - GFI Norte
This is really interesting, You're a very skilled blogger. I've joined your feed and look forward to
ReplyDeleteseeking more of your magnificent post. Also, I've shared your site in my social networks!
Also visit my webpage ... how to get rid of pimples