(አንድ አድርገን መጋቢት 28 2004 ዓ.ም) ፡- በባቦጋያ
መድሀኒአለም የቦታ ጉዳይ ላይ ውዝግቡ እንደቀጠለ ነው ፤ ይህን ጉዳይ ዳር ለማድረስ ከቤተክህነት የተላከው አቶ ጌታቸው ዶኒም የመሰሪ
ስራውን እያከናወነ ይገኛል ፤ ካህናቱ እና ህዝቡም ከአቋማቸው ሊንቀሳቀሱላቸው አልቻሉም ፤ የአቶ ጌታቸው ዶኒ ሀሳብ ዛሬ መልኩን
ቀይሯል ባለፈው እሁድ በአውደምህረት ላይ ያነበበውን ደብዳቤ የተቃወሙትን ካህናት ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት በደብረዘይት
መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ሁሉንም በግቢ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት
አሳግዷቸው ከቤተክህነት የወረደውን መመሪያ በግድ እንዲቀበሉት እያስገደዷቸው ይገኛሉ ቤተክርስትያኒቱን በታጠቀ ፖሊስ አስከብበው
ማንም እንዳይገባ ከልክለው ካህናቶቹን እያስጨነቋቸው ይገኛሉ ፤ እናንተ ናችሁ ህዝቡን የምታነሳሱት ፤ ህዝቡ በቦታው ላይ ምንም አላለም ፤ ህዝቡ ምንም ተቃውሞ የለውም በማለት የቦታው
ሽያጭን ተቀበሉ እያሏቸው ይገኛሉ ፤ ዛሬ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ቤተክርስያን መግባትም በፖሊሶች አይፈቀድም፡፡
ከቦታው ከታማኝ ምንጭ እንደሰማነው ዲያቆናቱንና ካህናቱን በአሁኑ ሰዓት ሰብስበዋቸው ከሲኖዶስ መጣ የተባለውን ደብዳቤ
መሰረት በማድረግ ተስማምተናል ብላችሁ ፈርሙ ብለው የመንግስት ባለስልጣናት
፤ ከፖሊስ የተወከሉ ሰዎች አቶ ጌታቸው ዶኒን ጨምሮ እየወተወቷቸው ይገኛሉ ፤ ቤተክርስትያኒቱን የሚያገለግሉትን ካህናትን የንስሀ
ልጆቻቸውን ቤት ለቤት እየሄዱ እንዲያሳምኑ እና በቦታው ላይ ጥያቄ እንዳይጠይቁ የማድረግ ስራ እንዲሰሩ እያስገደዷቸው ይገኛሉ ፤
ከተሰበሰቡት ካህናት ውስጥ ይህን ለማድረግ ፍቃደኛ አይደለንም ያሉት ፤ ሀሳባቸውንም ያልተቀበሉት ሁለት ካህናት ስብሰባውን ትተው
ወጥተዋል ፡፡
እረ ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ ? ፍርድ ቤቱ መብታችሁ ነው ፍርድቤት ጉዳዩን በተወካዮቻሁ አማካኝነት ይዛችሁ
መምጣት ትችላላችሁ ሲል ከቤተክህነቱ በኩል እየተሰራ ያለው ነገር በጣም አሳፋሪ እየሆነ እየመጣ ነው ፤ ይህ ሰው ለቀናት በደብረዘይት
ከተማ ሲሸርብ የነበረውን ነገር ጫፍ ለማድረስ በመንገድ ላይ ይገኛል ፤ በተለያየ ቦታ ላይ የሚገኙ ሰዎች ስለ ቦታው በቂ መረጃ
የሌላቸው መሆኑ ደግሞ ሌላ ፈተና ነው ፤ ሁሉም ይህን ጉዳይ በአግባቡ ማወቅ ቢችል መፍትሄ ለመሻት ህገወጦችን ለመቃወም ትንሽ መንገድ
ይከፍት ነበር ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው ነገር በእነ አቶ ጌታቸው ዶኒ አማካኝነት ከቤተክህነቱ በተወከሉ ሰዎች ፤ ከሪዞርት ባለቤቱ
ጋር በመነጋገር የቤተክርስያኒቱን ሳይሆን የግለሰቦችን መብት ማስከበር ላይ እየሰሩ መገኝታቸው ነው ፤ ቤተክርስትያኒቱ ህጋዊ የሆነ
ካርታ እያላት በእጅ አዙር በተደረገ ሴራ 10 ሺህ ካሬ የጥምቀት ቦታውን ልታጣው ጫፍ ደርሳለች ፤ እኛስ ምን ማድረግ አለብን ? አባቶችስ ይህን
ጉዳይ ሳያውቁት ቀርተው ነው ወይስ ሰምተው እንዳልሰሙ አልፈው ? ለእኛ ግልጽ አይደለም ፤ ጳጳሳት ተብለው እስከተሾሙ ድረስ ጉዳዩን በአግባቡ ተመልክተው የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ፤ የእነሱ በነገሮች
ላይ የሚያሳዩት ዝምታ ምዕመኑን ግራ እያጋባው ይገኛል ፤ ይህው የዋልድባ ጉዳይ ላይ ቃል እንኳን መናገር አልቻሉም ፤ አባ ሰረቀን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ለመሾም አስቸኳይ ስብሰባ የጠሩት ፓትርያርኩ በዋልድባ ጉዳይ ላይ ግን ዝም ማለታቸው ሰልፋቸው
ከወዴት እንደሆነ እንድናውቅ አድርጎናል ፤ ይህ የደብረዘይቱ ባቦጋያ አካባቢ የሚገኝው የመድሀኒአለም መሬት ውዝግብ ሲኖዶሱ ሊያውቀው ይገባል ፤ የሚደረገውን ስራም
ሊከታተል ይገባዋል ፤ ታዲያ ይህን የመሰለ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ በጊዜው አውቀው መፍትሄ ካልሰጡ ጠባቂነታቸው ጥያቄ ውስጥ የሚገባ
ይመስለናል ፤ እኛ የማይመለከተንን ጥያቄ እያነሳን አይደለም ፤ ነገር ግን ጉዳዩን አስጠንተው ተገቢውን መልስ መስጠት ባይችሉ እንኳን
ምዕመኑ የሚያደርገውን የቤተክርስትያን ጠበቃነት እንቅፋት ሊሆኑበት አይገባም የሚል እምነት አለን ፡፡ ከሰው መልስ ባናገኝ መድሀኒዓለም
መፍትሄ እንዳለሁ አንጠራጠርም፡፡
ባሳለፍነው እሁድ አቶ ጌታቸው ዶኒ ይዞት የመጣውን ስትራቴጂ የሚገርም ነበር ፤ ቀድሞ ከፖሊሶች ጋር በመነጋገር ፖሊሶች
በቦታው ላይ እንዲገኙ አስደርጎ ድንገት ከሲኖዶስ መጣ የተባለውን ጽሁፍ በሚያነብበት ጊዜ ችግር ቢፈጠር ፖሊሶቹ ችግር ፈጣሪዎችን
አፋፍሰው እስር ቤት ለማስገባት የተዘጋጁ ነበሩ ፤ ከዚህ ቀደም ዱላ ነበር የሚይዙት የባለፈው እሁድ ግን መሳሪያ የታጠቁት ነበሩ ፤ ይህ አካሄድ ጥቅምት 11 2004 ዓ.ም ተሀድሶያውያንን ለመቃወም በወጡት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ተሀድሶያውያን መካከል
በተደረገ ጸብ 11 ሰዎች በጊዜው መታሰራቸውን እናስታውሳለን ፤ ምዕመኑ ስለቤተክርስትያን ብሎ የሚሰማውን ስሜት በውስጥ መቆጣጠር
ሲያቅተው ለቤተክርስትያን ካለው ቅንአት የተነሳ ምን እንደሚያደርግ ቀድሞ ገብቷቸዋል ፤ ይህንም ነገር ልክ እንደ Advantage ተጠቅመው ህጋዊያን እኛ ነን ጉዳት የደረሰብን
እኛ ነን ፤ ለማለት እና ሰዎችን ለማሳሰር ፍርድ ቤትም ለማቅረብ የያዙት የስትራቴጂ መንገዳቸው ነው ፤ አቶ ጌታቸውም ይህችን ቴክኒክ ተጠቅሟል ፤ በቅርቡ በቦረና እና ጉጂ ዞን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያን የተፈጠረውን ነገር ጥሩ ማሳያ ይሆናል ፤ 40 ክርስትያኖች ስለ ህገ ወጥ ሰዎች ፤ ቤተክርስትያን የማይወክሉ ሰዎች ላይ ባደረጉት
ተቃውሞ መታሰራቸውን ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ ግማሹ በነፃ ሲለቀቁ ቀሪዎቹ ደግሞ በፍርድ ሂደት ላይ ናቸው ፡፡ ይህን መሰረት
አድርገን እውነት ስለተናገርን የምንታሰርበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ነገሮችን ሁሉ በብልጠት እና በብልሀት ማድረግ ተገቢ ነው እንላለን
፤ የጠላትን አሰላለፍ ቀድሞ መረዳት እኩይ ተግባራቸውን ለመዋጋት መልካም ነው፡፡የማቴዎስ ወንጌል 10 ፤16 ላይ እንዲህ ይላ
‹‹እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።››
የስብሰባውን
ጫፍ ሲጠናቀቅ እንነግሮታለን ፤፤
እግዚአብሔር
አሁንም ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን
amen
ReplyDeleteGod will help us.
ReplyDeleteere gude fella, what we shall to do? the main tharget of bete kehenet and our patriarik is to distroyed our church as well as our belief.so we must stand together to fight them by mehilla. by the way always i remember the word of kid chirkos when they were in examination.he said that " geta hoy kerinchafun allemilemeh gendun taderkaleh woy" i think it is a good saying for us as well as for our leaders. God bless Ethiopia.AMEN AMEN AMEN
ReplyDeleteእነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ
ReplyDeletewhat shall we do? Now days, a number of unwanted weeds have planted in Our church, who do not let them allow to grow?
we ourselves have to be together as part of a solution, to eradicate all of them in it. God is with us, he gives us a strength if you are in the difficulties
please pray to God, he helps us.
Glory to be our God
Glory to be the Virgin Mary
Glory to be the Cross
“ስጋን የሚገድሉትን አትፍሩ ነፍስን የሚገላትን ፍሩ”
ReplyDeleteበቃ እኔ መሮኛል እንደዚህ ያለ ነግር ከምሰማ ……ስለዚህ ከተንሰኤ በሁላ አነድነገር መድረግ አለብን በህብረት ሁንን መንግስትንም ሆነ ..ቤተ----ቶችን መነጋገር አለብን በዛው ልክ የሚመጣውንም መከራ ለመቀበል መዘጋጀት አለብን በቃበቃበቃበቃ..ዝምታው ይብቃ ከዚህ በላይ የቀረው ሃይመኖተህን ቀየር ብቻ ነው የቀረው ስለዚህ ቢገድሉንም መሞት ቢያሰሩንም ወደ ግዞት መወረድ ለተወህዶ የማልሆነው የልም በግለፅ መንግስትንም ሆነማንንነም በቅንንት በሃይማኖታቸህን ጉዳይ ያናግረን ….እመቢ ብሎ ሌላ ታፔላ መለጠፍ ከፈለገም ይለጥፍ …….ከእነግዲህ ዝምታ እና ፍራቻ የቁም ..የህን ስል አመፅ ወይም እነደ አህዛቦቹ ሀይል መጠቀም አላልኩም ነገር ግን ስለ ተዋህዶ እሞታለው እመጅ አልገድልም እታሰራለው እንጅ አላስርም ስለዚህ ለመታሰር እና ከከፋም ለመሞት እንዘጋጅ እና በሰለፍ መነግሰትንም ሆነ ጠቅላይ ቤተ ክነትእናነጋግር
“ስጋን የሚገድሉትን አትፍሩ ነፍስን የሚገላትን ፍሩ “ተብሎ ተጽፏል እና
Amen, Now a day our church is envaded by transformationists, so we should pray to GOD, just to make things peace. May GOD help & bluss us.
ReplyDeleteThanks Andadirgen, I wonder if this kind of information can reach to the people easily. I mean to locals. I believe most of us who check internet is those who have a better access to it (like the diaspora). Please just design something so that it can rich the people the locals. I have seen that the youngster are fast for using facebook, create a facebook page (if u did not yet). Creating some subscription file where whenever you have news, it can directly go to our emails.
ReplyDeleteThanks
I am proud of the owner of the site and thank you for your well elaborated explanation! You are doing what is expected from you but I am afraid of about "Abune Gorgoriwose". The Abune he knew all the cases of this church from the beginning around 12 yrs ago. These poor people struggling to their house all these yrs, now they are on the verge to loss the place. Sorry to say majority of our shippers almost they failed by love of money. Tadeyose ("the owner of BISHOFT Resort" ) also make handicapped both ("Abun Pawelose and Abune Gorgoriwose"). I heard the church now has very serious financial shortage also. Please continuous giving the information and the way how people help this church!
ReplyDeleteThe Holy God and his Mother St.Virgin Marry Blessed You!
Yidres le'Aba Paulos yihin yalkut eyandanduan asteyayet kal akebayot silemiyadersilot new. Minew yezerefutin genzeb yizew yetamemewin egirotin biyasakimubet kanesewot degimo min chigir ale hizibu asebasibo yisetotal yihich betekrstian eko yetemeseretechiw be Kirstos new yalat nibret degimo eyandandu miskin kalew lay keniso begulbetu redito yeseraw new. zare ersiwo yalehasab yimnesheneshalu yih albeka bilot degimo lemanim sisay eyaderegut new. be 20 ametat wist kedimo yalnebere wedefitim ersiwo kelekeku yemayihon fetena yekerefa lemesmat yemikebid sira eyeseru new. minale be'edime ekuyawo kehonut bimaru? edmewo endet new ende Matusala yihonal teblewal ende? gira agabun eko. endiya bayihonima bekagn yemibal kal endale ayitefawotim nebere. Lelaw mengist ahunis albekahim chikonaw adileo, megelel yemibalutin kalatoch ke ehageg beker lelelaw ayiseram malet new. 20 amet eko malet bizu new keteserabet werk mehal endegeba deha honachihu esa? yetun ansiche yetun litewow ayinet. ere lib gizu. alebelezia satibelutim.....Bemecheresha and neger libelachihu.
ReplyDeletearfo yetekemete yetegnawin bere
gotgutew gotgutew aderegut awre
berehab eyasekayachihu enante bedilot tinoralachihu. yeterabe hizib ke Amlaku gar dil yadergachihual. Fird le Egizeabher yenanten yasayen.
abatochin bakalelachihu kutir yemitakerbutn information mamen yikebdal hulgize yekiristian sira tihitina mehon alebet mejemeria enante plaesecome down .yebetekrstian guday stanesu ke akbirot gara bihon tedemachinetin tagegnalachihu .yezelefa kal bebetekiristian wust ayasfeligim .
ReplyDeletemister anonymous erswon degmo man enbelwot??? liyaskebrihm liyasnqhim yemichilew sirah new! kiber kefelegu yemiyaskebr sira biseru enkuan zare tiwled hulu siyakebrachew yinoral. yemetuben be tewahdo new eshi! haymanotachihun shitu new bezih degmo ayqeledim be waga yetegezan kibur lijochu nen,,,,enshitachihu silu amen endalu yihun linl new yetebequt? qentu meqorqor
Deleteአቤቱ የልዑላን ልዑ የነገስታት ንጉስ አምላካችን መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይሄን ሰይጣናዊ ፓትሪያርክ አስወግድልን እውነተኛ መሪም ስጠን
ReplyDeleteአቤቱ የልዑላን ልዑ የነገስታት ንጉስ አምላካችን መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይሄን ሰይጣናዊ ፓትሪያርክ አስወግድልን እውነተኛ መሪም ስጠን
ReplyDeleteአቤቱ የልዑላን ልዑ የነገስታት ንጉስ አምላካችን መድህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይሄን ሰይጣናዊ ፓትሪያርክ አስወግድልን እውነተኛ መሪም ስጠን
ReplyDeleteስለምታደርሱን ወቅታዊ ዜና እግዚአብሄር ይስጥልን፡፡መረጃው ለብዙሃኑ ይደርሰ ዘንድ ብታደርጉ ደግሞ በጣም ውጤታማ ይሆናል፡፡ አምላካችን ቤ/ክንን ይጠብቅልን፡፤
ReplyDeleteእግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን
ReplyDeleteGreat work! This is the type of info that
ReplyDeleteshould be shared across the internet. Shame on Google for not positioning this submit upper!
Come on over and consult with my site . Thank you =)
my site > maroc