(አንድ አድርገን መጋቢት 30 2004 ዓ.ም )፡- በቅርቡ በእሳት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት በምዕራብ ሀረርጌ
ሀገረ ስብከት ሜኤሶን ወረዳ ከሚገኝው የአሰቦት ቅድስት ሥላሴና የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም የመጡ ስምንት አባቶች ‹‹ ገዳሙ ይከለልልን ሰራዊት ተመድቦ ይጠበቅልን›› ሲሉ ለጠቅላይ ቤተክህነትና ለመንግስት አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡
በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአባ
ሳሙኤል ዘወገግ የተመሠረተው የአሰቦት ገዳም በተደጋጋሚ እየደረሰበት ያለውን ችግር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከገዳሙ የመጡት አባቶች ‹‹ በክልሉ ያለ የአንድ ጎሳ
አባላት አሳት በመለኮስ ገዳሙ እንዲቃጠል እያደረጉ ነው ፡፡›› በማለት መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል ፡፡ በተጨማሪ
ገዳሙ ካረፈበት ክልል አራት እና ክልል አምስት አስተዳደር ወጥቶ በፌደራል እንዲተዳደር በሰራዊት እንዲጠበቅላቸው ለቤተክህነት እና
ለመንግሰት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም ከመጋቢት 2/2004 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀናት የቆየ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ቃጠሎ ደርሶበት ነበር ፡፡ የገዳሙ አበምኔት አባ ተክለ ማርያም በጊዜው በደኑ ቃጠሎ ዙሪያ መፍትሔ እንዲፈለግለት በተለይም መንግስት ጥበቃ እንዲመድብ አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ መምጣታቸው ይታወቃል ከቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርገው ነበር ፡፡ አቡነ ጳውሎስም ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ እንደሚያሳውቁና በጥበቃ ዙሪያ ያለውን ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ በጊዜው ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡ በዚሁ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ፡፡
ስምንቱ አባቶች በመምራት የመጡት የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ተክለማርያም ከብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሁለት ሰዎች
ወክለው ከመንግስት ጋር እንዲነጋገሩ ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፤ መንግስት ጥያቄያቸውን እንደተቀበለ እና ውይይት አድርጎ ለሚያዚያ
1 2004 ዓ.ም መልስ እንደሚሰጣቸው ቃል እንደገባላቸው ለማወቅ ችለናል ፡፡
የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም ከመጋቢት 2/2004 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀናት የቆየ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ቃጠሎ ደርሶበት ነበር ፡፡ የገዳሙ አበምኔት አባ ተክለ ማርያም በጊዜው በደኑ ቃጠሎ ዙሪያ መፍትሔ እንዲፈለግለት በተለይም መንግስት ጥበቃ እንዲመድብ አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ መምጣታቸው ይታወቃል ከቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርገው ነበር ፡፡ አቡነ ጳውሎስም ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ እንደሚያሳውቁና በጥበቃ ዙሪያ ያለውን ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ በጊዜው ቃል ገብተውላቸው ነበር፡፡ በዚሁ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ፡፡
እስኪ በጠቅላይ ሚንስትራችን ላይ አድሮ አምላከ ቅዱሳ መልካሙን ይስራልን
ReplyDeleteእስኪ በጠቅላይ መከራችን ላይ አድሮ አምላከ ቅዱሳን መልካሙን ይስራልን
ReplyDeleteAmen
ReplyDelete