Thursday, April 26, 2012

የገዳማቱ ፤ የአድባራቱና የባቦጋያ መድሀኒአለም የመሬት ይዞታ ጉዳይ

ለወደፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
  • 120 ገዳማትና አድባራት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጣቸው
  • ጌታቸው ዶኒ ‹‹ቤተክርስትያኒቱን አዘጋለሁ›› በማለት ያበጠ ልቡን በአንደበቱ ሲናገር ለመስማት ተችሏል፡፡ 
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 18 2004 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ የሚገኙ 120 ገዳማትና አድባራት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጣቸው፡፡በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መጋቢ ካህናት ኃይለስሴ ዘማሪያም የማረጋገጫው ካርታ በተሰጠበት ወቅት እንደገለጹት ከመስከረም 9 1998 ዓ.ም በፊት የተሰሩት ገዳማትና አድባራ የጸበል ቦታዎች ፤ የመካነ መቃብር ፤ የበዓለ ጥምቀት ማበሪያ እና መሰል ስፍራዎች ሙሉ ይዞታቸውን ሳይቀነስ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳሪ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ተወካይ ኮማንደር መኮንን አሻግሬ እንደተናገሩት ፤ ‹‹ የአዲስ አበባ ከተማ የእድገትና የልማት አቅጣጫ ለማሳካት ከተማዋን በፕላን እንድትመራ እየተደረገ ነው ፡፡ በከተማዋ የሚገኙ ሰነድ አልባ ይዞታዎች ሁሉም ካርታ እንዲኖራቸው ለማድረግ እየተሰራ ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ገዳማትና አድባራት የይዞታ ሁኔታ በተመለከተ ከቤተክርስትያኒቱ ጋር በጋራ ሲሰራ ቆይቷል›› ብለዋል  ፡፡ ከመንግስት ተወካዩ ብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመሬት ይዞታ ካርታን ከተቀበሉ በኋላ  እንደተናገሩት ‹‹ገዳማቱ እና አድባራቱ በተሰጣቸው የይዞታ ማረጋገጫ መሰረት መሬቱን በተገቢው አገልግሎት ልያውሉ ይገባል ›› ብለዋል፡፡ ‹‹ የይዞታ ማረጋገጫ ይዞ መቀመጥ ዋጋ የለውም የተሰጠ መሬትን ለሀይማኖታዊና ለሌሎች ልማታዊ ስራዎች ልናውለው ይገባል›› ብለዋል፡፡

በከተማዋ ከ152 በላይ የቤተክርስትያኒቱ ገዳማት አድባራት እና የጸበል ቦታዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ 31 ገዳማትና አድባራ ቀደም ብሎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደተሰጣቸው በእለቱ ተጠቅሷ፡፡

እንደ እኛ ሀሳብ ይህ ተግባር ይበል የሚያስብል መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም ፤ ለብዙ ጊዜያት በቤተክርስትያኒቱ ቦታዎች የይዞታ ካርታ ባለመያዛቸው እየተቆረሱ ለባለሀብት የተሰጡበት ጊዜ ነበር ፤ ቦታው የቤተክርስትያኒቱ ነው የሚል ጥያቄ ሲነሳ የቤተክርስትያኒቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ አምጡ እየተባለ ብዙ እንግልት ይደርስ እንደነበር እናውቃለን ፤ በጥቂት ሰዎች መመሳጠር መሰል ቦታዎችን ለግለሰቦች አሳልፎ የተሰጠበትም ወቅት ነበር ፤ አሁን ግን ይህ የካርታ ጉዳይ በመኖሩ ችግሮቹን ከመሰረታቸው ይፈታል የሚል ግምት አለን፡፡

ከወራት በፊት በቦታ ጉዳይ የተነሳ የደብረዘይት ባቦጋያ መድሀኒአለም የመሬት ጉዳይ በህዝቡ ፤ በቤተክህነቱ እና በኩሪፍቱ በሪዞርት ባለቤት እሰጣ ገባ ውስጥ መሆናቸውን ገልጸን ነበር ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ራሱ የጻፈውን የቤተክህነት ማህተብ ያለበትን ደብዳቤ ለህዝቡ በማንበብ 10ሺህ ካሬ በላይ የሚሆን ቦታ የባቦጋያ ሪዞርት መሆኑን ማንም ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳያነሳ በማለት ከማስጠንቀቂያ ጋርም ለህዝቡ እና ለካህናቱ በአውደ ምህረት ላይ መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር፡፡ መልዕክቱም የቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይም ለማንም አቤት እደማይባል አሳስቧል ፤ በአውደ ምህረት ላይ ህዝቡ በግልጽ ያነበበውን መልዕክት የተቃወመ በመሆኑ በሚቀጥለው ቀን ካህናቱን ሰብስቦ ‹‹እናንተ ናችሁ ምዕመኑን የምታነሳሱት ፤ ምዕመኑ ስለ ጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ፤ ምእመኑ ጥያቄ እንዳያነሳ በንስሀ አባቶች በኩል ቤት ለቤት እየዞርን የማሳመን ስራ እንሰራለን›› ብለው እንዲፈርሙ አስገድዷቸዋል ፤ ይህን ሀሳብ ያልተቀበሉት ጥቂት ካህናት ስብሰባውን ትተው ሲወጡ ፤ 3 የሚሆኑት ደግሞ መፈረማቸውን ማወቅ ችለናል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ከስብሰባው በኋላ አቡነ ጳውሎ ጋር በመደወል ‹‹ ስራዬን እየጨረስኩ ነው ፤ ቃለ ጉባኤውንም አስፈርሜ በእጄ አስገብቻለሁ›› እያለ ሁኔታውን ሲያስረዳቸው በሰዎች ዘንድ ንግግራቸው ጆሮ ሊገባ ችሏል፡፡ እዚህ ላይ የማይጻፍ በርካታ ነገሮችንም ሲነጋገር ሚስጥር በማይደብቀው በቻይና የሞባይል ቀፎ ተሰምቷል፡፡

ይህ ቦታ የቤተክርስትያኒቱ ሲሆን በጥቂት ሰዎች ሴራ ካርታ እያለው ለሪዞርት ባለቤቱ መሸጡ ይታወቃል ፤ ‹‹ቤተክርስትያኒቱ ሳታውቅ ይህ ነገር መደረጉ አግባብ አይደለም ቦታው ሊመለስ ይገባዋል›› በማለት የአካባቢው ክርስትያኖች ፊርማ በማሰባሰብ ለቤተክህነት ፤ ለክልሉ መንግስትና ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ማስገባታቸውን ከቦታው የደረሰን ማስረጃ ያመለክታል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮም ደብዳቤውን ፈርመው ተቀብለዋቸዋል ፤ ትላንት 17/07/2004 ዓ.ም በተካሄደው ‹‹የፍትህ ቀን›› ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች በግልጽ ለክልሉ ባለስልጣናት ጉዳያቸውን እንዳስረዱ እና ‹‹ችግራችን የፍትህ ማጣት ነው›› በማለት ሲንከባለል የመጣውን ጉዳይ በፊት ለፊት አስረድተዋቸዋል ፤ ይህ ነገር ነገር ያልተዋጠለት አቶ ጌታቸው ዶኒ ‹‹ቤተክርስትያኒቱን አዘጋለሁ›› በማለት ያበጠ ልቡን በአንደበቱ ሲናገር ለመስማት ተችሏል፡፡  

ለእንደዚህ ያለው የማፊያ ስራ ለማስቆም የቤተክርስትያኒቱ ካርታ መኖሩ ጥሩ ጠቀሜታ አለው ፤ ወደፊት የሚነሱ ጥያቄዎችንም መልስ ይሆናል የሚል እምነት አለን ፤ ይህ የካርታ ጉዳይ ግን በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ ያሉትን ገዳማት አድባራት ፤ የጸበል ቦታዎች እና የቤተክርስትያኒቱ ተቋማት ሆላ ካርታ ሊኖራቸው ግድ ይላል ፤ ቤተክህነቱም ይህን የመስራት ሀላፊነት ያለበት ይመስለናል፡፡

3 comments:

  1. And Adirgen Betsam Des Yilal Melkam zena yizachihu Kerebachihu Ahun Yemyasifelgew Melkam were new Zewtir Bad News Makireb Kirstiyanochin betene Menafikann Asdesete Bete Kiristyan Melkam Neger tesertobat yemayawik meselech Karta Menoru lehulum neger yitsekimal Wedefitim Good News yizachihu kirebu Deje Selam -Ahat Tewahedo -And Adirgen -Selam Tewahedo Yemesaselut tebabirew Melkam Neger Bimezegibu Timihirt Bisetsu Yetebetatenew Hizib Hulu yimeles nebere Abune Ekele- Abba Ekele-Prist Ekele -Sebak Ekele -Zemar Ekele-Diyakon Ekele Eyalu Yesewn Neger Kemastelalef Abba Selam -Awde Mihiret -Merewa---Wezete yetebalu Yemenafikan Biloggch Yemilefelfutin eyeteketatelu mels mestset yibeltsal Ahun temelketu Sile Abune Tekile Hayimanot Dirsan Yemilutn Degimo tikikilnet Alew Zewtir Sele Abatoch & Sile AGelgayoch Hiyweti Sitmezegibuna Sitasadidu Akirari teblachihu Arefachihu -Hizibum betsam Teleyachihu Ahun Beka Good News akirbu Amlak Yitebkachihu Kelelochu Hulu Andi Adirgen Yeteshale Yimeslal Akbaryachihu neg

    ReplyDelete
  2. melkam zena...des yilal

    ReplyDelete
  3. ለወደፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
    http://www.andadirgen.blogspot.in
    betam desi yilale bertu ayizoachihu Egizabher kenanite gar new, hulachinem besolet enberta.

    ReplyDelete