Monday, April 30, 2012

በዋልድባ ገዳም ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበሉ


( አንድ አድርገን ሚያዚያ 23 2004ዓ.ም)፡-በዋልድባ ገዳም በጥበቃ ላይ የሚገኙ ከ4 በላይ ፌደራል ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ፤ ይህ ሶስተኛው ምልክት እንጂ የመጨረሻ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ ቦታው ላይ የሚገኙትን ፌደራል ፖሊሶች ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል ፤ ከፍተኛ ውጥረትም ነግሷል ፤  ቀጥሎ ማን እንደሚጎተት ስላላወቁ በሁኔታው እንቅልፍ አልወስድ ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች በዝተዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂ ግን መንግስት ነው ፤ በየጊዜው ለስራ ወደ ዋልድባ እየተላኩ ያሉ ባለሙያዎች እየታመሙ ይገኛሉ ፤ ስራውን የሚሰሩ መኪኖች እየተበላሹ ይገኛሉ ፤ በተጨማሪ አንድ አካባቢ የሚገኙ የማህበረሰቡ አባላት ስራው አይሰራም በማለት ስራውን ለ2 ቀናት ማስቆም ችለዋል ፤ ወደፊትም ከአካባው ይነሳሉ የተባሉት 8ሺህ አባዎራዎች መነሳታቸው አጠራጣሪ እየሆነ ይገኛል ፤ በማለት ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ምላካችን ታጋሽ ነው ፤ ‹‹እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ›› ኦሪት ዘጸአት 346 የምትሰሩት ስራ ከእርሱ የተደበቀ ሆኖ አይደለም ፤ ትንቢተ ኤርምያስ 17፤10 ላይ ‹‹እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።›› ተብሎ ተጽፏል አንዳች ከእርሱ የሚደበቅ ስራ የላችሁም አሁንም ከስራችሁ ተመለሱ በተጨማሪ የዮሐንስ ራእይ 223 ላይ ‹‹ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።›› ይላል ፡፡ 

ባለፈው 6 ሰዎች ተፈንግለው ሞተዋል ዛሬ ደግሞ 4 በላይ ፖሊሶች በጅብ ተበልተዋል ስለዚህ ከእርሱ የተደበቀ ከእርሱ የተሰወረ አንዳች ነገር የለም ዛሬ ላይ ልባችሁ አብጦ ጉልበትን መከታ በማድረግ የሚሰራ ስራ ውጤቱን እያያችሁት ነው፤ ከታሪክም ተወቃሽነትም ወደ የትም አያሸሽም በሰራችሁት ስራ ይመዝናችኋል ዋጋችሁንም ይሰጣችኋል፤ ‹‹የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። ትንቢተ ኤርምያስ 31 ፤15 ፤ አሁንም አባቶች ስለምታደርጉት ነገር እያለቀሱባችሁ መሆኑን እወቁ ፤ እንባቸው ጎርፍ ሆኖም እንዳይጠራርጋችሁ ለራሳችሁ ስጉ ፤ አምላካችን የራሄልን እንባ ከአይኗ የዳበሰ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው ፡፡‹‹ የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ›› መዝሙረ ዳዊት 46 ፤7 ባለፈው 9 ወር ሪፖርት ሲቀርብ የስኳር ሚኒስትሩ ስለ ዋልድባ ጥያቄ ተጠይቀው ‹‹ከእውነት የራቀ ነው ይህ ዋሺንግተን ላይ የተወራ ወሬ ነው›› በማለት መልስ ሰጥተው ነበር፡፡




በትንቢተ ኢሳያስ 1፤24 ላይ ‹‹የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል›› ይላል ሀይል የእግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን ፤ ነገር ግን ስጋውያን ትላንት ታይተው ከደቂቃዎች በኋላ እንደ ጤዛ ለሚደርቁ ጉልበተኞች በዘመናችን ቢያጋጥሙን ለሰው ልጅ ጉልበት የሚሆን ጉልበትንም የሚሰብር እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር እንደሆነ በዚህ ይወቁ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ›› ኦሪት ዘጸአት 1414 ፤ ይህን የዋልድባ የስኳር ልማት መቃወም እና ከእኩይ አላማቸው መግታት ቢያቅተን መጽሀፍ ቅዱስ ‹ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 17 ይላል እኛ ዝም እንላለን የእሱንም ስራ እያየን መከራችሁን እየቆጠርን እንቀመጣለን አሁን ሶስት ብለናል ነገ ሰላሳ እንደምንል አንጠራጠርም ካልተመለሳችሁ ቁጣው ይብሳል ሰይፉም ይሰላል ፡፡

አሁን ከታች ጀምሯል እያለ ወደ ላይ ይመጣል ፤ እጁን ዋልድባ ላይ ያሳረፈ ከቅጣቱ አያመልጥም ፤ እኛ አቅመ ደካሞች ነን ማስቆምም መቃወምም አልቻልንም ፤ እርሱ በመቅሰፍቱ ይቃወማችኋል ፤  ስለ እኛ ሳይሆን ስለ አባ ሳሙኤል ብሎ እግዚአብሔር ገዳሙን ይጠብቃል ፤ የማህበረ ቅዱሳን ሪፖርት መቼ እንጠብቅ? ለግንቦት የሲኖዶስ ስብሰባ ወይስ መቼ ?




ባለፈው ቀጣዩን ለማቅረብ ቃል ገብተን ነበር ፤ አሁንም ቀጣዩን ተዓምር ለማቅረብ ቃል እገባለን
ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ

15 comments:

  1. ahune alerefedebachewem ketefatachewe yemaru...betekirstiyanene medefere mechereshawe weredete newe..gena jemarea enji mecheresha ayedelem!!!!!

    Elelelelelelelelelelelele

    egiziabeheare yetemesegene yihune!!!

    betekirstiyanachenenen yitebeqelen

    ReplyDelete
    Replies
    1. Is it reliable information????

      Delete
  2. Ende Fareon Lebachawin bayatsenu Yeshalachewal! Belte Anbebo, Tayeko Yemaral Mogn Gin Bseu Lay Eskidarese Yetabekal!!! Sew kasew gar metalat ena mashanef sayechil ke Fetari Gar Endet Yetala? Yeabatochachen Amlak Botawen Yasedal Serategnochum Yehen Eyayu Kaseru Berasachew Lay Mafred Yemaselal Yemayamenem Gena Yehen Eyaye Yemaral Waldeba Gena Lateneka Tekaberalech!!! Daruan Be esat kalela yabatochachenen Atsem tetabekalech biyamenu yamifanakelut Atsem mut siyasenesa yayutal gena!!! Amlak yemasgen ye Rahelen enba yatamalakete yeabatochachenen enba fateno yabesal ayezoachehu. Gizew Eruk Ayehonem Hulum nager masmer yeyezal ayezoacheu yazenachehu tatsenanu!!!

    ReplyDelete
  3. Federal police wist gin eko betam berkata nitsu cristian wendimoch alu endeza kidusun sifra yetedaferut ergitegna negn tikit menafikanina ahizab polisoch yhonalu lenesum behon libona ystilin.

    ReplyDelete
  4. አቤቱ የዳዊት አምላክ ሀይልህን ግለጽ። ክርስቲያኖች እልል በሉ የዳዊት አምላክ ከኛ ጋር ነውና!!!!!!
    እንግዲህ ክርስቶስ ያለውን ማን ያሸንፈዋል? አሸንፋለሁ ባዬስ ማነው?

    ReplyDelete
  5. ‹‹እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ›› ኦሪት ዘጸአት 14፥14 ፤

    ReplyDelete
  6. ENAS AKEM YELEGM KEMALKES LALA E/R AEMLAK GEN YENAT HAGERUN NEKTEWBET ZEM ENDEMAYLACHEW AEWKEW NEBER TSELOTAGEN GIZAW ENDAYRK ENESUM BEZU ENDAYRAMEDU NEBER E/R AEMLAK DEG NEW AELNEFEGEGM LMENAYAN AEHUNM ENDEMILUT AEBATOCH ELLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLLL.

    ReplyDelete
  7. በትንቢተ ኢሳያስ 1፤24 ላይ ‹‹የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል

    eleleleleleleleleleelelelelelelelel we will continue to hearing the miracle a lot.
    GOD bless u Andadrgen excellent jobs, pls keep all of us praying to GOD, He will answer soon.

    ReplyDelete
  8. ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ (የዮሐንስ ራእይ 2፤23)ፍርድን ከአምላክ እንጂ ከሰው አንጠብቅም! በዚህ መሃል ግን የሚቀጠፉት ንጹሃን ያሳዝናሉ ምንም የስራ ግዳጅ ቢሆንባቸውም እዛ ያሉትም ተግተው መጸለይ ይኖርባቸዋል

    ReplyDelete
  9. Nisebiho(2) leigziabier.(2). Sibuha ze tesebia(2).

    ReplyDelete
  10. Nisebiho(2) leigziabier.(2). Sibuha ze tesebia(2).

    ReplyDelete
  11. EGZIABEHER YTADEGENAL BERTETEN ENTSELEY!!!!!!!!

    ReplyDelete
  12. Egziabher gasha meketachen new ersu ytadegenal

    ReplyDelete
  13. how much it is true?

    ReplyDelete
  14. bzatu gedeb yelelew amlak yamene hulu ewnetun yawqewal. atterater gena bzu tsemaleh. yamenew amlak talak new.

    ReplyDelete