Friday, April 27, 2012

‹‹ቤተክርስትያኒቱ አትዘጋም›› ያሉ 16 ክርስትያኖች ታሰሩ


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ


(አንድ አድርገን ሚያዚያ 19 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የባቦጋያ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ይገኛል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ እንዳሰበው ነገሮች እየሄዱ አለመሆናቸውን ሲረዳ የቤተክርስትያኒቱን ቄሰ ገበዝ ትላንት አመሻሽ ላይ የመቅደሱን ቁልፍ ካለመጡ ብሎ ጠይቋቸው ነበር ፤ እርሳቸውም ‹‹አንተ ማነህና ነው የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ የምሰጥ ›› በማለት እምቢ ሲሉት ጉልበት ተጠቅሞ ቁልፉን እጁ ለማስገባት ሙከራ አድርጎ  ነበር ፤ ቄሰ ገበዙ የመቅደሱን ቁልፍ አልሰጥም በማለት ለአካባቢው ክርስትያኖች ስልክ ደውለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስትያኖቹ የተሰበሰቡ ሲሆኑ ከደቂቃዎች በኋላ ጌታቸው ‹‹አመጽ ለማስነሳት ሰዎች ተሰብስበዋል›› ብሎ በደወለላቸው ፖሊሶች አማካኝነት በጊዜው የነበሩትን 16 ክርስትኖችን  እስር ቤት ሊያስገቧቸው ችለዋል ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ሶቶች ጎልማሶችና ፤ ወጣቶች ይገኙበታል ፤  የእነዚህ ንጹሀን ክርስትያኖች  ተቃውሞ ‹‹አቶ ጌታቸው ዶኒ  የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ ለምን ይቀበላል ? ቁልፉን ተቀብሎ ከዚህ በፊት ሲናገር እንደነበረው የባቦጋያን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ለመዝጋት የሚያደርገውን ተግባር እንቃወማለን ፤ ›› በማለታቸው ነው ለእስር የበቁት፡፡


 በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት ሄዶ ታሳሪዎችን መጠየቅ በራሱ ያሳስራል ፤ የአቶ ጌታቸው ዶኒ ሀሳብ አንድም ጽላቱን በማውጣት ቤተክርስትያኑ እንዳይቀደስበት ለማድረግ ሲሆን ያለበለዚያ የቤተክርስትያኒቱን በሮች ሁላ በመቆለፍ ካህናት እንዳያገለግሉ ለማድረግ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከክልሉ መንግስት መልስ ያጡት ምዕመናን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ገልጸናል ፤ ይህን ነገር የሰሙት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት እና  የክልሉ ፖሊስ ደብዳቤውን ይዘው አዲስ አበባ ድረስ በማምጣት ያስገቡትን ሰዎች ለመያዝ በተጠናከረ ሁኔታ እየፈለጓቸው መሆኑን ሰምተናል ፤ ይህን የሰሙትም ራሳቸውን ላልተወሰነ ጊዜ ከአካባቢው ማራቃቸውን ለማወቅ ችለናል ፡፡ እንዴት ሰው መብቱን ስለጠየቀ ለመታሰር ይታደናል ? ይህ ሁሉ ነገር የቤተክህነቱ ችግረ ነው ፤ ራሱ የቤተክርስትያኒቱን ቦታ መጠበቅ ቢያቅተው እንዴት ምዕመኑ እዳይጠይቅ በማድረግ ጌታቸውን የመሰለ ማፊያ  ሰው መፍትሄ ያመጣል ብሎ ይልካል ፤ ቢያንስ ቦታው ማስከበር ቢያቅተው ይህን ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ላይ እንቅፋት ሊሆንባቸው አይገባም ነበር ፤

አቶ  ጌታቸው ዶኒ ከምዕመኑ የከረረ ተቃውሞ ሲደርስበት የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ቤተክርስትያኑን አዘጋዋለሁ ታቦቱንም አወጣዋለሁ እያለ ሲደነፋ ተሰምቷል ፤   እኛ ግን የምንሰጋው የቤቱ ባለቤት መድሀኒአለም ቤቱን ሊያዘጋ ሲንቀሳቀስ የእርሱን አንደበት እንዳይዘጋው ነው ፡፡ የዛሬ ሳምንት አካባቢም ይህን ጥያቄ ያነሱ 6 ወጣቶች እስር ቤት መክረማቸውን ለማወቅ ችለናል ፤ ይህ ጉዳይ እንደ ፕሮቴስታንት  ሰዎችን ከቤተክርስትያኒቱ ራስ ላይ ለመቀመጥ የሚያደርጉት ሩጫን ያመላክታል ፤ ሁሉንም ነገር በአንድ ጉልበተኛ ሰው እጅ ስር ለማስገባት አጥብቀው እየሰሩ ነው ፤  የቤተክርስትያናችን ራስ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ይህንም ጉዳይ ቤተክህነቱ አስቸኳይ መፍትሄ ካልሰጠው ነገሩ መልኩን እዳይቀይር ስጋት አለን ፤ የማንም ቦዘኔ እየመጣ ቤተክርስትያናችን ላይ ሊፈነጭ አይገባውም ፤ አቡነ ጳውሎስም ጉዳዩን በደንብ ያውቁታል የህዝቡም ፊርማ እና መልዕክት ደርሷችዋል ፤ ዝምታን ለምን እንደመረጡ እኛ አናውቅም ፤ በመልካም አስተዳደር እጦት ምዕመኑ መከራን መሸከም የለበትም ፤ ችግሮች ተጠንተው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል ፡፡

አሁን ተስፋችን ከቤተክህነቱ እየተሟጠጠ ይገኛል ፤ መንግስት መፍትሄ ይስጠን ፤ የቤተክርስትያን ችግር የህዝብ ችግር ነው ፤ የህዝብ ችግር ደግሞ የመንግስት ችግር ሊሆንና መፍትሄ ሊሻን ይገባዋል ፡፡ ፈተናችን ዛሬ ደህና ነው ሲባል ነገ እየባሰ እያስቸገረን ይገኛል ፤ ለዚህ ሁሉ ችግር የአንበሳውን ድርሻ ሊወስዱ የሚገባቸው ጠቅላይ ቤተክህነትና አቡነ ጳውሎስ ናቸው ፤ እኛም መረጃዎችን በጊዜያቸው እናንተው ዘንድ እናደርሳለን ፤

የበፊት ብሎግ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለማይከፈት ለወደፊት ይህን መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን www.andadirgen.blogspot.in

7 comments:

  1. Haile Michael zemerahe berhanatApril 27, 2012 at 4:03 AM

    "አቡነ ጳውሎስም ጉዳዩን በደንብ ያውቁታል የህዝቡም ፊርማ እና መልዕክት ደርሷችዋል ፤ ዝምታን ለምን እንደመረጡ እኛ አናውቅም"
    እባካችሁ የሚታቀርቡትን ነገር ጥርት አድርጋችሁ አቅርቡ :አታምታቱ ::
    ቆይ አቡነ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ላይ ግፍ ስፈጸም መቼ ስናገሩ ሰምታችሁ ነው አሁን ለምን ዝም እነዳሉ አልገባንም የሚትሉን?
    አልገባችሁም እንዴ ?ሰውየው የዓለም አብያተክርስቲያናት አባት ነው እንጂ የእኛ አይደሉም::
    ስለዚህ ለአቡነ ጳውሎስ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው፡፡ በዚያ ላይ የወያኔ አጀንዳ አለባቸው እኮ፡፡
    እባካችሁ ሕዝቡን በማሳወቅ ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡
    በዚህች በኢትየጵያ ሁኔታ በጣት የሚቆጠር ሕዝብ በሚያገኛት መረጃ አዳርሰናል ማለት ይከብዳል::
    ሰው ሲያውቅና ስሰማ ነው ለመፍትሔ በአንድ ላይ መንቀሳቀስ የሚችለው::

    ReplyDelete
  2. And Adigen melkam neger makirebachihun esimamalehu Neger gin Ato Getachew Doni malet atchilum enante kinitin yemeshar mebit altesetsachihum Enanitem siltsanu yelachihum Yetselanewn meshar yewededinewn meshom yelebinm Ato Getachew Don yalachihachew Gileseb Kesis Getachew Doni endemibalu awkale Minim Neger biyatsefu Bedelachew Bibeza Ato Malet yemichilew Kidus Sinodos Mehonun Tawkalachihu Wondimoch Atisasastu YIhi ken Kifu New Yih Gize Yefetena GIze new Kahinun Kinetun atinku Lesewoch masawk yefelegachihut Kifu sirawn kehone yann tenager Beterefe Kelelochu bloggch And Adirgen yeteshale yimesileg nebere zarem temelso sile sew yemimezekib kehone Asadag new malet new?

    ReplyDelete
  3. ለመሆኔ ጌታቸው ዶኒ የተባለው ሰው ይህን ያህል ቤተ ክርስቲያን ለመዝጋት ምን ያህል ስልጣን ቢኖረው ነው የተነሳሳው ቤተ ክርስቲያንን የሚዘጉ አላውያን ከሐዲ ናቸው ከሆነ ተውት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይዘጋዋል አታስቡ እሱ ለቤቱ ያውቃል ግን በጣም የሚያሳዝነው ነገር ቤተ ክርስቲያናችን መሪ ሟጣቷ ነው 4ኪሎ ያሉት ይቅርታ ይደረግልኝና ለገንዘብ ያደሩ ፈርተው ለሥጋቸው የሚኖሩ ከክርስቶስ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያልተወጡ ናቸው ማለተ ይቻላል ይህ ሁሉ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ከባድ ፈተና ሲደርስ አንዱ አንኳን ድምጹን ያሰማ አባት የለም መሪ አባት አለን ብለን የማንተማመንባቸው ናቸው በመናፍቃን በቤተ ክርስቲያናችን ጠላቶች ፊት እራሳችንን እንድንደፋ ያደረጉን አውደ ምሕረቷ ለይ ቁጭ ብለው ምንም ስለማይናጋሩ ማንም ውርጋጥ ባሌለው ስልጣን ቤተ ክርስቲያን እዘጋለሁ በቤተ ክርስቲያን ክልል ውስጥ ሸንኮራ አገዳ እዘራለሁ ቤተ ክርስቲያን አፈርሳሁ ወዘተ ቢል ምን ይደንቃል እግዚአብሔር ግን አንድ ቀን ሥራውን ይሰራል

    ReplyDelete
  4. አንድ አድርገን ሠላም ለናንተ እንዲሁም ለቤተክርስቲያናችን ይሁን!! እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያንችን፣ ምዕምናንንና የቤተክርስቲያንን ንጹህ አገልጋዮች ይጠብቅ። እነ ጌታቸው ዶኒንና መሰሎቹን ለመከላከል፣ ተሀድሶዎችን ከስር መሰረታቸው ለማድረቅ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችን ያጋጠማትን የውስጥና የውጭ ወከባ ለመከላከል መጠንከር አለባችሁ። እግዚአብሔር አምላክ ይርዳችሁ ቤተክርስቲያናችን ም ይጠብቅ!!!

    ነገሠ ከባህርዳር

    ReplyDelete
  5. ተከርቸምን እያነበብኩ መሰለኝ ሰዎች! “በመልካም አስተዳደር እጦት ምዕመኑ መከራን መሸከም የለበትም ፤ ችግሮች ተጠንተው መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡” የቤተክርስትያናችን ራስ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

    ReplyDelete