Tuesday, April 17, 2012

ማህበራትና የቤተክርስትያን ፈተናዎች

…. በየጊዜው የተቋቋሙ መንፈሳዊ ማህበራት ለቤተክርስትያን ያመጡትን ጥቅምና ጉዳታቸውን ከወደፊት ስጋቶች ዳሰሳ ያደርጋል ፤ በአንድ ግለሰብ የተመሰረተን ማህበር ቤተክርስትያን ላይ ያሳደረው ተፅህኖ ያንብቡ

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 9 2004ዓ.ም )፡- የቀለም ቀንዱ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንደተረጎሙት ማህበር ማለት ‹‹በቁሙ አንድነት ፤ ሸንጎ ፤ ብዙ ሰው ›› ማለት ነው ፡፡ በሌላም አተረጓጎም ‹‹ወገን ፤ ነገድ ፤ ቤተሰብ ፤ ጭፍራ ፤ ሰራዊት›› የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል ፡፡ ጠቅለል ባለ መንገድ ማህበር አንድነትና ህብረትን የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ ቤተክርስትያናችንም ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ፤ አዛውንቶች ደግሞ በሰንበቴ ማህበራት በመታቀፍ አንድነታቸውን የሚፈጽሙበት ሁኔታ አመቻታላችዋለች ፡፡በዚህም ከ50 ዓመት በላይ ስትሰራበት ቆይታለች ነገር ግን ከ1980 ወዲህ ቤተክርስትያኗ አስቀድማ ካስቀመጠችው አወቃቀር የተለየ በተለየ በ1990 ዎቹ መጨረሻ የማበራት ቁጥር እጅግ እየበዛ መጣ፡፡


በአሁኑ ሰዓት በሺህ የሚቆጠሩ ማህበራ ይገኛሉ ፤ ባለፉት 20 ዓመታት በሁለት እግሩ የቆመ ማህበር ማህበረ ቅዱሳን አንድ ምሳሌ ነው ፤ ማህበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተዋቀረው እና በሰንበት ትምርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር ሆኖ ቤተክርስትያኗ ያሉባትን ክፍተቶች በተለያዩ ባለሙያዎች በተጠናና በሚጠቅም መልኩ እየሞላ የሚገኝ ማህበር ነው፡፡ ሌሎች መልካም ስራ ያላቸው ማህበራ ቢኖሩም በብዛት በቤተክርስትያኗ መዋቅር ስር አይደሉም ፤ መልካም ስራቸውንም በአደባባይ ማሳየት አልቻሉም ፤ ቅዱስ ሲኖዶስም አያውቃቸውም ፤ ማህበረ ቅዱሳን የከፍተኛ የትምህር ተቋማት ተማሪዎችን ተገቢ ሊባል በሚችል መጠን በሚችለው አቅም ያህል አስተምሮ አባል እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ሌሎች ማህበራት ግን አባላቶቻቸው በምን ያህል መጠን እንደተማሩ አይታወቅም፡፡

ስለሆነም ከስሜቶቻቸው ጋር የሚጣጣም ማንኛውንም ነገር ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚከለክላቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ለምን ቢባል የቤተክርስትያን አስተምህሮ በአባላቶቹ ዘንድ በጠለቀ መጠኑ ስለማይታወቅ ነው፡፡ ስለሆነም ቤተክርስትያን የወጣቱን መንፈሳዊ ስሜትን ተረድታ ጉድለታቸውን ሞልታ በበሳል አመራር ለመልካም ነገር ልትጠቀምበት ይገባል ፤ በተለይ የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትንና የመስቀል በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተለያዩ ደብሮች የተሰበሰቡ ወጣቶች የላቀ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በብዙ ድካም ልትሰበስባቸው ሲገባ ያለምንም ጥረት በፈቃደ እግዚአብሔር ተሰባስበዋልና ይህን መልካም አጋጣሚ ተጠቅማና ስሜታቸውን ጠብቃ መሰረታዊውን የሀይማኖት ትምህርት በማስተማር ወደሚፈለገው ደረጃ ልታደርሳቸው ይገባል ፤ የነገይቱን የቤተክርስትያን ተረካቢ መሆናቸውንም ልንዘነጋ አይገባም ፤

በመላ ሀገሪቱ ማህበራት አሁን ባሉበት ሁኔታ ልቅ ሆነው የተወሰነ መንገድ ከሄዱ ቀጣዩን ትውልድ በቤተክርስትያን አቅፍ ውስጥ ለመምራት እና የቤተክርስትያንን ቀኖና እና ዶግማ ጠንቅቀው እንዲያውቁ ለማድረግ እጅግ ያስቸግራል ፤ ነገ ይህን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ማህበር ለመቆጣጠርና ለመምራት ማጠፊያው እንዳያጥረን የብዙዎቻችን ስጋት ነው፡፡

የሀገራችን የወደፊት ስጋቶች ውስጥ የመጀመሪያው እና ቅድሚያ ቦታ የሚይዘው የሀይማኖት ግጭት ነው ፡፡ ይህ የኔ ሀሳብ ሳይሆን መንግስት ችግሩ መኖሩን አምኖ ስራ እየሰራ የሚገኝበት ጉዳይ ነው ፤ ባሳለፍናቸው ጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ ችግር እንዴት ጎልቶ እንደወጣ ሁላችን የምናውቀው ነገር ነው ፤ ይህን ችግር መኖሩን የተለያዩ ጥናቶች እየጠቆሙ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት ለቁጥጥር በማያመች መልኩ በየቦታው በጥቂት ሰዎች ፍቃደኝነት ላይ የሚመሰረቱ ማህበራ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል ፡፡ ማህበራት በአግባቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚያደራጃቸው እና መንገዳቸውን የሚከታተል አካል ከሌለ ከቤተክርስትያኗ ይልቅ የሀገርና የህዝብን ሰላም ሊያናጉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን ፤ እንደ ማህበረ ማርያም የተሀድሶያውያን ማህበር በጥቂት ሰዎች መዘውር ውስጥ የገባ ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ላይ የፈጠሩትን ችግር እንደ ማሳያ መውሰድ ይቻላል ፤ እነዚህ ማህበራት ጉዳታቸው መናፍቃንን እና ከቤተክርስትያን የታገዱ ሰዎችን በማካተት በማር የተለወሰ ውስጡ መርዝ የሆነ ስብከት ለምዕመኑ ይዘው መቅረባቸው ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በነዚህ ማህበራት አማካኝነት አጥንታቸው በወንጌል ያልጠነከሩ ወገኖቻችንን በየአዳራሹ እየሰበሰቡ ከመናፍቃን ዘንድ እንዲቀላቀሉ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ፡፡ አሁን ለማሰየት የፈለኩት በየጊዜው የተቋቋሙ መንፈሳዊ ማህበራት ለቤተክርስትያን ያመጡትን ጥቅምና ጉዳታቸውን ከወደፊት ስጋቶች ጋር ለማቅረብ ነው

በቤተክርስትያኒቷ ስር ያሉትን ማህበራት በ5 ከፍለን ለማየት ወደድን

1. ክፍተትን ለመሙላት የተቋቋሙ

እነዚህ ማህበራት ቤተክርስትያን በነበራት መዋቅር ልትሸፍነው ያልቻለችውን ክፍተት ለመሙላት የተቋቋሙ ማህበራት ናቸው ፤ ክፍተትን ተረድተው ለመሙላት የሚቋቋሙ ናቸው እነዚህ ማህበራት የአጭር እኛ የረዥም ጊዜ እቅድ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ለምሳሌ ህንጻ ቤተክርስትያን ለማሰራት ፤ እድሳት ለማከናወን ፤ ቤተክርስትያኒቷ የራሷ ተቋም እንዲኖራት የሚሰሩ ፤ የተዘጉ ቤተክርስትያናትን ለማስከፈት ..እና መሰል አላማን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፡፤ ዛሬ ማህበራቱ በመሰረቷቸው መልካም ሰዎች አማካኝነት ጠንካራ ማንነት ቢኖራቸውም እንኳን ነገ እነርሱን የሚተኳው ሰዎች ዓላማቸው ሊለወጥ ስለሚችል የቤተክርስትያን ስጋት ከመሆን አያልፉም ፤

2. የገጠሪቱን ቤተክርስትያን ለመርዳት በሚል የተዋቀሩ ማህበራት

በገጠሯ ቤተክርስትያን ያሉ አገልጋዮች ያለባቸው ፈተና በጣም ብዙ ነው፡፡ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኝት ቀን ቀን ከእርሻ ጀምሮ በልዩ ልዩ ስራዎች ተጠምደው ይውላሉ ፡፡ ማታ ማታ ደግሞ በትግሀ ሌሊት እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ያድራሉ፡፡ በብዙ መዋተት ያገለግላሉ ፤ በዚያ ላይ አልሞላ ብሏቸው ይኖራሉ ፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚቋቋሙ ማህበራት አሉ፡፡

እነዚህ ማህበራት የሚያዩትን ችግር አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ለመፍታት ብለው ተመሳሳይ ስሜትና መንፈስ ያላቸውን ወንድሞችንና እህቶችን በማሰባሰብ በግለሰቦች ቅንነት የተመሰረቱ ማህበራት ናቸው ፤ አላማቸው እና ምልከታቸው የሚደነቅ ነው ፤ ቤተክርስትያናት በጎደላት ጊዜ ደርሳችሁላታል ፤ ልትመሰገኑ ይገባል ፤ ነገር ግን ሩጫችሁን በድል ለማጠናቀቅ ስለሚቀጥሉት ነገሮች ተወያይቶ መፍትሄ ማስቀመጥ ያስፈልጋል

ü ማህበራቱ የሚዋቀሩት በሰዎች ማንነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ስለሆነም ግለሰቦች እንቅፋት በገጠማቸው ጊዜ በርካታ ተከታዮቻቸው የስብስቡን አላማ ከግብ ለማድረስ ሊሳናቸው ይችላል ፡፡ በወንጌል ትምህርት ያልበሰሉ ከሆኑ ደግሞ ዓላማቸውን በጥቂት መሰሪ ሰዎች ቀይረው መስመራቸውን ሊያስቷቸው ይችላሉ ፤

ü ማህበራ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ገንዘብ አሰባስበው ወደ ገጠሯ ቤተክርስትያን በመውሰድ አገልጋዮች ካህናትንና ዲያቆናትን የተወሰነም ቢባል ደመወዝ በመክፈልና ንዋያተ ቅድሳትን በሟሟላት የተቋረጠውን አገልግሎት እንዲቀጥል የተዘጋችዋን ቤተክርስትያን እንድትከፈት ፤ የተዳከመው እንዲበረታ በማድረግ ፤ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ጉልህ ድርሻ ጎን ለጎን ግን ስራው ተጠንቶና ዘላቂነቱ ተረጋግጦ የተጀመረ ባለመሆኑ በየወሩ የሚያወጡት ገንዘብ ከጊዜው የኑሮ ሁኔታ ጋር እየከበዳቸው ይሄዳል ፤ እንቅስቃሴያቸውም በጊዜያት ሂደት እየቀዘቀዘ ይመጣል ፤ በመሆኑም አባላት ወርሐዊ ክፍያቸውን ድንገት ሲያቋርጡ ማህበራቱ የሚያቀርቡት ገንዘብ ያጡና የጀመሩት ስራ ይቋረጣል፡፡ ይህን የመሰለ ችግር ወደፊት ለስራቸው እንቅፋት እንደማይሆንባቸው አውቀውት ቢገቡበት መልካም ነው፡፡


3. ቁጭት የመሰረታቸው ማህበራት

አህዛባዊ ግብር ባላቸው አካላት በቤተክርስትያን ላይ በደረሰው ጉዳት አንገብግቧቸው በቁጭት የተመሰረቱ ማህበራትን ይመለከታል ፤ ከአህዛብያውያን አኩይ ግብር የተነሳ አብያተክርስያናት በእሳት እንዲጋዩ ፤ ካህናትና ምዕመናንም በቤተ መቅደሳቸው በሰይፍ ሲታረዱ ፤ ቤተክርስትያን ላይ እሳት ሲሎከስባት ፤ በየቦታው የሚገኙ ክርስትያኖች ላይ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ችግር ሲደርስባቸው ባዩ እና በሰሙ ጊዜ አዝነው መፍትሄ ለማምጣት ብለው ወጣቶችን በማሰባሰብ የመሰረቸቷው ማህበራት ናቸው ፡፡ የማህበሩ አባላት በቤተክርስትያን ባላቸው ጥልቅ ፍቅርና ተቆርቋሪነት የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ስለ ቤተክርስያን ስርዓት አስተምህሮ ዶግማ እና ቀኖና ያላቸው እውቀት አናሳ ቢሆንም ፍቅራቸውና መቆርቆራቸው ግን በጣም ጥልቅ ነው፡፡

ቤተክርስያኗ ላይ አንድ ፈተና ቢመጣ እንኳን ከሁላችንም ይልቅ ቀድመው ከፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ እንዲህ አይነት ቅናትና መቆርቆር ይዞ የመጣን ሰው ደግሞ በአግባቡ ተቀብሎ ማስተናገድ የቤተክርስያኒቱ ተግባርና ሀላፊነት ይመስለናል ፡፡ መንፈሳዊ ከመሆን ጋር የሚመጣውን ፈተናና የቅዱሳንንም ሕይወት በውል ስለማያውቁ ትከሻቸው መከራንና መገፋትን ለመሸከም አይችልም፡፡ ስለዚህ በጥሞና እያስረዱ መስመር እንዲገቡ ቅንነታቸውና መቆርቆራቸው ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቀየር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

እንደዚሁም አብዛኛው እንቅስቃሴያቸው ስሜት የተቀላቀለበት ስለሆነ ቀስ በቀስ ጉዳት እንዳያደርስ ቤተክርስትያን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባታል ፡፡ አንዳንድ ተምረው ምግባረ ብልሹ የሆኑ ግለሰቦች ተቀላቅለው መስመር እንዳያስቷቸው ፤ ቤተክርስትያኗ ባላት መዋቅር ውስጥ ገብተው እንዲማሩ እና እንዲያገለግሉ በለዘበ ቋንቋ እስከሚገባቸው ድረስ ማስረዳት ይኖርባታል፡፡

ያላቸው ጥልቅ ስሜትና ተቆርቋሩነት ለቤተክርስትያን ስርአት አስተምህሮ ካላቸው እንግድነት ጋር በድምር ተጠቅመው የቤተክርስትያኒቱን ጉዞ ለማደናቀፍ እንቅልፍ አልባ የሆኑ ቡድኖች ወደ አልሆነ አቅጣጫ እንዳይመራቸው መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ የወቅቱ ስልታቸው እቅዳቸው ይህው መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉና፡፡

4. የንግድና የኑፋቄ ስራን ለመስራት የተቋቋሙ ማህበራት

በዚህ መስመር ያሉ ማህበራት የሚያንጹና የሚያስተምሩ ሳይሆኑ ስሜት የሚነኩ የተለያዩ ስራዎችን በመስራትና ንግዱ በዚህ መስመር ያዋጣል ብለው ሲያምኑ የቤተክርስትያኒቱን ሃላፊዎች ሳይቀር ስድብ በመሳደብና በማዋረድ ወደ ሕዝብ የሚገቡ ፤ አላዋጣ ሲላቸው ደግሞ እያወቁ ያዋጣናል ብለው የገቡበትን መስመር ጥለው ያለ ጥቂት ሀፍረት እንደ እባባ አቅጣጫ ቀይረው የሚጠመዘዙ ናቸው፡፡

በኑፋቄ ተልእኮታቸውና ስሜት የሚነኩና ልቅ የሆኑ ትምህርቶቻቸውና መዝሙሮቻቸው ምዕመናን ለቤተክርስያኗ ስርአት የነበራቸው ጥብቀት እንዲላላ ፤ ተቆርቆሪነታቸውም ደረጃ በደረጃ እየተሸረሸረ እንዲሄድ የሚሰሩ ተቋማት ናቸው ፡፡ በትኩረት ከተመለከትነው የዘወትር ስራቸው ምእመናን ቤተክርስትያኒቷን እንዲከተሉ ፤ ቅዱሳንን እንዲወዱ ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር እንዲኖራቸው ፤ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና ለጽድቅ የሚያበቃ ስራ እንዲሰሩ ሳይሆን የእነሱ ደጋፊዎችና የንግድ አጋሮቻቸው እንዲሆኑ ማድረግ ተቀዳሚ አላማቸው ነው ፡፡ አንድ ጊዜ አውደምህረት ላይ አንዱ አሁን ከአውደ ምህረት የታገደ ሰው ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ ህዝቡን እስኪ አንድ ጊዜ እጃችሁን ወደ ላይ አለ ፤ ምዕመኑም እጁን ወደ ላይ በማውጣት ተባበረው ፤ ከዚያ ቃል ግቡልኝ ካለ በኋላ ‹‹በማርያም ይህን ካሴት አንድ አንድ ግዙኝ›› ብሎ አረፈው …ይህ ሰው መጀመሪያም የመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሳይሆን ካሴት ለመሸጥ ነው፡፡

እነዚህ ማህበራት ምዕመናን ወደ ቤተክርስትያን የእግዚአብሔር ጉባኤ ሳይሆን የእገሌ ጉባኤ አለ ብለው እንዲመጡ በማድረገስ ስራዎችን በሰፊው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለእነዚህ አይነት ቡድኖች ማህበራት ቤተክርስትያን ልዩ አይን ሊኖራት ይገባል፡፡ ሲመች የሚሰሩ ሳይመች ምድር ቀደው የሚገቡ ቢሆኑም ቤተክርስትን ያላት ህጋዊ መብት ተጠቅማ ቢያንስ ይፋዊ እንቅስቃሴያቸውን መግታት ይኖርባታል፡፡

በአዲስ አበባ ውስጥ ‹‹ወይንዬ ተክለሀይማኖት›› በሚል ስም የተቋቋመ ማህበር ስሙ የማያውቅ ምዕመን አለ ብለን አንገምትም ፤ ይህ ማህበር ከደብረብርሀን በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝው የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያንን ለመርዳት መሰረት አድርጎ የተመሰረተ መንፈሳዊ ማህበር ነበር ፤ ቦታው ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜት ተጉዘው ደብረ ብርሀን ይደርሳሉ ፤ ከከተማው በስተ ግራ በኩል 5 ኪሎሜትር ያህል የእግር መንገድ ሄደው ያገኙታል ፤ ይህ ቦታ ሲሄዱ ቁልቁለት ሲመለሱ ደግሙ ጉልበት የማይችለው ዳገት ስለሆነ ማንም ምእመን በቀላሉ ሄዶ መሳለም የሚችልበት ቦታ ባለመሆኑ የተለያዩ ችግሮች ያሉበት ቤተክርስትያን ነው ፤ ይህን ችግር መሰረት አድርጎ ለመርዳት በማለት በአቶ ደረጀ አማካኝነት ከ10 ዓመት በፊት ማህበሩ ተቋቋመ ፤ መጀመሪያ አካባቢ ጥቂት ብሮችን እያመጣ ለቤተክርስትያኑ እንደሚሰጥ ለማወቅ ችለናል ፤ ከዚያ ግን ስሙን በመጠቀም ብቻ በርካታ መቶ ሺህ ብሮችን ቢሰበስብም ይህ ነው የተባለ ለውጥ ቦታው ላይ ማየት አልተቻለም ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ስለ ወይንዬ ተክለሀይማኖት በሰራው የቪሲዲ ስራ በምድረ አሜሪካ የሚገኙ አንድ አባት በሱ የባንክ አካውንት 50ሺህ ብር ልከውለት ነበር ፤ እኝህ አባት ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ፤ የተጀመረው ቤተክርስትያን ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ቦታው ሄደው የሰበካ ጉባኤውን ሲያናግሩ ምንም አይነት ብር እንዳልደረሳቸው ይገልጹላቸዋል ፡፡ እኝህ አባት በጊዜው በጣም ተናደው ፤ ገንዘባቸው ለቤተክርስትያኒቷ እንዳልደረሰ ተገነዘቡ ፤ ብራቸውም ጅብ እንደበላው አውቀው ፤ አቶ ደረጀን ፍርድ ቤት በዚህ ጉዳይ ቆሞ ነበር ፤ አቶ ደረጀም በጊዜው በወሎ ላስታ አካባቢ የማይታወቅ ቦታ በመጥራት እዛ ላለው ተክለኃይማኖት ቤተክርስትያን ነው የሰበሰብኩት ብሏል ፡፡

ü ይህ ሰው ‹‹ወይንዬ ተክለሀይማኖት››የሚለውን ስም አሁን እንኳን መልስ ቢባል ፍቃደኛ አልሆነም ፤ በማህበሩ ስም የሚያገኝው ገንዘብ ስለሚቋረጥ የእሱም እስትንፋስ የማህበሩ ስም ስለሆነ ለሚመለከተው አካል የማህበሩን ስም መስጠት አልፈለገም ፤ ቤተክህነቱ በማህበሩ ስም ያካበትከውን ሀብትና የሚሰራበትን ማህተብ አስረክብ የሚል ደብዳቤ የዛሬ አመት ሲደርሰው የማህበሩን ንብረት ብሎ የመዘገባቸውን እቃዎች ብትመለከቱ ባጣም ታዝናላችሁ ፤ እኔ ንብረት ብሎ ያስመዘገበውን ከቤተክህነት ደብዳቤ ጋር መመልከት ችዬ ነበር ፤ ከተጠቀሱት እቃዎችም የተበላሸ ካሜራ ፤ ድስት ፤ ጭልፋ ፤ ሰሀን የተበላሸ ኮምፒዩትርና ካሜራ ፤ .. እና የማየጠቅሙ ነገሮችን ዝርዝር አውጥቶ ነበር የሰጣቸው ፤ እቃዎቹ ሁሉም በ12 ዓመት ያካበትኩት ንብረት የማህበሩ ነው ብሎ ያቀረበው ንብረት ቢደመር 1000 ብር አይሞላም ፡፡ አሁንም ‹‹ወይንዬ ተክለኃይማኖት›› የሚለውን ስም እንደ Trade Mark እየተጠቀመበት ይገኛል ፤ እንደዚህ አይነቶች ማህበራት በርካታ ናቸው ፤


ü ከጀርመን ሀገር እሱ የሰራውን የወይንዬ ተክለሀይማኖት ሲዲን የተመለከቱ ከ10 በላይ ሰዎች በጣም በርካታ ብር በመላክ በአቶ ደረጀ አካውንት ልከውለት ነበር ፤ ከላኩት ሰዎች አንዱ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የላክነው ብር የተጀመረውን ቤተክርስትያን ምን ያህል ደረጃ ላይ እንዳደረሰው ቦታው ላይ ሄደው ሲመለከቱ ቪሲዲ ላይ ካዩት ምንም ሳይቀየር ያገኙታል ፤ ከዛ በጊዜው የነበሩት የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ አባላት ምንም እንዳልደረሳቸው ያስረዷቸው ፤ ምን ያህል ብር እንደላኩ ሲጠየቁ ፤ ‹‹ተውት በቃ ልጆቼ ያልደረሰ ብር ብነግራችሁ ምን ይሰራላችኋል ትርፉ መናደድ ነው›› ብለው ቅስማቸው ተሰብሮ ወደ መጡበት ወደ ጀርመን ሊመለሱ ችለዋል፡፡ (ይህስ ምን ይባላል?)



ü አንድ ወቅት የአቶ ደረጀ ሚስት ህልም አይታ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አባት ጋር በመሄድ ያየችውን ሁሉ ትነግራችዋለች ፤ እርሳቸውም በደንብ አድርገው ከሰሟት በኋላ‹‹ልጄ እግዚአብሔር ሰው ሊወስድብሽ ነው መሸለኝ ለማንኛውም ጸልዪ›› ብለዋት ነበር ፤ በጊዜውም በጣም ደንግጣ ስታለቅስ ነበር ፤ ከቀናት በኋላ ግን የመጀመሪያ ልጃቸው በመኪና አደጋ አማካኝነት አጥተዋል ፤ ይህ መቼስ ምን ይባላል ፤

ü ሌላ አስገራሚ ነገር ደግሞ የዚህው ግለሰብ ሚስት ኑሯቸውን የሚገፉበት ፤ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት በጠቅላላው የሚተዳደሩበት ብር የቤተክርስትያን ብር መሆኑን ስለምታውቅ ነገሩ ለጭንቅላቷ እረፍት ስለነሳት ብጹእ አቡነ ኤፍሬም ጋር በመሄድ ፤ ‹‹ከዚህ ሰው ጋር አብሬ መኖር አልፈልግም አፋቱኝ›› ስትላቸው ፤ እሳቸውም ለምን ልጄ ? በተክሊል ተጋብታችሁ እንዴት እንዲህ ትያለሽ ? ይህ ተገቢ አይደለም ብለው ሀሳቧን እንድትቀይር የአባትነት ምክር ሲመክሯት ፤ እርሷም አባታችን ‹‹እኛ እስከ አሁን የምንኖረው ለወይንዬ ተክለሀይማኖት ተብሎ በሚላከው ገንዘብ ነው ፤ ከአሁን በኋላ በዚህ ብር መኖር አልችልም ፤ ውስጤም እየተጨነቀ ነው›› ብላ ተናግራለች ፤ እሳቸውም በጊዜው ምን እንደሚደርጉ ግራ ገብቷቸው ነበር፡፡ አባታችን ምንም ባይሉም እርሷ ይህን ሁሉ እያየች መኖር ስላልቻለች በጊዜው ፍቺ ፈጽማ ነበር፡፡

አባታችን አቡነ ኤፍሬም በየጊዜው የሚሰሙት እሰጣ ገባ ስለሰለቻቸው ‹‹ልጅ ደረጀ እባክህን የሀገረ ስብከቴን ስም አታበላሽ ፤›› በማለት ተግሳጽ ተናግረውት ነበር ፡፡ አቶ ደረጀ የወይንዬ ተክለኃይማኖት ማህበር ስራ አስኪያጅ ብዙ ጊዜ ተመክሮ እና ተዘክሮ እምቢ ስላለ ሰዎች የእርሱን ነገር ለእግዚአብሔር አሳልፈው ሰጥተዋል ፤ ይህ ሰው ‹‹በወይንዬ ተክለኃይማኖት ማህበር›› ስም ህዳር 21 2003 ዓ.ም ጽዮን ማርያም ቤተክርስያን ለንግስ በርካታ መኪና ምዕመናንን ጉዞ ይዞ ሄዶ ነበር ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ወደ ጽዮን የተደረገ ጉዞ ላይ አደጋ ደረሰ ሲባል ሰምተን አናውቅም ነበር ፤ እሱ ይዞት የሄደው ትልቅ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በ24/03/2003 ዓ.ም ከንግስ መልስ በተክለኃይማኖት ቀን መኪናው ገደል ገብቶ ከ9 ሰው በላይ መሞቱን ፤ በርካታዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የዛሬ ዓመት ትውስታችን ነው ፤ በዚህ መኪና ውስጥም የአቶ ደረጀ አባትና በጊዜው ይዟት ሲዞር የነበረች ለማግባት ያሰባት አንዲት እህት አደጋው ደርሶባቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡ በጊዜው ለቅሶ ተቀምጦ ሳለ ከራሱ አንደበት ‹‹ከአቡነ ተክለኃይማኖት ጋር የምታረቅበት ጊዜ ደረሰ መሰለኝ›› ሲል ተሰምቷል፡፡ ሰው ልቡን እንዳያደነድን መጽሀፉ ያዛል ፤ ልቡን ያደነደነ ደግሞ ሳያስበው እግዚአብሔር ህይወቱን እንደሚቆርጣት ተፅፏል ፤ ‹‹አቡነ ተክለኃይማኖት ስር ነው የሚነቅሉት›› ሲባል ከአንድ አባት ሰምቻለሁ ፤ አሁን ከያዘው የሌብነት መንገድ እንዲመለስ ለሰራው ስራ ንስሀ እንዲገባ እግዚአብሔር ይፍቀድለት ፡፡‹‹ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፡›› የሐዋርያት ሥራ 3፤19-20 ፡፡ ይህ ካሉት መንፈሳዊ ስምን ከተላበሱ የንግድ ማህበራት አንዱ ነው ፡፡ ከሰራዎቹ ጥቂቱን ብቻ ነው የጻፍኩት ፤ የሰውየው ስራ ይህ ብቻ አይደለም ፤ እንዲያው ሰውን ለማንቃት ያህል እንጂ ስራው ቢዘረዘር አያልቅም ፤ ይህን አንብባችሁ ከእሱ ጋር ብትተባበሩ ለሱ የመጣው መቅሰፍት ለናንተም እንዳይተርፍ እንሰጋለን፡፡

የሰውን ግላዊ ህይወቱን በቀን ከ5ሺህ በላይ በሚጎበኝ ብሎግ ላይ መጻፍ ተገቢ ነው ብለን አናምንም ፤ ቤተክርስትያን ላይ የቆመ ደንቃራ ስለሆነ ይህን ልናደርግ ችለናል ፤ ወደፊትም ምዕመናን ይህን አይተው ከሱ ጋር ለአላማው እንዳይተባበሩ ከማንቃት አኳያ ስለጻፍነው ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

አቶ ደረጀ በሰራው የተበላሸ ስራ ምክንያት ሰዎች ገና ‹‹ወይንዬ ተክለኃይማኖት›› ሲባሉ ጥሩ ነገር ውስጣቸው እንዳይኖር አድርጓል ፤ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድና በምዕመናን ያላቋረጠ እርዳታ አሁን የዛሬ 10 ዓመት የተጀመረው የቤተክርስትያን ስራ ወደ መጠናቀቅ እየደረሰ ይገኛል፡፡ አንዲት እህት ከወራት በፊት ከአሜሪካ ለእረፍት በማጣችበት ወቅት ቦታው ድረስ ሄዳ ያለበትን ሁኔታ በማየት የ72 ሺህ ብር ለቆርቆሮ ማገር የሚሆን ሞራሌ እና 30 ሺህ ብር ቱቡላሬ ገዝታላችዋለች ፤ የመልካም ስራ ተቃዋሚ ዳቢሎስ ለጻድቁ አባታችን ተክለኃይማት ለቤተክርስትያን እንዳያልቅ እሾህ የሆነ እንደ አቶ ደረጀ ያለን ሰው 12 ዓመት ሊያቆም ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር ግን ሰው አለው 102 ሺህ ብር በአንድ ቀን አንድ ሰውን አነሳስቶ የተቀደሰ ስራ ሊያሰራ የሚችል አምላክ ነው ፤ ቦታው ድረስ ሄጄ በአይኔ እንደተመለከትኩትኝ ቤተክርስትያኑ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከ 600 ቆርቆሮ በላይ ይፈጃል ብለውኛል፡፡ (200 ሺህ ብር አካባቢ)፡፡

ሌሎችንም በርካታ ማህበራት የሚሰሩትን ስራ ማበረታታት ያለበትን እናበረታታለን ሰዎች እንዲረዷው እናደርጋለን ፤ እንደዚህ አይነት የዘቀጠውን ሰው ፤ ለመልካም ስራ እንቅፋት የሆነውን ደንቃራ ደግሞ ምዕመኑ እንዲያውቅ እናደርጋለን ፤ ‹‹እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም››የሐዋርያት ሥራ 4፤20 እኛ ያየነውን ከተናገርን የተቀረውን ለናንተ ትተናል ፤

የስብከተወንጌል ሰራተኞችና ሰ/ት/ቤቶች ምዕመኑ እገሌን ብሎ ሳይሆን እግዚአብሔርን ብሎ ወደ ቤተክርስትያን እንዲመጣ ተግተው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡‹‹ሀጥያተኛ በሃጥያቱ ይጠፋል ደሙን ግን ካንተ እሻለሁ›› ያለ አምላክ እግዚአብሔር እንድታገለግሉ በሰጣቸው እድል መጠን ይጠይቃችዋል፡፡ በየትኛውም ደረጃ ላይ የምታገለግሉ የቤተክርስትያኒቷ መሪዎች በሚያልፍ ዘመናችሁ የማያልፍ መከራ አስቀምጣችሁባት እንዳትሄዱ ልትጠነቀቁ ያስፈልጋል፡፡

5. የስነ ምግባር ያለባቸው ግለሰቦች የመሰረቷቸው ማህበራት

በመጨረሻ ደረጃ የምናያቸው ማህራት በተለያዩ ስነ ምግባር ችግሮች ከሰ/ት/ቤት ወይም በድምሩ ከቤተክርሰትያን አገልግሎት የታገዱና ለቤተክርስትያኗ አስተዳር ከላይ እስከ ታች ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች የሚያቋቁማቸው ማህበራት ናቸው፡፡

እነዚህ ማህበራት በቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ስራቸውም በተጨባጭ ይሁን በተፈጠረ ምክንያት ምዕመናን የቤተክርስትያን አስተዳደር በጥቅሉ እንዲጠሉ ማድረግና ቤተክርስትያን ውስጥ ቢሆኑ ልናገኝ እንችል ነበር ብለው የሚያስቡትን ማኛውንም ጥቅማ ጥቅም የማስጠበቅ ዓላማን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ግለሰቦች ከቤተክርስትያን አገልግሎት የታገዱት በፈጠሩት የስነ ምግባር ችግር አማካኝነት መሆኑን ማሰብ አይፈልጉም፡፡(እነዚህ በሌላ ጊዜ ሰፋ ባለ ዘገባ ልመለስባቸው ፤ ለዛሬ ይብቃ )

እኛ ምዕመናን ስለ ማህበራት ያለንን አመለካከት አሁን እናስተካክል ፤ እኛው ተሰናክለን ሌላውን አናሰናክል ፤ ሳናውቅ ለቤተክርስትያን የእግር እሳት አንሁንባት ፤ ይህን የማህበራት ችግር አሁን መፍታት ካልቻልን ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ስለሚፈጠር መጀመሪያ ራሳችን የቆምንበትንና ያለንበትን ማህበር እንመርምር ፤ እንደ በግ ከመነዳት ራሳችንን እንጠብቅ ፤ ለቤተክርስትያን እሾህ የሆናትን ከመቃወም ወደ ኋላ አንልም ፤ ለቤተክርስትያን በማይጠቅማት መንገድ የቆመን አይተን የምናልፍበት አይን የለንም ፤ ሰምተንም ከናንተ የምንደብቀው ሚስጥር የለም ፤ የምንፈራው እውነትም የለም ፤

‹‹ነገን ለማስተካከል ዛሬ ተግተን እንስራ››

11 comments:

  1. kalehiyot yasemalin tiru iyita new

    ReplyDelete
  2. It is nice article, continue to tell us such stupid persons who use our church name to make their life better.

    ReplyDelete
  3. Even though we lack Fathers to understand the church and the generation we never stop our shout to GOD and to the people.GOD BLESS U!!!

    ReplyDelete
  4. denk yetwahedo lejoche endnante aynetun amelak yabezalen edmana tsgawen yabezalchu emberhan yelbachun tefetsmelachu

    ReplyDelete
  5. Andadirgen Egziabher yebarkachu betam tiru asitemare negeri new betam leserabete yemegeba new beritu sile ewunet kumu.

    ReplyDelete
  6. lemehonu mk yemisebesibew genzeb begedamat erdata sebeb bebetekihnetu yimeremeral woy? mels bagegne des yilegnal.

    ReplyDelete
    Replies
    1. My Friend if your eyes are open and if your mind is free you can get the answer for your question not from paper but from a real jobs done by MK.
      our church knows each and every thing about MK's activities except the enemies of truth. You can see the projects accomplished in various monasteries and churches in the whole Ethiopia. Open your eyes and try to see the jobs done by MK as I have seen them before.

      Delete
    2. My brother, I can't believe what you said before. b/c they should be audited by Betekihnet and external auditors. Why you afraid to be open your account. God knows that MK doing what ever good or bad. My eyes are always open to see the truth , but the bad thing is i always see the members of MK are traveling to USA & European countries by the money of MK.

      Delete
  7. This the information i ve been looking for a long time. Thank you telling us. please keep investigating the rest of them so that the people will know with whom he/she is living with. May God be with u.

    ReplyDelete
  8. Ahun Manin Tsekemachihu ?Yesewn Bedel Lerasu menger yishalal Dereje leweyiyinye yetsekemewim neger ale Befit yihinin Gedam Man Yawkew Nebere ? Degimo sewn simun matsifat kibirun menkat kefi yale bedel mehonun ewku Andadirgen Maninetachuhu yetaweke new Lemins Sew Mahibere Kidusann Enditsela Tadergutalachihu Genzeb Bemesebseb Mahibere Kidusann Yemiyahil alewy ?Beteley yemyasazinew YeDerege Lij motech Liyagebat yeneberechiw lij motech abatu mote yihinin yaderegew Ye Dereje Bedel new malet min malet new yasazinal SEwn lemasaded Aba Selama Yetebalew blloog yibeka nebere Ahunim YEsewn Neger mawrat yikiribin SEwn YIgodal BEGIL binastemrew YIshalal Minalbatim Yewdedinewn Mamesige Yetselanewn masade yastseyik yihonali lehayimanot mekom malet yihi ayidelem yikir yibelen

    ReplyDelete